ያለ ክፍያ በሚሰሩ የእንክብካቤ ስራዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ማህበራዊ ጉዳዮችየጾታ እኩልነት

Script

ያለ ክፍያ
የሚሰራ
የእንክብካቤ
ሥራ
ምንድን
ነው
እና
ለምንድን
ነው
አስፈላጊ
የሆነው
?

ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ግለሰቦች ያለ ገንዘብ ማካካሻ የሚሰጡትን ድጋፎች እና አገልግሎቶችን ያጠቃልላል። እነዚህም ለምሳሌ እንክብካቤ መስጠትን፣ የቤት ውስጥ ስራዎች መስራትን፣ ስሜታዊ ድጋፍ ማድረግን፣ እንጨት መልቀምንና ውሃ መቅዳትን ያካትታሉ። በዋነኛነት የቤተሰብ አባላትን የሚጠቅሙ ተግባራትን ያካትታል፣ ነገር ግን ከቤት ውጭ ያሉ ግለሰቦችን እንደ ጓደኞች፣ ጎረቤቶች እና የማህበረሰብ አባላት ያሉ ግለሰቦችን ለመርዳት የሚሰሩ ስራዎችንም ያካትታል። ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ስራዎች ኃላፊነት ብዙውን ጊዜ በቤተሰብ እና በማህበረሰቦች ላይ በተለይም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ይወድቃል።

 

ያለ ክፍያ
የሚሰራ
እንክብካቤ
ሥራ
ምንድን
ነው
እንደ
ሥራ
እውቅና
እና
ዋጋ
ጠው
የሚ
ገባው
?

ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ በቀጥታ እንክብካቤ የሚያገኙትን ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡን በአጠቃላይ የሚጠቅሙ አገልግሎቶችን ያካትታል። እነዚህ ተግባራት በአንድ ሰው ለምሳሌ በቤት ሰራተኛ በክፍያ ሊከናወኑ ይችላሉ። ለማከናወን አካላዊ እና አእምሯዊ ጥረት ያስፈልጋቸዋል፣ ጊዜ እና ሀብ ት ይጠይቃሉ። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ብዙ ጊዜ የጊዜ እጥረትን ይፈጥራል፣ እናም በክፍያ በሚሰራ ስራ ተሳትፎ፣ የአመራር ቦታዎች እና ትምህርት ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ለኢኮኖሚ እና ማህበረሰቦች ወሳኝ መሆኑን መገንዘብ እንደ ወሳኝ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ፖሊሲ ጉዳይ ተደርጎ እንዲወሰድ ያስችለዋል።

ያለ ክፍያ
የሚሰራ
እንክብካቤ
ሥራ
ለማህበራዊ
እና
ኢኮኖሚያዊ
እድገት
እንዴት
አስተዋጽኦ
ያደርጋል
?

ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ግለሰቦችን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰቦችን በመደገፍ ለህብረተሰቡ አጠቃላይ ደህንነት አስተዋፅዖ በማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ጤናማ እና የሚሰራ ህዝብን ቀጣይነት በማረጋገጥ፣ ማህበራዊ ትስስርን በማስተዋወቅ እና ግለሰቦች በስራ ሃይል ውስጥ እንዲሳተፉ በማድረግ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊነት ያሳልጣል።

ያለ ክፍያ
የሚሰራ
የእንክብካቤ
ሥራ
ውስጥ
የሚሳተፈው
ማነው
?

በአለም አቀፍ ደረጃ እና ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ዋና ሃላፊነት የሴቶች ነው። ያለ ክፍያ የሚሰሩ የእንክብካቤ ስራዎችን በተመለከተ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ሴቶች ከወንዶች ይልቅ 3.4 እጥፍ የበለጠ ጊዜ እንደሚያሳልፉ ይገመታል። ያለ ክፍያ በሴቶች የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ብዙ ጊዜ እውቅና የሌለው እና ዝቅተኛ ዋጋ ያለው ሲሆን ሴቶች በገቢ ማስገኛ እና ሌሎች ተግባራት ላይ እንዳይሳተፉ እድሎችን ይገድባል።

በተለይ
ከሰሃራ
በታች
ባሉ
የአፍሪካ
ሀገራት
ያለ
ክፍያ
የሚሰራ
የእንክብካቤ
ስራ
ጋር
የተያያዙ
ችግሮች
ምንድናቸው
?

ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ እና በሌሎችም አካባቢዎች በስርዓተ-ፆታ አለመመጣጠን ምክንያት አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ላይ የተሰማሩ በተለይም ሴቶች እና ልጃገረዶች ብዙ ጊዜ እንደ የጊዜ ገደብ፣ የድጋፍ አገልግሎት ተደራሽነት ውስንነት እና ለስራቸው እውቅና ማጣት ያሉ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል። ይህ ጭንቀት፣ ድካም፣ መገለል,፣መሰላቸት እና ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነትን ሊያስከትል ይችላል።

የገንዘብ አቅም የሌላቸው ሴቶች በአሰልቺ፣ ጊዜ በሚወስዱ እና ለአካል አስቸጋሪ በሆኑ የቤት ውስጥ ኃላፊነቶች በብዛት ይያዛሉ። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ከከፍተኛ ጭንቀት ፣ የአእምሮ ጤና ችግሮች፣ ዝቅተኛ የህይወት ደረጃ፣ የጊዜ ድህነት፣ የመንቀሳቀስ ውስንነት እና የጤና እና ደህንነት መጓደል ጋር የተያያዘ ነው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በመካከለኛ ዕድሜ ላይ ያሉ እና የሙሉ ጊዜ የቤት ሠራተኞች በሌሎች ሙያዎች ውስጥ ካሉ ሴቶች ይልቅ የግንዛቤ እክል የመጋለጥ እድላቸው በአምስት እጥፍ ይበልጣል፣ የግንዛቤ/አስተውሎት እክል (cognitive impairment) የሚያመለክተው ማስታወስ፣ አዳዲስ ነገሮችን መማር፣ ማተኮር ወይም የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን በተመለከተ ውሳኔ መወሰን ችግርን ነው።

ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ የሴቶችን የትምህርት፣ የስራ እና የግል እድገት እድሎች በመገደብ የስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ሊያጠናክር ይችላል። ብዙ ጊዜ ዝቅተኛ ችሎታ በሚጠይቁ፣ ኢ-መደበኛ ወይም መደበኛ ያልሆነ ደመወዝ በሚከፈላቸው የስራ እድሎች ላይ ይገደባሉ። ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራ የግለሰብ ሴቶች በስራ ገበያ ውስጥ እንዳይሳተፉ ይገድባል። በማህበረሰብ ደረጃም፣ ምርታማነት፣ የኢኮኖሚ እድገት እና ድህነትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ላይም ተጽዕኖ ያሳድራል።

 

ያለ
ክፍያ
በሚሰራ
የእንክብካቤ
ስራ
ውስጥ
ለሥርዓተ
ፆታ
አለመመጣጠን
መፍትሄዎች
ምንድን
ናቸው
?

የእንክብካቤ ስራ መንግስታትን፣ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን፣ የግል አገልግሎቶችን እና ቤተሰቦችን ጨምሮ በበርካታ ወገኖች ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ያለ ክፍያ የሚሰራ እንክብካቤ ሥራ እውቅና እና ዋጋ መስጠት

  • መንግስታት ያለ ክፍያ ለሚሰራ የእንክብካቤ ስራ እውቅና እና ዋጋ ለመስጠት ፖሊሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ይችላሉ። ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን፣ ለቤተሰብ እንክብካቤ ሰጭዎች የስልጠና መርሃ ግብሮችን እና ልዩ የምስክር ወረቀቶችን ወይም ለእንክብካቤ ስራዎች የሚሰጡ ዲፕሎማዎችን ሊያካትት ይችላል። በቤት ውስጥ፣ የቤተሰብ አባላት ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ሥራን ለሚሰሩት እውቅና እና ድጋፍ መስጠት ይችላሉ።
የሥራ እና የቤተሰብ ሕይወት ሚዛንን መጠበቅ

  • መንግስታት መሰረታዊ መሠረተ ልማቶችን እና አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶችን እንደ መብራት፣ ጤና አጠባበቅ፣ ውሃ፣ የህጻናት እንክብካቤ፣ ትምህርት ቤቶች እና መጓጓዣን ተደራሽነት የሚያበረታቱ ፖሊሲዎችን ማውጣት ይችላሉ። ማሻሻያዎች እንክብካቤ መኖሩን እና ለሁሉም በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው።
ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራን ሸክም ለመቀነስ መሳሪያዎችን ማዘመን

  • ዘመናዊ ምድጃዎች፣ የማጠቢያ መሳሪያዎች፣ ተደራሽ ወፍጮዎች እና ሌሎች የመሳሪያ ዓይነቶች እንደ ውሃ መቅዳትን ፣ የቤተሰብ ምርትን ማቀነባበር እና ማገዶ መሰብሰብን የመሳሰሉ ተግባራትን ጊዜ እና ጉልበት ሊቀንስ ይችላሉ።በሴኔጋል ገጠራማ አካባቢ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በአነስተኛ የውሃ ቧንቧ መስመር ላይ ኢንቨስት ማድረግ ሴቶች አዳዲስ የእንስሳት እርባታ ንግዶችን እና የአትክልት ስራዎችን ለመመስረት የተጠቀሙበትን ጊዜ ማዳን ችሏል።
አወንታዊ ወንድነትን ያስተዋውቁየሴትነት እና የእንክብካቤ ሥራን ጥብቅ ግንኙነት ምስልን ያስወግዱ።

  • የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች እና የባህል መሪዎች ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራን በሴቶች ላይ የሚገድቡ ልማዶችን ለመለወጥ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ይችላሉ። ይህም የእንክብካቤ ስራን እኩልነት የማያራምዱ አድሎአዊ አመለካከቶችን በተመለከተ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እና አዋቂዎች፣ ወንዶች ልጆች፣ ሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ የማህበረሰብ አባላት፣ በንግድ፣ በፖለቲካ እና በመንግስት ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና ሚዲያዎች አዎንታዊ ወንድነትን የሚያንፀባርቁ እርምጃዎችን ማበረታታትን ያካትታል።
  • ወንዶች የእንክብካቤ ሥራን ዋጋ እና የሚፈልገውን የጊዜ እና የእውቀት መዋዕለ ንዋይ ሲያውቁ በስራው የመሳተፍ እድላቸው ሰፊ ነው። ስለ እንክብካቤ ሥራ ያለው የጋራ ግንዛቤ የበለጠ አዎንታዊ ከሆነ እና በተለይም ይህ በተከበረ የማህበረሰብ መሪ የሚደገፍ ከሆነ, ወንዶች የበለጠ የመሳተፍ እድላቸው ሰፊ ነው።
  • አብዛኞቹ የተዛቡ አመለካከቶች በቤተሰብ ውስጥ የሚፀነሱ እና የሚቆዩ ናቸው። የሬዲዮ ፕሮግራሞች እና የተግባቦት ስልቶች አማራጭ ራዕዮችን በመስጠት እና ውይይትን በማበረታታት እና አመለካከቶችን፣ ባህሪያትን እና እሴቶችን በመቀየር ለእንክብካቤ ስራ የጋራ ሃላፊነትን ሊያበረታቱ ይችላሉ።

የጋራ ኃላፊነት ባህልን ማሳደግ

  • ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ ስራን መጠን መቀነስ እና የቤት ውስጥ ስራዎችን በቤተሰብ ውስጥ እንዲሁም በግሉ ሴክተር እና በመንግስት መካከል መጋራት ሴቶችን በኢኮኖሚ ያጎለብታል። ምክንያቱም ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለሚከፈልባቸው ስራዎች ሰፊ ጊዜ ስለሚያገኙ ነው። የተባበሩት መንግስታት ሴቶች መ/ቤት (UN Women’s He-for-She) እሱ ለእሷ ዘመቻ ወንዶች ከሴቶች ጋር በመተባበር ለሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እንዲቆሙ መንገዶችን ይከፍታል፣ እናም ከሴቶች ጋር እና እርስ በርስ በመተባበር የንግድ ሥራዎችን ለመሥራት፣ ቤተሰብ ለመንከባከብ እና ለማህበረሰባቸው መልሰው በመስጠት አወንታዊ ወንድነትን ያበረታታል።

 

ዓለም አቀፍ የእንክብካቤ እና የድጋፍ ቀንን ማስተዋወቅ

  • እ.ኤ.አ. በጁላይ 2023 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ጥቅምት 29 ቀንን አለም አቀፍ የእንክብካቤ እና የድጋፍ ቀን ብሎ አውጇል። ያለ ክፍያ ከሚሰራ የእንክብካቤ ስራ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን እውቅና እና ትኩረት በመስጠት ስራውን የሚያስተጓጉሉ ስርዓተ-ፆታዊ የስርዓት እንቅፋቶችን የመፍታት አስፈላጊነትን አጉልቶ ያሳያል።

ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ዩኬርአንፔይድ ኬር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራትተነሳሽነት ሲሆን ይህም የፆታ እኩልነትን እና የሴቶችን አቅም ለማሳደግ ያለመ በቤተሰብ እና በቤተሰብ ውስጥ ያለ ያለ ክፍያ የሚሰራ የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራ ተገቢ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለመጋራት ቁርጠኝነት ነው።ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ. ሀገራት ፕሮጀክቱ ከግሎባል አፌርስ ካናዳ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከፋርም ራዲዮ ኢንተርናሽናል (FRI) የተባበሩት መንግስታት የሴቶች ቢሮ እና እና አፍሪካን ዊሜንስ ደቨሎፕመንት ኤንድ ኮሚኒኬሽንስ ኔትወርክ (FEMNET) ጋር በመተባበር ይተገበራል።