የአርሶ አደር የሬድዮ ፕሮግራምህን ለማሰናዳት ከሰባ አምስት ዘዴዎች የተቀመሩ ከፍተኛ ይዘቶች

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document.

ሬድዮ ከየትኛውም ዓይነት ሚድያ የአርሶ አደሮችን ቋንቋ ይጠቀማል፡፡ አርሶ አደሮችም የሚፈልጉትን መረጃ መስጠት ሲፈልጉ በሬድዮ ላይ እምነት ይጥላሉ፡፡ በተጨማሪ አርሶ አደሮች ቤተሰቦቻውን የሚመግቡባቸውን ሰብሎች በተሻለ ሁኔታ ለማምረት በሚያስችላቸው እና ገበያ ላይ ትርፋማ መሆን በሚችሉበት ዙሪያ ለመወያየት የሬድዮ ፕሮግራም በውይይት እንዲያሳትፉዋቸው ይፈልጋሉ፡፡.

በአብዛኛው ጊዜ ሬድዮ ለአርሶአደሮች ተገቢ ትኩረት አይሰጥም፡፡ አርሶ አደሮች ለእነሱ በጣም አስፈላጊ የሆነ መረጃ ካልተካተተ ወይም የምሁራን ፣ የፖለቲከኞች ፣ እና የአስተዋዋቂዎች ገለፃ ድምፆቻቸውን በሚደፍቁበት ሰዓት ከሬድዮው ጋር ይቆራረጣሉ፡፡

በዚህ መልኩ መሆን የለበትም፡፡ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ለአርሶ አደሮች የተሻለ ሮግራሞችን ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡ የአርሶ አደሮችን ፍላጎት በሟሟላት እና አርሶ አደሮችን በማካተት ስርጭታቸውን ይበልጥ ሳቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ዋናው ነገር መልካም ተመኩሮቻቸው በማጉላትና እንዲያንፀባርቁ በማድረግ ማስፋፋት ነው፡፡

በ 2010ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የአርሶ አደር ሬድዮ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ካሜሮን፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ታዘኒያ እና ማላዊ ከሚገኙ ሬድዮ ጣቢያዎች መረጃ አሰባስቧል፡፡ ሀያ ጣቢያዎችን እና ሁለት የፕሮደክሽን ተቋማትን በመጎብኘት የአርሶ አደር ፕሮግራሞቻቸውን አዳምጠናል፡፡ ለፕሮግራሞቹ አዘጋጆች እና ፕሮግራሙን ለሚያዳምጡ ሰዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥያቄዎችን አቅርበንላቸዋል፡፡ ግኝታችንን መሰረት በማድረግ ከአሁን ጀምረው የአርሶ አደር ፕሮግራሞቻቸውን ለማሻሻል ለሚፈልጉ አዘጋጆች ዝርዝር ማስታወሻዎችን እያሳተምን እንገኛለን፡፡

አዎንታዊ ለውጥ በአንዴ አይመጣም ሆኖም በአንድ እርምጃ ሊጀምር ይችላል፡፡ እነዚህን ሂደቶች በሶስት ከፍለናቸዋል፡፡ ፈጣን መፍትሄ (quick fixes) ፤መካከለኛ ማሻሻያ፤ (middle-sized improvements) እና ስር ነቀል ማሻሻያ (the big stuff.) በቅድሚያ ፈጣን መፍትሄውን (quick fixes) እንድትተገብር እናበረታታለን፡፡ እነሱ ከተሳኩልህ ከፍ ወዳሉት ማሻሻያዎች ቀጥል ባጠረ ጊዜ ውስጥም የተለወጠ ፣ ውጤታማ፣ አዝናኝ እና የስራ እርካታ ያለው የሬድዮ ፕሮግራም ይኖርሃል፡፡

ለዚህ የምንጭ ፓኬጅ ከዋናው ሰነድ ከሁሉም ክፍሎች በጥቂቱ አካተን ቶፕ ዶዘን “Top dozen” የተሰኘውን መፍትሄ ለመጠቀም መርጠናል፡፡ ለተሟላው ሰነድ በሚቀጥለው አድራሻ ይመልከቱ http://www.farmradio.org/broadcaster-resources/special-resources/.

ስለ ርዕሱ ማስታወሻ : “ሰባ አምስቱ የአርሶ አደር ፕሮግራምህ የዝግጅት ዘዴዎች ” ተሻሽለው ወደ “ዘጠና ዘጠኝ የአርሶ አደር ፕሮግራምህ የዝግጅት ዘዴዎች “! ቢያድጉ በጣም ደስተኞች እንሆናለን፡፡ ሆኖም በአንተ /አንቺ የሚወሰን ይሆናል፡፡የአርሶ አደር ፕሮግራሞችህን/ሽን ለማሻሻል የሚረዱህን/ሽን ሀሳቦች ብታካፍለነ/ዪ እንዲሁም መቀነስ ሚገባቸው ነገሮች ቢኖሩህ/ሽ ከእኛ ጋር ተነጋገር/ሪ፡፡ በቀጣይ እትማችን የምናካትታቸውን ሃሳቦች የሚሰጠን ሰው ስሙን በእትማችን ላይ እንጠቅሳለን፡፡ በሚከተለው የኢሜይል አድራሻችን ያግኙን፡፡ “ info@farmradio.org“ እና “ሰባ አምስት ” ሰብጀክት በሚለው የኢሜይሉ መስመር ላይ ያስቀምጡልን

ለሁላችሁም መልካም ዕድል!

Script

ሀ) ፈጣን ማሻሻያ: እነዚህ ያለ ምንም ምንጮች አሁን ፣ ለቀጠይ ሳምንት እና ለሚቀጥሉት ወራት የማንም ፈቃድ ሳትጠይቅ/ቂ ልትሰሩዋቸው የምትችሉዋቸው ነገሮች ናቸው፡፡

ማስታወሻ: በቅንፍ ውስጥ ያሉ ቁጥሮች ዋናውን ሰነድ የሚመለከቱ ናቸው

1. የአድማጮችህን ቀልብ ሊገዛ የሚችል መግቢያ ፃፍ/ፊ፡- በእያንዳንዱ የፕሮግራም ክፍል የአድማጮች ታማኝነት ልታገኝ/ኚ ይገባል፡፡ አድማጮች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሊዘጉህ/ሽ ይችላሉ፡፡ ስለዚህም የአንተን/ቺን ፕሮግራም ማዳመጣቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን ምክንያት ስሜት በሚሰጥ መልኩ አሳምናቸው፡፡ ሰለዚህ መግቢያህ/ሽ በፕሮግራምህ/ሽ ከያዝካቸው ዋና ዋና ቁምነገሮች አንዱ ሊሆን ይገባል፡፡ በተጨማሪም የይዘት ዓይነቶችን ከመደርደር ይልቅ የአድማጭህን ጉጉት እና ሰውኛ ፍላጎት ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡ አድማጭህን ሊያዳምጥህ የሚያስችለው ስሜታዊ ምክንያት ስጠው፡፡ ለምሳሌ ፡- “በ……….በሽታ ዙሪያ ላይ ባለሙያ እናነጋግራለን” ብለህ አትበል፡፡ በምትኩ “የቤቲ ሙሞ ፍየሎች በ……በሽታ እየሞቱ ነው፡፡ እንስሳቶቻችሁ በዚህ በሽታ እንዳይጠቁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ የሚነግራችሁ ባለሙያ ጋብዘንላችኋል” በል፡፡

2. ከወንዶች ጋር እኩል ክብር ያላቸው ሴት እንግዶችን ጥቀስ፡፡ አዘጋጅ “ከእርሻ ኮሌጁ ዶ/ር ስታንሊ ሉቦ ጋር እያወራሁ ነው” የሚል አነጋር የሚጠቀመው ለምንድነው ወደ መስክ ሲሄድስ ታዲያ ለምን “ሄሎ ማዘር ለምን ከአርሶ አደር ማሪያ ስሚዥጋር እያወራሁ ነው”? አይልም? ለምንስ “ዙምባ ገበያ ላይ በጣም ቆንጆ ከሆነች ልጅ ጋር እያወራሁ ነው” ይላል ታዲያ ?

3. ስዕላዊ ቃላትን ተጠቀም፡፡ ስለ ቦቆሎ በሽታ ለማውራት ወደ ገጠር ስትሄድ ከሁሉም አስቀድመህ የአድማጩ ዓይን መሆን ይኖርብሀል፡፡ ወደ መንደሩ ስትገባ መጀመሪያ ላይ ትልቁን ስዕል ግለፅ፡፡ ልጆች እየተጫወቱ፤ አዛውንቶች ከውጭ ተቀምጠው ፤እንዲሁም መንደሩን የሚገልፅ ማንኛውም ነገር ህንፃ፣ ወንዝ፣ ሱቅ፣ ሀውልት የመሳሰሉ ነገሮችን ግለፃቸው፡፡ ከዚያም የየኸውን ማሳ ፣ገበሬ እና የተበከለውን በቆሎ በቅርበት አጉልተህ ስዕላዊ በሆነ መንገድ ግለፃቸው፡፡ ይህ አድማጮችህ አብረውህ እንዲቆዩ ይረዳሃል ፍላጎታቸውንም ያነሳስልሃል፡፡

4. ታሪክ፣ ታሪክ፣ ታሪክ ፡- ሁሉም ሰው ታሪክን ይወዳል፡፡እናም ሬድዮ ታሪክን ሲተርክ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡ ታሪክ በኣብዛኛው ፈተና ታግሎ የሚያሸንፍ አስደናቂ ሰው ያካትታል፡፡ታሪኮችን ተጠቅመህ የአድማጮችህን ቀልብ እንዴት ማርከህ ለመያዝ እንደምትችል ተማር፡፡ ታሪኮች እውነታ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም እንደ ሚኒ ድራማ እውነታን የሚወክሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሁለቱም በጥሩ ሁኔታ ሊጠቅሙ ይችላሉ፡፡

5. ከሌሎች ሚድያ ጋር ስራ/ሪ፡- ሬድዮ ብዙ ስራዎችን ሊሰራ ይችላል ሆኖም ግን ሁሉንም ነገር ሊሰራ ይችላል ማለት አይደለም! የግብርና ጉዳይ በስዕል ብቻ የሚሰጥ ዓይነት ከሆነ ሥዕሎቹ ለአርሶ አደሮች የምታዳርስበትን ዘዴ ፈልግ፡፡ እነዚህ በሬድዮ አንድ ሁለቴ ብቻ አየር ላይ ተደምጠው እንደሚጠፉ ሳይሆን ለሁልጊዜ ለአርሶ አደሮች የማጣቀሻ ሰነድ አድርጎ መጠቀም ይቻላል፡፡ምናልባት የኤክስቴንሽን ክፍሎች ተማሪዎች ወደየቤታው እንዲወስዱት ለትምህርት ቤቶች ሊያከፋፍሉ ይችላል፡፡ ስዕሎች በገበያም ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ፕሮግራምህም ይህንን ለአድማጮችህ ሊያደርስ ይችላል፡፡ ጣቢያህ አርሶ አደሮች አየር ላይ ስለምታወራው የግብርና ተመክሮ በስዕል ለማየት የሚችሉበት ቤተ መፅሃፍት ካለው መጋበዝ ትችላለህ፡፡

ለ) መካከለኛ ማሻሻያዎች: እነዚህ ለውጦች የተወሰኑ ምንጮችን እና የአመራር ጣልቃ ገብነትን ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት እንድትተገብራቸው አስብበት

6. መንደር ውስጥ ወዳሉት አርሶአደሮች ግባ፡- በርካታ የአርሶ አደር ፕሮግራሞች በስቱዲዮ ብቻ ታጥረው ችግር ውስጥ ይገባሉ፡፡ የሞባይል ስልኮች በአርሶ አደሩ እና በአዘጋጆች መካከል ያለውን ክፍተት ሊሞሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም እሱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ የትራንስፖርት ክፍያ ውድ ነው ቢሆንም ግን ወደ አርሶ አደሮች ማሳዎች እና ቤቶች መሄድ ግድ ይላል፡፡ አርሶ አደሮች አንተ/ቺ በነፋሱ፣ በአቧራው ፣ በጭቃው እና በአጠቃላይ የሚገጥሟቸውን የዕለት ተዕለት ፈተናዎች በአካል መጥተህ ስታይላቸው ለአንተ ትልቅ ክብርን ይሰጡሀል፡፡ በየሳምንቱ ለመጓዝ ላይመችህ ይችላል ሆኖም ግን እንደ ዜና ሪፖርተሮች ያሉ ሌሎችም ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ የኤክስተንሽን ሰራተኛም እንዲሁ ፡፡ አንዴ በተካሄደ ጥናት ሃያ ሁለቱን ፕሮግራሞች ስንገመግም በመስክ ጉብኝ የተሰሩት ፕሮግራሞች ከሌሎቹ ይልቅ ከፍተኛ ጥራት እንደነበራቸው አስተውለናል፡፡ እዚያ የምታገኛቸውን ምንጮች ፈልግ፤ ከዚያም በአቅራቢያህ ወደሚገኝ ገበያ በመሄድ ከአርሶ አደሮች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርግ፡፡

7. አቅድ፣ አቅድ ፣ አቅድ የአርሶ አደር ፕሮግራም ድንገተኛ እና ዘና ያለ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ከ ምቹ እና ኢመደበኛ ከሆነው ድምፅ በስተጀርባ ከፍ ያለ እቅድ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህ ክፍል አጠቃላይ የአርሶ አደር ፕሮግራምን ግብህን ይመታል? ስር ወደ ሰደደው የአርሶአደር ችግር ጥልቅ ውይይት እና የመፍትሄ አቅጣጫ ያሸጋግራል? የአርሶ አደሮች በግብርና ስራዎቻቸው ላይ አስፈላጊ ውይየቶችን እንዲያካሂዱ ያደርጋል? የገበያ ዘገባችን አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበትን ትክክለኛውን ገበያ ይሸፍናል፡፡ የገበያ ዘገባችን አርሶ አደሮች የሚጠቀሙባቸውን ገበያዎች በትክክል ይዳስሳሉ ? እነዚህ አቅራቢ አዘጋጇ በየሳማንቱ ራስዋን የምትጠይቃቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ከዚያም ይዘቱን ለማሰራጨት የሚያስፈልገውን ስራ መስራት እና አየር ላይ ሁሉንም ቀለል ባለ መልኩ ማቅረብ፡፡

ሐ) ስር ነቀል ማሻሻያ the big stuff: እነዚህ ለውጦች ጊዜ የሚወስዱ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በዚያው ልክ ጠቃሚ ናቸው፡፡ ማቀድ እና የአመራር ጣልቃ ገብነትን ፤ ምናልባትም የተወሰኑ ልዩ የአንድ ጊዜ ምንጮችን ወይም ተጨማሪ ቀጣይ ምንጮችን ይጠይቃል፡፡ በቀጣይ ከ 3- 12 ወራት ለአንተ ጠቃሚ የሆኑትን ተግባራዊ አድርግ፡፡

8. የዓላማ መግለጫህን ፍጠር ፡- አንድ ጣቢያ የአርሶ አደር ፕሮግራምን ለመስራት ሲወስን በአብዛኛው ጊዜ በቀላሉ አንዱን /ዷን አዘጋጅ በመመደብ አዘጋጁ/ጇ ምን ምን መስራት እንዳለበት/ባት ሙሉ በመሉ በእርሱ/ሷ ላይ እንዲወድቅ ይደረጋል፡፡ ይህ ለአዘጋጅም ሆነ ለአድማጭ ፍትሃዊ አይደለም ! ከአመራርህ ጋር በመሆን ግልፅና ጠቃሚ የሆነ የዓላማ መግለጫ አዘጋጅ፡፡ የሚቀጥለውን ጥሩ ምሳሌ እንይ፡
“ቅድሚያ ለአርሶ አደሮች” ——-ክልል አርሶ አደሮችን በትክክለኛ መረጃ ተመስርተው የሚያስፈልጋቸው ምግብ ለቤተሰቦቻቸው እና ለገበያ እንዲያመርቱ ፤ እንዲሁም ንቁ የገጠር ማህበረሰብን ለመገንባት እንዲችሉ ይረዳቸዋል “”ቅድሚያ ለአርሶ አደሮች” አርሶ አደሮች የሚፈልጉትን መረጃ በሚስፈልጋቸው ጊዜ ከአስተማማኝ ምንጭ የሚያቀርብ ፤አዝናኝ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው፡፡ በተጨማሪም አርሶ አደሮች በሚፈልጉት ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲወያዩ ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡

9. ከኤክስቴንሽን አገልግሎቶች ጋር አጋርነት መፍጠር፡- ሬድዮ በዋናነት ከአማካኝ አቅጣጫ አርሶ አደሮችን ያገለግላል፡፡ የኤክስቴንሽን ወኪሎች በመደበኛነት ወደ መንደሮች ይሄዳሉ፡፡ ሁለቱም አካላት በጋራ ከሰሩ ለአርሶ አደሮች የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሻሻል ይችላሉ፡፡ (ይህ ማን ምን ይሰራል የሚለውን ለመለየት እንዲቻል መደበኛ የጋራ ስምምነት ማድረግ ሊጠይቅ ይችላል፡፡)

10. አርሶ አደሮች አስፈላጊ ነገሮች ላይ እንዲወያዩ አድርግ ፡- አርሶ አደሮች የልማታዊ ውይይት አካል መሆን ካልቻሉ በአካባቢው ውጤታማ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት አይኖርም፡፡ፕሮግራምህ ውይይቶችን ስለሚጀምሩበት ነጥብ ፤ ምን ላይ ይበልጥ በጥልቀት መወያየት እንደሚያስልግ አንዲሁም ምን ላይ ከሁለቱም ፆታዎች ተጨማሪ አርሶ አደሮችን ማሳተፍ እንዳለበት የሚያሳይ ምቹ ሁኔታ መስጠት ይችላል፡፡

በመጨረሻም ፤ መወገድ ያለባቸው ጥቂት ነገሮች !

አንድ ጊዜ በተካሄደ ጥናት (እና በሌሎች ፕሮግራሞች ሞኒተሪንግ) ለአርሶ አደር ፕሮግራም ጭራሽ ቦታ የሌላቸው የሬድዮ ጣብያዎች እንዳሉም ታዝበናል፡፡ ቀጥሎ ቀርበዋል፡፡ ቀድሞ መጠንቀቅ ማለት ቀድሞ መታጠቅ ማለት ነው !

11. አርሶ አደሮችን በፍፁም ዝቅ አታድርግ፡፡ አርሶ አደሮችን ሃላፊነት እንደማይሰማቸው ህፃናት አድርገው የሚሰሩ ፕሮግራም አቅራቢዎች እንዳሉ አዳምጠናል፡፡ የኤክስቴንሽን ሰራተኞች የሚያስተዋውቁትን አዲስ አሰራር አልተገበሩም በሚል አርሶ አደሮችን ሲቆጡ ሰምተናል፡፡ በአንፃሩም አርሶ አደሮችን በተጋነነ አድናቆት የውሸት የሚያሞካሹ አቅራቢዎችንም ታዝበናል፡፡ አንዳንዴ አዘጋጆች አርሶ አደሮችን ከፍ ያደረጉዋቸው ዓይነት ስሜት በማንፀባረቅ አንዳነዴ ደግሞ በዕውቀትም ባለማወቅም ዝቅ ሲያደርጉዋቸው ይታያል፡፡ ምርጥ የግብርና አዘጋጆች አርሶ አደሮች የቤተሰቦቻቸውን ጤንነት ለማሻሻል በዘላቂነት ጠንክረው እንደሚሰሩ ያውቃል፡፡ እነዚህ አዘጋጆች አርሶ አደሮችን ለማገልገል ሬድዮን ሲጠቀሙ ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው በዚያ መሰረትም በአክብሮት እንደሚሰሩ ይገነዘባሉ፡፡

12. ኣታጭቀው! አንዳንድ አዘጋጆች ፕሮግራማቸውን እንደ ጋሪ አድርገው ያስባሉ : መልካሙን ሁሉ ስለከመሩ ጥሩ ይመስላቸዋል ፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ ፕሮግራሙ በአቅራቢ እና በአድማጭ መካከል የሚደረግ የድምፅ ግንኙነት ነው፡፡ አድማጮች ላያቸው ላይ በሚጫነው የመረጃ መዓት አይበረታቱም፡፡ እነሱ የሚመሰጡት ሊረዱት በሚችሉት ፍጥነት እና ይዘት ባለው ዘዴ ሲመሩ ብቻ ነው፡፡ መረጃውን በጣም ካጨቅከው በርካታ አርሶ አደሮች ራሳቸውን ችሎታ እንደሌላቸው አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡(የራሳቸው ባልሆነ ስህተት) እናም ተጠቃሚ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡

Acknowledgements

ምስጋና
አስተወፅኦ ያበረከቱ: ማርቪን ሃንክ (ብላንቲር, ማላዊ) እና ዱዋግ ዋርድ(ኦታዋ, ካናዳ)

ስለ ደራሲያኑ

ማርቪን ሃንክ በማላዊ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በፕሮግራም አዘጋጅነት ለ 24 ዓመታት አገልግሏል (1975 – 1999) ሽልማት ባሸነፈበት “የአየሩ ቲያትር” በተሰኘ የሬድዮ ድራማ ዝግጅት በጣም የታወቀም ነበር፡፡ በ 1999 he co-founded በሬድዮ ኮሚዩኒኬሽን ላይ የሚያተኩር የሚድያ ተቋም በሚድያ ዳይሬክተርነት ቀጥሎም በ ኤክዘኪዩቲቭ ዳይሬክተርነት ከሰራበት ፓሜላ ብሩክ ጋር ማቋቋም ችሏል፡፡ በሬድዮ ፕሮግራሙም ዚማቺቲካ በተሰኘውና ኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ በሚያጠነጥን ዝግጅቱ ዘ ቾመን ኸልዝ የተሰኘውን ሽልማት ለማሸነፍ በቅቷል፡፡ ሁለት የገጠር ልማት ላይ የሚያተኩሩ የሬድዮ ፕሮግራሞችንም በኤክዘኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰርነት ሲሰራ ነበር፡፡ (በጥሩ የግብርና አሰራር ላይ ተከታታይ ድራማ እና በምግብ ዋስትናም ለስድስት ዓመታት የተሰራጨ ማገዚን ፕሮግራም ) በ2008 በፈቃደኝነት ከስራ የተሰናበት ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የራሱን የኦዲዮ ሚድያ ድርጅት ያስተዳድራል፡፡በሬድዮ ፕሮግራም ዝግጅት ሙያም በአማካሪነት ይሰራል፡፡ በማላ በፋርም ሬድዮ ማላዊ ቦርድ በምክትል ሊቀ መንበርነት እና የፕሮግራሞቹ ኮሚቴ ሊቀ መንበርነት እየሰራ ይገኛል፡፡ ማርቪን ሃንክን በሚቀጥለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ marvinhanke54@yahoo.com.

ዱዋግ ዋርድ ፡ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ሊቀ መንበር ነው፡፡ በካናዳው ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፕሬዚዳንትነቱ ዱዋግ የ ካብኮ ን ሰቨንቲ ፕላስ ዋን የተሰኘውን ክልላዊ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ማዕከላትን አስተዳድሯል፡፡ ቀደም ሲል ዱዋግ የ ካብኮ ሰሜናዊ አገልግሎት ዳይሬክተር በመሆን በዘጠኝ የተወላጆች ቋንቋዎች ከ…ወደ… በተወላጆቹ ካናዳውያን በኩል ያስተላልፍ ነበር፡፡ ዱዋግ 43 ኛ ዓመት ባስቆጠረው እና በስልክ በሚያሳትፈው አዝ ኢት ሀፐንስ “As It Happens” የተሰኘው ዝነኛ ፕሮግራም በፈጠረው ቡድን በኤክዘኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰርነት ሰርቷል፡፡ በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ዱዋግ የአነስተኛ ግብርና አርሶ አደሮች ለምግብ ዋስትና አስፈላጊ በሚሉት የግብርና ልምድ የተሻሻሉ ልምዶችን ለመተግበር እንዲነሳሱ የሚያስችል አሳታፊ የሬድዮ ዘመቻን ቀርፆአል ፡፡ ዱዋግ በካናዳው ብሮድካስቲንግ ደረጃዎች ካውንስል በካናዳ ኮመርሻል ብሮድካስቲንግ ዙሪያ ለሚነሱ ሁሉንም ቅሬታዎች ጠበቃ ነው\፡፡ ዱዋግን በሚቀጥለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ marvinhanke54@yahoo.com.

Information sources

gac-logoይህ ፕሮጀክት የካናዳ የፋይናንስ ድጋፍ ተቋም ለካናዳ ዓለምዓቀፍ የልማት ኤጀንሲ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የሚሳለጥ ነው፡፡

ይህ ሰነድ ወደ አማርኛ የተተረጎመው በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለስቴፕልስ ፕሮጀክት በሰጠው ድጋፍ ነው፡፡