Notes to broadcasters
Save and edit this resource as a Word document.
ማስታወሻ ለአዘጋጅ
ይህ የአዘጋጅ መረጃ ሰነድ በአድማጮች ጥናት የክፍል 1 አካል ነው፡፡ በማላዊ- ንኮታኮታ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ አዘጋጅ ከሆነው ከፊሊፕ ቺንኮክዌ ጋር የተካሄደ ቃለ መጠይቅን ያስቃኛል፡፡ በቃለ መጠይቁ ፊሊፕ የሚሰራበት ጣቢያ የአድማጮች ጥናት የሚካሄድበት ዘዴን አብራርቷል ፤ እንዲሁም በአፈር ጥበቃ ዙሪያ በተዘጋጁ ፕሮግራሞች የተካሄደውን የአድማጮች ጥናትን በምሳሌነት አቅርቧል፡፡ የዚሁ ሰነድ ሁለተኛው ክፍል በቃለ መጠይቁ የተብራራውን የድማጮች ጥናት መሰረት በማድረግ በአፈር ጥበቃ ላይ ከተዘጋጁ የሬድዮ ፕሮግራም የተወሰደ ፅሁፍ “ ነው፡፡
ይህን ፅሁፍ አንብበህ የሬድዮ ጣቢያህ የአድማጭ ጥናት የሚያካሂድበት ዘዴ የንኮታኮታ የሬድዮ ጣቢያ የአድማጮች ጥናት ከሚያካሂድበት ጋር ተመሳሳይነት ካለው አረጋግጥ፡፡ ከንኮታኮታ ተሞክሮ መማር የምትችለው ትምህርት አለ? በንኮታኮታ ፕሮግራሞች ዝግጅት የአርሶ አደሮች ድምፅ ምን ያህል ጎልቶ መውጣቱን እና ጣቢያው የምንጭ እጥረት ያለባቸው ይዘቶችን የሌሎች ፕሮግራሞች በጀት በመጠቀም እና የሌሎች ድርጅቶች ፕሮግራሞችን እንደ መልካም የተጠቀመበትን ሁኔታ አስተውል ፡፡
በክፍል 1 እንደተጠቀሰው ከአድማጮችህ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ስኬታማ የግብርና ፕሮግራም ለመፍጠር በቅድሚያ አድማጮችህን ማወቅ እንዲሁም ምን ዓይነት የግብርና መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው መገንዘብ ግድ ይላል፡፡
ጥሎ ፊሊፕ ከገለፃቸው የጥናት ስራዎች መካከል አድማጮችህን ለማወቅ እና ፍላጎቶቻቸውንም ለመለየት ጥሩ ዘዴዎች ናቸው፡፡
Script
ሬድዮዎች አድማጮቻቸው በሬድዮ ሊደምጡት የሚፈልጉትን መረጃ ማስደመጥ ሲችሉ ጣቢያዎቹ በተሸለ ደረጃ ዒላማቸውን መትተዋል ማለት ነው፡፡ አድማጮች ምን ማድመጥ እንደሚፈልጉ ፤ መቼ ማዳመጥ እንደሚፈልጉ በመግለፅ እና ድምፆቻቸውን አየር ላይ እንዲደመጥ በማድረግ በፕሮግራም ዝግጅት ተሳታፊ መሆን ይችላሉ፡፡
የሚከተለው የአዘጋጅ መረጃ ሰነድ ሁለት ክፍሎች አሉት፡፡ የመጀመሪው ክፍል በማላዊ- ንኮታኮታ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ አዘጋጅ ከሆነው ከፊሊፕ ቺንኮክዌ ጋር የተካሄደ ቃለ መጠይቅ ነው፡፡ በቃለ መጠይቁ ፊሊፕ የሬድዮ ጣቢያው እንደ ግብርና ሚኒስቴር እና ለትርፍ ካልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት የአርሶ አደሮች ፕሮግራሞች ለማዘጋጀት ያካሄደውን ጥናት ያብራራል፡፡ ሁለተኛው ክፍል ፊሊፕ እና ባልደረቦቹ ባካሄዱት ጥናት ተመስርቶ ፊሊፕ ያዘጋጀው የፅሁፍ (ቃለ መጠይቅ) አካል ነው ፡፡
ክፍል 1: ከሬድዮ አዘጋጅ ጋር ቃለ መጠይቅ
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
እባክህን ስምህን እና እዚሁ በንኮታኮታ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ውስጥ ያለህን የስራ ድርሻ ብትገልፅልን?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ስሜ ፊሊፕ ቺንኮክዌ ነው ፤ የሬድዮ አዘጋጅ እና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኦፊሰር ነኝ፡፡ አብዛኛው ስራዬ መስክ ላይ እየቀረፅኩ የፕሮግራም ግብአት ማሰባሰብ ፤ ስኬታማ ታሪኮችን መሰነድ ፤ ከአድማጮች ግብረ መልስ ማሰባሰብን ያካታል፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
እዚሁ በንኮታኮታ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ውስጥ እንዴት ነው ጥናት የምታካሂደው?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
አብዛኛዎቹ ፕሮግራሞቻችን – ለምሳሌ፡- የግብርና፣ የጤና፣ ወይም የትምርት ፕሮግራሞች
በቀጣናችን ከሚገኝ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው የምናዘጋጀው፡፡ ለግብርና ፕሮግራሞች የግብርናው ዘርፍ በተወሰኑ የግብርና መስኮች ላይ የፍላጎት ዳሰሳ በማድረግ አርሶ አደሮች ሊተገብሩት የሚችሉት መልካም ተሞክሮ ይለያል፡፡ በመቀጠል አርሶ አደሮች በሬድዮ ፕሮግራማችን የምናስተዋውቀውን ሰብል በትጋት ወደሚያበቅሉ ይመሩናል፡፡በፕሮግራሞቹ ሂደት፤ ለምሳሌ ቦቆሎ በዚህ ግብርና ያሉ አርሶ አደሮችን በመደበኛነት እንጎበኛለን፡፡ ድምፆቻቸውን በመቅረፅም በፕሮግራማችን እናቅርብላቸዋለን፡፡ በተጨማሪ ስኬታማ ታሪኮችን እንሰንዳለን፡፡ አርሶ አደሮች ቀጥተኛ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን ያገኛሉ፡፡ እነዚህ አርሶ አደሮች ትጉ አድማጮች ይባላሉ፡፡ የግብርናው ዘርፍ እነዚህን ሰብሎች ወደሚያመርቱባቸው ኣከባቢዎች ይመራናል ፤ ሆኖም ትጉ ባልናቸው የአርሶ አደሮች የብዛት ደረጃ መልካም ተሞክሮ አልለየንም፡፡ እነዚህ አርሶ አደሮች በቀላሉ ሬድዮውን እያዳመጡ ግብረ መልስ ይሰጡናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስኬታማ ታሪኮችን ለመቅረፅ እና ፕሮግራሞቻችን በአድማጮቻችን ዘንድ የፈጠሩትን ተፅዕኖ ለመዳሰስ እንጎበኛቸዋለን፡፡ እነዚህን ደግሞ ትጉ ያልሆኑ አድማጮች እንላቸዋለን፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
እነዚህን አርሶ አደሮች በመለመሪያ ስትጎበኛቸው ምን ታደርጋለህ ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
አርሶ አደሮችን ስለ ጥንካሬያቸው ፤ ስለ ድክመታቸው እና ስለ መልካም ዕድሎቻቸው እና ፈተናዎቻቸው እንጠይቃቸዋለን፡፡ከዚያም ሰዎች ፕሮግራሙ የመረጃ ፍላጎታቸውን ያሟላልናል የሚል ስሜት እንዲኖራቸው ፍላጎት ያለቸው የማህበረሰቦች የአድማጮች ክለብ እንፈጥራለን፡፡ ክለቦቹን ከኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና ከሃላፊዎች ጋር በመተባበር እናደራጃቸዋለን፡፡ ሃላፊዎቹ በመንደሩ ስብሰባ ይጠራሉ፤ እኛም ከጤና ኤክስቴንሽን ጋር ሆነን ስብሰባውን እንከታተላለን፡፡ ክለቦቹ እስከ 10 የሚደርሱ ኣባላት አሏቸው፡፡ በቀጣይ ፕሮግራሞች አድማጮችን መመሪያ እንሰጣቸዋለን፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
የአድማጭ ክለቦች ከተደራጁ በኋላ ምን ይደረጋል?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ቀጥሎ ስለ ቀጣዩ ፕሮግራም ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ የፕሮግራም ማስታወቂያዎችን እናዘጋጃለን በተጨማሪ ትጉ እና ትጉ ያልሆኑ አከባቢዎች በማስታወቅያዎቻችን አማካኝነት ስለ ፕሮግራሙ ሰምተው ወደ ጣቢያው በመደወል ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት የሚገልፁ አድማጮች አሉ፡፡ እነዚህ አድማጮች ክለቦች ፈጥረው እንደ ትጉ እና ትጉ ያልሆኑት አድማጮች ሁሉ በፕሮግራሙ ሂደት እና ከፕሮጀክቱ መጠቃለል በኋላ እንቅስቃሴዎቻቸውን እና ማሻሻያዎቻቸውን እንከታተላለን ፡፡ ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀ በኋላ የግብርና ልምዶች በምን መልኩ ቀጠሉ የሚለው ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አለን፡፡ ምናስተላልፋቸው ማስታወቂያዎች አድማጮች የአድማጭ ክለብ ሲያደራጁ ወደ ጣቢያው የሚደውሉበትን የስልክ ቁጥር ይሰጣሉ፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
እነዚህን የስልክ ቁጥሮች የምትሰጡበት ዓላማ ምንድነው?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
እያንዳንዱ የፕሮግራም ይዘት ሰዎች ግብረመልስ ሊሰጡባቸው የሚችሉባቸው የየራሳቸው ስልክ ቁጥሮች አሉዋቸው፡፡ለምሳሌ፡- ለጤና ፕሮግራም አንድ ስልክ ቁጥር አለን ፤ ለትምህርትም ፤ለግብርናም እንዲሁ የየራሳቸው ቁጥር አሉዋቸው፡፡
የተወሰኑ አድማጮችም ደብዳቤ ይፅፉልናል፡፡ በመንደሩ መሃል የፖስታ ሳጥን ቁጥር አለን፡፡ አንድ የመንደሩ ሰው በወር አንዴ ወይም ሁለቴ ደብዳቤዎቹን ይሰበስብልናል፤ የእኛ የገበያ ባለሙያም ወደ መንደሩ በመሄድ ደብዳቤዎቹን ይቀበላል፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
አድማጮች ጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ አንድ ፕሮግራም በምሳሌነት ልታካፍለን ትችላለህ ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
በግብርና ጵሮግራም ዝግጅት ተሳታፊ ነኝ፡፡ እንደ አዘጋጅ ለአርሶ አደሮች የምሰጠው መረጃ ትክክለኛነቱን፣ ሚዛናዊነቱን፣ እና አስተማማኝነቱን አረጋግጣለሁ፡፡ አንደኛው ፕሮግራሜ በአየር ሁኔታ መዛባት ጋር በተያያዘ አርሶ አደሮች የተወሰኑ የግብርና ልምዶቻቸውን እንዲቀይሩ የሚጠይቅ ነው፡፡አርሶ አደሮች ከመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ወጥ የሆነ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነ አረጋገጥኩኝ ፡፡አንዳንዴ አርሶ አደሮች እንደነዚህ ዓይነቶች ወጥነት የሌላቸውን መረጃዎችን በመተው እየተበረታታ ስላለው የግብርና አሰራር ምንም የማይሰሩበት ሁኔታ አለ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አርሶ አደሩ የጀመረውን አዲስ አሰራር የሚምታታ መረጃ ሲደርሰው የሚያቋርጥበት ሁኔታ አለ፡፡ አርሶ አደረዱ ማንን ማመን እንዳለበት አያውቅም፤ ስለዚህም እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ ያቆመዋል፡፡ስለዚህ እኔ በእነዚህ ወጥነት በሌላቸው መረጃዎች በተለይም በአፈር ጥበበቃ ዙሪያ ጥኛት አካሂጃለሁ፡፡ በማላዊ ብሄራዊ የአነስተኛ እርሻ ባለየዞታ አርሶ አደሮች ማህበር የኤክስቴንሽን አገልግሎት ወደሚሰጥበት አከባቢ ሄድኩኝ፡፡ በተጨማሪም መንግስታዊ ያልሆነው “ከንሰርን ወርልድ ዋይድ” የተሰኘው ዓለምዓቀፋዊ ድርጅት የኤክስቴንሽን አገልግሎት ወደሚሰጥበት አከባቢ ሄጃለሁ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ “ቶታል ላንድ ኬር” የተሰኘ ድርጅት የኤክስቴንሽን አገልግሎት ወደሚሰጥበት አከባቢ፤ ለአራተኛ ጊዜ ደግሞ የመንግስት የኤክስቴሽን ሰራተኞች አገልግሎት የሚሰጡበትን ቦታ ጎብኝቻለሁ፡፡ በሁሉም አራቱ አከባቢዎች አርሶ አደሮች የአፈር ጥበቃን እየሰሩባቸው ያሉትን ልምዶቻቸውን አይቻለሁ፡፡ በጎድጓዳ አዘራር (ተክሎች እርጥበትን ለመጠበቅ መሬት ውስጥ ተጋድመው የሚተከሉበት) ልምድ ላይ ትኩረቴን አደረግኩ፡፡አርሶ አደሮች ይጠቀሙበት ከነበረው የአፈር ጥበቃ ልምድ ምን ልዩነት እንዳለው ለማወቅ ፈለግኩኝ፡፡ ቀጥሎ በሬድዮ አየር ላይ ለማዋል እችል ዘንድ በአፈር ጥበቃ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ፤ አስተማማኝ መረጃ ሊሰጠኝ የሚችለውን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ሰጪ የትኛው እንደነ ማወቅ ፈለግኩ፡፡
በአራቱም ቦታዎች አንድ አንድ አርሶ አደሮችን ከኤክስቴንሽን ሰራተኞች ስለሚያገኙት የመረጃ ዓይነት ቃለ መጠይቅ አደረግኩኝ ፡፡
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
መጀመሪያ፡- አርሶ አደሮች የአፈር ጥበቃ ስራ የአየር ሁኔታ መዛባት የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅኖ ለመቀነስ ያለውን ጠቀሜታ መገንዘባቸውን አረጋገጥኩኝ፡፡
በተጨማሪም የተለያዩ ድርጅቶች በጎድጓዳ አዘራር (አተካከል ) እና የፀረ ተባይ አጠቃቀም ላይ የሚሰጡዋቸው ሃሳቦች የተለያዩ እንደሆነ አረጋግጫለሁ፡፡ አራቱም የጠየቅኳቸው አርሶ አደሮችእና ሌሎች የተወሰኑ አርሶ አደሮች ጭምር የሚሰጡት ሃሳቦች ወጥ መሆን እንደሚገባ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተውኛል፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
ከጥናቱ የተገኙ ሌሎች ግኝቶችም ነበሩ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ
እርስ በእርስ የሚጋጩ መረጃዎች ባሉበት ሁኔታም አርሶአደሮቹ ልምዶቹን እንደሚተገብሩአረጋግጫለሁ፡፡በመንደራቸው ሰብሰብ በማለት ከተለያዩ የኤክስቴንሽን ሰራተኞች መልዕክቶች መካከል የትኞቹን ተግባራት በምን መልኩ መተግበር እንዳለባቸው ራሳቸውን ችለው ይወያሉ፡፡ አንዳንዴ የተለያዩ የአሰራር መልዕክቶችን አጣምረው አዲስ አሰራር ይፈጥራሉ፡፡በተወሰነ ደረጃ በጎድጓዳ አዘራር (አተካከል) የተጠቀሙ አርሶ አደሮች እንዳሉ፤ ነገር ግን መሬት መሸፈኛ መጠቀማቸውን አረጋግጫለሁ፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
በጥናትህ ያልጠበቅክካቸው ግኝቶች ገጥመውህ ነበር?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
አዎ ፤ አርሶ አደሮች በገኙት መረጃ መሰረት በየሳምንቱ እርስ በእርስ ይእንደሚማማሩ አውቄያለሁ፡፡ በአሉታዊ ጎኑ አርሶ አደሮች አደስ አሰራር ከተማሩ በኋላ አዲሱ ይበልጣል ብለው ስለሚያስቡ ነባሩን ይጥሉታል ፡፡ ለምሳሌ ፡- አንድ ሴት አጋድሞ የመትከል አሰራርን ትከተል ነበር በአሰራ በጥልቀት በመሰልጠኗ ሌሎችን አርሶ አደሮች በማስተማር ጭምር መሪ ሆናለች፡፡ ሆኖም ሌላ ድርጅት መጥቶ ስለ አተካከል, ሲያስተምራት አጋድሞ የመትከል አሰራሩን ሙሉ በሙሉ በመተው ሙሉ ትኩረትዋን በ አተካከል ላይ አድርጋለች፡፡ አንድ ጊዜ አንድን ተግባር ሲማሩ እዚያው በጣም ተቆራኝተው ሌላ አዲስ ነገር የመማር ተነሰሽነታቸውን ይገድሉታል፡፡ “እንዲህ አድርጌ ነው የሰራሁት፤ ሰለጠንኩበትም የተሻለም ይህ መንገድ ነው” የሚል ዝንባሌ ይፈጠርባቸዋል፡፡ የሚያሰለጥናቸው ባለሙያው ላይ ከፍተኛ እምነት ስላላቸው የተለየ መረጃ ይዞ የሚመጣን ሌላ ሰው ቶሎ ለመቀበል ይቸገራሉ፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
የእነዚህ ትናት ግኝቶችን እንዴት ነበር በፕሮግራም ዝግጅትህ የተካከቱት?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
የኔ ትልቁ ፍላጎቴ የነበረው በአፈር ጥበቃ ዙሪያ ደረጃውን የጠበቀ መረጃ አየር ላይ ማዋል ነበር ፡፡ አርሶ አደሮችን ቃለ መጠይቅ ካደረግኩ በኋላ ባለ ሙያዎችንም ቃለ መጠይቅ አደረግኩላቸው፡፡ ስለ አፈር ጥበቃ ስለዚህ መረጃው ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ ከባለሙያዎቹ እና ከአርሶ አደሮቹ ያሰባሰብኳቸውን አንድ ላይ አመጣሁዋቸው፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
፤ቀጥሎስ ምን አደረግክ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ፕሮግራሙን አቀናበርኩና ከጥናቱ በስተጀርባ ያለውን ታሪክ እንዲረዱ በማለት የኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ለሚያካትተው የዝግጅት ቡድን አቀረብኩት፡፡በመቀጠል ሮግራሙን በድጋቢ አርሜ ለአድማጮች እንዲሰራጭ ዝግጁ አደረግኩት፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
በአጭሩ በጥናቶችህ መሰረት ምን ላይ ደረስክ ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
የአተካክል ዘዴው ድርቅን ለማቋቋም እና ምርትን ለመጨመር ይረዳቸዋል ወይ በሚለው ሃሳብ ላይ የ 30 ደቂቃ ፕሮግራም አዘጋጀሁ፡፡ ለፕሮግራሙ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ሰዎች ተግባሩ እንዴት እንደሚካሄድ አብራሩ፡፡ የአየር ሁኔታ ለውጥ ትግሉ ጋር በተያያዘ ያለውን ጠቀሜታ ፤ ምርታማነት፤ ተግባሩን ለመከታተል አንድ ሰው ምን ያስፈልገዋል ስለሚሉ ጉዳዮች ተናግረዋል፡፡ ፕሮግራሙ ከተላለፈ በኋላ ልምዱን የተገበሩ አርሶ አደሮች ምስክርነታቸውን ለመግለፅ ስልክ ደወሉ፡፡ የምስክርነት ድምፆቻቸውን አርሜ ወደ 5 ደቂቃ ማስታወቂያዎች አሳጥሬ ሌሎች አርሶ አደሮች እንዲማሩበት እና ተበረታትተው እንዲተገብሩት አየር ላይ አዋልኩት፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
ለአድማጮቹ ጥናት ፖንሰር የሚያደርግ አጋር ተገኝቶ ነበር ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ለአድማጮቹ ጥናት ፖንሰር የሚያደርግ አልተገኘም ነበር፡፡ በአከባቢጉዳዮች ፕሮግራማችን ካለን ምንጭ ነበር የተጠቀምነው፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
ንኮታኮታ ከአድማጮቹ ግብረ መልስን ለመሰብሰብ ቀጥሎ ምን እያደረገ ነው ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ከፕሮግራሞቻችን የወደዱትን እና ያልወደዱትን ነገር እንዲነግሩን ሰዎችን እንጠይቃለን፡፡
ይህ የሚሰራው የሁላችንም ግብረ መልስ በሚተዳደርነበት የጥናት ክፍል በኩል ነው፡፡ እኛ ኤስ ኤም ኤስ የመልዕክት መቀበያ እና ከቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን በተለየ የስልክ መደወያ እና መቀበያ ስርዓት አለን፡፡ በቅርቡም የድምፅ መለዕክት መግባቢያ “IVR” ስርዓት ዘርግተናል፡፡ይህ ስራ ሲጀምር ከአድማጮቻችን የፅሁፍ እና የድምፅ ግብረመልስ እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ የማህበረሰብ የፖስታ ወኪሎች ስለ ዝግጅቶቻችን እና አድማጮቻችን እንድናዘጋጅላቸው የሚፈልጉትን ነገር እንዴት ማጥናት እንደሚችሉ መመሪያ ተቀብለዋል፡፡ በተጨማሪም የኤክስቴንሽን ሰራተኞች በተለይም በግብርና እና በጤና ዘርፍ ግብረመልስ በመስጠት ከጎናችን ነቸው፡፡ጣቢያው ከማህበረሰቡ ጋር የሚያቀራርብ የእግር ኳስ ቡድን አለው፡፡ ከማህበረሰቡ ባለሃብቶች ጋር በመተባበር ፤ ግጥሚያ እያዘጋጀን በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍ እናደርጋለን፡፡ ይህ የዝግጅት ቡድኑ ወደ ማህበረሰቡ በመጓዝ ከአድማጮቹ ጋር እንዲገናኝ ይረዳዋል፡፡ ሰዎች ሲደውሉ ከየትት እንደሚደውሉ እንጠይቸዋለን ፡፡ ይህ የሽፋናችን መጠንን የምናውቅበት ዘዴ ጭምር ነው፡፡ከእያንዳንዱ የመስክ ፕሮግራም ግብረመልስ እንቀርፀለን፡፡ ነፃ የስልክ መልዕክት መቀበያ መስመር አለን ፡፡ አርሶ አደሮች በነፃ መልዕክታቸውን ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ በአንዱ ፕሮግራም አንዲተገብሩት በተላለፈ አሰራር መሰረት አሰራሩን የተገበሩ አርሶ አደሮች ምን እንደሰሩ፤ ምን እንደተማሩ፤ እንዴት እንደተጠቀሙ፤ እንደዚሁም እጋጠሙዋቸው ስለሚገኙ ችግሮችን አስመልክተው መልዕክቶቻቸውን የልኩልናል፡፡ይህን ግብረመልስ ሰዎች የሚያነሱትን ጥያቄ በፅሁፍም ሆነ በመደወል ሲጠይቁን መልስ ለመስጠት እንጠቀምበታለን፡፡ ጥያቄዎቹ እንደ በሽታ እና ወረርሽኝ ዓይነት ቴክኒካዊ ከሆኑ የግብርና ስፔሻሊስቶችን እናማክራለን፡፡ ባለሙያዎቹም ከአርሶ አአደሮች የተቀበልናቸውን መልዕክቶች ያጠናክራሉ፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግብርና ክፍሎች በመንደሩ ዝግጅት ሲኖርባቸው በስነስርዓቱ ወቅት ቀረፃ እና ዘገባ እንድንሰራ እንጋበዛለን፡፡ ይህም የአድማጮቻችንን አንደበት የምናዳምጥበት ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ከዚሁ በተለየ ንኮታኮታ አጠገብ የሚገኙ የአድማጭ ክለበች ዘንድ በመሄድ የማህበረሰብ ጉብኝት እናካሂዳለን፡፡ ይህ ጉብኝት ሰዎችን በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን ላይ ሰዎችን አስተሳሰብ፤ እንድናዳምጥ እና እንድንቀርፅ ይረዳናል፡፡ ጣቢያውን ለመጎብኘት ነፃ ከሆኑ የኤክስቴንሽን ሰራተኞች ጋር ጥሩ ግንኙነት አለን፡፡ አርሶ አደሮችም የኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ሬድዮ አዘጋጆች ወደ እነርሱ እንዲመጡ እና የተገበሩዋቸውን አዳዲስ ስራዎች እንዲጎበኙላቸው እና እንዲቀርፁላቸው እንደሚፈልጉ ይነግሩዋቸዋል፡፡ ስራችን በሚበዛበት ጊዜ የግብርና ክፍል ሞተር ብስክሌቶችን በመስጠት ይተባበረናል፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ :
እንደ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ የአድማጮች ጥናትን በማከሄድ ዓቅምህን ለሟሟጠጥ ዝግጁ ነህ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
እውነቱን ለመናገር ለማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ዓቅምን ለአድማጮች ጥናት ማሟጠጥ በጣም ከባድ ነው፡፡እኔ በራሴ ፍላጎት በአፈር ጥበቃ ፕሮግራም ላይ ጥናቱን ሰርቼዋለሁ፡፡ ከጣቢያው የተመደበልኝ በጀት ሲያንሰኝ ከግሌ መጨመር ነበረብኝ ፡፡ ሆኖም ግን ጣቢያው ግብረመልስ መሰብሰብ ላይ በተለይም የጥናት ክፍሉ አግዞኛል፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያዎች የፋይናንስ አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ ጥናት ለማካሄድ ይቸገራሉ፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
ጀት ቢመደብልህ ኖሮ ጣቢያው ለጥናቱ ያውለው ነበር ብለህ ታምናለህ ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
አወን፡- እንደ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ የምንዳስሳቸው ብዙ ሃሳቦች አሉን ሆኖም ግን የፋይናንስ ውሱንነት ሊያሰራን አልቻለም፡፡ ፕሮግራሞችን እናሰራጫለን የትራንስፖርት ችግር ግን ራቅ ያሉትን እንዳንዳስስ አድርጎናል፡፡ በቅርባችን ያሉት ብቻ በፊት ለፊት ጉብኝት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ራቅ ያሉ ቦታዎች ፕሮጀክቶች ያሉዋቸው ድርጅቶች ሲኖሩ ራቅ ወዳሉ ማህበረሰቦች የመድረስ ዕድል ይኖረናል፡፡
ቃለ መጠይቅ አድራጊ:
እንደ ሬድዮ ጣቢያ የንኮታኮታ ዲሞግራፊን በተመለከተ መረጃ ታፈላልጋላችሁ9ለምሳሌ ፆታ እና ዕድሜ) ?
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
በአጠቃላይ የቀጠናውን ምክር ቤት የግብርና ክፍሉን እንዲሁም ጤና ቢሮን በዲሞግራፊ ዙሪያ እንጠይቃቸዋለን፡፡ ይህ መረጃ ወሳኝ ነው ምክንያቱም ፕሮግራምህ በተወሰን የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ሰዎች የተዘጋጀ ቢሆን እና አነዛ ሰዎች በዚያ ባይኖሩ ፕሮግራሙ ግቡን አይመታም ማለት ነው፡፡
ክፍል II: ከጥናቱ የተዘጋጀ የፕሮግራም ስክሪፕት (ፅሑፍ)
ሚከተለው በንኮታኮታ ማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ በ” pit farming” ዙሪያ ተዘጋጅቶ ነሐሴ 1፣ 2012 የተላለፈ እና በድጋሚም በነሀሴ 5, 2012 የተላለፈ የ 4 ደቂቃ ንባብ ነው፡፡ ንባቡ ከ ቺቸዋ ቋንቋ የተተረጎመ ነው፡፡ ፕሮግራሙ ፊሊፕ ቺንኮክዌ በቁጥብ እርሻ ዙሪያ የተሳተፉ መሪ አርሶ አደሮችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ባዘጋጀው ጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው፡፡. ንባቡ የአየር በዛባት ንድፈ ሃሳብን ያስተዋውቃል ፤ በተጨማሪም ” በቁጥብ እርሻ ን በድርቅ ጊዜ ቦቆሎን የመከላከል ዘዴ እንደሆነ ያስተዋውቃል፡፡ አርሶ አደሩ ” በቁጥብ እርሻ ን እንዴት እንደሚሰራ እና ጥቅሞቹን ያብራራል፡፡
የመግቢያ ድምፅ ከአቅራቢው ድምፅ ጋር አገባቡ እና አወጣጡ
አቅራቢ:
እንደ አርሶ ቸደሮች በዚህ ጊዜ የአየር ሁኔታ እየተቀየረ መሆኑን እና በግብርናው ላይ ውስብስብ ችግሮች እያስከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ በጉዳዩ ላይ ምንም የማንሰራ ከሆነ ግብርናችን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል፡፡ ግብርና ደብሞ በተፈጥሮአዊ ምንጮች ላይ የተመሰረተ መሆኑን አንዘንጋ፡፡ እነዚህ ምንጮች ከተመናመኑ ግብርናም አብሮ አደጋ ላይ ይወደወቃል፡፡ አርሶ አደሮች ይህንን የአየር ሁኔታ የመዛባት ችግር ለመቋቋም ምን እየሰራችሁ ነው፡፡ ? የተፈጥሮ ሃብትን ለመታደግ ምን ዓይነት ተግባራትን ነው እየተከተላችሁ ያላችሁት? የአየር ሁኔታ የመዛባት ችግር እየተከሰቱ ካሉ ችግሮች አንዱ ድርቅ ነው፡፡ ሰብሎች ከመድረሳቸው እና ከመሰብሰባቸው በፊት የዝናብ መቆም ሁኔታን መስማት አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ይህ በውሃ እጥረት ሳቢያ እንደ ቦቆሎ ያሉ ሰብሎች ይወድማሉ፡፡ ዛሬ በድርቅ ጊዜ ቦቆሎን እንዳይወድም እንደ “pit planting” ያሉ የድርቅ ቅነሳ ዘዴዎችን በመጠቀም መከላከል የምንችልበትን መንገድ እናያለን፡፡ በፕሮግራሙ በንኮታኮታ ቀጠና ከ ነኮንጎ ሃላፊ አግነስ ማቸሶ ጋር ቃለ መጠይቅ ይኖረናል፡፡
አግነስ ማቸሶ:
ቁጥብ እርሻ ጉድጓዶችን በመቀፈር ቦቆሎ የምንተክልበት የግብርና ስራ ነው፡፡ በአንድ ጉድጓድ አራት የቦቆሎ ዘሮችን እንተክላለን ፡፡ እያንዳንዷን በየማዕዘኑ በማኖር፡፡ የጉድጓዶቹ ጥልቀት 25 ሰንቲ ሜትር ሲሆን ስፋታቸው ደግሞ 30 ሳንቲ ሜትር ይሆናል፡፡
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
የዚህ ዓይነት ግብርና የት ነው የተማርሽው ?
አግነስ ማቸሶ :
ህ ዘንድሮ የተማርነው የግብርና ዘዴ ነው፡፡ በዛምቢያ እየተተገበረ ነው ያለው፡፡ የኤክስቴንሽን ሰራተኞች በሚሰጡን መመሪያ እየታገዝን በማላዊ በዚህ ዓመት ልንተገብረው ወስነናል፡፡ ውጤቱ ጥሩ ከሆነ ቴክኖሎጂው በቀጣይ ዓመት በአገሪቱ ሌሎች አከባቢ ዎች ጭምር እንዲስፋፋ ይደረጋል፡፡
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
እንደ ዛምቢያ ባሉት ሀገራት መተግበሩን ከሰማሽ በኋላ ይህ ዓይነቱን ግብርና ለመጀመሪያ ጊዜ ለመተግበር ምን አነሳሳሽ?
አግነስ ማቸሶ :
እንደ መሪ አርሶ አደር ራሴን ጨምሮ የማላዊ አርሶ አደሮችን ፍላጎት እንዲኖራቸው ያደረገው ይህ ዓይነቱ አተካከል አንድ የቦቆሎ ዘር በአንድ ጉድጓድ ውስጥ መትከል ይልቅ የተሻለ ምርት እንደሚያስገኝ ሳይንቲስቶች በማረጋገጣቸው ነው፡፡ ዝናብ ሲዘንብ ውሀው በቀጥታ ወደ ጉድጓዶቹ እንዲገባ ያደርጋል በተለመደው አስተራረስ ላይ ሲተከል ግን ዘሩ ያለበት ቦታ ውሃ ስለማይቋጥር ቦቆሎው በተለይ በፀሃያማ ወቅት ቶሎ እንዲደርቅ ያደርገዋል፡፡ በጉድጓዶቹ ውስጥ ሚበቅሉ ቦቆሎዎች ግን ዝናቡ በሚያቆምበት ጊዜም ቢሆን ቶሎ አይደርቁም፡፡ ምክንያቱም በዝናቡ ወቅት የተጠራቀመው ውሃ ጉድጓዱ ውስጥ በመቆየት ቦቆሎውን ድርቅ እንዲቋቋም ይረዳዋል፡፡
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ይህ ግብርናሽን በምን መልኩ ይረዳል ትያለሽ ?
አግነስ ማቸሶ :
ምንም እንኳን እንደዚህ ዓይነት እርሻ ተጠቅሜ ባላውቅም በጥናቱ ግኝት መሰረት የዚህ ዓይነቱ ግብርና ማላዊያኖችን የሚጠቅም ይመስለኛል፡፡
እናም በቀጣዩ ዓመት በርካታ የማላዊ አርሶ አደሮች ዘዴውን ይከተላሉ፡፡ በዚሁ ዘዴ ጥናት ባካሄዱ ባለሙያዎች መሰረት ቦቆሎ በሚገባ እንደሚበቅል ግልፅ ነው ፡፡ ምክንያቱም የሚዘንበው ዝናብ ወደ ጉድጓዶቹ ስለሚጠራቀም ነው፡፡
ፊሊፕ ቺንኮክዌ :
ጉድጓዶቹን Aካዘጋጀሽ በኋላ እና ዝናቡ ሲዘንብ ቦቆሎውን ትተክያለሽ፡፡ ለዘሮቹ ምርታማነት ሌላ የምታደርጊው ነገር አለ?
አግነስ ማቸሶ:
ጉድጓዶቹ ከተሰሩ በኋላ በጉድጓዱ ውስጥ ባሉት አራት ቦቆሎዎች ላይ ማዳበሪያ ትጨምራለህ ፡፡ ማዳበሪያውን ከጨመርክ ከሁለት ወራት በኋላ አራቱም ቦቆሎዎች በተመሳሳይ ዕድገት ይበቅላሉ፡፡ በምርት ጊዜ ትልቅ ውጤት ይኖርሃል፡፡
Acknowledgements
አስተዋፅኦ ያደረጉ: ምስጋና
አስተዋፅኦ ያደረጉ : ቪጄ ኩድፎርድ በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ኤዲተር እና በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ሲልቪ ሃሪሰን የሬድዮ ሙያ ዝግጅት ቡድን መሪ፡፤ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የዳይረክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ዱዋግ ዋርድ
ይህ ሰነድ ወደ አማርኛ የተተረጎመው በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለስቴፕልስ ፕሮጀክት በሰጠው ድጋፍ ነው፡፡