ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራን በተመለከተ የተዘጋጁ የሬዲዮ ስፖቶች

የጾታ እኩልነት

Notes to broadcasters

ማስታወሻ ለአሰራጭ/ሬዲዮ ጣቢያ

እንደ የተባበሩት መንግስታት የሴቶች መ/ቤት ገለጻ የእንክብካቤ ስራ የአዋቂዎችን እና ህጻናትን ፣ አዛውንቶችን እና ወጣቶችን፣ አቅም ያላቸውን እና አቅመ ደካሞችን አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ስሜታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የታሰቡ እንቅስቃሴዎችን እና ግንኙነቶችን ያቀፈ ነው።ህጻናትን፣ አረጋውያንን ፣ ህመም ያለባቸውን እና አካል ጉዳተኞችን ከመንከባከብ ጋር የተያያዙ ቀጥተኛ የእንክብካቤ ስራዎችን እንዲሁም እንደ ምግብ ማብሰል፣ ማጽዳት እና ውሃ፣ ምግብ እና ማገዶ መሰብሰብን ቀጥተኛ ያልሆነ ወይም የቤት ውስጥ ስራዎችንም  ያጠቃልላል። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ የሚያመለክተው በቤተሰብ ወይም በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ለአባላቱ ምንም አይነት የገንዘብ ካሳ ወይም ጥቅማ ጥቅሞች ሳያገኙ  የሚሰጡትን አገልግሎት ነው። አብዛኛው ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ በቤተሰብ ውስጥ ይከናወናል። በማህበረሰብ ደረጃም ከቤት ውጭ ላሉ ሰዎች (ጓደኞች፣ ጎረቤቶች እና የማህበረሰብ አባላት) ይከናወናል።”

በመላው ዓለም፣ የእንክብካቤ ሚናዎች በአብዛኛው በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ይወድቃሉ። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ሴቶች ከወንዶች በ3.4 እጥፍ ያህል ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ይሰራሉ። ይህ የሴቶችን የትምህርት እና የስራ እድሎች ይገድባል፣ እናም በማህበራዊ ተሳትፎ እና በመዝናኛ ጊዜያቸው ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፣ በዚህም የሴቶችን የጤና እና የደህንነት ደረጃ ይጎዳል።

በእነዚህ የሬዲዮ ስፖቶች ውስጥ ስለ ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ እና ከእሱ ጋር የተያያዘውን የስርዓተ-ፆታ ኢፍትሃዊነትን የበለጠ ይማራሉ። የሬዲዮ ስፖቶቹ የሚከተሉትን ርዕሶች ያካትታሉ።

  • የሴቶችን ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ የማድነቅ እና ዋጋ የመስጠት አስፈላጊነት
  • ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ውጤታማ ስራ ነው።
  • በቤተሰብ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው የእንክብካቤ ሥራን የመጋራት አስፈላጊነት
  • ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሰራተኛ ህይወት ውስጥ የአንድ ቀን የሥራ ውሎ
  • ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ በሴቶች ላይ የሚያሳድረው ድብቅ ተጽእኖ
  • የቤት ውስጥ ኃላፊነቶችን ስለመጋራት ልጆችን ማስተማር
  • ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ማብቃት የማህበረሰብ ጥረት ነው።
  • የትዳር ጓደኛዎን ያለ ክፍያ በሚሰራ የእንክብካቤ ስራ መርዳት
  • ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞች ላይ የሚቃጡትን ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መቃወም
  • አሰሪዎች ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ስራ እና ህይወት ሚዛን እንዲጠብቁ መርዳት ይችላሉ ።
  • የህዝብ ሀብት ተደራሽነትን ማሻሻል ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ይረዳል።
  • ሚዲያው ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ዙሪያ ያሉ ትርክቶችን እንዴት መለወጥ እንደሚችል

የሬዲዮ ስፖቶቹ ከ45-60 ሰከንድ ርዝማኔ አላቸው እና በጤና እና በጾታ እኩልነት እና በሌሎች ተዛማጅ ፕሮግራሞች ላይ ብዙ ጊዜ መቅረብ ይችላሉ። የሬዲዮ ስፖቶቹ ርዕሶች የስፖቶቹን ጭብጥ ለመለየት ብቻ የታሰቡ ናቸው።  እንደ ስፖቶቹ አካል ጮክ ብለው እንዲነበቡ የታሰቡ አይደሉም።

Script

ስፖት #1፡ ያለ ክፍያ የሚሰራ የሴቶችን የእንክብካቤ ስራ ማድነቅ

ተራኪ: ወንዶች! በመጨረሻም አርብ መጣ፣ እና የሌላ ረጅም የስራ ሳምንት መጨረሻ! ጠንክራቹ ሰርታችኋል!

ግን ልክ እንደ ስራዎ አስፈላጊ የሆነውን ያውቃሉ? የትዳር ጓደኛዎ በቤት ውስጥ የሚሰሩት ስራ

ከረጅም እና አስቸጋሪ የስራ ቀን በኋላ ወደ ደስተኛ ቤተሰብ መምጣት ጥሩ አይደለምን? ልጆቹ ደህና መሆናቸውን ማወቅስ? በጥሩ ሁኔታ የተያዘ ቤት እርስዎ በስራ ላይ በተሻለ ሁኔታ እንዲያተኩሩ የአእምሮ ሰላም ይሰጥዎታል.።

ስለዚህ ዛሬ የትዳር ጓደኛዎን ቤት ውስጥ ለሚሰሩት ስራ ሁሉ ያድንቁ!

 

ስፖት #2: ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ አሁንም ውጤታማ ስራ ነው።

ትዕይንት: የእይታ ማዕከል

SFX: ድምጾች ሳቅ፣ የጠርሙሶች ድምፅ

ኡመር: ዳዊት! የመጀመሪያው አጋማሽ አምልጦሀል! የት ነበርክ?

ዳዊት፡ (በሀዘን ስሜት) ዑመር፣ አታምነኝም ያቺ እብድ ባለቤቴ ነች።

ኡመር: እንዴት? ዳዊት- አቢ አሁን ምን አደረገች?

ዳዊት፡ (በንዴት ስሜት) መገመት ትችላለህ? ከአስቸጋሪ ረጅም የስራ ሳምንት በኋላ ይህች ሴት አስጨነቀችኝ። ሳምንቱን ሙሉ ቤት ነች። ነገር ግን ቤተሰቡን ለመመገብ ወጥታ ስራ የምትሰራ ታስመስላለች።. (የብስጭት ድምጽ) ወንበሮችን በማንቀሳቀስል እሷን መርዳት እንዳለብኝ ተናገረችኝ።

ኡመር: ተረጋጋ ጓደኛዬ. ምን ተፈጠረ?

ዳዊት፡ ሁለት ወንበሮችን አንቀሳቀስኩ። ከዚያ ሄድኩ። ከንቱ! እግዚአብሔር እንኳን አርፎ ነበር ! ፍትሃዊ አይደለም። ገንዘቡን ሁሉ የማመጣው እኔ ነኝ፣ እሷ የምታመጣው ጭቅጭቅ እና ጭንቀት ብቻ ነው !

ኡመር: እንዴ ዳዊት፣ ያ እውነት እንዳልሆነ ታውቃለህ። አቢ ስለምታዘጋጃቸው ጣፋጭ ምግቦች እና መንታ ልጆቻችሁ ምን ያህል ብልህ እና ጤናማ እንደሆኑ ሁልጊዜ ታወራለህ። ያስ ያን ያህል አስፈላጊ አይደለምን?

ዳዊት፡ (በጥልቀት በማሰብ) እገምታለሁ!. ገንዘብ ላታመጣ ትችላለች፣ ነገር ግን ሁላችንም ደስተኛ እና ጤናማ እንድንሆን የምታደርገው ስራ በዋጋ ሊተመን የማይችል ነው!

ኡመር: በትክክል! የቤት ስራዋ ልክ እንደ አንተ ስራ አስፈላጊ እና ውጤታማ ነው።

ተራኪ: ያለ ክፍያ የሚሰራ ሥራ ውጤታማ ሥራ ነው! ያለ እሱ ቤተሰብህ የት ይደርሳል?

 
ስፖት #3: ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ የሁሉም ሰው ሃላፊነት ነው።

ተራኪ: ሴቶች አብዛኛውን የጽዳት፣ የሕጻናት እንክብካቤ እና ሌሎች ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሥራዎችን በቤት ውስጥ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ይሰራሉ።

ይህ ዓይነቱ ሥራ ብዙውን ጊዜ የሴቶች የቤተሰብ ኃላፊነት እና ሚና ተደርጎ ይታያል። ነገር ግን ሴቶች የዚህን ማለቂያ የሌለው ያለ ክፍያ የሚሰራ ሁሉንም የእንክብካቤ ሥራን ሃላፊነት ብቻቸውን መሸከም የለባቸውም!

በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሰዎች፣ ሴቶች እና ትልልቅ ልጆች እንኳን ያለ ክፍያ በሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ መርዳት ይችላሉ። ሸክሙ በእኩልነት መከፋፈል አለበት።

አንድ የሚሰራ ቤተሰብ ውጤታማ ከሆነ ፋብሪካ፣ ቢሮ ወይም የምርት መስመር የተለየ እንዳልሆነ አስታውስ። የሁሉንም ትብብር ይጠይቃል።

ስለዚህ ሁላችንም ለስኬታማ እና ደስተኛ ቤተሰብ እውን መሆን ተባብረን እንስራ።

 

ስፖት#4: የሥራ መስፈርቶች: ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሰራተኛ ህይወት ውስጥ የአንድ ቀን የሥራ ውሎ

ማሪያ: ዘይነብ ለዚህ ሥራ የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ተመልከቺ። የማይታመን ነው።

ዘይነብ: ያን ያህል መጥፎ ሊሆን አይችልም ማሪያ።

ማሪያ: ታያለሽ የመጀመሪያው መስፈርት “በዓመት 24/7፣ 365 ቀናት የስልክ ጥሪ መቀበል እና መመለስ መሆን አለበት።”

ዘይነብ: ምን? በዓላት የሉም? ብትታመሚስ!

ማሪያ: ብትታመሚም ትመጪያለሽ ተብሎ ይጠበቃ። እና ምንም የወሊድ ፈቃድ የለም። ከዚህ ያለ ክፍያ ከሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ እረፍት የምታገኝበት ብቸኛው ጊዜ ልጅ ስትወልጅ እና ምናልባትም ለማገገም የሚኖር ትንሽ ጊዜ ይመስላል።

ዘይነብ: አዎ! ግን ልጅ መውለድ ጨዋታ አይደለም። ያ የሥራ ድርሻ በጣም ተገቢ አይደለም፣ ግን ገንዘቡ ጥሩ መሆን አለበት። አይደል?

ማሪያ: (እየሳቀች) የምን ገንዘብ? ደመወዙ በወር ዜሮ ናይራ፣ በዓመት ዜሮ ናይራ ነው።

ዘይነብ: (በድንጋጤ) ምን?

ማሪያ: ገቢሽን በሌሎች ስራዎች መደጎም ትችያለሽ፣ ነገር ግን በጥሪ ላይ ከመሆን ጋር ማመጣጠን አለብሽ ይላል። ተጨማሪም አለ፣ የሚከተሉትን ክህሎቶች ሊኖርሽ ይገባል፡ ምግብ ማብሰል፣ መስፋት፣ የሂሳብ ሥራ፣ መሰረታዊ ሂሳብ፣ የሳይንስ ችሎታ፣ ግዢ…

ዘይነብ: (እያቋረጠቻት) ያ መጥፎ ይመስላል። ግዢ? ይህ ምን ዓይነት ሥራ ነው? የሥራው መደቡ ምንድን ነው?

ማሪያ: የቤት እመቤት እና ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ ሰራተኛ

ተራኪ: ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ ከምታስቢው በላይ ከባድ ነው። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ ሰራተኞችን እንደግፍ፣ በቤት ውስጥ ያለውን የሥራ ጫና እንጋራ፣ እና በቤተሰባችን፣ በማህበረሰባችን እና በግሉ ሴክተር ውስጥም ቢሆን ለበለጠ እኩልነት እንታገል።

 

ስፖት#5: ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ የተደበቁ ተጽዕኖዎች

ተራኪ: ሴቶች እና ልጃገረዶች አብዛኛዎቹን ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ስራዎችን ይሰራሉ (ጽዳት፣ ህጻናትን መንከባከብ፣ ልብስ ማጠብ፣ እንጨት መልቀም እና ውሃ መቅዳት) ።

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ሴቶች ይህን ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ከወንዶች በ3.4 እጥፍ የበለጠ ይሰራሉ። ይህ ከፍተኛ ተጽእኖዎች አሉት። ሴቶችን በአካል እና በስነ-ልቦና ይጎዳል፣ ግን ሌሎች የተደበቁ ተጽዕኖዎችም አሉ።

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ እና የትምህርት እድሎች እና በማህበራዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ይገድባል።

ስለዚህ ሴቶች ከሱ ውጭ ህይወት እና ህልም እንዲኖራቸው ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራን በትክክል እናመጣጥን።

 
ስፖት #6: ስለ ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሥራ ቀጣዩን ትውልድ ያስተምሩ።
ተራኪ: የቤት ውስጥ ሥራን ጨምሮ ሴቶች ያለ ክፍያ የሚሰሩትን የእንክብካቤ ሥራን/ኃላፊነትን በተመለከተ ያለንን አመለካከት መለወጥ አለብን። ይህንን ለመጀመር በጣም ጥሩ ጊዜ ልጆች ዕድሜያቸው ትንሽ ሲሆን ነው።

ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ጠቃሚ እና ለቤተሰቡ አስፈላጊ እንደሆነ ለልጆቻችሁ ያስተምሩ። የሁሉም ሰው ሃላፊነት ነው፣ እና በልጃገረዶች እና በወንዶች፣ እና አዋቂ ወንዶች እና ሴቶችም መካከል እኩል መካፈል አለበት።

የቤት ውስጥ ክህሎቶች ለሁሉም ሰው ጠቃሚ ናቸው። በተፈጥሯቸው ለወንዶች ወይም ለሴቶች የታሰቡ ተግባራት የሉም። ለምንድነው ወንዶች ምግብ ማብሰል ወይም ልጃገረዶች መኪና ማጠብ የማይችሉት?

ለብሩህ ተስፋ ልጆችዎን አሁን ማስተማር ይጀምሩ።

 

ስፖት #7: ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ማብቃት የማህበረሰብ ጥረት ነው።

ተራኪ: ዛሬ፣ ቁጥራቸው ብዙ ሰዎች ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞች በህብረተሰባችን ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ያውቃሉ እናም ይራሩላቸል። እነዚህ ሴቶች በቤት ውስጥ እና ሌሎች በቤተሰብ እና በማህበረሰብ ውስጥ ባሉ የእንክብካቤ ስራዎች ላይ ያለማቋረጥ ያለ ክፍያ እና ያለ አድናቆት የሚሰሩ ናቸው።

ነገር ግን በራሳችን ቤተሰብ ውስጥ ለውጥ ማድረግ በቂ አይደለም። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ እና ሰራተኞች የሚከበሩበትን እና በክብር የሚስተናገዱበትን ሙሉ ማህበረሰብ መፍጠር አለብን።

ይህን ለማድረግ አንዱ መንገድ የእንክብካቤ ሰራተኞችን መብት የሚያበረታቱ እና የሚጠብቁ ፖሊሲዎችን እና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ነው።

ስለዚህ ለቤተሰብዎ የበለጠ ተጠቃሚነት ድምጽ ይሁኑ!

 

ስፖት #8፡ የትዳር ጓደኛዎን ያለ ክፍያ በሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ያግዙ።

SFX፡ የስልክ ጥሪ

ኢኔ: (በደስታ ስሜት) ልጄ፣ ዛሬ አስታወስከኝ። እንዴት ነህ?

ጄምስ፡ (እየሳቀ) እማማ፣ መቼም ልረሳህሽ አልችልም። ደህና ነኝ። ስለ ሉሲ ምክርሽን መጠየቅ ፈልጌ ነበር።

ኢኔ: ሚስትህ? ደህና ናት?

ጄምስ፡ አላውቅም፣ እንዴት እንደማናግራት ምክርሽን እፈልጋለሁ። ጁኒየር ከተወለደ ጀምሮ ምንም ትጉህ አይደለችም።

ኢኔ: ምን ማለትህ ነው?

ጄምስ፡ ትላንትና አንዳንድ ጓደኞቻችንን ጋብዝን ነበር፣ እና በመጡበት ጊዜ አሁንም ቤት እያጸዳች ነበር? ለእነሱ የማቀርበው ምንም ነገር አልነበረም። ከውርደት ለመዳን ሮጬ ትንሽ ዶሮ መግዛት ነበረብኝ። ምን እንደምላት ባላውቅም እሷ ግን መሻሻል አለባት።

ኢኔ: (ቆፍጠን በማለት) ልጄ፣ በአንተ ደስተኛ አይደለሁም።

ጄምስ፡ ምነው?

ኢኔ: እኔ እንደዛ አላሳደኩህም። እሷ ቤቱን ስታጸዳ አንተ ምን እያደረግክ ነበር?

ጄምስ፡ (ግራ በመጋባት) እኔ … ግን …

ኢኔ: አስታውስ፣ በአባትህ ልደት ቀን አንተ እና ወንድሞችህ ትረዱኝ ነበር። እሱ እንኳን አንዳንድ ጊዜ ይረዳኝ ነበር። አንድ ቡድን ነበርን! ታዲያ ለምን ሚስትህን አትረዳም?

ጄምስ፡ (በለሆሳስ) ልረዳት ይገባ ነበር።

ኢኔ: አዎ አለብህ! የትዳር ጓደኛህን ከረዳህ ቤተሰብህ በጣም የተሻለ ይሆናል!

 

ስፖት #9: ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞች ላይ የሚቃጡትን ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ይቃወሙ

ዳንጁማ፡ እርባና ቢስ (በማጥላላት)

ቡሉስ፡ ዳን፡ ምን ተፈጠረ?

ዳንጁማ፡ አይሻ ምግቤን እንደገና አቃጠለች። እርግጠኛ ነኝ የህንድ ፊልም እያየች ነበር እና ምግቡ እሳት ላይ መሆኑን ረሳችው።

ቡሉስ፡ (እየሳቀ) አንድ ቀን በሾርባህ ውስጥ ከጨው ይልቅ ስኳር ትጨምራለች!

ዳንጁማ፡ ቡሉስ አየሽ? አንዳንድ ወንዶች ቢሆኑ ይህ ስሜት እንዲሰጣት ይደበድቧት ነበር። እኔ በሴት ላይ እጅ ላለማንሳት ምያለሁ። ኮከቦቿን ማመስገን አለባት (በማጥላላት)።

ቡሉስ፡ (በድንጋጤ) ገበታ ላይ? ዳን እርግጠኛ ነኝ ስህተት ነበር።. እንደዛ ማሰብ የለብህም። ላንተ ምግብ ማብሰልን ጨምሮ ሁሉንም ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ስራዎችን መስራት ሁልጊዜ የእርሷ ሃላፊነት የሆነው ለምንድን ነው? ያ ፍትሃዊ አይደለም!

ዳንጁማ፡ አዎ ትክክል ነሽ። (አጭር ዝምታ) አልደበድባትም። አንዳንድ ወንዶች ያደርጉት ነበር እያልኩ ነው።

ቡሉስ፡ አውቃለሁ ግን እንደዚህ አይነት ነገር አሁንም ትክክል አይደለም። ልክ እንደ… በዚህ እርሻ ላይ ሁሌም ስህተት ሠርተን ቢሆን አቶ ሱሌ ይደበድበን ነበር? በዚያን ጊዜ በሩን አልቆለፍክም እና ስድስት ፍየሎች አምልጠዋል? ታስታውሳለህ?

ዳንጁማ፡ የጥንት ታሪክ ማምጣት አቁም።

ቡሉስ፡ አለቃችንን ገንዘብ በማስወጣትህ ካልደበደበህ የተቃጠለ ምግብ ይቅር ሊባል የሚችል ይመስለኛል።

ዳንጁማ፡ (በረጅሙ በመተንፈስ) ምሳዬን እራሴ ለማዘጋጀት ቀደም ብዬ መነሳት ያለብኝ ይመስለኛል። በዚህ መልኩ ክብደት ልቀንስ አልችልም።

ተራኪ: ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በምንም ምክንያት መከሰት የለባቸውም፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አጋርዎ በቤት ስራ እየታገለች ባለችበት ወቅት።

 

ስፖት#10: አሰሪዎች ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ስራ እና ህይወት ሚዛን እንዲጠብቁ መርዳት ይችላሉ

አቅራቢ: እንኳን በድጋሚ በቁጥር አንድ የሬዲዮ ጣቢያዎ ላይ ወደ ሚተላለፈው የሴቶች የንግድ ሰዓት (Women’s Business Hour) በደህና መጡ። ከያንካት ፍራንክ ጋር በንግድ ስራዋ ቦታ በያንካት ቺፕስ ነን። ወ/ት ፍራንክ ስላገኘሽን እናመሰግናለን።

ያንካት: በደስታ ነው።

አቅራቢ: የድንች ቺፕስሽን በግዛቱ ውስጥ ሁሉም ቦታ እያየሁ ነበር። በጣም ጥሩ እየሰራሽ ነው።

ያንካት: አዎ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በእውነት አስፋፍተናል። ቺፕሱን መሸጥ ስጀምር ትንሽ ኃላፊነት ወስጄ መስፋፋት እንዳለብኝ አውቅ ነበር። በዙሪያዬ ጥሩ ስብስብ በማግኘቴ ተባርኬያለሁ።

አቅራቢ: እዚህ ብዙ ሴቶች እንደሚሰሩ አይቻለሁ። ያ ታቅዶበት ነበር?

ያንካት: ሴቶችን ማብቃት ሁሌም ህልሜ ነበር፣ እና ይህን የማቀነባበሪያ ስራ ስጀምር ጥሩ እድል ነበር።

አቅራቢ: በጣም ጥሩ ስራ ነው።

ያንካት: ስራ የሚሰሩ ወጣት እናቶች ስራን እና የቤት ስራን ማመጣጠን በተመለከተ የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች ከራሴ ልምድ ተምሬአለሁ። ለዚህ ነው ተለዋዋጭ የስራ ሰዓታት እንዲኖረን የምንሞክረው። በሚቀጥለው አመት እናቶች በስራ ሰዓት ልጆቻቸውን በስራ ቦታ የሚያስቀምጡበት ስፍራ እንደሚኖረን ተስፋ አደርጋለሁ።

አቅራቢ: በእውነት እየረዳሻቸው ነው።

ያንካት: አሰሪዎች ሰራተኞቻቸው የተሻለ እንዲያመርቱ መርዳት አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ። በጥሩ ሁኔታ መያዝ መብታቸው ነው! እና ሰራተኞቼን በመርዳት በተሳካ ሁኔታ እየሰሩ ለቤታቸው የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ!

 

ስፖት #11: የሀብት ተደራሽነትን ማሻሻል ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ይረዳል።

ንግሥት፡ ባለቤቴ- ትናንት ወደ ቤተ መንግሥት የመጡት ሴቶች እነማን ነበሩ? ለረጅም ጊዜ ካንተ ጋር ተነጋግረው ነበር።

አለቃ፡ ምን? ገባኝ እነዚያ አሁን በከተማው ውስጥ የሚኖሩ አንዳንድ የአካባቢው ሴቶች ነበሩ። ሊያመሰግኑኝ ነበር የመጡት፣ እና ለማህበረሰቡ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር እንዳለ ለማወቅ ፈልገውም ነበር። ለእቅዳቸው ዋና ኃላፊ ሆኜ ፈቃድ እና ድጋፍ እየጠየቁ ነበር።

ንግሥት፡ (በደስታ ስሜት) ያ ጥሩ ነው። ብዙ ሰዎች እንደዛ እንዲያስታውሱን እመኛለሁ። ሊያመሰግኑህ ይፈልጋሉ አልክ? እንዴት?

አለቃ፡ አዲሱን ጉድጓድ መቆፈር እንደፈለግን አስታወስክ እና ወደ ከተማው አቅራቢያ እንድንገነባው ሀሳብ አቅርበህ ነበር?

ንግሥት፡ አዎ፣ ውሃው ከሌላው ቦታ ይልቅ ከመሬት በታች ጥልቅ ስለነበር ሰዎች ተቃውመውታል፣ ግን ሌላኛው ቦታ ደግሞ በጣም ሩቅ ነበር።

አለቃ፡ (በደስታ ስሜት) ሴቶቹ ያሉት ይህንኑ ነው። ከተማ ውስጥ የውሃ ጉድጓድ መገንባት ውሃ ለመቅዳት የሚያጠፉትን ጊዜ በመቀነሱ ትምህርት ቤት ገብተው ለመማር ብዙ ጊዜ እንዳገኙ ተናግረዋል።

ንግሥት፡ ውሃ ለመቅዳት የሚደረገው ጉዞ ቀልድ እንዳልሆነ አልገረመኝም። በቀን ሁለት ጊዜ! ጉድጓዱ ከተቆፈረ በኋላ, በትምህርት ቤት የማጠቃለያ ፈተናዎች ውስጥ የማለፊያ መጠን ጨምሯል። እነዚያ ልጃገረዶች ሊያመሰግኑህ መምጣታቸው ምንም አያስደንቅም።

አለቃ፡ በጣም ምቹ በሆነ ቦታ ላይ የውሃ ጉድጓድ መገንባት ብቻ ያንን ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል አላውቅም ነበር።

ንግሥት፡ ስለዚህ ሚስትህ ንግስቲቱ በጣም ጥበበኛ ነች እያልክ ነው? (ሁለቱም ይስቃሉ)።

ተራኪ: መሠረተ ልማትን ስለመገንባት ሲያስቡ፣ ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሠራተኞችን ያነጋግሩ! የሚፈልጉትን እና የሚያስፈልጋቸውን ይጠይቁ እና ውሳኔውን ሲወስኑ ያካቷቸው። ፍላጎታቸውን ስታስቡ ብዙ የወደፊት ሕይወታቸውን ብሩህ ማድረግ ትችላላችሁ!

 

ስፖት #12: ሚዲያው እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ዙሪያ ያሉ ትርክቶችን እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ

ተራኪ: ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞች ሁኔታዎችን ለማሻሻል ብዙ መንገዶች አሉ። አንደኛው መንገድ በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መድረኮቻቸውን ተጠቅመው ሁሉም የእንክብካቤ ስራዎች የሴቶች ኃላፊነት ናቸው የሚለውን ትርክት ለመቃወም እና ለመለወጥ ነው ።

የወንድነትን ጽንሰ-ሐሳብ በማስተካከል እና ወንዶች ጥሩ እና ብቁ ተንከባካቢ እና የእንክብካቤ ሰራተኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሳየት እንችላለን።

ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ሰራተኞችን ድምጽ በማጉላት ድምፃቸውን እና ጭንቀታቸውን ማዳመጥ እንችላለን።

የሚዲያ ባለሙያዎች-ክፍያ በማይከፈላቸው የእንክብካቤ ሰራተኞች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት የእኛን መድረክ እንጠቀም።

Acknowledgements

ምስጋና: 

አዘጋጅ፡- ቴድ ፊዶ፣ ፍሪላንስ ጸሐፊ፣ ሌጎስ፣ ናይጄሪያ  

ገምጋሚ-፡ ዛህራ ሼክ አህመድ፣ የፕሮግራም ተንታኝ፣ የሴቶች ኢኮኖሚ ማጎልበቻ፣ የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ክልላዊ ቢሮ፣ ናይሮቢ.

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው በ‘ዩኬር– አንፔይድ ኬር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት‘ ተነሳሽነት ሲሆን ይህም የፆታ እኩልነትን እና የሴቶችን አቅም ለማሳደግ ያለመ በቤተሰብ እና በቤተሰብ ውስጥ ያለ ያለ ክፍያ  የሚሰራ የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራ  ተገቢ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለመጋራት ቁርጠኝነት ነው። – ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ. ሀገራት ፕሮጀክቱ ከግሎባል አፌርስ ካናዳ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከፋርም ራዲዮ ኢንተርናሽናል (FRI)፣ የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ቢሮ እና እና ዘ አፍሪካን ዊሜንስ ደቨሎፕመንት ኤንድ ኮሚኒኬሽንስ ኔትወርክ (FEMNET) ጋር በመተባበር ይተገበራል።