ድራማኤስ

ሁሉ
  • ሁሉ
  • ማህበራዊ ጉዳዮች
  • የመሬት ጉዳዮች
  • የሰብል ምርት
  • የአካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ
  • የአየር ንብረት ለውጥ
  • የአፈር ጤንነት
  • የእንስሳት እርባታ እና ንብ ማነብ
  • የድህረ-መከር እንቅስቃሴዎች
  • የጾታ እኩልነት
  • ግብርና
  • ጤና

የእግድ እብደት፡ ጾታዊ ጥቃት በኮቪድ-19 ወቅት

ክፍል 1 መቼት: የፎሪዋ ቤት ገጸ-ባህርያት: ፎሪዋ፣ ዳንኤል፣ ልጆች (ሴርዋ፣ ቤቢ እና ፓፓ) የድምጽ ኢፌክት: ሙዚቃ ዳንኤል: ውዴ መነጋር አለብን፡፡ ራዲዮውን ቀንሽውና ወደዚ ነይ፡፡ ፎሪዋ: እሺ ውዴ፡፡ ዳንኤል: እየውልሽ ቤት ውስጥ ስላለንበት ሁኔታ ሳስብ ነበር፤ እንዴት እንደምንኖር በጣም ጨንቆኛል፡፡ ይሄ ኮቪድ-19 የሚሉት ነገር ከመጣ ወዲህ ሕይወታችን በፍጥነት ከጥሩ ወደ መጥፎ ተቀይሯል፤ እየባሰበት ነው፡፡ አሁን በሃገሪቱ…

Farming wisdom: የእርሻ ጥበብ እርሻ አቀባ ለተሻለ ኑሮ

ገፀ ባህሪዎች፡- ባዩ አባተ፡- ዕድሜ 50፣ የወይኒቱ ባለቤት፣ የተከበረ እና ሀብታም ገበሬ፣ በዘልማድ የሚያርስና ጥሩ የእርሻ ምርት የሌለው ነገር ግን በእንስሳት እርባታ የሚተዳደርና ጥሩ ኑሮ ያለው፡፡ ወይኒቱ ተሻለ፡- ዕድሜ 36፣ የአቶ ባዩ ባለቤት እና የአራት ልጆች እናት፣ ተመስገን የራሱ መሬት እንዲኖረው የምትፈልግና ባለቤቷ እንዲሰጠው ሁሌም የምትጠይቅ፡፡ ተመስገን ባዩ፡- ዕድሜ 20፣ የአቶ ባዩ እና የወይኒቱ ልጅ…

የኔዲ ታሪክ፡ የማህበረሰብ እንስሣት ጤና ባለሙያው የአንድ መንደር ነዋሪዎች የኒውካስል በሽታን መቆጣጠር እንዲችሉ ረዳ

ተራኪ: ማላዊን ጨምሮ በብዙ የአፍሪካ ሃገሮች አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች ቢያንስ አንድ ዶሮ አላቸው፡፡ እነዚህ ዶሮዎች ጭረው የሚበሉ የአካባቢው ዝርያዎች ናቸው፡፡ የኒውካስል በሽታ ወረርሽኝ ቢፈጠር እነዚህ ዶሮዎች በቀላሉ ያልቃሉ፡፡ ኒውካስልን በክትባት መከላከል ይቻላል፡፡ ታዲያ ለምንድን ነው ብዙ አርሶ አደሮች ለዶሮዎቻቸው ክትባት የማይገዙተ ለምንድን ነው? አብራችሁን ቆዩና መረጃ ታገኛላችሁ፡፡ የድምጽ ኢፌክት፦ ብረት በትንሽ መዶሻ ሲመታ ድምጽ ሚስት:…