English, Français

Script .0

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ለአዘጋጆች ማስታወሻ

ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ኮቪድ-19ን በሚመለከት ለአድማጮች ጠቃሚ መረጃዎችን ያዘሉ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት እና የአድማጮችን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲረዳችሁ የተለያዩ የመረጃ ግብዓቶ አዘጋጅቷል። እነዚህን ግብዓቶች ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማግኘት ይቻላል፦ http://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/covid-19-resources/

በተለይ የክትባት ተደራሽነትን በሚመለከት በአካባቢው የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ማነጋገሩ ይመከራል። ኮቪድ- 19 እና ክትባቶችን በሚመለከት ያሉ ጥያቄዎችን ለመረዳት አድማጮችን እንዲሁም በማህበረሰቡ ላሉ ስጋቶች ምላሽ መስጠት የሚችሉና ክትባት መከተብን ማበረታታት የሚችሉ የሃገር ሽማግሌዎችን ማነጋገር ይመከራል።

Script

መሰረታዊ መረጃ

የኮቪድ-19 ክትባቶች አገልግሎት ላይ አዋዋል ምን ይመስላል?

የኮቪድ-19 ክትባቶች እንዴት አገልግሎቶችን በዝርዝር ለመረዳት እነዚህን ሦስት ነገሮች መረዳቱ አስፈላጊ ነው፡በሽታ አምጪ ተህዋስ፣ ፀረ እንግዳ አካል እና አንቲጂን።

በሽታ አምጪ ተህዋስ ወይም ፓቶጂን በሽታን የሚያስከትል ጥቃቅን ተህዋስ ነው። ሳርስኮቭ-2 የተሰኘው ቫይረስ የኮቪድ-19 በሽታን የሚያስከትለው በሽታ አምጪ ተህዋስ ነው።

ሰውነታችን በሽታ አምጪ ተህዋሶችን ለመከላከል ጸረ አንግዳ አካላትን ወይም አንቲቦዲስ ያመርታል። በጸረ አንግዳ አካላቶች አማካኝነት ሰውነታችን በሽታ አምጪ ተህዋስያንን ለይቶ ያስወግዳል።

ሰውነታችን ፀረ እንግዳ አካላት እንዲያመርት የሚያደርገው የበሽታ አምቺ ክፍል አንቲጂን ይባላል። ሰውነታችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንቲጂን ሲጋለጥ የበሽታ መከላከያ ስርዓታችን ለዚያ አንቲጂን የተለየ ፀረ እንግዳ አካላት በማምረት ምላሽ ይሰጣል

ለኮቪድ-19 በሽታ የሚሆኑ ሁለት አይነት ክትባቶች አሉ። በአብዛኛው የተለመደው አይነት (ለምሳሌ አስትራ ዜነኤካ፣ ሲኖፋርም ቤይዢንግ፣ ጋሜላያ (ስፐትኒክ አምስት) ፣ ሲኖቫክ፣ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን፣ እና ብሃራት ባዮ ቴክ) በውስጣቸው የተዳከመ ወይም የማይንቀሳቀስ የሳርስኮቭ-2 አንቲጂን ይዘት አላቸው። አንድ ሰው ክትባቱን ሲከተብ አንቲጅንን የሚዋጋ የበሽታ መከላከያ ምላሽን በሰውነቱ ውስጥ ይቀሰቀሳል።

ሌላው የክትባት አይነት (የኤም.ኤን.አር. ክትባት ተብሎ የሚጠራው እና ፋይዘር እና ሞደርና ክትባቶች የተወከለው ሲሆን) አንቲጂንን በውስጡ አልያዘም። በምትኩ በውስጡ የአንቲጂን ጄኔቲክ ንድፍ ይዟል። አንድ ሰው የኤም.ኤን.አር. ክትባት ሲከተብ የሰውነቱ የበሽታ መከላከያ ስርዓቱ ሳርስኮቭ-2 አንቲጂን ላይ የመከላከል ምላሽ ለማስነሳት ያንን ንድፍ ይጠቀማል።

ክትባቱ የተዳከመ ወይም የማርንቀሳቀስ የአንቲጂን አካል ወይምሰውነት ፀረ እንግዳ አካላትን ለማምረት ሊጠቀምበት የሚችለውን ንድፍ ቢያካትትም አንድ ሰው በኮቪድ-19 በሽታ እንዲታመም አያደርገውም። ይልቁንም ሰውነት ውስጥ ያለው የበሽታ መከላከያ ስርዓት ትክክለኛው በሽታ አምጪ ተህዋስያን እንዳጋጠመው ቆጥሮ የሳርስቾቭ-2 ፀረ እንግዳ አካላት እንዲፈጠሩ በማድረግ ምላሽ እንዲሰጥ ያነሳሳል

ክትባቶቹ እንዴት በፍጥነት ሊፈጠሩ ቻሉ?

ከዚህ ቀደም በነበሩ ጊዜያቶች ክትባት ፈጥሮ ለህዝብ ለማሰራጨት በርካታ አመታትን ይፈጅ ነበር። ነገር ግን የኮቪድ-19 ክትባቶች ቫይረሱ ከተከሰተ አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ለህዝብ ቀርቧል። ይህ ሊሆን የቻለበት በርካታ ምክንያቶች አሉ።

ለብዙ አሥርተ ዓመታት ክትባቶችን በመፍጠሩ ዘርፍ ሲታይ የቆየው በጣም አዝጋሚ ሂደት የገባቸው የምርምር ቡድኖች እና የህዝብ ጤና ኤጀንሲዎች የክትባት ፈጠራ ስራቸውን ጥራትና ፍጥነት አሻሽለዋል። እንዲሁም ተመራማሪዎች የኮሮና ቫይረስ በሽታዎችን ላለፉት 20 ዓመታት ሲያጠኑ የቆዩ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በሰዎች ላይ ጉዳት ከደረሱት ሳርስ እና መርስየተባሉ ሁለት የኮሮና ቫይረስ በሽታዎች ትምህርት ወስደዋል። የኮቪድ-19 በሽታን የሚያመጣው ሳርስኮቭ-2 ቫይረስ ከታወቀ በኋላ ሳይንቲስቶች የዲ.ኤን. ጂኖም (የዘረመል ኮድ) መለያውን በሁለት ሳምንታት ውስጥ ነውሰሩት። ይህ ደግሞ በኮቪድ-19 ላይ ምንን ዒላማ አድርጎ ክትባት መሰራት እንደሚገባው በትክክል እንዲለዩ ረድቷቸዋል።

በተጨማሪም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ጠንካራ አጋርነቶች ተፈጥረዋል። በብዙ አገራት ውስጥ ያሉ ተመራማሪዎች እና በርካታ ድርጅቶች መረጃን አጋርተዋል ቫይረሱን ለመዋጋት ተመራጭ ናቸው ያሏቸውንም መንገዶች ተወያይተውባቸዋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ ለትርፍ ያልተቋቋሙ አካላት፣ የመንግስት አካላት፣ የግል ዜጎች፣ የጤና ኩባንያዎች እና ሌሎች ምንጮች የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

አብዛኛውን ጊዜ በክሊኒካዊ ሙከራዎች ውስጥ ክትባቶችን ለመሞከር ዓመታት ፈጅቷልሙከራዎችን ማደራጀት፣ በጎ ፈቃደኞችን ማሰባሰብ እና ደህንነት እንዲሁም ውጤታማነትን በተረጋገጠበት መልኩ የሚያስፈልጉትን ሶስት የተለያዩ ክሊኒካዊ ሙከራ ደረጃዎች ማከናወኑ አብዛኛውን ጊዜ ክትባቱን ለማዘጋጀት ረጅም ጊዜ ሲፈጅ የቆየ አሰራር ነው።

ነገር ግን ለኮቪድ-19 ክትባቶች የተለያዩ የሙከራ ደረጃዎች ከተለያዩ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ጋር በተደራራቢ መርሃ ግብሮች ከመካሄዳቸውም በላይ የክትባት ማረጋገጫ ኤጀንሲዎች የሙከራ ውጤቶቹ እንደተገኙ ከስር ከስር አጥንተዋል።

በተጨማሪም በርካታ ኩባንያዎች ሙሉ በሙሉ ከመጽደቃቸው በፊት ክትባቶቹን ማምረት እንዲጀምሩ የሚያስችልገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ይህ መደረጉ በኋላ ለፀደቁት ክትባቶች ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ የፈጅ የነበረውን ጊዜ በወራት በማሳጠር ውጤት አስገኝቷል።

ምስጋና የሚገባቸው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶች በላብራቶሪዎች ውስጥ ብዙ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን እንዲያልፉ የበኩላቸውን ሚና መጫወታቸውን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ክትባቶቹ በዓለም ዙሪያ ባሉ ሀገራት በመንግስት የጤና ኤጀንሲዎች የተቀመጡን ጥብቅ ደረጃዎች የሚያሟሉ ናቸው።

ክትባቶቹ በመጀመሪያ የተሞከሩት በእንስሳት ላይ ነው። ከዚያም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ባካተቱ ተከታታይ ክሊኒካዊ ሙከራዎች ተፈትነዋል። ከእነዚህ ሙከራዎች የተገኘው መረጃ ተሰብስቦ ለጤና ባለስልጣናት እና በዓለም ዙሪያ ላሉ ሌሎች የምርምር ቡድኖች ቀርቧል። እነዚህ ቡድኖች በአሁኑ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉ ክትባቶች ደህንነታቸውን የተጠበቁ እና ውጤታማ መሆናቸውን ከመወሰናቸው በፊት መረጃውን በጥንቃቄ ገምግመዋል።

በተጨማሪም በክትባቶቹ ላይ ሳይንሳዊ እና የቁጥጥር ስራዎች እንዳልቆሙ ልብ ሊባል ይገባል። ክትባት የሚወስድ ማንኛውም ሰው ስለ ግል ልምዱ መረጃንማጋራት ክትባቶቹ እንዴት እንደሚሠሩ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር ማድረግ ይችላል።

ክትባቱን የተከተቡ ሰዎችሁሉንም የኮሮናቫይረስ አይነቶች መቋቋም ይችላሉ?

ኮቪድ-19 ከኮሮናቫይረስ ዝርያዎች መካከል አንዱ ምሳሌ ነው። ኮሮናቫይረሶች በአዕዋፋትና አጥቢ እንስሳቶች ላይ የቫይረስ በሽታዎችን የሚያስከትሉ ተያያዥ ቫይረሶች ናቸው። በነዚህ ቫይረሶች ከሚከሰቱ በሽታዎች መካከል እንደ ምሳሌ ሆነው ሊጠቀሱ ከሚችሉት መሃል ጉንፋን (በሌሎች የቫይረስ አይነቶችም ሊከሰት ይችላሉ) አንዲሁም በሰው ጤና ላይ ከፍታኛ ተጽኖ የሚያሳድሩት እንደ ሳርስ፣ መርስ እና ኮቪድ-19 በሽታዎች ይገኙበታል።

የኮቪድ-19 ክትባቶች የተዘጋጁት ኮቪድ-19 በሽታን የመቋቋም አቅምን ከፍ ለማድረግ እንጂ ሌሎች በኮሮናቫይረስ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመቋቋም አይደለም።

ሁሉም ቫይረሶች ያለማቋረጥ የመለዋወጥና አዲስ ሆኖ በየጊዜው የመመለስ ባህሪ አላቸው። የተወሰኑት የኮቪድ-19 ተለዋጭ ቫይረሶች ከመጀመሪያው የኮቪድ-19 ቫይረስ በበለጠ የመሰራጨት አቅም ያላቸው እና/ወይም በጤና ላይ ከፍ ያለ ተጽኖ የማረግ አቅም ያላቸው ናቸው። ከመስከረም 2014 አንስቶ ስራ ላይ እየዋሉ የሚገኙ ክትባቶች ዴልታን ጨምሮ በሁሉም የኮቪድ-19 ቫይረሶች ምክንያት በከፍታኛ ደረጃ አሳሳቢ ህመምን እና በሃኪም ቤት ተኝተው የሚታከሙ ህሙማንን ቁጥር እንዲቀንስ አድርገዋል።

ሆኖም፣ የዴልታ ተለዋጭ ስርጭትን ለማስቆም ክትባቶች በተወሰነ ወይም በመጠኑ ውጤታማ አይደሉም። ሁለቱንም ዙር የተከተቡ ሰዎች በከባድ ሕመም የመጠቃት እና ሆስፒታል የመተኛት እድላቸው በጣም አናሳ ነው።

ከክትባት በኋላም በኮቪድ-19 የመያዝ ስጋቱ ይኖራል? ወይስ ይህ ሃሰተኛ ዜና ነው?

ሙሉ በሙሉ ክትባት የወሰዱ ሰዎች በኮቪድ-19 በተለይም በአዲሱ እና በሽታው የመሰራጨት ሃይሉ ከፍተኛ በሆነው በዴልታ ተለዋጭ በሽታ ሊያዙ የሚችሉበት ዕድል አለ። ተከትበው በበሽታው የተያዙ ሰወችም በሽታውን ማስተላለፍ ይችላሉ። ሆኖም ግን በሽታውን የማሰራጨት ደረጃቸው ካልተከተቡ ወይም በከፊሉ ከተከተቡ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ነው። በተጨማሪም ክትባቱን የተከተቡ ሰዎች ከልተከተቡት ጋር ሲነጻጸሩ በበሽታው ቢያዙ እንኳን በህመም የመዳከም ዕድላቸው እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው።

ክትባቱን ከተከተብኩኝ በኋላም በኮቪድ-19 የመያዝ እድል እንደሚኖር እረዳለሁ። የክትባቱን የጎንዮሽ ጉዳቶች ላለማስተናገድ ከመከተብ ብቆጠብስ?

የሚመከረውን ክትባት መከተብ ከከባድ በሽታ ከመከላከሉም በላይ በኮቪድ-19 በሽታ ምክንያት ሃኪም ቤት ከመተኛትና ከመሞት ይታደጋል። መከላከያው ከፍተኛ የመሰራጨት አቅም ያለውን የዴልታ ተለዋጭ ቫይረስን ጨምሮ ሁሉንም ተለዋጭ ቫይረሶችን ይከላከላል። የሚመከሩ ክትባቶች ላይ በቂ መረጃ እንዲኖሮት የአለም ጤና ድርጅት አደጋ ጊዜ አጠቃቀም ዝርዝርን ያንብቡ። በፋይዘር፣ አስትራዜኔካ፣ ጆንሰን እና ጆንሰን፣ ሲኖፋርም እና ሞደርና በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል።

ክትባት ከወሰዱ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የጎንዮሽ ጉዳቶች ይከሰታሉ። የመጀመሪያው የጅምላ ክትባት መርሃ ግብር ታህሳስ 2013 ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በዓለም ዙሪያ 6.5 ቢሊዮን በላይ የኮቪድ -19 ክትባት ተሰጥቷል። የክትባት የጎንዮሽ ህመሞች ሁልጊዜ ቀላል እና በተለምዶ የሚከተሉትን ምልክቶች ያጠቃልላሉ፡የእጅ ህመም፣ መለስተኛ ትኩሳት፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና ጡንቻ ወይም መገጣጠሚያ ላይ ህመም። እነዚህ ምልክቶች ሰውነትዎ ለኮቪድ-19 ቫይረስ መከላከያ እየገነባ መሆኑን ያሳያሉ።

የአስትራዜኔካ እና ጃንሰን (ጆንሰን እና ጆንሰን) ክትባቶችን ከወሰዱ ሰዎች መካከል 3 እስከ 30 ቀናት ውስጥ የደም መርጋት ሪፖርት ተደርጓል። እነዚህ ውጤቶች እጅጉን አሳሳቢ ቢሆኑም ከስንት አንዴ ነው የሚከሰቱት።

የሆነ ሆኖ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ላልወሰዱ ሰዎች ምክር ሲለግሱ በኮቪድ-19 የመያዝ ስጋቱ በፍቃድ ያለውን ክትባትባት በመውሰድ ምክንያት ተጓዳኝ ህመሞችን ከሚያስተናግዱ ሰዎች ጋር ድጽዝውው ያልተከተቡ ሰዎች ጤናቸው ላይ የከፋ አደጋ እንደሚጋረጥ ያስረዳሉ።

የዓለም ጤና ድርጅት የአስቸኳይ ጊዜ አጠቃቀም ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ክትባቶች ኮቪድ-19 የሚያመጣው የቀጥታ ቫይረስን እንደማይዙ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ይህ ማለት የኮቪድ-19 ክትባቶች በኮቪድ-19 በሽታ እንዲያዙ አያደርጉም ማለት ነው።

በኮቪድ-19 ተይዞ የሚያቅ ሰው ክትባቱን መከተብ ይችላል?

አዎ፣ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ሙሉ ክትባቱን እንዲወስዱ ይመከራል። በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው የሚያቁ ሰዎች በመጠኑም ቢሆን በሽታውን የመቋቋም አቅምን ቢያዳብሩም በሽታውን የመቋቋም አቅማቸው እስከ መቼ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል እና ምን ያህል ጠንካራ እንደሚሆን በእርገጠኝነት ለመናገር አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ የዓለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች የጤና ድርጅቶች ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ እንዲከተቡ ይመክራሉ። ለዚህም ነው የአለም ጤና ድርጅትና ሌሎች የጤና ድርጅቶች የተሟላ ክትባቱ እንዲወሰድ የሚመክሩት።

ክትባቱን ከተከተብኩ በኋላ የፊት ጭምብል ማድረጌ ለምን አስፈለገ?

ኮቪድ-19 ክትባቶች ከከባድ ሀመምና ከሞት በጥሩ ሁኔታ ይከላከላሉ። ተጨማሪ ጥናት ቢያስፈልገውም አሁን አሁን እየተገኙ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኮቪድ-19 ክትባቶች በበሽታው የመያዝና የቫይረሱን የስርጭት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንሱ ያሳያሉ። በዚህም ምክንያት እና ብዙ ሰዎች ገና ሙሉ በሙሉ ክትባት ስላልወሰዱ፣ እራስዎን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ሲባል ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን መጠቀሙን መቀጠሉ ግድ ይላል።

የራሳቸውንና የሌሎችን ጤና ለመጠበቅ ሲባል፣ ክትባት የወሰዱ ሰዎች ጭምብል ማድረጋቸውን መቀጠል፣ ቢያንስ 1 ሜትር ርቀት ከሌሎች መጠበቅ፣ በሳልና ማስነጠስ ወቅት አፍና አፍንጫን በክርን መሸፈንና እጃቸውን በተደጋጋሚ ማጽዳት አለባቸው። ግለሰቦች በተዘጋ፣ በተጨናነቁ ወይም በደንብ አየር በማይተላለፍባቸው ቦታዎች ውስጥ ሲሆኑ በተለይ እነዚህን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል በጣም አስፈላጊ ነው። እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ተመርኩዘው በተገቢው ባለስልጣን የሚወጡ መመሪያዎችን ሁልጊዜ ይከተሉ።

መከላከያ መንገዶች ዙሪያ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡ ኮቪድ-19 በሚመለከት ለአዘጋጆች ቁልፍ መረጃዎች

ህንድ የክትባቱ መገኛ ብትሆንም ህንዶች ለምን በኮቪድ-19 ምክንያት እየሞቱ ይገኛሉ?

የህንድ የህዝብ ብዛት ቁጥር በግምት 1.4 ቢሊዮን ይሆናልበዚህም ምክንያት ሁሉንም ሰው መከተቡ ፈታኝ ስራ ነው። ሃምሌ 17, 2013 ድረስ በግምት 33% የሚሆነው የህንድ ህዝብ አንደኛ ዙር ክትባቱን ተከትቧል፣ 9.5% ብቻ የሚሆነው የሃገሪቱ ዜጋ ነው ሁለቱንም ዙር ክትባት የተከተበው። ከዚህም በተጨማሪ የሕንድ የጤና አገልግሎቶች ከኮቪድ-19 ጋር በተዛመዱ ሕመሞች የሚሰቃዩ ሰዎችን የመለየት፣ የማግለል እና የማከም አቅማቸው በተለይ በገጠራማ አካባቢዎች ውስን ነው።

የክትባት መጠኖች

ምንም ያልተከተቡ, አንዴ ብቻ የተከተቡ ወይም ሁላቴ የተከተቡ ታማሚዎች ወይም 2 ጊዜ የተከተቡ ኮቪድ-19 እንዴት እየተቋቋሙት ይገኛሉ?

በአለም የጤና ድርጅት የአደጋ ጊዜ አጠቃቀም ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት አብዛኛዎቹ የኮቪድ19 ክትባቶች በሳምንታት ልዩነት ሁለቴ መከተብን እንደ መስፈርት ሲያስቀምጡ የጃንሰን (ጆንሰን እና ጆንሰን) ክትባት ግን አንድ ክትባት ብቻ ብቁ ነው ይላል።

ሁለት ዙር ክትባት ከሚጠይቁ የክትባት አይነቶች አንዱን ዙር ብቻ የሚወስዱ በሽታውን የመከላከል አቅማቸው ሁለቱንም ዙር ከወሰዱ ሰወች ይልቅ በጣም ያሽቆለቆለ ነው።

እንደ ሌሎች ክትባቶ ሁሉ (ኩፍኝን የመሳሰሉት) የኮቪድ-19 ክትባትን አሟልቶ መከተቡ በበሽታው ላለመያዝ ወይም ላለመታመም ዋስትና አይደለም። ሆኖም የሚፈለገውን ክትባት መጠን አሟልቶ መከተቡ በበሽታው ቢያዙ እንኳን ከከባድ ህመም ወይም ሃኪም ቤት ከመተኛት ከማዳኑም በላይ ለሞት የመዳረግ እድሉ በጣም ጠባብ ነው።

የኮቪድ-19 ክትባትን አሟልተው ቢከተቡም 2-4 ሳምንታት ድረስ ክትባቱ ከበሽታው መከላከል እንደማይጀምር ማስታወስ ያስፈልጋል።

የመጀመሪያው ዙር ክትባት ውጤታማነቱ ምን ያህል ነው?

ክትባቱ በሁለት ዙር ማለቅ ያለበት ሲሆን የመጀመሪያ ዙሩን ብቻ መከተቡ ሁለቱንም ዙር ከመከተብ ጋር ሲነጻጸር በሽታውን ከመከላለል ረገድ አንድ ዙር ብቻ መከተቡ ደካማ ነው።

በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ዙር ክትባቶችንመከተቡ ኮቪድ-19 እስከ ምን ያህል ጊዜ እንደሚከላከል በግልጽ አይታወቅም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ክትባቶቹ ከተገኙ አንድ አመት እንኳን ስላልሞላቸው በቂ መረጃ ስለሌለ ነው።

ሆኖም በተለይ በዕድሜ ገፋ ላሉ ሰወች የክትባቶች ውጤታማነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እንደሚሄድ የታወቀ ነው። በቅርቡ የአለም ጤና ድርጅት የስትራቴጂክ አማካሪ ኮሚቴ ሲኖቫክ እና ሲኖፋርም ክትባቶችን የወሰዱ በእድሜ ገፋ ያሉ ሰወች ሶስተኛ ዙር ክትባት እንዲከተቡ ሃሳብ አቅርቧል። በተለያዩ ምክንያቶች በሽታን የመቋቋም አቅማቸው የተዳከመ ሰወችም ከሁለቱ ዙር ክትባቶች ብቻ በሽታን የመቋቋም አቅማቸው በበቂ ሁኔታ ላይደራጅ ስለሚችል ሶስተኛ ዙር ክትባት እንዲከተቡ ይመከራል።

ሁለተኛ ዙር ክትባቱን አለመከተብ ምን አይነት ተጽእኖ ያስከትላል?

ክትባቱ በሁለት ዙር መከናወን ሲኖርበት አንዱን ዙር ብቻ መከተቡ ኮቪድ-19 በሽታ የመከላከል አቅምን አዳክሞ የመታመም ስጋትን ከፍ ያደርገዋል።

ክትባቱ በሽታውን የመከላከል ስራውን የሚጀምረው የመጨረሻው ዙር ክትባት ከተሰጠ ከሳምንታት በኋላ እንደሆነ መረዳቱ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ሁለቱንም ዙር የተከተበ ሰው የክትባቱን ሙሉ ጥቅም ማግኘት የሚጀምረው ሁለተኛውን ዙር ከተከተቡ በኋላ 2-4 ባሉት ሳምንታት ውስጥ ነው።

የክትባት አይነቶችን አቀላቅሎ መጠቀሙ ለምሳሌ የሁለተኛ ዙር ክትባቱ ከመጀመሪያው ዙር የክትባት አይነት ጋር አንድ አይነት ያልሆነን መከተቡ ከውጤታማነትና ከስጋት ነጻነት አንጻር ምን ያህል አስተማማኝ ነው?

በአሁኡ ወቅት ተመራማሪዎች በሁለቱ የክትባት ዙሮች የትተለያዩ አይነት ክትባቶችን መጠቀሙ ተቀባይነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ጥናቶችን እያከናወኑ ነው። የአለም ጤና ድርጅት እንዳሳወቀው የአስትራ ዜኔካ ክትባት እጥረት ባሉባቸው አካባቢዎች የመጀመሪያ ዙር ክትባቱ የአስትራ ዜኔካ ሆኖ ሁለተኛው ዙር ደግሞ የፋይዘር ክትባት ቢሆን ጤና ላይ የሚያስከትለው ስጋት አይኖርም እንዲሁም ውጤታማ ይሆናል።

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጅ፦ ቪጄይ ከደፈርድ፣ አስተባባሪ ኤዲተር፣ ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል

ሃያሲ፦ የአለም ጤና ድርጅት

ይህ ግብዓት የተዘጋጀው በጀርመን የፌዴራል ኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር እና በናይጄሪያ በሚገኘው የጂ.አይ.ዜድ ፕሮጀክት በሆነው የግብርና እና የምግብ ዘርፍ አረንጓዴ ፈጠራ ማዕከል በኩል በተደረገ ድጋፍ ነው።