ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ

ጤና

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

 

ለአሰራጮች የቀረበ ማስታወሻ

ፋርም ሬዲዮ ኢንተርናሽናል በኮቪድ-19 ዙሪያ አስተማሪ ግሮግራሞችን ለማዘጋጀትና የአድማጮቻችሁን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚረዱ በርካታ ግብአቶችን አዘጋጅቷል፡፡ እነዚህን ሁሉ ግብአቶች በዚህ ገጽ ማግኘት ይችላሉ፡
https://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/covid-19-resources/

ለታዳሚዎቻችሁ ጠቃሚ የሚሆኑትን ጉዳዮች ለመረዳት፣ ከአድማጮቻና ከማህበረተብ መሪዎች ጋር ለመነጋገር፡፡ ኮቪድ-19 ክትባቶችን በተመለከተ ለሚነሱ የአድማጮች ጥያቄዎችን ከመመለስ በፊት አስቀድሞ ከአካባቢው የጤና ባለሙያዎች ጋር፣ በተለይ ክትባት መኖሩን በተመለከተ መነጋገር ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች በየ ፕሮግራሞች አልያም በሳምንታዊ መደበኛ ፕሮግራሞች መሃል ለአድማጮቻችሁ ከፍ ብለው መነበብና መደመጥ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ፕሮግራሞች በምታዘጋጁበት ወቅት በዓለም ጤና ድርጅት እና በሀገር ውስጥ የጤና ሚኒስቴር እውቅና የተሰጣቸው ክትባቶች መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

እነዚህን በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለማሰስ ከታች ያለውን ማውጫ ይጫኑ፡፡ በሚጫኑበት ወቅት በኮምፒውሮ ኪቦርድ ላይ “ctrl” በመጫን በመያዝ ወደ ፈለጉት ጥያቄ ቀጥታ ይወስዶታል፡፡

በአፍሪካ ቋንቋዎች የተተረጎሙትን ይህን መሰልና ሌሎች የኮቪድ-19 ግብአቶችን ለማግኘት፣ ይህን ይጫኑ፡
https://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/translations-available/

Script

 

ማውጫ

 

መሰረታዊ መረጃ 2

በርካታ የኮቪድ-19 ክትባት አይነቶች በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡ እስከ ሚያዝያ 2022 ድረስ የሚከተሉት የክትባት አይነቶች አሉ፤ 3

የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዴት በፍጥነት ሊበለፅጉ ቻሉ? 4

የኮቪድ-19 ክትባቶች በዋነኝነት የኮቪድ-19 ቫይረስን ለመከላከል የሚያስች የሰውነት አቅምን ለመገንባት ነው የተሰሩ ሲሆን ለሌላ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ማለትም ለሳርስ እና መርስ አይሆኑም፡፡ 5

መላመድ በሚባል ሂደት ሁሉም ቫይረሶች ተለዋዋጭ ናቸው፣ በዚህም አዳዲስ ዝርያዎች በቋሚነት ይከሰታሉ፡፡ ከኮቪድ-19 ዝርያዎች ጥቂቶቹ የሆኑት ዴልታ እና ኦሚክሮን ከመጀመሪያው የኮቪድ-19 ቫይረስ ይበልጥ ተላላፊ ናቸው፡፡ 5

የኮቪድ-19 ክትባቱ የደም መርጋትን ያስከትልብኝ ይሆን? 6

ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የሞቱ ሰዎችስ? 7

የኮቪድ-19 ክትባቱ ኮቪድ-19ን በሰውነቴ ያሰራጫል? 7

የትኛውን የኮቪድ-19 ክትባት ልምረጥ? 7

ከዚህ ቀደም ኮቪድ-19 ይዞኝ የሚያውቅ ከሆነ ክትባቱን መከተቤ ይመከራል? 7

ህጻናትና ታዳጊዎች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ? 7

የኮቪድ-19 ክትባቱን የተከተብኩ ከሆነ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ፣ የመከላከያ እርምጃዎችን መጠቀም እና ሌሎች ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይጠበቅብኝል? 8

የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰድኩ በኋላ አንቲባዮቲኮችን ብወስድ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው? 9

የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰድኩ በኋላ አልኮል መጠጥ መጠጣት ለእኔ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው? 9

በኮቪድ-19 ተይዞ የሚዳብር የበሽታ መከላከያ አቅም እና የኮቪድ-19 ክትባትን ከወሰደቡ በኋላ የሚዳብር የበሽታ መከላከያ አቅም መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 9

የኮቪድ-19 ክትባት በፒ.ሲ.አር ወይም አንቲጂን ምርመራ ላይ ፖሰቲቭ ውጤትን ሊያስከትል ይችላል? 10

የስኳር በሽታ አለብኝ፡፡ ኮቪድ-19 እኔን ከሌላው በተለየ የሚጎዳኝ እንዴት ነው? 10

አሁን የካንሰር ህመምተኛ ነኝ ወይም ካሁን ቀደም የካንሰር ህመምተኛ ነበርኩ፡፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መከተብ እችላለሁ? 10

ኤችአይቪ በደሜ ውስጥ ይገኛል። የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መከተብ እችላለሁ? 11

ኤችአይቪ በደሜ ውስጥ ይገኛል። ራሴን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ ልወስዳቸው የሚገቡ የተለዩ እርምጃዎች አሉ? 11

የጋሜላያ (ስፑትኒክ ቪ) ክትባትን መከተብ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ያደርገኝ ይሆን? 11

የሰውነት አለመታዘዝ ችግር ስላለብኝ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱ ይከብደኛል፡፡ ቤት ውስጥ መከተብ እችላለሁ? 12

ኮቪድ-19 ሴቶች ላይ ከሚያስከትለው የጤና ተጽእኖ በወንዶች ላይ የሚያስከትለው የጤና ተጽእኖ ጋር ሲነጻጸር ልዩነት አለው? 12

የወሲብ እና የስነ ተዋልዶ ጤና እና ኮቪድ-19 12

ነፍሰ ጡር ሆኜ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ እችላለሁ? 12

የኮቪድ-19 ክትባቶች መካን ወይም አቅመ ቢስ ያደርጉኛል? 12

ጡት እያጠባሁ ከሆነ ኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ እችላለሁን? 12

በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መከተብ ይችላሉ? 13

ዶዞች 13

ሁለት ዙር የክትባቱ መጠን ከአንድ ዙር ብቻ በተሻለ መልኩ ከበሽታው ይጠብቀኛል? 13

ክትባቶችን መቀላቀል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው – ለምሳሌ የአንድ ክትባት የመጀመሪያ ዙር እና የሁለተኛ ዙር የተለያየ ክትባት መውሰዱ? 13

የኮቪድ-19 “የማጠናከሪያ ክትባት ዙሮች” ወይም “የማጠናከሪያ ክትባቶች” ምንድናቸው? 13

ለኮቪድ-19 ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ክትባት ያስፈልጋቸዋል? 14

Acknowledgements 14

መሰረታዊ መረጃ

 

በአፍሪካ የሚገኙት የኮቪድ-19 ክትባቶች የትኞቹ ናቸው?

በርካታ የኮቪድ-19 ክትባት አይነቶች በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡ እስከ ሚያዝያ 2022 ድረስ የሚከተሉት የክትባት አይነቶች አሉ፤

 • ባህራት ባዮቴክ (ኮቫክስ)
 • ጋሜላያ (ስፑትኒክ V)
 • ጃንሰን (ጆንሰን እና ጆንሰን)
 • ሞደርና
 • ኦክስፎርድ/አስትራ ዜኔካ
 • ፋይዘር
 • ሲኖፋርም
 • ሲኖቫክ

የአንድ ክትባት መገኘት አሀገር ሀገር ይለያያል፡፡ እነዚህ ሁሉ ክትባቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በተደጋጋሚ ሙከራ ተደርጎባቸው ከባድ ህመምን፣ ሆስፒታል መተኛትንና በኮቪድ-19 የሚመጣን ሞት ከማስቀረት አኳያ ደህንነታቸውና ውጤታማነታቸው ተረጋግጧል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ምን አይነት ጥቅሞች አለው?

ክትባት መከተብ ህይወትን ይታደጋል፡፡ የኮቪድ-19 ክትባቶች ከከባድ ህመም፣ ሆስፒታል መተኛትን እና በቫይረሱ የሚከሰት ሞትን ለማስቀረት ጠንካራ መከላከልን ያስችላል፡፡ መከተብ ቫይረሱን ወደ ሌሎች የማስተላለፍ እድልን ይቀንሳል ይህም ማለት የእርሶ ለመከተብ መወሰን በዙሪያዎ ያሉትን ሁሉ ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቶች የሚሰሩት እንዴት ነው?

የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዴት እንደሚሰሩ ለመረዳት እነዚህን ሶስት መሰረታዊ ቃላት ማወቅ ያስፈልጋል፤ በሽታ አምጪ (ፓቶጂን)፣ በሽታ ተከላካይ (አንቲቦዲ) እና መድሐኒት (አንቲጂን)፡፡

በሽታ አምጪ (ፓቶጂን) የሚባለው በሽታ አምጪ ጥቃቅን ህዋሳት ናቸው፡፡ የኮቪድ-19 የሚያመጣው ቫይረስ በሽታ አምጪ ይባላል፡፡

የሰው ልጅ በሽታ የመከላከል አቅም በሽታ ተከላካዮችን (አንቲቦዲስ) በማምረት ለበሽታ አምጪዎች ምላሽ ይሰጣል፡፡

የሰውነት አካል በሽታ ተከላካዮችን እንዲያመርት የሚያደርገው የተለየ የበሽታ አምጪ ክፍል መድሐኒት (አንቲጂን) ይባላል፡፡ ሰውነት ለመጀመሪያ ጊዜ ለመድሐኒት ተጋላጭ ሲሆን የሰውነት ተፈጥሮአዊ በሽታን ተከላካይ ከመድሐኒቱ ባህሪ ጋር የሚሄድ በሽታ ተከላካዮችን (አንቲቦዲስ) ያመርታል፡፡

ሁለት አይነት የኮቪድ-19 ክትባቶች አሉ፡፡ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት እንደ ባህራት ባዮቴክ (ኮቫክስ)፣ ጋሜላያ (ስፑትኒክ V) ፣ ጃንሰን (ጆንሰን እና ጆንሰን) ፣ ኦክስፎርድ/አስትራ ዜኔካ፣ ሲኖፋርም እና ሲኖቫክ የተዳከመ የኮቪድ-19 አንቲጆን በውስጣቸው አለ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ክትባቶች ሲከተብ በሰውነት ውስጥ ያለውን ተፈጥሮአዊ በሽታን የመከላከል አቅምን ያነቃቃሉ፡፡ ይህም በሽታን መከላከያ ሰውነት ኮቪድ-19 በሽታን ለመከለከል ዝግጁ እንዲሆን ያዘጋጀዋል፡፡

mRNA በመባል የሚታወቁት ሌላ አይነቶቹ ክትባቶች ማለትም የፋይዘርና ሞደርና ክትባት አይነቶች የኮቪድ-19 አንቲጂን በውስጣቸው የለም፡፡ ይልቅንም የአንቲጂኑ ባህሪ የያዘ መረጃ በውስጣቸው አካተዋል ፡፡ አንድ ሰው የmRNA ክትባት ሲወስድ በውስጡ ያለውን መረጃ በመጠቀም የኮቪድ-19 በሽታ የመከላከልን ምላሽን ያነቃቃል፡፡

የትኛውንም የክትባት አይነት ቢከተቡም የኮቪድ-19 ክትባቶች ለህመም አያጋልጥም፡፡ ይልቁንም ሰውነት በኮቪድ-19 በሽታ የተጠቃበት ያህል የመከላከል አቅሙን ያዘጋጃል፡፡ ይህም የሰውነት የበሽታ መከላከል አቅምን በመፍጠር ቫይረሱን ይገታል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዴት በፍጥነት ሊበለፅጉ ቻሉ?

ቀደም ሲል በነበሩ ጊዜአት ክትባቶችን አበልፅጎ ለህብረተሰቡ ማዳረስ ብዙ ዓመታትን ወስዷል፡፡ ነገር ግን የኮቪድ-19 ክትባቶች ለህብረተሰቡ መቅረብ የቻሉት ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለበት በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡

ክትባቶቸን በመፍጠር የዓመታት ጉዞ ውስጥ የምርምር ቡድኖችና የህብረተሰብ ጤና ተቋማት ሂደቱ እጅግ ዘገምተኛ መሆኑን ስለተገነዘቡ የሥራውን ጥራትና ፍጥነት ማሻሻል ችለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ተመራማሪዎች ኮሮና ቫይረስን ለበርካታ አስርት ዓመታት ሲያጠኑ የቆዩ በመሆኑ ባለፉት 20 ዓመታት የሰው ልጆችን ካጠቁት ከሌሎች ሁለት የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ማለትም ከSARS እና MERS መማር ችለዋል፡፡ ኮቪድ-19 አማጭ የሆነውን ቫይረስ ካወቁ በኋላ የዘረ መል መረጃውን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለማወቅ ችለዋል፡፡ ይህም ኮቪድ-19ን ለመከላከል ምን አይነት ክትባት እንደሚያስፈልግ ለይቶ ለማወቅ ረድቷቸዋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመግታት በርካታ ዓለም አቀፍ ጥምረቶችም ተፈጥረዋል፡፡ በበርካታ ሀገራት ያሉ ሳይንቲስቶችና ተቋማት ቫይሱን ለመዋጋት በሚያስችል የተሻለ መንገድ ላይ መረጃዎችን እየተለዋወጡ መክረዋል፡፡

ለኮቪድ-19 ክትባቶች የሚሆን የገንዘብ ድጋፎች ከየአቅጣጫው ተገኝቷል ይህም ለትርፍ ካልተቋቋሙ ቡድኖች፣ መንግሥታት፣ ግለሰቦች እና መድሐኒት አምራች ኩባንያዎችን ያካተተ ነው፡፡

ቀደም ሲል ክትባቶችን ለመሞከር ዓመታትን ይፈጅ የነበረ ሲሆን ምርመራዎችን በማዘጋጀት፣ በጎ ፈቃደኞችን በማሰባሰብ እና የክትባቱን ዘላቂ ደህንነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ ሶስቱን የሙከራ ምዕራፎች ማሟላት ይጠበቃል፡፡ ሆኖም የኮቪድ-19 ክትባቶች የተለያዩ የሙከራ ምዕራፎች በተጓዳኝ መልኩ እንዲከናወኑ ተደርጓል፡፡ ለክትባት እውቅና የሚሰጡ ተቋማትም ክትባቶቹ ደህንነታቸው ጸረጋገጠና ውጤታማ መሆናቸውን ለመወሰን የሙከራ መረጃውን ተጓዳኝ ሂደቱን ተከትለው ማከናወን ችለዋል፡፡

ብዙ ኩባንያዎችም የገንዘብ ድጋፍ በማግኘታቸው ክትባቶቹ ሙሉ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እውቅና ከማግኘታቸው አስቀድሞ ወደ ምርት መግባት ችለዋል፡፡ ዘግይቶ እውቅና የተሰጣቸው ክትባቶችቸ ለማምረት የሚፈጀውን ጊዜ በመቀነስ ለህብረተሰቡ አስቀድመው ማሰራጨት እንዲችሉ መልካም አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል፡፡

በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ቀድመው ለሞከሯቸው ሰዎች ምስጋና ይግባና የኮቪድ-19 ክትባቶች በርካታ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን እንዳለፉ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ እውቅና የተሰጣቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች በዓለም ዙሪያ ካሉ መንግሥታትና የጤና ተቋማት ጠበቅ ያለ መመዘኛ ተቀምጦላቸዋል፡፡

በክትባቶቹ ላይ የሚደረጉ ሳይንሳዊና የቁጥጥር ሥራዎች አሁንም አልተቋረጡም፡፡ ማንኛውም ክትባቱን የወሰደ ሰው ስላጋጠመው ነገር መረጃ ማካፈል የሚችል ሲሆን ይህም ክትባቱ እንዴት እንደሚሰራ በተሻለ ለመረዳት ይረዳል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት መቼ መከተብ አለብኝ?

የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በተቻለ ፍጥነት መከተብ አለቦት፡፡ የመከተቢያ ጊዜ ገደም መመሪያ ከሀገር ሀገር ይለያያል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በአካባቢዎ ያለ የጤና ጣቢያ ያነጋግሩ፡፡

የተከተቡ ሰዎች ሳርስ (SARS) እና መርስ(MERS)ን ጨምሮ ሁሉንም አይነት የኮሮና ቫይረሶችን መቋቋም ይችላሉ?

የኮቪድ-19 ክትባቶች በዋነኝነት የኮቪድ-19 ቫይረስን ለመከላከል የሚያስች የሰውነት አቅምን ለመገንባት ነው የተሰሩ ሲሆን ለሌላ የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ማለትም ለሳርስ እና መርስ አይሆኑም፡፡
ኮቪድ-19 አንዱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ነው፡፡ ኮሮና ቫይረሶች ሰዎችን ቸምሮ ወፎችና አጥቢ እንስሳትን ለበሽታ የሚያጋልጡ ተዛማጅ የቫይረስ አይነቶች ናቸው፡፡ በኮሮና ቫይረስ ከሚከሰቱ የበሽታ አይነቶች አንዱ በሌሎች ቫይረሶችም ሊከሰት የሚችለው ጉንፋንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉት እንደ ሳርስ፣ መርስ እና ኮቪድ-19 የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የተከተቡ ሰዎች ሁሉንም የኮቪድ-19 ዝርያዎችን መቋቋም ይችላሉ?

መላመድ በሚባል ሂደት ሁሉም ቫይረሶች ተለዋዋጭ ናቸው፣ በዚህም አዳዲስ ዝርያዎች በቋሚነት ይከሰታሉ፡፡ ከኮቪድ-19 ዝርያዎች ጥቂቶቹ የሆኑት ዴልታ እና ኦሚክሮን ከመጀመሪያው የኮቪድ-19 ቫይረስ ይበልጥ ተላላፊ ናቸው፡፡
እስከ ሚያዝያ 2022 ድረስ ሁሉም ለጥቅም እንዲውሉ የተፈቀቀደላቸው ክትባቶች ዴልታና ኦሚክሮንን ጨምሮ በሁሉም በኮቪድ-19 ዝርያዎች የሚከሰትን ከፍተኛ ህመም፣ በሆስፒታል መተኛትን እና ሞትን ከመከላከል አኳያ ውጤታማ ናቸው፡፡

በዋነኝነት ኦሚክሮንን እና የዴልታ ዝርያዎችን ተላላፊነት ከመከላከል አኳያ የኮቪድ-19 ክትባቶች እምብዛም ውጤታማ አይደሉም፡፡ ሆኖም ከተከተቡ በኋላ በበሽታው የሚጠቁ ከሆነ የሚታይቦት የህመም ስሜት ካልተከተቡት ይልቅ ቀለል ያለ ሲሆን ወደ ሆስፒታል የመተኛት አልያም ሞት ሊያጋጥም የሚችልበት እድል ያነሰ ነው፡፡

ከተከተቡ በኋላ በኮቪድ-19 ይያዙ ይሆን?

በተረጋገጠ የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ከከፍተኛ ህመም፣ ሆስፒታል መተኛትንና ሞትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡ መከተብ በኮቪድ-19 በሽታ መያዝንም ሆነ ወደ ሌሎች የማስተላለፍ እድልን ይቀንሳል፡፡

የኮቪድ-19 ሙሉ ክትባት የከተቡ ሰዎች በኮቪድ-19 ሊያዙም ሆነ ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ ይህ በተለይ በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ በሆነው የኦሚክሮን ዝርያ የታየ ነው፡፡

ይሁንና ከተከተቡ በኋላ በበሽታው የሚጠቁ ከሆነ የሚታይቦት የህመም ስሜት ካልተከተቡት ይልቅ ቀለል ያለ ሲሆን ወደ ሆስፒታል የመተኛት አልያም ሞት ሊያጋጥም የሚችልበት እድል ያነሰ ነው፡፡

ከክትባቶች ጋር የተያያዙ ጊዜያዊ ተጓዳኝ ችግሮችን ለማስቀረት ባልከተብስ? ተጓዳኝ ችግሮቹ የረዥም ጊዜ ችግር ይኖራቸዋል?

ተጓጋኝ ችግሮችን ለማስቀረት ሲሉ ከክትባት መራቀ የለቦትም፡፡ እናም የትኛውም የክትባት ተጓዳኝ ችግሮች ለረዥም ጊዜ የሚቆዩ አይደሉም፡፡

በተረጋገጠ የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ከከፍተኛ ህመም፣ ሆስፒታል መተኛትንና ከሞት ይከላከላል፡፡ የህም በጣም ተላላፊ ለሆኑት ዴልታና ኦሚክሮን ዝርያዎችንም ጭምር ይከላከላል፡፡

ተጓዳኝ ችግሮች ብዙ ጊዜ የኮቪድ-19 ክትባት በተከተቡ ጥቂት ቀናት ውስጥ ይከሰታል፡፡ መጀመሪያ ክትባቱ በዓለም ላይ በስፋት መሰጠት ከጀመረበት ከታህሳስ 2020 ጀምሮ 11 ቢሊዮን የሚሆኑ የኮቪድ-19 ክትባቶች የተሰጡ ሲሆን የረዥም ጊዜ የቆየ ተጓዳኝ ችግር አልገጠመም፡፡

የክትባት ተጓዳኝ ችግሮች ብዙ ጊዜ ቀለል ያሉ ሲሆኑ በስፋት የተለመዱት፤ የእጅ ህመም፣ ቀላል ትኩሳት፣ ድባቴ፣ ራስ ምታትና የጡንቻና መገጣጠሚያ ህመሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ሰውነታችሁ የኮቪድ-19 ለመከላከል የሚያስችለውን አቅም እየገነባ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ ሰዎች ከተከተቡ በኋላ ምንም ተጓዳኝ ችግሮች የማያጋጥማቸው ሲሆን ተመሳሳይ የመከላከል አቅምም ይኖራቸዋል፡፡

በኮቪድ-19 የመጠቃት አደጋው ክትባት ወስዶ ሊመጣ ከሚችል ተጓዳኝ ችግር በእጅጉ የላቀ ነው፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቱ የደም መርጋትን ያስከትልብኝ ይሆን?

የአስትራ ዘነካ እና ጃንሰን (ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን) ክትባት በተከተቡ ከሶስት እስከ 30 ቀናት ውስጥ የደም መርጋት እንደተከሰተ አንዳንድ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ እነዚህ ክስተቶች ከባድ ተደርገው ቢወሰዱም በቁጥር በጣም ጥቂቶች ላይ ነው የሚከሰተው፡፡

እንዲያውም ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኮቪድ-19 በሽታ መያዙ ከክትባቱ በበለጠ የደም መርጋትን ሊያስከስት የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፡፡

ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ የሞቱ ሰዎችስ?

የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህንነታቸው በሚገባ ተፈትኗል፡፡ ክትባቶቹ ከባድ ህመምን፣ ሆስፒታል መተኛትን እና ሞትን ለመከላከል ውጤታማ እንደሆኑም ተረጋግጧል፡፡ ከክትባት በኋላ ከባድ ጤና ላይ የሚከሰቱ አይታዩም፡፡ አንድ ሰው ከተከተበ በኋላ አሉታዊ ክስተት ስላጋጠመው ብቻ ክትባቱ ችግሩን አስከትሏል ማለት አይቻልም፡፡ ይልቁንም ችግሩ ቀደም ሲል ከነበረ የጤና ሁኔታ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቱ ኮቪድ-19ን በሰውነቴ ያሰራጫል?

ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከተፈቀደላቸው ክትባቶች ውስጥ የትኛቸውም ኮቪድ-19ን የሚያመጣው የቀጥታ ቫይረስ አልያዙም፡፡ ስለዚህ የኮቪድ-19 ክትባቶች በኮቪድ-19 እንዲያዙ ማድረግ አይችሉም፡፡

የትኛውን የኮቪድ-19 ክትባት ልምረጥ?

ሁሉም በሚመለከተው አካል እውቅና የተሰጣቸው የኮቪድ-19 ክትባቶች ከከባድ ሕመም፣ ሆስፒታል ከመተኛት እና በኮቪድ-19 ምክንያት ከመሞት ለመከላከል እጅግ ውጤታማ ናቸው፡፡ የጤና ባለሙያዎች ማህበረሰቡን በመጀመሪያ የሚሰጠውን ክትባት እንዲወስዱ እና በተቻለ ፍጥነት እንዲከተቡ ይመክራሉ፡፡

በጤና ባለሙያ ክትባቱን ከመከተብ እንዲዘገዩ ካልተመከሩ በስተቀር ከመከተብ አይዘገዩ፣ ምክንያቱም ይህ መዘግየት በኮቪድ-19 የመያዝ አደጋ ላይ ሊጥልዎት ይችላል፡፡

መከተብ ሕይወትዎን ሊያተርፍ ይችላል፡፡ ተመራጩ የኮቪድ-19 ክትባት በአቅራቢያዎ የሚገኘው ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ኮቪድ-19 ይዞኝ የሚያውቅ ከሆነ ክትባቱን መከተቤ ይመከራል?

አዎ ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 ተይዘው የሚያውቁ ሰዎችም ሙሉ የክትባት ዙሮቹን እንዲወስዱ ይመከራሉ፡፡ በኮቪድ-19 ተይዘው የሚያውቁ ሰዎች በተወሰነ መልኩ ሰውነታቸው በሽታውን የመከላከል አቅም ሊያዳብር ቢችልም ይህ በሽታውን የመከላከል አቅሙ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እና ጥንካሬው እስከ ምን ድረስ እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመናገር አስቸጋሪ ነው፡፡

ክትባቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መተኛትን እና ሞትን ለመከላከል በጣም አስተማማኝ እና ውጤታማ መንገዶች ናቸው፡፡

ለዚህም ነው የዓለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች የጤና ባለስልጣናት ሰዎች በተቻለ ፍጥነት ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ የሚመክሩት፡፡

የኮቪድ-19 ምልክቶች መታየታቸውን ሲያቆሙ ወዲያውኑ መከተብ ይችላሉ፡፡

ህጻናትና ታዳጊዎች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ?

ለህጻናት እና ታዳጊዎች የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራዎች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳን ዝቅተኛው የክትባት ዕድሜ እንደየሃገሮቹ ቢለያይምእስካሁን ድረስ በርካታ አገሮች የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለልጆች እና ታዳጊዎች እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ሥር በሰደደ የጤና ችግር የሌለባቸው ሕፃናት በኮቪድ-19 ምክንያት ለጠና የመታመም እድላቸው ከአዋቂዎች ያነሰ ነው፣ ስለዚህ ሕፃናትን መከተቡ ዋና ዓላማው ሥርጭትን መቀነስ ነው፡፡

ሆኖም የኮቪድ-19 ክትባቶች የኦሚክሮን ተለዋጭ ስርጭትን በመቀነስ ረገድ ብዙም ውጤታማ አይደሉም፡፡ ስለዚህ ክትባቱን ከመውሰድ በተጨማሪ ህጻናትን ለመጠበቅ ተመራጭ መንገድ የሚሆኑት ሁሉም ሰው አፍና አፍንጫውን በሚገባ በጭምብል መሸፈኑን መቀጠል፣ አንድ ሜትር የሚያክል የአካል ርቀትን መጠበቅ፣ በሳልና ማስነጠስ ወቅት በክርን አፍና አፍንጫን መሸፈን እንዲሁም እጅን በሳሙና እና በውሃ በተደጋጋሚ ማጽዳቱ ነው፡፡

ወላጆች እና የህጻናት ጠባቂዎች ህጻናቶችሁ ጤናማ ካልሆኑ ከትምህርት ቤት እንዲቀሩ በሚደረጉ ልጆች ዙሪያ መመሪያዎችን መከተል አለባቸው፡፡ የበሽታ ምልክቶች ሲታዩ እና ምርመራዎች በሚገኙበት ቦታ ልጆቻቸውን የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲወስዱ ማድረግን በተመለከተ ወላጆች መመሪያዎችን ማክበር አለባቸው፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቱን የተከተብኩ ከሆነ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ፣ የመከላከያ እርምጃዎችን መጠቀም እና ሌሎች ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይጠበቅብኝል?

አዎ ይጠበቅብዎታል፡፡ የኮቪድ-19 ክትባቶችን መውሰዱ ከከባድ ህመም፣ ሆስፒታል ከመተኛት እና ከሞት ለመከላከል በጣም ጥሩ መንገድ ነው፡፡ ክትባቶቹ የኦሚክሮን ተለዋጭ ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ብዙም ውጤታማ ባይሆኑም ኢንፌክሽንን እና የቫይረሱን ስርጭት ይቀንሳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት እንዲሁም ብዙ ሰዎች እስካሁን የክትባቱን ሙሉ ዙር ያልተከተቡ ስለሆኑ እራስዎን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ሲባል ተከታዮቹን በሽታውን የመከላከያ መንገዶች መጠቀምዎን መቀጠሉ አስፈላጊ ነው፦

 • አፍንጫ፣ አፍና እና አገጭ የሚሸፍን ጭንብል ያድርጉ፣
 • ከሌሎች ቢያንስ የአንድ ሜትር ርቀት ይጠብቁ፣
 • በሳል እና ማስነጠስ ወቅት በክርኖ አፍና አፍንጫዎን ይሸፍኑ እንዲሁም
 • በተደጋጋሚ እጅዎን በሳሙና እና በውሃ ያጽዱ፡፡

እነዚህ እርምጃዎች በተለይ በቂ አየር በማያገኙና በርካታ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

ጥሩ ጥራት ያለው፣ ለተወሰነ ጊዜ ሊጠቀሙበት የሚችሉት የህክምና ጭምብሎች እርስዎን ከበሽታ ከመጠበቁ እና የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ተደጋግመው ጥቅም ላይ ከሚውሉ የጨርቅ ጭምብሎች ይልቅ የበለጠ ውጤታማ ናቸው፡፡ እርስዎን ከበሽታው ለመጠበቅ እና ሌሎችም በበሽታው እንዳይያዙ ሲባል ጭምብልዎ ከጉንጭዎ እና ከአፍንጫዎ እንዲሁም ከአገጭዎ በኩል በደንብ መገጣጠም አለበት፡፡

ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሕክምና ጭምብሎችን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በደንብ ገጥመው አፍና አፍንጫን የሚሸፍኑ እና በተደጋጋሚ ሊጠቀሟቸው የሚችሉ የጨርቅ ጭምብሎችን ማድረግዎን ይቀጥሉ፡፡ የጨርቅ ጭምብልን መጠቀም ምንም ጭምብል ካለመጠቀም ይመረጣል፡፡

ሁሌም የጤና ጥበቃ መመሪያዎችን ይከተሉ፡፡

ስለመከላከያ እርምጃዎች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ለስርጭት ባለሙያዎች የተዘጋጀውን በኮቪድ-19 ላይ ቁልፍ መረጃ ለስርጭት ባለሙያዎች የተዘጋጀውን በኮቪድ-19 ላይ ቁልፍ መረጃ ያንብቡ : https://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/covid-19-resources/key-information-covid-19-broadcasters/፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰድኩ በኋላ አንቲባዮቲኮችን ብወስድ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

የጤና ባለሙያ ከክትባትዎ በፊት ወይም በኋላ አንቲባዮቲክ መድኃኒት ካዘዘልዎ ሙሉውን ጨርሶ መውሰድ አለብዎት፡፡ ትኩሳት ካለብዎት ትኩሳቱ እስኪለቅዎት ድረስ የኮቪድ-19 ክትባቱን መከተብ የለብዎትም፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰድኩ በኋላ አልኮል መጠጥ መጠጣት ለእኔ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

ክትባቱ ከመከተቡ በፊትም ሆነ በኋላ አልኮልን ጨምሮ ማንኛውንም ነገር መብላት ወይም መጠጣት የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነት ወይም ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ተጽኖ ያደርጋል የሚል ምንም ማስረጃ የለም፡፡ ሆኖም አልኮል መጠጣት ከክትባት በኋላ ሊያጋጥሙ የሚችሉ እንደ ራስ ምታት እና ድካም ያሉ መለስተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያባብስ ይችላል፡፡ ስለዚህ የክትባቱ የጎንዮሽ ህመሞች እስኪያልፍ ድረስ አልኮል ከመጠጣት መቆጠብ እንዳለብዎት የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

በኮቪድ-19 ተይዞ የሚዳብር የበሽታ መከላከያ አቅም እና የኮቪድ-19 ክትባትን ከወሰደቡ በኋላ የሚዳብር የበሽታ መከላከያ አቅም መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

ሰዎች ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ የሚያዳብሩት የበሽታ መከላከል አቅም ጠንካራ ወይም ደካማ ሊሆን ይችላል፡፡ ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ የሚዳብረው የበሽታ መከላከያ አቅም ጥንካሬው እና የቆይታ ጊዜው እንደየሰዉ ስለሚለያይ ከክትባት ከሚገኘው የበሽታ መከላከያ አቅም ጋር ሲወዳደር ውጤታማነቱ በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም፡፡

ኮቪድ-19 ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ ሲሆን የተለያዩ የረጅም ጊዜ መዘዞች ያለው ነው፡፡ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ተከትበዋ

፡፡ ስለዚህ በኮቪድ-19 ከመያዝ ይልቅ መከተብ በጣም አስተማማኝ ነው፡፡

ክትባቶች ሲኖሩ ወዲያውኑ ይከተቡ እንዲሁም እራስዎን እና ሌሎችን ለመጠበቅ የተቻለዎትን ሁሉ ያድርጉ፡፡

የተከተቡ ሰዎች ከኮቪድ-19 የሚጠበቁት እስከ መቼ ነው?

አሁን ያለው ጥናት እንደሚያመለክተው አብዛኞቹ የተከተቡ ሰዎች ሙሉ ዙሩን ከተከተቡ በኋላ እንደተከተቡት የክትባት አይነት ከሦስት እስከ ስምንት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ከከባድ ሕመም፣ ሆስፒታል መተኛት እና በኮቪድ-19 ምክንያት ከመሞት የተጠበቁ ናቸው፡፡

በተጨማሪም የባለ ሁለት ዙር ክትባትን የመጀመሪያ ዙር ብቻ መከተቡ ሁለቱንም ዙሮች ከመከተብ ያነሰ መከላከያ እንዳለው ልብ ማለት ይገባል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባት በፒ.ሲ.አር ወይም አንቲጂን ምርመራ ላይ ፖሰቲቭ ውጤትን ሊያስከትል ይችላል?

የኮቪድ-19 ክትባቱ በሁለቱ ምርመራዎች ላይ ፖዘቲቭ ውጤት አያመጣም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ምርመራዎቹ ንቁ የኮቪድ-19 በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ስለሚመረምሩ እንጂ አንድ ግለሰብ ለኮቪድ-19 የመከላከል አቅም እንዳዳበረ አይደለም፡፡

የስኳር በሽታ አለብኝ፡፡ ኮቪድ-19 እኔን ከሌላው በተለየ የሚጎዳኝ እንዴት ነው?

በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የበለጠ ከባድ የኮቪድ-19 ምልክቶች እንደሚታይባቸው እና የስኳር በሽታ ከሌላቸው ሰዎች በበለጠ በኮቪድ-19 ምክንያት የመሞት እድላቸው ሰፊ መሆኑን ያሳያሉ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የስኳር ህመም በሽታ መከላከል አቅምን ስለሚያዳክም እንዲሁም የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ እንደ ደም ግፊት እና ከመጠን በላይ ውፍረት እንዲሁም ሌሎች የጤና እክሎች ስለሚኖርባቸው ነው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ሰውነት ኮቪድ-19ን ለመዋጋት የበለጠ አስቸጋሪ ያደርጉበታል፡፡

ለዚህም ነው የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች በኮቪድ-19 የመያዙን ስጋት በመከተብ እና ቅድመ ጥንቃቄዎችን በማድረግ መቀነስ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው፡፡

የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባትን ከመከተብ በተጨማሪ የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡-

 • አፍ አፍንጫና የሚሸፍን ጭምብል ማድረግ፣
 • ከሌሎች ቢያንስ የአንድ ሜትር ርቀት መጠበቅ፣
 • በሳልና ማስነጠስ ወቅት አፍና አፍንጫን በክርን መሸፈን እና
 • እጅን በተደጋጋሚ መታጠብ፡፡

እነዚህ እርምጃዎች በተለይ በተዘጉ፣ በተጨናነቁ ወይም አየር በደንብ በማያገኙ ቦታዎች ላይ አስፈላጊ ናቸው፡፡

ያለበለዚያ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች ከሐኪማቸው ወይም ከአካባቢው የጤና ባለሙያ ጋር በተመከሩት መሰረት አመጋገባቸውን እና አኗኗራቸውን መመራታቸውን መቀጠል አለባቸው፡፡ ይህ እንደ አስፈላጊነቱ የኢንሱሊን እና ሌሎች የታዘዙ መድኃኒቶችን መደበኛ አወሳሰድን ያጠቃልላል፡፡

አሁን የካንሰር ህመምተኛ ነኝ ወይም ካሁን ቀደም የካንሰር ህመምተኛ ነበርኩ፡፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መከተብ እችላለሁ?

አንዳንድ ካንሰር ታማሚ የሆኑ ወይም በፊት የካንሰር ታማሚ የነበሩ ሰዎች ክትባቱን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ሊከተቡ ይችላሉ፡፡ የካንሰር ህመም የነበረባቸው ሰዎች ክትባቱን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መውሰድ መቻል አለመቻላቸው ሊለይ የሚችለው እንደ ክትባቱ አይነት፣ የካንሰሩ አይነት፣ ግለሰቡ አሁንም የካንሰር ሀክምናን እየተከታተሉ መሆኑ እና በሽታን የመቋቋም አቅማቸው በትክክሉ እየሰራ መሆኑን ታይቶ ይወሰናል፡፡

ካንሰር ህመምተኛ ከሆኑ ወይም ከዚህ ቀደም የካንሰር ታማሚ የነበሩ ከሆነ የኮቪድ-19 ክትባትን ጨምሮ ማንኛውንም አይነት ክትባት ከመውሰድዎ በፊት ከሐኪምዎ ወይም ከአከባቢዎ የጤና አገልግሎት ሰጪ አካል ጋር ይማከሩ፡፡

ኤችአይቪ በደሜ ውስጥ ይገኛል። የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መከተብ እችላለሁ?
የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነት እና ውጤታማነት የገመገሙ አብዛኛዎቹ ጥናቶች ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ያካትታሉ፡፡ እነዚህ ጥናቶች በአለም ጤና ድርጅት የጸደቁት የኮቪድ-19 ክትባቶች ኤችአይቪ ያለባቸው ሰዎች ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታመከተብ እንደሚችሉ ያሳያሉ፡፡

ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከተፈቀዱት ክትባቶች መካከል የትኞቹም ኮቪድ-19ን የሚያመጣውን የቀጥታ ቫይረስ አልያዙም፡፡ ስለዚህ ክትባቶቹ ለሌሎች ሰዎች እንደሚደረገው ሁሉ ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ላለ ሰዎች በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ነው፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቶች በፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒቶች ስራ ላይ ተጽኖ አያደርጉም፡፡ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ከተከተቡ በኋላ እና በጤና ባለሙያዎች በታዘዙት መሰረት የፀረ-ኤችአይቪ መድሃኒቶችን መውሰድ መቀጠል አለባቸው፡፡

ኤችአይቪ በደሜ ውስጥ ይገኛል። ራሴን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ ልወስዳቸው የሚገቡ የተለዩ እርምጃዎች አሉ?

ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በኮቪድ-19 በጠና የመታመም ዕድላቸው ከፍ ያለ እንደሆነ እውነታው ነው፡፡ ስለዚህ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ለሆኑ ሰዎች ልክ እንደሌላው ሰው የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ መቀጠሉ አስፈላጊ ነው፦

 • አፍ አፍንጫና የሚሸፍን ጭምብል ያድርጉ፡፡
 • ከሌሎች ቢያንስ የአንድ ሜትር ርቀት ይጠብቁ፡፡
 • በሳልና ማስነጠስ ወቅት አፍና አፍንጫን በክርን ይሸፍኑ፡፡
 • እጅን በተደጋጋሚ ይታጠቡ፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት፣ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በጤና ባለሙያዎች በተደነገገው መሰረት የፀረ ኤችአይቪ መድሐኒቶችን መውሰድ መቀጠል አለባቸው፡፡

የጋሜላያ (ስፑትኒክ ቪ) ክትባትን መከተብ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ያደርገኝ ይሆን?

የትኛውም የኮቪድ-19 ክትባት ኤች አይ ቪ አያስይዝም፡፡

ይሁን እንጂ ሚያዝያ 2014 ጀምሮ ደቡብ አፍሪካ የጋሜላያ (ስፑትኒክ ቪ) ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል እንደማትፈቅድ አሳውቃለች፡፡ ምክንያቱም በአንዳንድ ጥናቶች መሰረት ክትባቱ በኤች አይ ቪ የመያዝ አደጋን ሊጨምር እንደሚችል ስለሚጠቁሙ ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ተመራማሪዎች ጥናታቸውን ቀጥለውበታል፡፡

የሰውነት አለመታዘዝ ችግር ስላለብኝ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱ ይከብደኛል፡፡ ቤት ውስጥ መከተብ እችላለሁ?

እያንዳንዱ አገር ስለክትባት አቅርቦት የራሱ ዕቅድ አለው፡፡ በአካባቢዎ ክትባቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በአካባቢዎ ያለ የጤና አቅርቦት አካልን ያነጋግሩ፡፡

ኮቪድ-19 ሴቶች ላይ ከሚያስከትለው የጤና ተጽእኖ በወንዶች ላይ የሚያስከትለው የጤና ተጽእኖ ጋር ሲነጻጸር ልዩነት አለው?

ተመራማሪዎች ሴቶች እና ወንዶች በኮቪድ-19 ሲያዙ ሰውነታቸው ምላሸ አሰጣጡ ላይ ያገኙት ልዩነት የለም፡፡ ነገር ግን ኮቪድ-19 ለወንዶች፣ ለሴቶች ፣ ለወንዶች ለህጻናት ከባድ የጤና አደጋ መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ሁሉም ሰው በኮቪድ-19 ለከባድ ሕመም፣ ሆስፒታል ለመተኛት እና አልፎ ተርፎም ለሞት ተጋላጭ ነው፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጣም አስጨናቂ ነበር፡፡ እርዳታ ማግኘት እችላለሁ?

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጣም አስጨናቂ እና አሰቃቂ ጊዜ ነበር፡፡ ድብርት፣ የመንፈስ ጭንቀት፣ የአእምሮ ውጥረት፣ ወይም ሌላ ችግር ከተሰማዎት ምን አይነት አገልግሎቶች እርዳታዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ለማየት የአካባቢዎን የጤና አገልግሎት ሰጪ ያነጋግሩ፡፡ የአእምሮ ጤና እና የስነ-ልቦና ድጋፍ አገልግሎቶች በየአገሮች እና በአገር ውስጥም ይለያያሉ፡፡

የወሲብ እና የስነ ተዋልዶ ጤና እና ኮቪድ-19

 

ነፍሰ ጡር ሆኜ የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ እችላለሁ?

አዎ ነፍሰ ጡር ሆነውም የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መከተብ ይችላሉ፡፡ ተመራማሪዎች ለነፍሰ ጡር ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባቶችን ደህንነት ማጥናታቸውን ቀጥለዋል፣ እናም እስካሁን ምንም አይነት የደህንነት ስጋቶችን አላገኙም፡፡

በተለይ ለነፍሰ ጡር እናቶች መከተብ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በእርግዝና ወቅት በኮቪድ-19 ለከባድ ህመም የተጋለጡ ናቸው፡፡ በእርግዝና ወቅት በኮቪድ-19 ከተያዙ ልጃቸውን ያለጊዜው የመውለድ ወይም ለሌላ የእርግዝና ችግሮች የተጋለጡ ናቸው፡፡ የኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ለነፍሰ ጡር ሴቶች እነዚህን አደጋዎች ለማስወገድ አስተማማኝ እና የተረጋገጠ መንገድ ነው፡፡

የኮቪድ-19 ክትባቶች መካን ወይም አቅመ ቢስ ያደርጉኛል?

የኮቪድ-19 ክትባቶች መካን ወይም አቅመ ቢስ አያደርጉም፡፡ የኮቪድ-19 ክትባቶች በሴቶች ሆነ በወንዶች ላይ መካንነት ወይም አቅመቢስነትን እንደሚያስከትሉ የሚያሳይ ምንም ማስረጃ የለም፡፡

ጡት እያጠባሁ ከሆነ ኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ እችላለሁን?

አዎ ጡት እያጠቡ ከሆነ የኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ይችላሉ፡፡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ከተፈቀዱት ክትባቶች መካከል የትኛውም የቀጥታ ኮቪድ-19 ቫይረስ አልያዘም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የተከተቡ ሴቶች ኮቪድ-19ን በእናት ጡት ወተት ለልጆቻቸው የማስተላለፍ ስጋት የለባቸውም፡፡ እንዲያውም በተከተቡ እናቶች የጡት ወተት ውስጥ ያሉ ፀረ ተህዋስ አካላት ወደ ልጆቻቸው ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ ይህ ጡት የሚያጠቡ እናቶች ሕፃናትን ከኮቪድ-19 ለመከላከል ሊረዳ ይችላል፡፡

በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባትን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መከተብ ይችላሉ?
አዎ ወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባትን ቢከተቡ ምንም ችግር የለውም፡፡ አንዲት ሴት በክትባት ቀጠሮዋ ቀን የወር አበባዋ ቢመጣም መከተብ አለባት፡፡

የወር አበባ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማዘግየት ምክንያት አይደለም፡፡

ዶዞች

 

ሁለት ዙር የክትባቱ መጠን ከአንድ ዙር ብቻ በተሻለ መልኩ ከበሽታው ይጠብቀኛል?

ምንም እንኳን ጃንሰን (ጆንሰን እና ጆንሰን) ክትባት የሚያስፈልገው አንድ ብቻ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የኮቪድ-19 ክትባቶች በየሳምንቱ ልዩነት ሁለት ዙር ያስፈልጋቸዋል፡፡

ከሚያስፈልጉት ሁለት የክትባት ዙሮች አንዱን ብቻ መውሰድ ከኢንፌክሽን እና ከከባድ በሽታ የመከላከል ሃይሉ በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡

በኮቪድ-19 ላይ ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ ሰዎች ኮቪድ-19 ሊይዛቸው ይችላል፡፡ አልፎ ተርፎም በሽታውን ወደ ሌሎች ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን መከተብ እነዚህ አደጋዎችን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡

ሙሉ የክትባት ዙሮቹን የተከተቡ ሰዎች የመጨረሻ ዙር ክትባታቸውን ባጠናቀቁ ከ2-4 ሳምንታት በኋላ ነው ሙሉ ለሙሉ ከበሽታው የሚጠበቁት፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውነታቸው ኮቪድ-19ን ለመዋጋት የሚያስፈልጉትን ፀረ ተህዋሲያን አካላት እየፈጠረ የፈጥራል፡፡

ክትባቶችን መቀላቀል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው – ለምሳሌ የአንድ ክትባት የመጀመሪያ ዙር እና የሁለተኛ ዙር የተለያየ ክትባት መውሰዱ?
ተመራማሪዎች የኮቪድ-19 ክትባቶችን መቀላቀሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆኑን አለመሆኑን እያጠኑ ነው፡፡ በዚህ ጥያቄ ላይ ያሉ መመሪያዎች ከአገር አገር ይለያያሉ፡፡ የብሔራዊ የጤና ባለሥልጣናት መመሪያዎችን ሁል ጊዜ ይከተሉ፡፡

የኮቪድ-19 “የማጠናከሪያ ክትባት ዙሮች” ወይም “የማጠናከሪያ ክትባቶች” ምንድናቸው?

ሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት ማለት ከቫይረሱ ሙሉ ጥበቃ ለማግኘት አስፈላጊውን የክትባት ዙሮች መከተብ ማለት ነው፡፡ እንደ አስትራ ዘኔካ እና ሞደርና ያሉት አብዛኛዎቹ ክትባቶች፣ ሙሉ የክትባት ዙሮች ሁለት ናቸው፡፡ ለሌሎች ክትባቶች፣ እንደ ጃንሰን ክትባት (ጆንሰን እና ጆንሰን) ፣ ሙሉ ክትባቱን በአንድ ዙር ይገኛል፡፡

“የማጠናከሪያ ክትባት ዙሮች” ወይም “የማጠናከሪያ ክትባት” ከሙሉ የክትባት ጊዜ በተጨማሪ የሚሰጥ የኮቪድ-19 ክትባት ነው፡፡ የኮቪድ-19 ክትባቶች ከበሽታው ለዘለዓለም ላይከላከሉ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ አገሮች ዜጎቻቸው በዘላቂነት ጤናቸው እንዲጣበቕ ማጠናከሪያ ክትባቱን እንዲወስዱ እያቀረቡላቸው ነው፡፡

ለኮቪድ-19 ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ተጨማሪ ክትባት ያስፈልጋቸዋል?

የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመውን ጨምሮ ለኮቪድ-19 ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ሙሉ ክትባት ከተከተቡ በኋላ ሙሉ በሽታውን የመከላከል አቅም አያገኙም፡፡ ስለዚህ እነሱን ለመጠበቅ ተጨማሪ የክትባት ዙር ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

ይህ ተጨማሪ ክትባት ከማጠናከሪያ ዙር ክትባቱ የተለየ ነው፡፡ ከአንድ ወይም ከሁለት ዙር በኋላ በቂ መከላከያ ለማያገኙ ሰዎች እንደ ክትባቱ ሙሉ ዙር አካል ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ተጨማሪ ክትባቶች እነዚህ ግለሰቦች ከኮቪድ-19 የተሻለ መከላከያ እንዲያዳብሩ ይረዷቸዋል፡፡

 

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጆች፦ ቪጄይ ከደፈርድ፣ በፋርም ሬዲዮ ኢንተርናሽናል አስተዳዳሪ ኤዲተር እና

ሃና ቴሊየር፣ ፋርም ሬዲዮ ኢንተርናሽናል የሀብት አስተባባሪ

ይህ ግብአት እንዲዘጋጅ የደገፈው የጀርመን ፌዴራል የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር በዶይቸ ጌሴልስቻፍት ፉር ኢንተርናሽናል ዙሳምሜናርቤይት ጂኤምቢኤች (ጂአይዜድ) እና በናይጄሪያ የሚገኘው አረንጓዴ ፈጠራ ማዕከል ለግብርና እና የምግብ ዘርፍበተሰኘው ፕሮጄክት ነው፡፡