ቃለ ምልልስኤስ

ሁሉ
 • ሁሉ
 • ማህበራዊ ጉዳዮች
 • የመሬት ጉዳዮች
 • የሰብል ምርት
 • የአካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ
 • የአየር ንብረት ለውጥ
 • የአፈር ጤንነት
 • የእንስሳት እርባታ እና ንብ ማነብ
 • የድህረ-መከር እንቅስቃሴዎች
 • የጾታ እኩልነት
 • ግብርና
 • ጤና

ኮቪድ-19 በፍሬሽ አትክልት አቅርቦት ላይ ያሳደረው ተጽእኖ እና አርሶ አደሮች እና ሌሎችም ከችግሩ አንጻር እየወሰዷቸው ያሉ እርምጃዎች

የድምጽ ኢፌክት: ስልክ ይደውላል ካምቦሊ: ሃሎ፣ ካምቦሊ ካንያንታ ነኝ ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት፡፡ ማን ልበል? ፊሊዩስ: ፊሊዩስ ቻሎ ጄሬ እባላለሁ፡፡ ብሪዝ ኤፍኤም ላይ ግብርና የንግድ ሥራ ነው የሚለው ፕሮግራም አዘጋጅ ነኝ፡፡ በስልክ ቃለመጠይቅ ላደርግሎት እችላለሁ? ካምቦሊ: ስለምን ጉዳይ? ፊሊዩስ: የግብርናው ማሕበረሰብ እና የገበያ አጋሮቻቸው ላይ ኮቪድ-19 ያመጣው ተጽእኖን በተመለከተ፡፡ ካምቦሊ: ኮቪድ-19 ተብሎ ስለሚጠራው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማለትህ…

የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የመጤ ተምች መንጋን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ መጤ ተምቹ

ኒዮ ብራውን፡- እንደምን አደራችሁ (ዋላችሁ/አመሻችሁ)! ዛሬ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የመጤ ተምች መንጋን ለመከላከል እንዴት እየጣሩ እንደሆነ እና ማሳቸው ላይ ትልቅ ጉዳት ከማድረሱ በፊት እንዴት እየተከላከሉት እንደሆነ እናወራለን፡፡ የድምፅ ግብአት፡- ኒዮ ብራውን፡- በኢትዮጵያ በልግ አየተባለ የሚጠራው ደረቅ ወቅት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ እና ሰሜን መካከለኛ ክፍል ወደሚገኘው የአማራ ክልል ተጓዝኩ፡፡ በአማራ ክልል ከ85 ከመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ…

የዕቀባ እርሻ

መሸጋገሪያ ድምፅ አቅራቢ 1: ጤና ይስጥልኝ ! ወደ አርሶ አደር ፕሮግራምዎ እንኳን በሰላም መጡ ! የዛሬ ፕሮግራማችን የዕቀባ እርሻ እና የአነስተኛ የእርሻ ድግግሞሽ ጠቀሜታ ላይ ያተኩራል፡፡ የትዮጵያ አርሶ አደሮች ምርትን ይጨምራል ብለው በመተማመን ማሳዎቻቸውን ደጋግመው የማረስ ዝንባሌ አላቸው፡፡ አነስተኛ የእርሻ ድግግሞሽ ከማሳዎቻቸው ማግኘት የሚችሉትን የምርት መጠን እንዳያገኙ ምክንያት እንደሚሆንባቸው ያምናሉ፡፡ በእርግጥ አይደለም አንዴ፣ ሁለቴ፣  ለብዛኛዎቹ ሰብሎቻቸው…

ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን በአንክሮ መከታተል: የቦቆሎ ምርትዎን እንዳያወድም ተምቹን መቆጣጠር

አቅራቢ: ጤና ይስጥልኝ አድማጮች ፡፡ በዛሬው ፕሮግራማችን የቦቆሎ ሰብሎቻቸው በፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች እንዳይጠቃ ጥረት እያደረጉ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ የኢትዮጵያዊ ሴት አርሶ አደር ወይዘሮ አይናዲስ ተመኩሮን እናካፍላችኋለን፡፡ ወይዘሮ አይናዲስ እባክዎትን ስምዎን ለአድማጮቻችን ያስተዋውቁልኝ፡ ወይዘሮ አይናዲስ: አመሰግናለሁ፡፡ ስሜ አይናዲስ ጥላሁን እባላለሁ፡፡ የምኖረው በጎጃም ዞን በምትገኝ አብደጎማ ጣቢያ ነው፡፡ ዕድሜዬ 45 ዐመት ሲሆን…

በደቡብ ወሎ አርሶ አደሮች ማሽላን በመንከባከብ ኑሮአቸውን እያሻሻሉ ነው

ነፃነት ኃይሉ፡          ጤና ይስጥልን፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች የማሽላ ምርታቸውን ተንከባክበው እንዴት ኑሮአቸውን እንዳሻሻሉ እንመለከታለን፡፡ የድምፅ ግብዓት፡- የመኪና ድምፅ እና የዝናብ ድምፅ፣ ከስር በትንሹ ይሰማል ነፃነት ኃይሉ፡          ወሩ ነሓሴ ነው፡፡ ይህ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች ዝናባማ የክረምት ወቅት ነው፡፡ መሬቱ ረጥቦ አካባቢው አረንጓዴ ለብሷል፡፡ መላከዓ ምድሩ ማራኪ ነው፡፡ በመንገዳችን ላይ…

የመሬት አዘገጃጀት ለባቄላ

አቅራቢ: እንኳን ወደ (የሬድዮ ፕሮግራሙ) በደህና መጡ፡፡ ዛሬ ከርዕሰ መዲናችን አዲስ አበባ ወጣ ብለን በአማራ ክልል የበቃሎ ቀበሌ ማህበረሰብን እየጎበኘን ነው፡፡ በባቄላ ዙሪያ እንነጋገራለን፡፡ ሰኔ ወር የመጀመሪያው ሳምንት ነው፡፡ የባቄላ ዘር የሚዘራበት ወቅት ደርሷል ማለት ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከ ዮሃንስ ከሊለ እና ከአስካለ ካሳየ ጋር መሬታቸውን እንዴት እያዘጋጁ እንደሆነ እያነጋገርኳቸው ነው ፡፡ ይህ መሬቱ እና…

የዶሮዎች ውጫዊ ጥገኛ ተዋሲያን፤ ተፅዕኖ እና ቁጥጥር/አስተዳደር

አቅራቢ ፡ የተወደዳችሁአድማጮችእንደምንአደራቹ; በዚህማለዳእንዴትየዶሮውጫዊጥገኛተዋሲያንንመቆጣጠርእንደምንችልእንማራለን፡፡ጥገኛተዋሲያንእንደቁንጫ፣ቅማልእናመዥገርያሉፍጡራንናቸው፡፡ ባላንዶጉውስጥበሰብልእርሻእናዶሮእርባታላይከተሰማሩትአቶአዳማሳኮጋርእናወጋለን፡፡ባላንዶጉበማሊየመጀመሪያክልልበኦሶቢዲያኛክፍለሀገርውስጥየምትገኝትንሽገጠራማመንደርነች፡፡ የማሳላይድምïች ፡ ዶሮዎች፣እንሰሳት/ከብቶች አቅራቢ ፡ በማሽላማሳዎችበተከበበችአነስተኛመንደርውስጥእንገኛለን፡፡በርቀትጥቂትየጭቃቤቶችንንማየትእንችላለን፡፡በዙሪያውባሉትማሳዎችአርሶአደሮችከማሽላገለባጋርየተገኛኙስራዎችንእየሰሩነው፡፡ሌላኛውየመንደሩጎንፀጥያለነው፡፡ልጆችመንገድላይእየተጫወቱነው፡፡እዚህያለነውስለውጫዊጥገኛተዋሲያንየዶሮእርባታላይየተሰማራአርሶአደርንአግኝተንጥያቄዎችለመጠየቅነው፡፡ እንደምንአደሩአቶሳኮ? አዳማሳኮ ፡ እንደምንአደርክ? አቅራቢ ፡ ለአድማጮቻችንራስዎንማስተዋወቅይችላሉ; ምንእንደሚሰሩይንግሩአቸዋል፡፡ አዳማሳኮ ፡ እንደምንአደራቹ? ስሜአዳማሳኮነው፡፡ባላንዶጉመንደርውስጥነውየምኖረው፡፡የሰብልአርሶአደርነኝ፡፡ከግብርናባሻገርሌላስራላይምተሰማርቻለሁ፡፡በዚህሀገርበአንድሥራብቻኑሮንመምራትከባድነው፡፡ለዛነውሁልጊዜበተለያዩየስራመስኮችላይመሰማራትየሚመከረው፡፡ አቅራቢ ፡ ሌላውሥራዎምንድነው? አዳማሳኮ ፡ እዚህእንዳሉሌሎችአርሶአደሮችሁሉዶሮእናጅግራአረባለሁ፡፡ከምዕራባዊያንአገራትከሚመጡትዝርያዎችበስተቀርሁሉንምአይነትየዶሮዝርያዎችንአረባለሁ፡፡ከምዕራባዊያንአገራትየሚመጡትንብዙምአልወዳቸውም፡፡ አቅራቢ ፡ ዛሬዶሮዎችንሊያስቸግሩስለሚችሉትጥቃቅንፍጡራን፣ስለውጫዊጥገኛተዋሲያንእናወጋለን፡፡እንደደርሶአደርስለነዚህጥገኛተዋሲያንሊነግሩኝይችላሉ? አዳማሳኮ ፡ ዶሮዎችንየሚያጠቁአንዳንድጥገኛተዋሲያንንአውቃለሁ፤በተለይቁንጫወይምበባምባራቋንቋንዴሌስለሚባሉትቀይጥገኛተዋሲያን፡፡ቁንጫዎችዶሮዎችማታማታበሚያርፉበትየዛፍቅርንጫፎችላይነውየሚኖሩት፡፡ሙሉስብስቡንማጥፋትየሚችሉበጣምአደገኛጥገናተዋሲያንናቸው፡፡ አቅራቢ ፡ ዶሮዎችዎማታማታየዛፍቅርንጫፎችላይነውየሚያሳልፉት? አዳማሳኮ ፡ አዎአንዳንዶቹግንሁልጊዜአይደለም፡፡እነዚህጥገኛተዋሲያንዶሮዎችየሚተኙበትንቦታይወዳሉ፣ለምሳሌየዶሮቤቶችንወይምዛፎችን፡፡የዶሮዎችንደምሙሉበሙሉሊመጡይችላሉ፡፡ግድግዳዎችላይ፣በጡብመካከልባሉአርማታዎችውስጥእናበዛፍቅርፊትውስጥይኖራሉ፡፡ማታዶሮዎችበሚተኙበትሰዓትይወጣሉ፡፡የዶሮዎችእግርናታፋላይጥቃትያደርሳሉ፡፡የዶሮቤትአቅራቢያያለንዛፍቀረብብለህካስተዋልክእነዚህንተዋሲያንታያለህ፡፡እነሱንለመግደልመደረግየሚገባውነገርምሽትላይቢሆንየተሻለነው፡፡ አቅራቢ ፡ ለምንድነውይኼእርምጃምሽትላይመወሰድያለበት? አዳማሳኮ ፡ በዛንወቅትነውመኖሪያቸውንትተውዶሮዎችንየሚያጠቁት፡፡ወደዶሮቤትበቀንቢሄዱምንምነገርአያዩም፡፡ የዶሮቅማልየሚባልሌላትንሽነጭጥገኛህዋስአለ፡፡በባምባራቋንቋቼግኒሚይባላል፡፡ይኼጥገኛህዋስበርግጥትንሽነው፡፡አዲስበሚጣሉእንቁላሎችላይበመቆየትወደእናትዶሮዎችላባዎችውስጥይገባል፡፡ይኼሲከሰትዶሮዎችንወዲያውኑማከምአለባቹ፡፡ካልሆነዶሮዎችንበማስቸገርእንቁላሎቻቸውንትተውእንዲሄዱያደርጋቸዋል፡፡በጣምትንሽከመሆኑየተነሳየዶሮቅማልንበአይንለማየትይከብዳል፡፡የተወሰኑቀናትዕድሜያላቸውንጫጩቶችብቻነውመግደልየሚችለው፡፡ያደጉትንአይገድልም፡፡ መዥገርወይምበባምባራቋንቋትሬፊንየሚባልሌላጥገኛህዋስአለ፡፡ጥቁርእናእንደቅማልትንሽነው፡፡በዶሮክንፎችእናታፋዎችሥርእናበሁሉምበተደበቁየዶሮክንፎችውስጥቀስቀስያድጋል፡፡ጥገኛተዋሲያንበሬዎችእናላሞችንበሚያጠቁትመልኩዶሮዎችንምያጠቃሉ፡፡ይኼማለትዶሮዎችንካልገደሉበቋሚነትበላባቸውስርይቆያሉ፡፡መዥገርዶሮዎንበፍፁምትቶትአይሄድም፡፡የዶሮዎችንደምበመምጠጥበፍጥነትስለሚገድላቸውበጣምአደገኛጥገኛህዋስነው፡፡ አቅራቢ፡እነዚህጥገኛተዋሲያንእርሶበከፍተኛደረጃበሚተማመኑበትየዶሮእርባታ/ግብርናላይከፍተኛጉዳትእንደሚያደርሱእገነዘባለሁ፡፡ነገርግንእነዚህጎጂፍጡራንከዬትእንደሚመጡሊነግሩኝይችላሉ? አዳማሳኮ ፡ ስለዚህጉዳይእራሴንብዙጥያቄዎችእጠይቃለሁ፡፡አንዳንድጊዜከኩስይሆንየሚመጡትብዬራሴንእጠይቃለሁ፡፡ለዶሮዎችዎአዲስቤትየሚገነቡከሆነመጀመሪያአካባቢምንምአይነትጥገኛተዋሲያንንአያዩም፡፡ነገርግንየዶሮቤቱእያረጀሲሄድተዋሲያንንበየቦታውያያሉ፡፡ አቅራቢ ፡…

ፍየል በማርባት በምስራቅ ኬንያ የተከሰተውን ድርቅ መቋቋም

የመግቢያ ሙዚቃ ከፍ ብሎ ከዚያ ዝቅ ይላል አቅራቢዋ:                               እንደምን አደራችሁ፤ ወደ አርሰ አደር ለአርሶ አደር ፕሮግራማችን እንኳን በሰላም መጣችሁ፡፡ በዛሬው ፕሮግራማችን የድርቅን ተጽእኖ እና አርሶ አደሮች እንዴት እየተቋቋሙት እንደሆነ እንነጋራን፡፡ በምስራቃዊ ኬንያ በምትገኘው በምዊንጊ ያሉ አንዳንድ አርሶ አደሮችን ጎብኝቻለሁ፤ እነዚህ አርሶ አደሮች በተሳካ ሁኔታ ከከብት አርቢነት ወደ ወተት ፍየል አርቢነት ተቀይረዋል፡፡ በመጀመርያም የአርሶ አደሮች አስተባባሪ…

ጭንቀትና ተስፋን ማመዛዘን፡- የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችየአየር ጸባይ ለውጥ ስላሳደረባቸው ተጽእኖ ይናገራሉ

የፕሮግራም ሙዚቃ አስተናጋጅ፡ የአየር ጸባይ ለውጥ በዓለም ዙርያ የአየር ንብረትን እየለወጠው ነው፡፡ የሞቃት ቀኖች ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ከባድ የዝናብ ኩነቶችም ካለፉት አሥርት ዓመታት በተለየ እየተደጋገሙ ነው፡፡ በኢትዮጵያና በሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች አርሶ አደሮችእየተቸገሩ ነው፡፡ ዛሬ የአየር ጸባይ ለውጥ ጋር ከፊት ሆነው እየታገሉ ያሉ አርሶ አደርዎችን ትሰማላችሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች እያጋጠሟቸው ስላሉ ችግሮች እና ከሁኔታው ጋር ለመለማመድ ምን…