መነሻ: የገብስ ምርት በኢቲዮጵያ

የሰብል ምርት

Script

ይህ ርዕሰ ጉዳይ ለአድማጮች አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ምንድነው ?

  • ገብስ በኢትዮጵያ ባህላዊ ሰብል ነው፡ ፡ በአገሪቱ ለተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች በመዋል ጥልቅ ታሪክ አለው፡፡
  • የብቅል ገብስ ምርት በጣም አጭር ታሪክ ያለው ሲሆን አመራረቱም ከ1920ዎች መጀመሪያ ጀምሮ በኢትዮጵያ የጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ መቋቋም ጋር ተያይዞ በዋናኛት ከቢራ ዝግጅት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡
  • በደጋማ አካባቢዎች የብቅል ገብስንማምረት በኢንድስትሪ ግባአትነቱ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የሰብል ዓይነትበ መሆኑን የማስተዋወቅ እና ማስፋት ሰፊ ዕድሎች አሉት፡፡

የብቅል ገብስን ለማምርት ፍላጎት ያላቸው አርሶ አደሮች የሚከተሉትን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል

  • የብቅል ገብስን አመራረትና አያያዝ
  • የአግሮ ኢኮኖሚ ልምዶችንእና ተሞክሮዎችን በአግባቡ መከተል (በመስመር መዝራት፤ ማረም፤ የውሃ መውረጃ ማዘጋጀት) ጨምሮ የሚመከሩ የብቅል ገብስ የአመራረት ዘዴ ተመኩሮዎች የዘር አይነቶችንባህሪ ማወቅ ፤ ማዳበሪያ አጨማመር፤ የኬሚካል(የፀረ አረም እና የፀረ ፈንገስ) አጠቃቀምን፤
  • የብቅል ገብስን እንዴት መሰብሰብ፣ መውቃት እና ንፁህ ምርት ማግኘት እንደሚቻል፤
  • ከሚፈለገው ዝርያ ውጭ የሆነውን መለየትና መስወገድ፤
  • ከምርት መሰብሰብ በኋላ ብቅል ገብስ አያያዝ፤እና አከመቻቸት፤
  • የብቅል ገብስን ለማከማቸት የሚያስፈልግ ትክክለኛ የእርጥበት መጠን፤ እንዲሁም
  • የብቅል ገብስ ምርት ንፅህናውን ከሚያጎድፉ እንደ ጠጠር፣ የሌሎች ሰብሎች ዘሮች፣ የተሰባበሩ ዘሮች፣ እና ሳር መሰል ማናቸውም ነገሮች ፅዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

የተወሰኑ ቁልፍ እውነታዎች ምን ምን ናቸው?

  • ከተዘራ በኋላ የብቅል ገብስ እንደየ ዝርያው ከ አራት እስከ አምስት ወራት ባሉት ጊዚያት ውስጥ ይደርሳል፡፡ ቶሎ የሚደርሱት ዝርያዎች እስከ ሶስት ወር ተኩል ሊደርሱ ይችላሉ፡፡
  • ለምርት የደረሱ የብቅል ገብስ ግንድ ጠንከር ያሉ እና በእጅ ሊሰበሩ የሚችሉ ይሆናል፡፡
  • የብል ገብስ ፍሬው ወደ መሬት ማጎንበስ ሲጀምር ለመታጨድ ዝግጁ መሆኑን ያመለክታል፡፡
  • የብቅል ገብስ ከደረቀ በኋላ የእርጥበት መጠኑ ከ 12-12.5% በታች በሆነ ቦታ በማከማቸት በተባዮች እና ጎጂ በሆኑ ፈንገስ ነክ ታህዋስያን ከመጎዳት መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
  • የሚመከረው የዘሮቹ አጣጣል በአንድ ሜትር ካሬ ከ250-300 ሰብሎች መሆን አለበት፡፡
  • የብቅል ገብስ ውሃ የመቋጠር ችግር ባለባቸው ጥቁር ሸክላማ አፈር በሚገባ ሁኔታ አይበቅልም፡፡ ሰብሉ የሚመርጠው የተንጣፈፈ እና ወደ ቡኒ የሚያደላ ቀይ አፈርን ነው፡፡
  • በመካከለኛ ደጋ የብቅል ገብስ የሚያበቅሉ ስፍራዎች በአፈር አሲዳማነት ይጠቃሉ፡፡ ለተሸለ ምርት ኖራ እና ማዳበሪያ እንዲጠቀሙ ይመከራል፡፡
  • ብቅል በቢራ ምርት ቁልፉ ግብአት ነው፡፡ ብቅሉን ወደ አልኮልነት የመቀየር ብቃት ያላቸውን የተብላሉ ስኳሮችን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ስታርች እና ኢንዛይሞችን ይሰጣል፡፡
  • የብቅል ውጤት ለቢራ ፋብሪካዎች ቁልፍ ግብአት ነው፡፡ ሁሉንም የሚሟሙ ይዘቶች በተለይም ካርቦሀይድሬትን እና ፕሮቲኖችን ከነ ውጤቶቻቸው እንዲሁም የቀለም እና የቃና(ጣእም) ይዘትን ይሰጣል፡፡
  • በብቅል አዘገጃጀት ሂደት በገብሱ ፍሬ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ የስታርች ይዘት ወሳኙ ግብአት ነው፡፡
  • ብቅል ገብስ የፕሮቲን መጠን ከ 9-11.5 % መሆን አለበት፡፡ የፕሮቲን መጠኖች በተለያዩ ምክንያቶች ይለያያሉ፡፡ በተለይም የአበቃቀል ሁኔታዎች የራሳቸው ተፅእኖ ይኖራቸዋል፡፡ በናይትሮጅን የበለፀጉ ማዳበሪያዎችን መጠቀምም የመጨረሻውን የፕሮቲን መጠን ላይ ተፅእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 2፣3፣ 5፣ 6፣ እና 13 ን ይመልከቱ፡፡

የብቅል ገብስ ምርት ላይ የሚያጋጥሙ ዓበይት ፈተናዎች ምን ምን ናቸው ?

  • ኋላ ቀር የመሬት አያያዝ እና ዝቅተኛ የአግሮ ኢኮኖሚ ልምዶች፤
  • የመሬት አፈር ለምነት እና ይዘት መሳሳት፣ የአፈር አሲዳማነት፣ እና በአፈር መሸርሸር እና በተደጋጋሚ አንድ ዓይነት ሰብል በማብቀል (ለምሳሌ፡ የብቅል በብስ፣ ስንዴ፣ እና ጤፍ) በየዓመቱ በተመሳሳይ መዝራት፡፡
  • ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የተሻሻሉ ዝርያዎች እጥረት፤
  • በብቅል ገብስ ምርት ስብሰባ ወቅት የሚያጋጥሙ በጣም እርጥበታማ ሁኔታዎች ለተባይና ፈንገስ ማጋለጡ፤
  • ብዙ ምርት የሚሰጡ አና ከፍተኛ የብቅልነት ባህርይ ያላቸው ዝርያዎች ውሱን መሆናቸው፡
  • ዝቅተኛ የገበያ እና የአቅርቦት ትስስር መኖር፡
  • የተሸሻሉ የምርጥ ዝርያዎችዘር በበቂና በጥራት ተባዝቶ ለተጠቃሚዉ አለመዳረሱ የሚየባዙ አካላት ዉስንነት፣ ኬሚካሎች ፣እና ማዳበሪያዎች ያሉ ግብአቶች በበቂ ሁኔታ አለመኖር መሰል ችግሮች፡
  • የአግሮ ኢኮኖሚ፣ የመሬት አያያዝ ፣ ተባዮችን እና በሽታዎችን የመከላከልልምዶች ላይ አርሶ አደሮች በብቅል አመራረት ዙሪያ ያላቸው መሰረታዊ እውቀት አናሳ መሆን ፡
  • አርሶ አደሮች የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የብቅል ገብስ ማምረት ላይ ዕውቀት ማነስ ይስተዋላል፡፡

ስነ ፆታ እና የብቅል ገብስ ምርት

  • በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ የብቅል ገብስ አምራች አካባቢዎች ሴቶች በገብስ ጥራት፣ ጥንካሬ፣ የዱቄት ውጤት፣ ከምግብነት ፣ ከብቅልነት ጥራት፣ እንዲሁም ለመጠጥነት ካለው ተመራጭነት አኳያ ሴቶች የተሻለ ዕውቀት አላቸው፡፡ ወንዶች ደግሞ በአግሮ ኢኮኖሚ ማለትም እንደ ሰብሎች ቁመት ፣ ዕድገት፣ በሽታ የመቋቋም ሁኔታ፣ ምርታማነት፣ ያሉ ጉዳዮች ላይ የተሸለ እውቀት አላቸው፡፡
  • አጨዳ እና ውቂያ መካናይዝድ በሚሆኑበት ጊዜ ወንዶች በሴቶች በባህላዊ መንገድ የሚከናወኑት ስራዎች ላይ በንቃት ይሳተፋሉ፡፡
  • በኢትዮጵያ ሴቶች ገብስን አዘጋጅተው በመሸጥ ለቤት አስቤዛ መጠቀሚያነት ይገለገሉበታል፡፡
  • በሰሜናዊ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሴት እማዎራዎች በሬ የማግኘት አቅማቸው አናሳ በመሆኑ እና ሴቶች ራሳቸው የማረስ ችሎታ ባለማግኘታቸው ተጎጂ ሆነው ይገኛሉ፤ ምክንያቱም ለገብስ የሚሆን ማሳ ለማዘጋጀትም ሆነ ለማረስ ወንዶችን እንዲጠብቁ ግድ ስለሚላቸው ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 7፣10፣ እና 14ን ይመልከቱ

በብቅል ገብስ ምርት ላይ በአየር ለውጥ ሳቢያ ሊፈጠር እንደሚችል የሚጠበቅ ተፅዕኖ

  • በአየር ለውጥ ሳቢያ የሚከሰት ድርቅ ማሳ ላይ ያለው ገብስ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡
  • በገብስ መብቀያ ወቅት የዝናብ ወቅት እና ስርጭት መዛባት ሲያጋጥም የብቅል ገብስ እድገትን በመግታና በማዛበት የብቅል ሰብል ጥራት( ፕሮቲንን በመጨመር) እና ምርታማነት ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡
  • የአየር ሁኔታ መዛባት በሽታዎችን እና ተባዮችን እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል
  • በዘልማድ ምስራቅ አፍሪካ አካባቢዎች የሚመረተው የገብስ ምርት በሚያጋጥመው የሙቀት መጨመር እና የዝናብ እጥረት ምክንያት ዕድገቱ ሊታይ አልቻለም፡፡
  • በምርት ወቅቶች ሞቃታማ እና ደረቅ የአየር ሁኔታ መጠን እየጨመረ መምጣቱ የገብስ ምርት ላይ ፕሮቲን እንዲጨምር በማድረግና የስታርች ይዘቱ እንዲቀንስሰለሚያደርግ ለቢራ ግብአት የመሆን እድሉን እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡
  • በምርት ወቅት የሙቀት መጠን መጨመር ለቢራ ምርት ግብአትነት ወሳኝ የሆነውን የስታርች ይዘቱን እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 6፣ 8፣ 9እና 11ን ይመልከቱ ፡፡

ስለ ብቅል ገብስ ቁልፍ መረጃዎች

 
እርሻ

የብቅል ገብስ ለቢራ ጠመቃ ፣ ለእንስሳት መኖ፤ እንዲሁም ለሰው ልጆች በምግብነት ያገለግላል፡፡ የብቅል ገብ በትክክል እንዲያድግ አርሶ አደሮች የሚከተሉትን ልምዶች መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡-

  • የብቅል ገብስ ከመዘራቱ በፊት የጎደሉ ይዘቶችን ለመለየት የአፈር ምርመራ ያድርጉ፡ አፈሩ አሲድነት ካለው ኖራ ይጨምሩበት፡፡ በምርመራ አፈሩ የጎደለውን በመለየት አልሚ ይዘቶችን ወይም ማዳበሪያዎችን ይጨምሩ፡፡
  • ለገብስ ማብቀየ የሚሆን መሬት በዘላቂነት ውጤታማ እንዲሆን በየሶስት እና አራት ዓመቱ በደጋ ጥራጥሬ፤ ደጋ ቅባት ና ድንች ስብሎች መቀያየር ይኖርበታል፡፡
  • ብቅል በማብቀል ሂደት በተመሳሳይ ደረጃ እንዲበቅል ዝርያው አንድ አይነትእና የተሰተካከል ፍሬ ያለዉ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • አጨዳው በተመሳሳይ ወቅት እና በጥራት እንዲከናወ ሜዳማ በሆነ መሬት ላይ መዝራት አስፈላጊ ነው፡፡ በወጣ ገባ መሬት ላይ በሚዘራበት ጊዜ ሰብሎቹ ላይ የተዘበራረቀ የዕድገት ደረጃ ያጋጥማል፡፡
  • የማይበቅሉ ዘሮችን ለመለየት በአንድ ካሬ እስከ 28 ዘሮችን ይዝሩ፡፡ ይህ በአማካኝ 25 የብቅል ገብሶችን ያስገኛል፡፡
  • የብቅል ገብሶችን ከ 1.5 እስከ 2 ኢንች በሚደርስ ጥልቀት ይዝሩ፡፡ ጥልቀቱ በጣም ዝቅ ካለ ሰብሉ ደካማ እንዲሆን ብሎም በሚገባ እንዳይበቅል ያደርገዋል፡፡
  • ከመዝራት በፊት አርሶ አደሮች ዘሮችን ከተለያዩ ተባዮች እና በሽታዎች ለመጠበቅ በፀረ ፈንገስ ማከም ይኖርባቸዋል፡፡ ሰብሎችን ማቀያየር እና ከመዝራት በፊት የተበከሉ ተረፈ ምርቶችን ማቃጠልም የበሽታ የመዛመት ፍጥነትን ይቀንሳል፡፡
  • የብቅል ገብስ በእንጭጩ እያለ ማረም አረሞች የሰብሉን ንጥረ ምግብ እንዳይሻሙ እና እድገቱንም እንዳያደናቅፉ ይረዳል፡፡ ባለ ሰፋፊ ቅጠሎችን እና ሳር መሰል(እንደ ስናር እና ሙጃ ) አረሞችን ለመቆጣጠር በእጅ ወይም በፀረ አረም ያስወግዱ፡፡
  • የብቅል ገብስ የተሻለ ዕድገት እንዲኖረው በቂ ናይትሮጅን ይፈልጋል፡፡ ከተቻለ እንደ አተር፤በቄላ እና ሽምብራ ያሉ የጥራጥሬ እህሎች ከተመረተበት ማሳ ላይ አስከትሎ መዝራት በይዘት የበለፀገ አፈር ለማግኘት ይረዳል፡፡
  • በሄክታር የሚመከረው የናይትሮጅን መጠን የሚወሰነው በአፈሩ የለምነት ሁኔታ ሲሆን እንደየአካባቢውም ይለያያል፡፡
  • የብቅል ገብስ አርሶ አደሮች ማሳዎቻቸው ከመጠን በላይ ናይትሮጅን እንዳይጨመርበት መጠበቅ አለባቸው፡፡ ይህ የብቅል ገብሱ ላይ የፕሮቲን መጠኑን ከሚፈለገው በላይ ማለትም ከ 9.5-11.5% በላይ በማድረግ ለብቅል ምቹ እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡
  • የብቅል ገብስን የብርዕና አገዳ ስብሎች በተመረቱበት ማሳ መዝራት ምርትን ዝቅተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ከስንዴ፣ ከጤፍ፣ እና ከቦቆሎ ቀጥሎ ከተዘራ እንደ ዋግ ላሉ ፈንገሶች ሊያጋልጠው ይችላል፡፡
  • ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ለሚዘራበት አካባቢ የአየር ሁኔታ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ ዝርያ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
  • የበሽታዎችን ዑደቶች እና የገብስ እርሻ ተባዮችን ለማስወገድ አርሶ አደሮች ገብስን በሌሎች ሰብሎች በማቀያየር መዝራት ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይም እንደ ዐተር እና ባቄላ ካሉ አፈርን በናይትሮጅን የማበልፀግ ብቃት ባላቸው የደጋ ጥራጥሬዎች ማቀያየር ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ገብስ እንደ ተልባ እና ድንች ካሉ የደጋ ሰብሎች ጋርም እያቀያየሩ ማብቀል ይቻላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 4፣ 5፣ 6 ፣ 9፣ 1፣5 እና 16ን ይመልከቱ፡፡

አጨዳ (ምርት ስብሰባ)

አርሶ አደሮች ምርቱን መሰብሰብ ያለባቸው ማሳው ወደ ቢጫማ ቀለም በሚቀየርበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የገብስ ሰበሎች ከወደ አናታቸው ወደ መሬት ጎንበስ ብለው እና አረንጓዴ ቀለማቸውንም በቢጫ በመተካት ለመሰብሰብ ዝግጁ መሆናቸውን ያስታውቃሉ፡፡ የብቅል ገብስን በወቅቱ መሰብሰብ ሰብሉን መሰባበር እና የጥራት መጓደልን ለመከላከል ይረዳል፡፡

  • የብቅል ገብስ እንደየ አርሶ አደሩ የገቢ አቅም በማጭድ፣ አልያም በኮምባይነር ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
  • ቶሎ እንዲደርቅ ደግሞ ገብሱን በማጨድ በመስመር ማስቀመጥ
  • ሰብሉ እየታጨደ በሚጠቀለልበት ጊዜ የእርጥበት ይዘቱ ከ 20-30% መሆን አለበት፡፡
  • አርሶ አደሮች የእርጥበት መለኪያ አቅርቦት ከሌላቸው አውራ ጣታቸውን ዘርግተው ጠበቅ አድርገው ፍሬው ላይ መጨበጥ ይችላሉ፡፡ የገብስ ፍሬው በሚገባ የደረቀ ከሆነ ፍሬዎቹ በአውራ ጣት ሊጨበጡ አይችሉም፡፡
  • የታጨደ የብቅል ገብስ ዝናብ ከመታዉ እርጥበቱን ከ 12-12.5% ድረስ እስኪቀንስ ማሳው ላይ መቆየት አለበት፡፡

ድህረ-ምርት

ውቂየ (Threshing)

አርሶ አደሮች ውቂያ በሚያካሂዱበት ወቅት ገብሱ እንዳይጎዳ እና እንዳይሰባበር ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ የተሰባበሩ እና የተላላጡ ፍሬዎች ወደ ብቅል ላይቀየሩ ይችላሉ፤ አልያም የመብቀል ውጤቱ አነስተኛ ይሆናል፡፡ አርሶ አደሮች የብቅል ሰብሎቻቸውን የመውቂያ ማሽን ባለው ትራክተር ፤ በቤት በሚዘጋጅ መሳሪያ፤ ወይም በሬዎችን ወይም ፈረሶችን በመጠቀም መውቃት ይችላሉ፡፡ የብቅል ገብስ እርጥበቱ ከ 12-12.5 ሲሆን መውቃት ይቻላል፡፡

ማድረቅ (Drying)

የብቅል ገብስን አዘጋጅቶ ከማከማቸት በፊት ማድረቅ ያስፈልጋል፡፡ የታጨደ ገብስ እርጥበቱ ከ12.5% በታች እስኪደርስ በፀሀይ ብርሃን ይደርቃል፡፡ በዚህ የእርጥበት ደረጃ ሻጋታ እንዳይፈጥር የተወሰነ ስጋት ቢኖርም መከማቸት ይቻላል፡፡

ክምችት (Storage)

የብቅል ገብስ እንዳይበላሽ ለመከላከል እርጥበቱ ከ12.5% በታች ሆኖ በቀዝቃዛ፣ ደረቅ፣ እና ንፁህ ቦታ ማከማቸት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ሻጋታን ለመከላከል እና በሚፈልገው መጠን እንዲበቅል ያስችለዋል፡፡

ብቅል የማብቀል ሂደት (The malting process)

የብቅል ገብስን ወደ ማብቀል ሂደት ከመግባት በፊት ጤነኛ ያልሆኑ ፍሬዎችን እና ሌሎች ባዕድ ነሮችን መልቀም ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ደረጃ ይወጣለታል፡፡
ማብቀል ገብስ ወደ ብቅል የሚቀየርበት ባዮከሚካልያዊ ሂደት ነው፡፡ ሂደቱ ሶስት ደረጃዎችን ማለትም መዘፍዘፍን፣ ማብቀልን፣ እና ማድረቅን ያካትታል፡፡ ሂደቱ ከ 4-5 ቀናትን ይጠይቃል፡፡

በመዘፍዘፍ ሂደት የእርጥበት ይዘቱን ጨምሮ ለብቅልነት ዝግጁ ይሆናል፡፡

ብቅል ማብቀል ፍሬዎቹ ወደ ብቅልነት በሚቀየሩበት ጊዜ ለቢራ ጠመቃ ተፈላጊ የሆነውን ኢንዛይም እንዲጠብቁ ከአየር ሁኔታ፣ ከእርጥበት መጠን፣ እና ከጊዜ ጋር በጥንቃቄ ቑጥጥር የሚደረግበት ሂደት ነው፡፡

ማድረቅ (drying) የፍሬዎቹን የእርጥበት መጠን ይቀንሳል፤ በፍሬዎቹ ውስጥ የባዮኬሚካል ሂደቱን ያስቆማል፤ በመብቀል ሂደት የሚመነጨውን ኢንዛይም በጥንቃቄ ያቆያል፤ እንዲሁም የቀለም እና የቃና (flavor) ውህዶችን ያመነጫል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 1፣ 2፣ 12 እና 13ን ይመልከቱ

የብቅል ገብስን በከፍተኛ ጥራት ለማብቀል የሚከተሉት ባህርያት ያስፈልጋሉ፡

  • ንፁህ እና ተቀባይነት ያለው ዝርያ
  • 95 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ማብቀል (በሶስት ቀን ሙከራ)
  • ከ 9%-11.5% የፕሮቲን ይዘት
  • ቢበዛ እስከ 12.5% የሚደርስ የእርጥበት መጠን
  • ተመሳሳይ መጠን ያላቸው ፍሬዎች
  • ሙሉ በሙሉ የደረሰ
  • የቅድመ ስብሰባ የብቅል ምልክቶች አለመታየት
  • ከሰብል አናት በሽታ ነፃ መሆን
  • ከሌሎች በሽታዎች ነፃ መሆን
  • ከውርጭ አደጋ ነፃ መሆን
  • በአየር ሁኔታ ሳቢያ አለመበላሸት
  • ከ 5% በታች የተላላጠ ወይም የተሰባበረ ፍሬ
  • ከከተባዮች ፣ ከዝርያ ውጭ ከሆኑ ዘሮች ፣ ከፈንገስ ፣ እና ቃና ነፃ መሆን
  • ከኬሚካል ዝቃጭ ነፃመሆን

ፍች (Definitions)

ብቅል : በቢራ ጠመቃ ቁልፉ ግብአት የሆነው ብቅል እርሾን ወደ አልኮልነት የመቀየር ብቃት ያላቸው የተብላሉ ስኳሮችን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ስታርች እና ኢንዛይሞችን ይሰጣል፡፡ ብቅል በተጨማሪም የቢራ ቀለምን የሰጣል፡፡

የብቅል ውጤት: ይህ ማለት ከብቅል የሚወጣ ሊብላላ የሚችል የስኳር የዘት ነው፡፡ ይህም በቶን ደረጃ ከብቅል ሊዘጋጅ የሚችለው የአልኮል መጠንን ይወስናል፡፡ ከብቅል የሚገኘው የውጤት መጠን ከፍ ባለ ቁጥር ሊገኝ የሚችለው የአልኮል መጠንም ከፍ ይላል፡፡

ብቅል ማብቀል: በውሃ አማካኝነት በላቀ ቁጥጥር ገብስን ወደ ብቅል ለመቀየር የሚደረግ ሂደት ነው፡፡ ብቅል ማብቀል በገብስ ፍሬ ያለውን የስኳር መጠን እንዲለቅ ያደርጋል፡፡

በዚህ ርዕስ ተጨማሪ መረጃ ከየት መግኘት እችላለሁ ?

ሰነነዶች

  1. ፋኦ (FAO) (የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የግብርና ድርጅት) 2009፡፡ የገብስ ብቅል ቢራ ፤ http://www.fao.org/fileadmin/user_upload/tci/docs/AH3_BarleyMaltBeer.pdf (783KB).
  2. ማክሊዮድ፣ አሮን ቀኑ ያልተጠቀሰ፡፡ የብቅል ገብስን መረዳት ጥራት፡. http://msue.anr.msu.edu/uploads/234/78941/Understanding_Malting_Barley_Quality_-_Aaron_MacLeod.pdf (145KB).
  3. ኖርዝ ዳኮታ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፣ ቀኑ ያልተጠቀሰ የተሸሻለ ገብስ አግሮኖሚ፤. http://msue.anr.msu.edu/uploads/235/92786/Horsley_Rich_2017_Great_Lakes_Hop__Barley_Conference.pdf (2.657MB).
  4. የቢራ ጠመቃ እና ብቅል ምርምር ተቋም ፡፡ (Brewing and Malting Barley Research Institute) (BMBRI), ቀኑ ያልተጠቀሰ.Quality Factors in Malting Barley. http://bmbri.ca/wp-content/uploads/2016/10/Quality-Factors-in-Malting-Barley-May-2010.pdf (431KB)
  5. ቬርበተን ቢል ፤ ቀኑ ያልተጠቀሰ የብቅል ንጥረ ነገርን ማብቀል (Malting Barley Nutrient) Management. http://agresearch.montana.edu/wtarc/producerinfo/agronomy-nutrient-management/Barley/MaltBarleyNutrientManagement.pdf (2.13MB).
  6. የግብርና ፣ ደን፣ እና የዓሳ ንግድ፤ ዲፓርትመንት ደቡብ አፍሪካ ፤ 2009 ፡፡ Barley. https://www.daff.gov.za/Daffweb3/Portals/0/Brochures%20and%20Production%20guidelines/Brochure%20Barley.pdf (7.11MB).
  7. ኬር ኢንተርናሽናል ዩኬ ዲያጎ ፤ ቀኑ ያልተጠቀሰ ሴቶች እና ገብስ እርሻ https://www.diageo.com/PR1346/aws/media/6246/care-diageo_summary_women-in-barley-farming-ethiopia_2018.pdf (589 KB)
  8. ቬየርጌቨር ፣ካሪን እና ቲፐር ፣ ሪቻርድ ፣ 2014 ፡፡ የአየር ፀባይ ለውጥ በኬንያ ገብስ ህልውና ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለዲያጎ ማቀድ( Projecting the impact of climate change on the availability of barley in Kenya) ፣ 2013-2033 ፡፡ https://ecometrica.com/assets/Impact-of-climate-change-on-barley-in-Kenya-to-2033-Ecometrica-final-v1.4.pdf (4.96MB).
  9. አልበርታ ግብርና ፤ 2009. ብቅል ማብቀል Barley. https://www1.agric.gov.ab.ca/$department/deptdocs.nsf/all/agdex98/$file/114_20-2.pdf?OpenElement (205KB).
  10. CGIAR, 2013. CGIAR Research Program on Dryland Cereals. https://cgspace.cgiar.org/bitstream/handle/10947/2829/Dryland_Cereals_-_Concept_Note_for_Discussion_with_Donors_and_Partners_-_June_2013_(Discussion_Document).pdf?sequence=1 (947KB).
  11. የግብርና ፣ ደን፣ እና የዓሳ ንግድ፤ ዲፓርትመንት ደቡብ አፍሪካ ፤2017፡፡ የግብርናው ዘርፍ ልምድ (Trends in the Agricultural Sector) ፤ https://www.daff.gov.za/Daffweb3/Portals….pdf (1.808MB).
  12. ፔተርሰን፣ C.G. 2006፡፡ በገብስ ብቅል ማብቀል በምርት እና በፕሮቲን ይዘት ያለ ልዩነት (Variation in yield and protein content of malting) barley. https://pub.epsilon.slu.se/1056/1/cgp_lic.pdf (1 MB)
  13. አካር ቲ ፣ አቪክ ኤም ፣ እና ዳሰንቸሊ ኤፍ ፤ 2004፡፡ የገብስ ድህረ ምርት እንቅስቃሴ http://www.fao.org/fileadmin/user_upload/inpho/docs/Post_Harvest_Compendium_-_BARLEY.pdf (1.56MB).
  14. አባይ ኤፍ ፤ ጆርንስታድ ኤ ፣ እና ስማል ኤም፡ 2009፡፡የእርሻ ስብጥርን መለካት እና የገብስ ስብጥርን የሚወስኑ ወሳኝ ነጥቦች በ ትግራይ : ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ፤ http://www.mu.edu.et/mejs/pdfs/v12/7-Fetien.pdf (380 KB)
  15. McFarland, A., et al, 2014. የገብስ ምርትን ማብቀል በሚቺጋን ፤ http://www.canr.msu.edu/uploads/396/36753/Research_Files/Malting_Barley_Production_in_Michigan_-_GMI035.pdf (4.573MB).
  16. የኖርዝ ዳኮታ የገብስ ፤ ቀኑ ያልተጠቀሰ ፡፡ የብቅል ገብስ ምርት መመሪያዎች ለ ኖርዝ ዳኮታ http://ndbarley.net/image/cache/Malt_Barley_Production_Guide_for_Web_Site.pdf (195 KB).

Acknowledgements

ምስጋና
አስተዋፅኦ ያበረከቱ: በኬንያ የግብርና ጋዜጠኛ ጀምስ ካሩራ
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የገብስ አዳቃይ በብርሃነ ላቀው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ሁኔታ ተገምግሞ የተዘጋጀ – ኢትዮጵያ፡፡

ይህ ድህረ ታሪክ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ነው