Notes to broadcasters

መግቢያ እና የዚህ ጥቅል አጠቃቀም

ይህ ጥቅል የራዲዮ ጋዜጠኞች ስለዶሮ በሽታዎችና መፍትሄዎቻቸው ውጤታማ እና አዝናኝ የራዲዮ ፕሮግራሞችን ለመፍጠር የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ይዞ ቀርቧል።
መረጃው ስለማሊ ዶሮዎች ቢሆንም ከሰሃራ በታች ላሉ ሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች እንዲሆን ማመቻችት ይቻላል።

ጥቅሉ በመግቢያ ይጀምርና ክፍል 2 ላይ ማሊ ውስጥ የዶሮ በሽታን ለመቋቋም እየሰሩ ስላሉ አርሶ አደሮች ሁለት እውነተኛ ታሪኮችን ያቀርባል።

ክፍል 3 ስለዶሮ የእሴት ሰንሰለት የምርት ደረጃ በተመለከተ ጠቅላላ መረጃ ይሰጣለ። (ስለእሴት ሰንሰለት ትርጉምና ስለእሴት ሰንሰለት የተሻለ ግንዛቤ መያዝ ለጋዜጠኞች እና አርሶአደሮች ምን እንደሚጠቅም ለመረዳት የሚከተለውን መረጃ ይመልከቱ፡ Resource Pack 95, Item 9 – An introduction to value chain

በመጨረሻም በክፍል 4 ስለዶሮ በሽታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚረዱ ሰነዶቸን እንዘረዝራለን። ዝርዝሩ ውስጥ ድርጅቶችን፣ የኢንተርኔት ራዲዮ ፕሮግራሞችን እና ኢንተርኔት ላይ ያሉ ቪዲዮዎችን እና ሌሎች ሰነዶችን አካትተናል።
በዚህ ጥቅል ውስጥ ያለውን መረጃ በብዙ መልክ መጠቀም ትችላላችሁ። ለምሳሌ፡

  • በክፍል 2 ውስጥ ያሉትን ታሪኮች ስለዶሮ በሽታዎች የራሳችሁን የራዲዮ ፕሮግራሞች ለማዘጋጀት መነሻ አድርጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። ዶሮ የሚያረቡ አርሶ አደሮችን እና ስለዶሮ በሽታ እውቀት ያላቸውን ባለሙያዎቸ ቃለ መጠይቅ ማድረግ ትችላላችሁ።
  • በክፍል 3 ውስጥ ያለውን መረጃ ለማንኛውም በዶሮ በሽታ ዙርያ ለሚዘጋጅ ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ አድርጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
  • ክፍል 4 ውስጥ የተዘረዘሩትን ድርጅቶች ለተጨማሪ መረጃ ወይም ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ።
  • በክፍል 4 ውስጥ ያሉትን የድምጽ፣ የቪዲዮ እና የኢንተርኔት መረጃዎቹን ስለዶሮ በሽታዎች ፕሮግራም ለመፍጠር ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ።

ማስታወሻ: ይህ ጥቅል ሙያዊ ስያሜዎችን ይጠቀማል። ሙያዊ ስያሜዎች ሲኖሩ ኮከብ ይደረግባቸዋል። ኮከብ የተደረገባቸው ስያሜዎች ሁሉም ከጥቅሉ መጨረሻ ላይ ፍቺ ይሰጣቸዋል።

Script

1. የዶሮ በሽታን ስለመቋቋም የተዘጋጀ ታሪክ

ሶጎዶጎ ሳራታ በርቴ ከማሊ ዋና ከተማ ከባማኮ 165ኪሜ እርቆ በሚገኘው በቡጉኒ የሚኖሩ ባለቤታቸው የሞቱባቸው የ65 ዓመት ሴት ናቸው። ከማላዊ ፖስታ ድርጅት ጡረታ ከወጡ በኋላ ሳራታ ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ ዶሮ እርባታ ላይ አድርገዋል። ስራ ፈጣሪ መሆን እንደሚፈልጉ ማንኛውም ሴቶች ኝ ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል።

ስራውን ሲጀምሩ ግቢውን በዶሮ ኩስ አበላሸሽው የሚለውን የባለቤታቸውን ወቀሳ ተቋቁመው የአካባቢውን ዝርያ ዶሮዎች በቤታቸው በተሳካ ሁኔታ አርብተው ነበር።

አማታቸው እያገዟቸው የተሻለ የዶሮ ቤት ሰርተው የመጀመርያ ዙር እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በመግዛት የዶሮ ንግድ ስራቸውን ጀመሩ። ነገር ግን ዶሮዎቹን እንዴት እንደሚከትቧቸው ባለማወቃቸው ታመሙባቸው። ዶሮዎቹ በጉምቦሮ በሽታ እንደተጠቁ ተነገራቸው። ባጠቃላይ 250 ዶሮዎች ሞቱባቸው።

ሳራታ ግን ተስፋ አልቆረጡም። አንድ ቀን የአርሶ አደሮችን ቡድን ከሚመራው ከእንጎሎ ጋር ተገናኙ። እንጎሎ ለአነስተኛ ዶሮ እርባታ ስራ የርቢ አውራ ዶሮዎችን እንዴት መጠቀም እንድሚቻል የሚያስተምር ስልጠና እንዲሳተፉ ጋበዛቸው። በእንጎሎ ድጋፍ እና ምክር ሳራታ እንደገና ጀመሩ። እንደገና በእግራቸው ቆሙ፣ የሥራ እቅድ አዘጋጅተው ከባንክ ብድር በመውሰድ 1000 እንቁላል ጣይና 1000 የስጋ ዶሮዎች ገዙ። ዶሮዎቹን በየጊዜው በመቀየር አሁን ጤናማ ገቢ አላቸው።

ከዶሮው በተገኘ ገቢ እቃ ጫኝ ባጃጅ ገዙ። ዛሬ የሳራታ ዶሮ ቤት በጸሃይ ሃይል ይሰራል፣ ከፊል ጣሪያው ተሸፍኗል፣ ብዙ የጀመሯቸው ፕሮጀክቶችም አሏቸው።

2 ስለዶሮ በሽታ አጠቃላይ መረጃ

መግቢያ
ዶሮዎች ለአፍሪካ የገጠር ቤተሰቦች በጣም አስፈላጊ ናቸው። አፍሪካ ውስጥ ከ80% በላይ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ አእዋፎች ዶሮዎች ናቸው። በየቤቱ ከ5 እስከ 20 የሚደርሱ ዶሮዎች አሉ። አርሶ አደሮች ዶሮዎችን ጭረው እንዲበሉ ግቢ ውስጥ በመልቀቅ ነፍሳት፣ ትላትል፣ የቤት ጥራጊ እና የሰብል ትርፍራፊ እየተመገቡ ያድጋሉ። እነዚህን አእዋፍ በመንከባከብ ሴቶች እና ህጻናት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

ጭረው የሚበሉ ዶሮዎችን በተለይ በራሳቸው በቂ ምግብ ማግኘት በማይችሉበት ወቅት አርሶአደሮች እንደ ሩዝ፣ በቆሎ እና ዳጉሳ ገለባ ያሉ የግብርና ተረፈ ምርቶችን ይመግቧቸዋል። ማታ ማታ ከመሬት ከፍ ብሎ በተሰራ ቆጥ ያሳድሯቸዋል። እነዚህ ቆጦች ዶሮዎቹን ከመጥፎ አየር ሁኔታ እና ሌሊት ከሚመጡ አውሬዎች ይጠብቋቸዋል። ስለዚህ አርሶ አደሮች በትንሽ መሬት፣ ጉልበትና ካፒታል በጣም ድሃ የሆኑ የገጠር ቤተሰቦች እንኳን ሳይቀሩ ዶሮ ማርባት ይችላሉ።

የኤክስቴንሽን እና ምርምር ተቋማት በገጠራማው የአፍሪካ ክፍል የሚደረገውን የዶሮ እርባታ ቸል ብለውታል፤ አርሶ አደሮችም ከሌሎች የግብርና ስራዎች አንጻር ብዙም እንደሚጠቅም ስራ አይቆጥሩትም። ነገር ግን ከከተማ ውጪ አሳ በማይገኝባቸው አካባቢዎች ዶሮ ዋነኛ የገምቢ ምግብ እና የገቢ ምንጭ ነው፣ በብዙ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓሎችም ትልቅ ሚና ይጫወታል።

የዶሮ እርባታ ትልቁ ፈተናው በሽታ ነው። ናይጄሪያ ውስጥ በሃገር ውስጥ ዝርያዎች ላይ ለ15 ዓመት የተደረገ ጥናት ዋነኛዎቹ ዶሮ ገዳይ በሽታዎች የሚከተሉት እንደሆኑ አሳይቷል፡ ፈንግል፣ ተላላፊ የጭጓራ በሽታ፣ ፈንጣጣ፣ እንደ ቅማል እና መዥገር ያሉ የውጭ ጥገኞች፣ እና እንደትላትል ያሉ የውስጥ ጥገኞች።

ጫጩቶች በበሽታ በጣም ሊጥቁ ይችላሉ። የአገር በቀል ዝርያዎች እንደሚከተለው እንደሆነ ጥናት ያሳያል፡

  • 53% እስከ አራት ሳምንት የሆናቸው ጫጩቶች በካሜሩን
  • 31% እስከ አራት ሳምንት የሆናቸው ጫጩቶች በማሊ
  • 68% ስድስት ሳምንት የሞላቸው ጫጩቶች በናይጄሪያ
  • 50% እስከ ስምንት ሳምንት የሞላቸው ጫጩቶች በቡርኪና ፋሶ እና በሰሚናዊ ጋና
  • 66% 12 ሳምንት የሞላቸው ጫጩቶች በሴኔጋል

ባህላዊ መድሃኒት
ድሃ አርሶ አደሮች ኬሚካላዊ መድሃኒቶች የሚገዙበት ገንዘብ የላቸውም፣ መድሃኒቶቹም ተደራሽ አይደሉም። ከሰሃራ በታች ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች የአእዋፍ ከትባት የለም ማለት ይቻላል፤ አልፎ አልፎ ለሰው የተዘጋጁ የአንቲባዮቲከ መድሃኒቶች ሊሰጧቸው ይችላሉ።

ማሊ ውስጥ ለአርሶ አደሮች ትክክለኛ የክትባት ዘዴዎችን የማስተማር ሙከራዎች አሉ። ነገር ግን በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ ብዙም ውጤታማ አልሆኑም፡

  • ለአእዋፍ ክትባት ማስቀመጫ የሚያገለግሉ መሳርያዎች እጥረት
  • ትናንሽ የተባሉት የክትባት ቢልቃጦች የሚይዙት መጠን ከ100 እስከ 1000 ለሚሆኑ ዶሮዎች የሚበቃ መሆኑ፣ በዚህም ምክንያት አነስተኛ ቁጥር ዶሮዎች ላሏቸው አርሶ አደሮች ተስማሚ አለመሆኑ
  • የአርሶ አደሮች የጽዳትና የህክምና እውቀት አነስተኛ መሆን

ባህላዊ መድሃኒቶች ተደራሽነታቸው በአንጻራዊ ከፍተኛ ነው፣ ዋጋቸውም በጣም ርካሽ ወይም ነጻ ነው። እነዚህ መድሃኒቶች ከእጸዋት ውጤቶች የሚስሩ ሲሆን ለአንዳንድ በሽታዎች ውጤታማ ናቸው።
የባህላዊ እና ዘመናዊ መድሃኒቶች ተመራጭነት በምን በምን ሁኔታዎች እንደሆነ ለማወቅ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል።

በዚህ ጥቅል ውስጥ የተወሰኑ በሽታዎች ላይ ሳይንሳዊ ፍተሽ ተደርጎባቸው ውጤታማ የሆኑ እንዳንድ መድሃኒቶችን እንጠቅሳለን። ሌሎች ባህላዊ መድሃኒቶች ውጤታማ አይደሉም ማለት ግን አይደለም፤ ባብዛኛው በጥንቃቄ ፍተሻ አልተደረገባቸውም።

ክፍል ሀ፡ በሽታዎች፡ መንስኤዎች፣ ምልክቶች፣ እና ቁጥጥር

ፈንግል

መንሳኤ

ፈንግል በሽታ የመተንፈሻ አካልን* (respiratory*) እና የነርቭ ስርዐትን በሚያጠቃ ቫይረስ የሚመጣ በሽታ ነው። በጫጩቶች እና በትላልቅ ዶሮዎች እንደቫይረሱ ጎጂነት መጠን* (virulence*) ከ0 እስከ 100% ሞት ያመጣል።

chicken-and-rooster

የሴት (ከላይ) እና የአውራ (ከስር) ዶሮዎችን የሰውነት ክፍል የሚያሳይ ስእል

ምልክቶች

ጫቹቶች ያስላቸዋል፣ ያስነጥሳቸዋል፣ ሲተነፍሱ ይቃትታሉ። ትላልቆቹ ዶሮዎች በእግራቸው መጋጠሚያ ሊቀመጡ ይችላሉ፤ ወደ ኋላ ወይም በክብ ሊሄዱ ወይም ጭንቅላታቸውን በእግሮቻቸው መሃል ሊደብቁ ይችላሉ።

በትላለቆቹ ዶሮዎች ምልክቶች የመተንፈሻ አካል* መጨነቅ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ እና ማናወዝ ሊታይባቸው ይችላል። የእንቁላል ምርት በድንገት ሊቀንስ ይችላል፣ በሽታው በያዛቸው በአራት ቀናት ውስጥ የእንቁላል ምርት ዜሮ ሊሆን ይችላል። ዶሮዎቹ እንደገና እንቁላል መጣል ሲጀምሩ ቅርጹ የተበላሸ ሸካራ እና አንዳንድ ጊዜ የነጣ ቀፎ ያለው እንቁላል ሊጥሉ ይችላሉ።

ቁጥጥር

ፈንግል በሽታን ለመቆጣጠር ሶስት መንገዶች አሉ፡

  • ንጽህና: ከፊል ቁጥጥር በሚደረግባቸው እና ዶሮዎች አጥር ውስጥ ወይም ቤት ውስጥ በሚለቀቁባቸው ሁኔታዎቸ ንጽህና ሁልጊዜ አስፈላጊ ነው። ንጽህና የሚከተሉትን ይጨምራል፡ ማጽዳት፣ ጀርም ማጥፋት፣ የዱር አእዋፍ እንዳይገቡ ማድረግ፣ እና የሰራተኞች የግል ንጽህና።
  • የታመሙ ዶሮዎችን ማስወገድ: ይህ ከበሽታ ንጹህ በሆኑ ከሌሎች አካባቢዎች በርቀት በሚገኙ ቦታዎቸ ወይም በደሴቶች ላይ በስኬት የተተገበረ የመጨረሻ እርምጃ ነው።
  • ክትባት ከአስፈላጊ የንጽህና እርምጃዎች ጋር፡ ፈንግል በሽታን ለመከላከል ዋነኛው መንገድ ይህ ነው። ከ3-4 ሳምንት የሆናቸውን ጫጩቶች ከትባችሁ ከ16-24 ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ ድገሟችው። ከዚያ በኋላ በአካባቢው ወረርሽኝ ሲኖር ከትቧቸው።

ከሰሃራ በታቸ ባሉ የአፍሪካ ሃገሮች የፈንግል በሽታ ክትባት ዝቅተኛ ስኬት የሚያሳየው ክትባቱ በትክክለኛው የሙቀት መጠን ባለመቀመጡ ምክንያት ክትባቱ ስለማይሰራ ነው። ከሌሎች ምክንያቶች ውስጥ የዶሮዎች ሰፊ ስርጭት፣ የተበላሹ መንገዶች እና የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር ይገኙበታል።

ባህላዊ ቁጥጥር

  • ናይጄሪያ የተደረገ አንድ ጥናት ከባኦባብ ዛፍ ቅርፊት የተሰራ መድሃኒት በሚሊሊትር 250ሚግ መጠን ሲሰጥ እንቁላሎች በፈንግል በሽታ እንዳይበከሉ ይከላከላል።
  • ፓኪስታን የተደረገ አንድ ጥናት 7 ግራም የኒም ቅጠሎችን ለንግድ የሚቀርቡ የስጋ ዶሮዎች መኖ ውስጥ መቀላቀል ኒውካስል በሽታን የመከላከል አቅማቸውን እንደሚጨምር አሳይቷል።

ስፈንግል በሽታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

  1. World Organisation for Animal Health (OIE), Newcastle disease. Technical disease card. http://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Animal_Health_in_the_World/docs/pdf/Disease_cards/NEWCASTLE_DISEASE.pdf (220 KB)
  2. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.14: Newcastle diseasehttp://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Health_standards/tahm/2.03.14_NEWCASTLE_DIS.pdf(495 KB)
  3. Farm Radio International, 2009. Adventures of Neddy: A community animal health worker helps a village manage Newcastle disease. Resource Pack 88, Script 3. http://www.farmradio.org/radio-resource-packs/package-88/adventures-of-neddy-a-community-animal-health-worker-helps-a-village-manage-newcastle-disease/
  4. University of New Hampshire Cooperative Extension, 2008. Newcastle Disease. http://extension.unh.edu/resources/files/Resource000792_Rep815.pdf (360 KB)
  5. NobiVet, non daté. Aviculture familiale – Introduction au contrôle durable de la maladie de Newcastle.https://www.nobivet.fr/maladies/maladie-newcastle.aspx

 
የወፍ ጉንፋን

መንስኤ

የወፍ ጉንፋን በዳክዬ እና ሌሎች የውሃ ዎፎችን የሚያጠቃ በቫይረስ የሚመጣ በሽታ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ እና አደገኛ ሊሆን በሚችል መልኩ ወደ ዶሮዎች ሊተላለፍ ይችላል። የወፍ ጉንፋን ከታመሙ ወፎች ከሚወጡ ፈሳሾች በተለይም ከኩሳቸው ጋር ንክኪ ሲኖር ይተላለፋል። በተበከለ መኖ፣ ውሃ፣ መሳርያዎች እና የሰዎች ልብሶች አማካኝነትም ሊሰራጭ ይችላል።

ምልክቶች

ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ:

  • ሰማያዊ እና ያበጠ ኮክኒ እና ኩልኩልት (ስእሉን ተመልከቱ)
  • ማሳለና ማስነጥስ
  • ከአይን እና ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ
  • እግሮቻቸው ቀያይ መስመሮች ያወጣሉ
  • የምግብ ፍላጎት ማጣት
  • ተቅማጥ

ቁጥጥር

በሽታው በቫይረስ የሚመጣ ስለሆነ መድሃኒት የለውም። የተሻለው የመከላከያ መንገድ ንጽህና መጠበቅ እና የታመሙትን መግደል ነው። የወፍ ጉንፋን በአሁኑ ጊዜ በክትባት መከላከል አይቻልም።

የበሽታ ወረርሽኝ ከታየ በኋላ መንጋው ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዶሮዎች ማስወገድ እና የዶሮ ቤቶችን በጥንቃቄ ማጽዳት ነው። ወረርሽኝ እንዳለ ከጠረጠራችሁ ሁልጊዜ የእንሥሣት ጤና ባለሙያ ጥሩ። የታመሙ ዶሮዎችን አትብሉ።

ስለ ወፍ ጉንፋን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Questions and answers on avian influenza. http://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Media_Center/docs/pdf/Q_A_influenza_may2015.pdf (300 KB)
  2. World Organisation for Animal Health (OIE), undated. Avian influenza portal. http://www.oie.int/en/animal-health-in-the-world/web-portal-on-avian-influenza/
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.4: Avian influenza https://www.biosecuritycentral.org/resource/core-guidance-and-recommendations/terrestrial-manual/ (570 KB)
  4. Peter Sykanda, 2006. Avian influenza spots. Farm Radio International. http://www.farmradio.org/radio-resource-packs/package-79/avian-influenza-spots/
  5. CJRD-CIAH, 2007. Grippe aviaire et maladie de poulet. http://www.latitudesciences.ird.fr/images/photos/CIAH/Cahier_CIAH_bd.pdf (379 KB) (available only in French)

ፈንጣጣ

መንስኤ

የዶሮ ፈንጣጣ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ የተለመደ እና በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ የሆነ በሽታ ነው። ሁለት አይነት ፈንጣጣዎቸ አሉ። አንደኛው በቢምቢ እና በተበከሉ ቁስሎች አማካኝነት የሚተላለፈው ደረቅ ፈንጣጣ ነው። እርጥብ ፈንጣጣ የተባለው አይነት ደግሞ ቫይረሱን በመተንፈስ የሚመጣ ሲሆን አፍና ጉሮሮ ውስጥ የቁስል ቅርፊት ይሰራል። እርጥብ ፈንጣጣ የከፋው አይነት ሲሆን መታፈን እና መሞት ያመጣል።

ምልክቶች

በላባ ባልተሸፈኑት የዶሮዎቸ ሰውነት ክፍሎች በተለይም ፊት፣ ኩክኒ እና ኩልኩልት ላይ ኪንታሮት መሰል እባጭ ያሳያል። ደረቅ ፈንጣጣ ለተወሰነ ጊዜ የእንቁላል ምርት የሚቀንስ ሲሆን በማደግ ላይ ያሉ ዶሮዎችን እድገት ይቀንሳል።

እርጥብ ፈንጣጣ የአየር ቧንቧ (trachea*) ቀልቶ ሊታይ ይችላል፣ የተቆጣ እና ቅርፊት የመሰለ ቁስለትም (lesions*) በውስጥ በኩል ሊያወፍረው ይችላል። እነዚህ ቁስሎች የአየር ቧንቧውን ሙሉ በሙሉ ከደፈነው ሞት ሊያስከትል ይችላል። አፍ ውስጥ እና የአይን ጥግ ላይም ቁስለት ሊፈጠር ይችላል።

ቁጥጥር

  • መከላከያ:
    • በጀርም ማጥፊያ ውህድ እግርን ማጠብ
    • ጎብኝዎችን መቀነስ
    • ሠራተኞች ዶሮዎችን ሲያዩ ከጫጩቶች ጀምረው ወደ ትላልቆቹ ዶሮዎች መሄድ አለባቸው
    • አንድ ዙር የዶሮ ምርት ካበቃ በኋላ የዶሮዎችን ቤቶች እና መሳርያዎችን እጠቡ፤ ከዚያ ለአንድ እስከ ሁለት ሳምንት አትጠቀሙባቸው።
    • ቢምቢዎችን መቆጣጠር ወረርሽኝ እንዳይፈጠር ይረዳል።
    • የቢንቢዎች ቁጥር ብዙ ካልሆነ በስተቀር ወይም አስቀድሞ በሽታ ካልተፈጠረ ክትባት አብዛኛውን ጊዜ አያስፈልግም። ጫቹቶቸ ከአንድ ቀን እድሚያቸው ጀምሮ ሊከተቡ ይችላሉ። እንቁላል ለመጣል ወይም ለርቢ የሚያድጉ ዶሮዎችን ሁሉ እድሚያቸው ከ6-10 ሳምንት ሲሆን ለዶሮ ፈንጣጣ ይከተቡ። አንዴ የተሰጠ የዶሮ ፈንጣጣ ክትባት ለእድሜ ልክ ይከላከላቸዋል።
  • ህክምና:
    • ዶሮዎቹ አንዴ ከታመሙ በኋላ የዶሮ ፈንጣጣ ህክምና የለውም። ዶሮዎቹ መመገብ እና መጠጣት እስካላቆሙ ድረስ ደረቅ ፈንጣጣ ለሁለት ሳምንት ያህል የሚቆይ ሲሆን ብዙም የሞት አደጋ የለውም። የታመሙ ዶሮዎች በተሳካ ሁኔታ ከዳኑ መካከለኛ ደረቅ ፈንጣጣ ሊይዛቸው ቢችልም በሽታ የመከላከል አቅም ይሰጣቸዋል። የታመሙ ዶሮዎች መለየት ወይም መገደል አለባቸው።

ስለዶሮ ፈንጣጣ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. Backyard poultry website, undated. Fowl pox. http://forum.backyardpoultry.com/viewtopic.php?f=5&t=7971445
  2. Hy-Line International, 1982. Hy-Line Redbook: Management and Disease Control. Fowl Pox Prevention. http://www.hyline.com/aspx/redbook/redbook.aspx?s=2
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.10:Fowl pox.https://www.biosecuritycentral.org/resource/core-guidance-and-recommendations/terrestrial-manual/ (65 KB)

የዶሮ ኮሌራ

መንስኤ

የዶሮ ኮሌራ ፓስተሬላ አቪሲዳ በተባለ ሕዋስ የሚመጣ ሲሆን ይህ ሕዋስ ደም ውስጥ በፍጥነት በመባዛት እና መንጋው ውስጥ በፍጥነት በመዛመት ዶሮዎችን ይመርዛል። የዶሮ ኮሌራ በአጣዳፊ እና ረጅም ጊዜ በሚቆይ (ክሮኒክ) መልክ ይከሰታል። አጣዳፊው ከባድ ሲሆን ከፍተኛ የመታመም (morbidity*) እና የሞት መጠን አለው። ያደጉ ዶሮዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።

ምንም የበሽታ ምልክት የማያሳዩ ለረጅም ጊዜ የታመሙ ዶሮዎችና ተሸካሚዎች ዋነኛ የበሽታ አስተላላፊዎች ናቸው። የዶሮ ኮሌራ አብዛኛውን ጊዜ ከንፍጥ፣ ደም ወይም ሌሎች ከታመሙ ዶሮዎች እና የዱር ወፎች አፍ፣ አፍንጫና አይን ከሚወጡ ፈሳሾች ጋር በሚኖር ንክኪ ይተላለፋል። በቢምቢ፣ ሰዎች እና ሌሎች እንሥሶች አማካኝነትም ይተላለፋል። ፓስተሬላ አቪሲዳ አካባቢ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ በጋሪዎች፣ የምግብ ከረጢቶች፣ ጫማዎች እና ሌሎች እቃዎቸ አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል።

ምልክቶች

የአጣዳፊ ኮሌራ የተለመዱ ምልክቶች የምግብ ፍላጎት አለመኖር (anorexia*)፣ የላባዎች መንጨብረር፣ የአፍና ያፍንጫ ፈሳሽ፣ ሲያኖሲስ (ደም ውስጥ በሚኖር አነስተኛ ኦክሲጅን የተነሳ ቆዳ ሰማያዊ ቀለም ሲኖረው)፣ ነጭ ወይም አረንጓዲያማ ተቅማጥ ናቸው። ለረጅም ጊዜ የሚቆየው ኮሌራ ምልክቶች የኩልኩልት ማበጥ እና ሳይነስ ናቸው።

ቁጥጥር

በተወሰነ ቦታ በሚያድጉ ዶሮዎች ውስጥ የሚፈጠረውን ወረርሽኝ ቢምቢዎችን ለመግደል በመርጨት መቆጣጠር ይቻላል። የዶሮ ፈንጣጣ ባካባቢው ሁልጊዜ ካለ ክትባት ማድረግ ይመከራል። ዶሮዎች ከ4-6 ሳምንት እድሜ ሲሞላቸው ሊከተቡ ይችላሉ።

አጣዳፊ የዶሮ ኮሌራ በሽታ ያለባቸው ዶሮዎች ባሰቸኳይ መገደል እና መቃጠል አለባቸው፣ ቤታቸውም ሙሉ በሙሉ መታጠብ እና ከጀርም መጽዳት ኣለበት። ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮሌራ መድሃኒት የለውም፣ ነገር ግን ዶሮዎቹ ለተጓዳኝ ተላላፊ በሽታዎች* በሰልፋድራግስ ሊታከሙ ይችላሉ።
ስለዶሮ ኮሌራ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. Poultry Hub, undated. Fowl cholera (or pasteurellosis) http://www.poultryhub.org/health/disease/types-of-disease/fowl-cholera-or-pasteurellosis/
  2. The Merck Veterinary Manual, 1982.Overview of fowl cholera. http://www.merckvetmanual.com/mvm/poultry/fowl_cholera/overview_of_fowl_cholera.html?qt=&sc=&alt=
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.9: Fowl cholera.https://www.biosecuritycentral.org/resource/core-guidance-and-recommendations/terrestrial-manual/ (519 KB)

የዶሮ ተስቦ

መንስኤ

በሽታው ሳልሞኔላ ጋሊናሪየም በተባለ ባክቴሪያ አማካኝነት ይመጣል። በታመሙ ዶሮዎች እና እንደ ጫማ እና ቆሻሻ ባሉ በተበከሉ ነገሮች አማካኝነት ሊተላለፍ ይችላል። ሰገራ ከአፍ ጋር ንክኪ ሲኖር ወይም እንቁላል በመብላት በጫጩቶች እና ትላልቅ ዶሮዎች መካከል ሊተላልፍ ይችላል። ባክቴሪያው አካባቢ ውስጥ ለወራት መኖር ቢችልም የተለመዱ ጀርም ማጥፊያዎች ይገድሉታል።

ምልክቶች

የሚከተሉት ምልክቶች አሉት፡ መፍዘዝ፣ የተንጨበረሩ ላባዎች፣ ትኩሳት፣ የጭንቅላት መገርጣት፣ እና ነጣ ያለ ብርቱካናማ ተቅማጥ። ምልክቶቹ በሽታው በያዛቸው ከ3-4 ቀናት ውስጥ ይታያሉ፣ ሞት በሁለት ሳምንታት ውስጥ ይፈጠራል። ከመንጋው ውስጥ ከ10-100% የሚሆኑት በበሽታው ሲጠቁ፣ በተጨነቁ ወይም በሽታ የመከላከል አቅማቸው በቀነሰ ዶሮዎች መካከል የሞት ምጣኔ 100% ሊደርስ ይችላል።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • ዶሮዎችን ሰባት ሳምንት ሲሞላቸው ከትቧቸው
  • የሞቱ ዶሮዎችን በሙሉ በማቃጠል አስወግዱ
  • ጎብኝዎች ጀርም ማጥፊያ ካልተረጩ ወደ ዶሮ እርባታው ቦታ እንዲገቡ አታድርጉ።

መከላከያ:

  • በጸረ ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክስ) መታከም ይችላል
  • የተሻላቸው ዶሮዎች በሽታውን መቋቋም ይችላሉ፣ ተሸካሚ* ሆነው ሊቆዩ ግን ይችላሉ።

ስለዶሮ ተስቦ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. The Poultry Site, undated. Salmonella Gallinarum, Fowl Typhoid. http://www.thepoultrysite.com/diseaseinfo/130/salmonella-gallinarum-fowl-typhoid/
  2. University of New Hampshire Cooperative Extension, undated. 2008. Pullorum disease and fowl typhoid.http://extension.unh.edu/resources/files/Resource000793_Rep817.pdf (372 KB)
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.11: Fowl typhoidhttp://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Health_standards/tahm/2.03.11_FOWL_TYPHOID.pdf (239 KB)

ፑሎረም በሽታ

መንስኤ

ፑሎረም በሽታ ሳልሞኔላ ፑሎረም በተባለ ባክቴሪያ የሚመጣ የሴት ዶሮ የኦቫሪ በሽታ ነው። ጀርሙ በዶሮዋ አንጀት ውስጥም ይገኛል። አብዛኛውን ጊዜ በሽታው የሚተላለፈው ጀርሙ ያለባት ዶሮ በጣለችው እንቁላል እና ከዚያ እንቁላል በተፈለፈሉ ጫጩቶቸ አማካኝነት ነው። አብዛኛዎቹ በበሽታው የተያዙ ዶሮዎች ሲያድጉ የጀርሙ ተሸካሚዎች (carriers*) ይሆናሉ።

የበሽታው ምልክቶቸ

ጀርሙ ካለበት እንቁላል እንደተፈለፈሉ ጫጩቶቹ ታመው ሊሞቱ ይችላሉ። በሽታው ያለባቸው ዶሮዎች ደካማ፣ የቀነጨሩ እና የምግብ ፍላጎታቸው የቀነሰ ይሆናሉ። በጣም የሚጮህ ድምጽ ይወጣቸዋል፤ ከፊንጢጣቸውም ነጭ ኩስ ለማወጣት ይሞክራሉ። አንዳንድ ጊዜ ጫጩቶቹ ከተፈለፈሉ ከ5-10 ቀን ድረስ የበሽታው ምልክቶች አይታዩም። አብዛኛው ሞት ጫጩቶቹ በተፈለፈሉ በሁለተኛው ወይም በሶስተኛው ሳምንት ይፈጠራል። ያደጉ ዶሮዎች በውጭ የሚታይባቸው ምልክት የለም።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • የተረጋገጡ የበሽታውን ተሸካሚዎች (carriers*) በሙሉ ግደሉ።
  • የዶሮዎቹን መኖርያ እና ሌሎችን አካባቢዎች ኢንኩቤተሮችን ጨምሮ አጽድታችሁ ከጀርም የጸዱ አድርጉ።
  • ጥሩ የበሽታ ቁጥጥር ፕሮግራም ካላቸው መፈልፈያዎች ጫጩቶች አምጡ።

ህክምና:

  • የዳኑ ዶሮዎች አብዛኛውን ጊዜ የበሽታው ተሸካሚዎች ስለሚሆኑ ህክምና አስፈላጊ አይደለም።

ስለ ፑሎረም በሽታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. University of New Hampshire Cooperative Extension, undated. 2008. Pullorum disease and fowl typhoid.http://extension.unh.edu/resources/files/Resource000793_Rep817.pdf (372 KB)
  2. The Poultry Site, undated. Salmonella Pullorum, Pullorum Disease, ‘Bacillary White Diarrhoea.http://www.thepoultrysite.com/diseaseinfo/131/salmonella-pullorum-pullorum-disease-bacillary-white-diarrhoea/
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.11: Fowl typhoid and pullorum disease. http://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Health_standards/tahm/2.03.11_FOWL_TYPHOID.pdf (239 KB)

ኮክሲዲዮሲስ
መንስኤ

በሽታው በኮክሲዲያን ይመጣል። ኮክሲዲያን በወፍ አንጀት ውስጥ በጣም በፍጥነት የሚራቡ ጥቃቅን ጥገኛ ሕዋሳት ናቸው። ኮክሲዲዮሲስ ጫጩቶች ከ8-10 ሳምንት እድሜ ሲኖራቸው የሚፈጠር ሲሆን አጣዳፊ እና የሚቆይ አይነት አለው። በአጣዳፊው በሽታ ጫቹቶች ከ5-7 ቀናት ውስጥ ይሞታሉ። የሚቆየው አይነት ወዲያው በመግደል ፋንታ ለረጅም ጊዜ ይቆያል።

ምልክቶች

የታመሙ ወፎች ወይም ጫጩቶች ጭንቅላታቸው ያዘቀዝቃል፣ ደካማ እና ዝልፍልፍ ይሆናሉ፣ የምግብ ፍላጎታቸው ሊቀንስ ይችላል፣ እራሳቸውን አያጸዱም፣ ላባቸው ይንጨባረራል፣ መንቆራቸው እና ከጉልበታቸው በታች ያለው እግራቸው ይገረጣል። ባንዳንድ ኮክሲዲዮሲስ አይነቶች ኩሳቸው ደም ይታይበታል። የሞት መጠን ከፍተኛ እና ድንገተኛ ሊሆን ይችላል።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • ውጭ ለሚኖሩ ዶሮዎች ቤት ውስጥ ያለውን መተኛቸውን ንጹህ እና ደረቅ አድርጋችሁ አስቀምጡ።
  • ውሃ መጠጫቸውን እና መመገቢያቸውን ከመሙላታችሁ በፊት አጽዱ።
  • በአንድ ቀን እድሚያቸው ክትባት ስጡ፣ የኮክሲዲዮሲስ ክትባት የተሰጣቸውን ጫጩቶች ግን ክትባቱን ስለሚያመክነው መድሃኒት ያለበት መኖ አትስጡ።

ህክምና:

  • በሽታው ከያዛቸው በኋላ ባለው አንድ ወር ሰልፋ ድራግስ መድሃኒት መኖ ውስጥ በመጨመር አክሙ።

ባህላዊ ቁጥጥር

  • ፓኪስታን ውስጥ የተደረገ አንድ ጥናት የኒም ቅጠል፣ የትምባሆ ቅጠል እና የሶዶም አፕል (ካሎትሮፒስ ፕሮሴራ) አበባ እና የትራኪስፐርመም አሚ ፍሬዎች ባንድ ላይ ተቀላቅለው ከመደበኛው የእንሥሣት መድሃኒት እኩል ኮክሲዲዮሲስን መከላከል ይችላል።
  • ሌላ ጥናት ደግሞ ለስጋ ዶሮዎች የተዘጋጀ መኖ ውስጥ 0.3% የተፈጨ የኒም ፍሬ በመጨመር ከመደበኛው የእንሥሣት መድሃኒት እኩል ኮክሲዲዮሲስን የመቀነስ ብቃት አለው።
  • ካሜሩን የተደረገ ጥናት ደግሞ የፓፓያ ፍሬ ዉጤት ውሃ ውስጥ በመቀላቀል መስጠት ለስጋ በሚረቡ ዶሮዎች ውስጥ ኮክሲዲዮሲስን ለመቀነስ ይረዳል።

ስለኮክሲዲዮሲስ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. Poultry Hub website. Coccidiosis. https://www.poultryhub.org/all-about-poultry/health-management/disease/coccidiosis
  2. The Merck Veterinary Manual, 1982. http://www.merckvetmanual.com/mvm/poultry/coccidiosis/overview_of_coccidiosis_in_poultry.html

የውጭ ጥገኞች

እነዚህ በዋናነት ቅማል፣ ቁንጫ፣ ቢምቢ እና ሌሎች ዝንቦች ናቸው።

ምልክቶች

የቆዳ መለብለብ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ የደም ማነስ*፣ ክብደት መቀነስ፣ ምርት መቀነስ።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • ጥሩ ንጽህና፣ በቂ ምግብ
  • ዶሮዎችን በየወሩ የውጭ ጥገኛ እንዳላቸው መርመሩ። ዶሮዎቹን ወደ ማደርያቸው ከገቡ እና ከተረጋጉ በኋላ መመርመር ይመከራል። ፊንጢጣቸው አካባቢ እና ክንፋቸው ስር ቅማል ወይም ትኋን መኖሩን እዩ፣ ጭንቅላታቸውን እና አንገታቸውን ቅማል እንዳይኖርበት እዩ። ማደርያ ቆጣቸውን እና እንቁላል መጣያ ሳጥኖቻቸውንም መርምሩ። አንድ ዶሮ ተባይ ከተገኘባት ሌሎቹም ይኖርባቸዋል።

ሕክምና:

  • መንጋው ውስጥ እና ዶሮ ቤት ውስጥ ያሉትን ዶሮዎች ለዶሮ በተፈቀደ ተባይ ማጥፊያ እርጩ። ጽሁፉ ላይ ያለውን መመርያ በሙሉ ተከተሉ። ይህምመከላከያ አልባሳትን እና የታከሙ ዶሮዎች ሰጋቸውን እና እንቁላላቸውን ከመጠቀም በፊት ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለበት ይጨምራል።
  • ኦርጋኒክ ፓይሬትረም (ከክሪሳንቲመም የሚገኝ) ለሰዎች እና ለዶሮዎች ጉዳት የማያመጣ ሲሆን ለነፍሳት ግን ከፍተኛ መርዛማ ነው። ፊንጢጣቸው አካባቢ እና ክንፋቸው ስር ዱቄቱን ነስንሱ፤ የዶሮ ቤቶች ላይ ያሉ ስንጥቆችን እና ጎድጓዳ ቦታዎችንም መድሃኒት ጨምሩባቸው።

ስለ ውጭ ጥገኞች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. M.S.K. Mashishi, 1996. External parasites of chickens. Directorate Agricultural Information Services, Department of Agriculture in cooperation with ARC-Onderstepoort Veterinary Institute (South Africa). http://www.nda.agric.za/docs/Infopaks/parasites1.pdf (473 KB)
  2. Carol Cardona and Peter L. Msoffe, editors, undated. Handbook of poultry diseases important in Africa. http://afghanag.ucdavis.edu/c_livestock/poultry/Man_Poultry_Diseases_GLCRSP.pdf(pages 31-38) (1.388 KB)

የውስጥ ጥገኞች
የውስጥ ጥገኞች ወስፋት እና ኮሶን ይጨምራሉ። እነዚህ ጥገኞች ዶሮዎችን በማወክና እድገታቸው እና እንቁላል ምርታቸው ላይ ተጽእኖ በማሳደር ቀጥተኛ ጉዳት ያደርሳሉ። አንዳንድ በሽታዎችንም ያሰራጫሉ።

ከፍተኛ የወስፋት በሽታ ሲኖር አንድ እንስሳ ምልክት ከማሳየቱ በፊት ሊሞት ይችላል። ኮሶ ዶሮዎች ላይ ብዙም አካላዊ ጉዳት አያደርስም፣ ነገር ግን ለእድገታቸው የሚፈልጉትን ምግብ ለራሱ ይወስዳል።

ምልክቶች

እንደ ጥገኛው አይነት ጥቂት ምልክቶች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ወይም ከባድ ተቅማጥ፣ በጣም መቀጨጭ፣ የደም ማነስ* እና ሞት ሊከተል ይችላል።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • ተገቢ የጥንቃቄ እርምጃዎች
  • አእዋፎችን እንደ ዝርያቸውና እንደ እድሚያቸው መለያየት

ሕክምና:

  • በእንስሳት ሐኪም የተመከረ መድሃኒት ተጠቅማችሁ መንጋውን አክሙ። ለአንዳንድ ጥገኞች የዶሮዎችን ማደርያ ወይም አካባቢውንም ማከም ያስፈልጋል።

ባህላዊ ቁጥጥር

  • በዛምቢያ በተደረገ ጥናት መሠረት ከ5-6 ወር ለሞላቸው ዶሮዎች በክብደታቸው ልክ ለአንድ ኪሎ የዶሮው ክብደት 0.7 ሚሊ ሊትር የ20% የፓፓያ ላቴክስ ውህድ የሚጠጡት ውሃ ውስጥ በመቀላቀል የትላትል ጥቃትን መቀነስ እና ክብደት እንዲጨምሩ ማድረግ ይቻላል።
  • ቤኒን በተደረግ ጥናት መሠረት በሊትር 4 ግራም የፖፓያ ፍሬ መጨመር ልክ እንደ መደበኛ የእንስሣት መድሃኒት ወስፋትን ለመቆጣጠር ይረዳል።

ስለ ውስጥ ጥገኞች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. Mississippi State University. Poultry production in Mississippi: Parasitic diseases (internal).http://msucares.com/poultry/diseases/disparas.htm
  2. Department of Agriculture and Environmental Affairs, Province of Kwazulu-Natal, South Africa, 2013. Household Chicken Production. http://www.heifer.org.za/assets/attachments/5.%20Household%20Chicken%20Production.pdf (2,395 KB)
  3. Carol Cardona and Peter L. Msoffe, editors, undated. Handbook of poultry diseases important in Africa. http://afghanag.ucdavis.edu/c_livestock/poultry/Man_Poultry_Diseases_GLCRSP.pdf(pages 39-47). (1,388 KB)

የማሬክ በሽታ

መንስኤ

የማሬክ በሽታ አካባቢ ውስጥ ለረጅም ጊዜ መቆየት በሚችል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ክፍተኛ ተላላፊነት ያለው በሽታ ነው። በቫይረሱ የተያዙ ዶሮዎች ለእድሜ ልክ የቫይረሱ ተሸካሚ* እና አሰራጭ ሊሆኑ ይችላሉ። አዲስ የተወለዱ ጫጩቶች ለጥቂት ሳምንታት ከእናታቸው ባገኙት አንቲቦዲ* ሊጠበቁ ይችላሉ። ቫይረሱ ከዶሮዎቹ ላባ በሚረግፍ ቁንቋን አማካኝነት ተሰራጨቶ በትንፋሽ አማካኝነት ይተላለፋል።

ምልክቶች

የማሬክ በሽታ ከ3–4 ሳምንት እና ከዚያ በላይ እድሜ ባላቸው ዶሮዎች ሲከሰት በብዛት ግን ከ12-30 ሳምንት እድሜ ባላቸው ዶሮዎች ላይ ይከሰታል። ከባድ የሆኑት የበሽታው አይነቶች ከ1–2 ሳምንት እድሜ ባላቸው ጫጩቶች መካከል ከፍተኛ ሞት ሊያስከትል ይችላል። ብዙ ዶሮዎች የበሽታውን ምልክቶች ሳያሳዩ እድሜ ልካቸውን ተሽካሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

የሚታዩት ምልክቶች እንደ በሽታው አይነት ይለያያሉ:

የቆዳ ማሬክ በሽታ (Cutaneous form):

  • ያበጠ እና የቀላ የላባ ሥር (follicles*) እና ቡናማ ቅርፊት የሚፈጥሩ ነጫጭ የቆዳ እባጮች

የነርቭ ማሬክ በሽታ (Neural form): (ከዚህ በታች ያሉት ሁሉም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ ወይም ምንም ላይታይ ይችላል)

  • እግር ወይም ክንፍ ቀስ በቀስ ሽባ መሆን
  • ክብደት መቀነስ
  • ለመተንፈስ መቸገር
  • ተቅማጥ
  • መመገቢያውን እና ውሃ መጠጫውን ለመድረስ ባለመቻል በረሃብ እና በሌሎች ዶሮዎች በመረጋገጥ መሞት

የአይን ማሬክ በሽታ (Ocular form):

  • ግራጫ የአይን ቀለም
  • የአይሪስ ቅርጽ መለወጥ
  • ክብደት መቀነስ
  • አይነ ስውርነት
  • ሞት

የሆድ ማሬክ በሽታ (Visceral Form): ልብ፣ ኦቫሪ፣ ጉበትና እና ሳንባን ጨምሮ የውስጥ ብልቶች ላይ እባጭ ይወጣል።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • ጫጩቶችን በአንድ ቀን እድሚያቸው ከትቧቸው። ክትባት የበሽታውን ምልክቶች በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል፣ ደግሞ መያዝን ግን አያስቀርም፤ ቫይረሱ መኖሩ እና ወደ አካባቢ መለቀቁን ይቀጥላል። ክትባት የበሽታውን መተላለፍም አያስቀርም፣ ነገር ግን የታመሙ ዶሮዎች የሚለቁትን የቫይረስ መጠን በመቀነስ የበሽታውን ስርጭት ይቀንሳል።

ሕክምና:

  • በቫይረሱ ለተያዙ ዶሮዎች ምንም ህክምና የለም።

ሰለ ማሬክ በሽታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት:

  1. Carol Cardona and Peter L. Msoffe, editors, undated. Handbook of poultry diseases important in Africa. http://afghanag.ucdavis.edu/c_livestock/poultry/Man_Poultry_Diseases_GLCRSP.pdf (Page 63) (1,388 KB)
  2. University of New Hampshire Cooperative Extension, 2008. Marek’s Disease. http://extension.unh.edu/resources/files/Resource000791_Rep813.pdf (368 KB)
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.13: Marek’s Diseasehttp://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Health_standards/tahm/2.03.13_MAREK_DIS.pdf (93 KB)

ተላላፊ ብሮንካይቲስ (bronchitis)

መንስኤ

የወፎች ተላላፊ ብሮንካይቲስ በሽታ መንስኤው ቫይረስ ነው። በአየር፣ በዶሮና ዶሮ ንክኪ፣ እና በተበከሉ የዶሮ መሳርያዎች ወይም እንቁላል ማሸጊያዎች፣ ለማዳበርያነት በሚውል አዛባ፣ እርሻዎችን በመጎብኘት ወዘተ ይተላለፋል።

ምልክቶች

ዋናዎቹ ምልክቶች ከመተንፈሻ አካል* ጋር የተያያዙ ናቸው፣ ነገር ግን በተጨማሪ የእንቁላል ምርት እና ጥራት መቀነስንም ይጨምራል። ሳል እና ኩር ኩር የሚል ትንፋሽ በተለይ በትናንሽ ዶሮዎች ይታያል፣ በአንድ ቦታ ተወስነው በሚኖሩ ዶሮዎች መካከል በፍጥነት ይሰራጫል። ክትባት ባልተሰጣቸው የዶሮ መንጋ ውስጥ ሁሉም በበሽታው ይያዛሉ።

የሞት መጠን እንደቫይረሱ አይነት የሚለያይ ሲሆን ባለተከተቡ ዶሮዎች መካከል እስከ 60% ይደርሳል። የመተንፈሽዐ አካል ምልክቶች በሁለት ሳምንት ውስጥ ያልፋሉ፣ በአንዳንድ የቫይረሱ አይነቶች የኩላሊት መመርቀዝ ይከተልና ሞት ያመጣል። ትናንሽ ዶሮዎች የመተንፈሻ አካላቸው ተደፍኖ ወይም ኩላሊታቸው ሥራ አቁሞ ሊሞቱ ይችላሉ።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • ለበሽታው ክትባት ያለው ሲሆን መጠነኛ የመተንፈስ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ክትባት መጀመርያ ላይ ከ1-14 ቀን ለሚሆናቸው ጫጩቶች ይሰጣል፣ ከመጀመርያው ክትባት ሰባት ቀን ቆይቶ ማጠናከርያ ክትባት እንደገና ይሰጣቸዋል።
  • የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር የንጽህና እርምጃዎችን በመውሰድ የታመሙ ዶሮዎችን መለየት እና መኖርያዎችን ከጀርም ማጽዳት ያስፈልጋል።

ሕክምና:

  • ሕክምና የለውም፣ ነገር ግን አንቲባዮቲክ መጠቀም ተጓዳኝ ተላላፊ በሽታዎችን (secondary infections)* ሊከላከል ይችላል።
  • ከመኖ ውስጥ የገምቢ ምግብ መጠንን መቀነስ እና በሚጠጡት ውሃ ውስጥ ኦ.አር.ኤስ. (electrolytes)* መጨመር ከአንዳንድ የቫይረሱ አይነቶች የሚመጣውን ወረርሽኝ ሊቀንስ ይችላል።

ለተጨማሪ መረጃ:

  1. Carol Cardona and Peter L. Msoffe, editors, undated. Handbook of poultry diseases important in Africa. http://afghanag.ucdavis.edu/c_livestock/poultry/Man_Poultry_Diseases_GLCRSP.pdf (Page 57-58) (1,388 KB)
  2. Poultry Hub. Infectious bronchitis. http://www.poultryhub.org/health/disease/types-of-disease/infectious-bronchitis/
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.2: Infectious Bronchitis http://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Health_standards/tahm/2.03.02_AIB.pdf (140 KB)

የጉምቦሮ በሽታ

መንስኤ

ጉምቦሮ በሽታ በቫይረስ የሚመጣ በጣም ተላላፊ የሆነ የጫጩቶች በሽታ ነው። የበሽታ መከላከል አቅምን በማድከም ከ3-6 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሞት ያመጣል።

ምልክቶች

በሽታው በድንገት ሊከሰት ይችላል፤ በመንጋው ውስጥ ያሉትን ዶሮዎች ሁሉ ይይዛል። በአጣዳፊው የበሽታው አይነት ዶሮዎቹ ይተኛሉ፣ ላባቸው ይንጨባረራል፣ ደካማ ይሆናሉ፣ ሰውነታቸውም ፈሳሽ ያጣል። ውሃማ ተቅማጥ ይኖራቸዋል፣ ፊንጢጣቸው ያበጠና በኩስ የቆሸሸ ይሆናል። አጣዳፊው አይነት የበለጠ ሕመም ሲኖረው ከፍተኛ የሞት ምጣኔ አለው።

ትልቁ የበሽታው ተጽእኖ ከሦስት ሳምንት እድሜ በታች ያላቸውን ጫጩቶች በሽታ የመከላከል አቅም ማቆሙ ነው። ቫይረሱ ያለባቸው ዶሮዎች ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን በሽታ የመከላከል አቅማቸው ስለወረደ ሊገድሏቸው ለሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች ሊጋለጡ ይችላሉ።

ቁጥጥር

መከላከያ:

  • የመከላከያ መንገዶች ወደ እርባታ ቦታው ጉብኝት መቀነስ እና የታመሙትን ከሌሎች መለየትን ይጨምራሉ
  • ወረርሽኝ ከተፈጠረ በኋላ ቫይረሱ በማደርያ ቦታና ውሃ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚኖር የንጽህና እርምጃዎች ብዙም ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ።
  • የርቢ ዶሮዎች ቢከተቡ በሽታ የመከላከልን አቅም ለልጆቻቸው ማስተላለፍ ይችላሉ
  • በሽታው በፍጥነት ስለሚሰራጭ በወረርሽኝ ጊዜ ክትባት መስጠት ብዙም ውጤታማ ላይሆን ይችላል

ሕክምና:

  • በቫይረሱ ለተያዙ ዶሮዎች ምንም ሕክምና የለም። ነገር ግን ዶሮዎች ከእናቶቻቸው ወይም ጉዳት በማያመጡ የቫይረሱ ዝርያዎች (non-virulent*) በመያዝ ባገኟቸው አንቲቦዲዎች * አማካኝነት በሽታ የመከላከል አቅም ሊያገኙ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ:

  1. Carol Cardona and Peter L. Msoffe, editors, undated. Handbook of poultry diseases important in Africa. http://afghanag.ucdavis.edu/c_livestock/poultry/Man_Poultry_Diseases_GLCRSP.pdf (Page 58) (1,388 KB)
  2. Washington State University, Washington Animal Disease Diagnostic Lab, undated. Infectious Bursal Disease. http://waddl.vetmed.wsu.edu/animal-disease-faq/infectious-bursal-disease
  3. World Organisation for Animal Health (OIE), 2015. Manual of Diagnostic Tests and Vaccines for Terrestrial Animals, 2015. Chapter 2.3.12: Infectious Bursal Disease http://www.oie.int/fileadmin/Home/eng/Health_standards/tahm/2.03.12_IBD.pdf (160 KB)

ተባይ ማጥፊያ አጠቃቀም ጥንቃቄ

የተባይ ማጥፊያ ተደጋግሞ ወይም በብዛት ከተጠቀሙ ዶሮዎች ሊመረዙ ይችላል። እቃው ላይ ያለውን መመርያ በጥንቃቄ ተከተሉ። ለዶሮ እንደሚያገለግሉ ምልክት ያልተደረገባቸውን ተባይ ማጥፊያዎች አትጠቀሙ።
ለቤት እና ለግቢ ተስማሚ የሆኑ አንዳንድ ተባይ ማጥፊያዎች ዶሮዎቹን ራሳቸውን ለማከም ተስማሚ አይደሉም፣ ርጭት በሚደረግበት ጊዜ ዶሮዎች መራቅ አለባቸው። ተባይ ማጥፊያዎቹ ዶሮዎቹን ሳይጎዱ ሲቀሩ እንኳን እንቁላል እና ስጋ ውስጥ ስለሚገባ ለምግብነት ተስማሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል። ዶሮዎቹ ራሳቸው ሲረጩና በተረጨ ቤትና ግቢ አማካንነት ሲጋለጡ ይህ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። የተጋለጡት ላጭር ጊዜ ከሆነ መርዙ ይጠፋል፣ እንቁላሉ እና ስጋውም ከተወሰነ ቆይታ ጊዜ በኋላ ለምግብነት ተስማሚ ይሆናል። የቆይታ ጊዜው መጠን የተባይ ማጥፊያው እቃ ላይ ስለሚጻፍ በትክክል መከተል ያስፈልጋል።


ክፍል ለ: አጠቃላይ የበሽታ መከላከያ

ለያንዳንዱ በሽታዎች ከላይ ከተጠቀሱት እርምጃዎች ባለፈ የዶሮ በሽታዎችን በሚከተሉት ጥሩ የቁጥጥር እና የንጽህና መንገዶቸ መከላከል ይቻላል።

ቁጥጥር

  • ጫጩቶችን ለማሳደግ ትክክለኛውን መንገድ ተጠቀሙ፦ ትክክለኛ የሙቀት መጠን፣ ጥሩ ጥራት ያለውና ትክክለኛ መጠን ያለው ምግብና ውሃ እንዲሁም ትክክልኛ ንጣፍ ወዘተ ተጠቀሙ።
  • ለቦታው የሚበቃ ትክክለኛ የጫጩቶች ቁጥር ተጠቀሙ፣ ባንድ ቦታ ብዙ ዶሮዎችን አታጨናንቁ
  • አቧራማ ያልሆነ ንጣፍ ተጠቀሙ። አቧራ የመተንፈሻ* በሽታ ያመጣል
  • ቶሎ ቶሎ እንዲጸዳ እና አየር እንዲገባ አድርጉ
  • አይጥና ዝንቦችን ተቆጣጠሩ
  • ከውጭ የሚመጣ ሰው የዶሮ ቤቱን እንዳይጎብኝ አድርጉ
  • የዶሮዎቹን ምግብ እንዳይበሉና በሽታ እንዳያስተላልፉባቸው ወፍ የማያስገባ ቤት ሥሩ
  • የሚያፈሱ የውሃ ገንዳዎችን ጠግኑ
  • የመኖ እና የውሃ መያዣዎችን በየቀኑ አጽዱ፤ በየቀኑ አዳዲስ ምግብ እና ንጹህ ውሃ አቅርቡላቸው
  • ቤቶቹ በብርድ ጊዜ የሚሞቁ በሞቃት ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ የሚሉ እና አየር የሚገባባቸው እንዲሆኑ አድርጉ
  • ቤታቸው ውስጥ ስለታማ ጠርዝ እንዳይኖር አድርጉ
  • ከጥሩ እና አስተማማኝ አቅራቢ አንደኛ ድርጃ ጫጩቶችን ብቻ ግዙ
  • ጫጩቶቹን ለዋና ዋና በሽታዎች ክትባት ስጧቸው
  • ተመሳሳይ እድሜ ያላቸውን ጫጩቶች ባንድ ቤት አኑሩ።

ጽዳት

  • የዶሮ ቤቶችን ወይም ቅርጫቶችን በየሁለት ወሩ ከጀርም አጽዱ
  • ኩስ፣ ላባ እና የሞቱ ዶሮዎች የተላላፊ በሽታ ምንጭ ስለሆኑ ከማደርያ ቤት እና ዶሮዎች ከሚጭሩበት ግቢ መወገድ አለባቸው፤ የሞቱ ዶሮዎች 1.5-2ሜትር ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ በመቅበር ወይም በማቃጠል በአግባቡ መወገድ አለባቸው። ይህን በማድረግ የበሽታ ስርጭትን እና የውጭ ጥገኞችን መቀነስ ይቻላል።
  • ወደ መንጋው የሚቀላቀሉ አዳዲስ ዶሮዎችን ቢያነስ ለ15 ቀን በቅርጫት ወይም ጎጆ ውስጥ ለዩ። ጤናማ ሆነው ከቆዩ ከሌሎች ዶሮዎች ጋር መቀላቀል ይችላሉ።
  • አዲስ የሚመጡ ዶሮዎችን በሙሉ ለውጭ እና ለውስጥ ጥገኞች ሕክምና አድርጉላቸው፤ ከተቻለም ክትባት ስጧቸው።
  • የታመሙ ዶሮዎችን ለዩ ወይም ቶሎ ግደሉ እና ቅበሩ።
  • የዶሮ መተኛዎችን ቶሎ ቶሎ አገላብጡ፣ ሲረጥብ ቀይሩ።
  • ያደሩባቸውን ቅርጫቶች በጸሃይ አድርቁ ወይም በዝናባማ ወቅት እሳት አጠገብ ስቀሉ።
  • ለውሃ መጠጫ የሚያገለግሉ ገሎችን (የተሰበሩ ሽክላዎችን) መልሳቸሁ በውሃ ከመሙላታቸሁ በፊት በእሳት አሙቁ።
  • የዶሮ ቅርጫቶች ለማደርያ ካገለገሉ ጨርቅ ወይም ጆንያ አታንጥፉባቸው
  • የዶሮ ጎጆዎችን ወይም ቅርጫቶችን የአዛባ ክምር ወይም የጉድጓድ ሽንት ቤት አጠገብ አታስቀምጡ
  • ራሳቸውን ችለው መመገብ የጀመሩ ጫቹቶችን እና ከፍ ያሉ ጫጩቶችን ማደርያቸውን ለዩ። እንቁላል እየጣሉ ያሉ እና የታቀፉ ዶሮዎችን አትረብሹ።
  • አንድ የዶሮ ዝርያ ብቻ ቢኖር የተሻለ ነው።ካልተቻለ የበሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የተለያዩ ዝርያዎችን ለይታችሁ አሳድሩ።

Acknowledgements

ምስጋና
የጽሑፉ አዘጋጅ: ቪጃይ ከደፎርድ፣ ማኔጂንግ ኤዲተር፣ ፋርም ራዲዮ ኢንተርናሽናል
ገምጋሚ: ሙሳ ኮኔ፣ ላየቭስቶክ ኢንደስትሪ ዩኒት ሃላፊ፣ ሎካል ሰርቪስ ኦፍ አኒማል ፕሮዳክትስ (SLPIA)፣ ቡጉኒ፣ ማሊ

ይህ የርእሰ ጉዳይ ጥቅል በኢትዮጵያ የዶሮ እርባታ የራዲዮ ፕሮገራምን ለማሳደግ ከአይኤፍሲ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጀ።

Information sources

IV. በማሊ እና ከሰሃራ በታች ባለው አፍሪካ ስላሉ የዶሮ በሽታዎች ተጨማሪ መረጃዎች

Videos

Documents

የቃላት ፍቺ
ደም ማነስ/Anemia: ከቀይ የደም ሴል ክፍሎች ውስጥ የአንዱ ማነስ ሲሆን በደም ውስጥ ያለው የኦክስጅን መጠን አነስተኛ እንዲሆነ በማድረግ ድካምና መገርጣት ያመጣል
አኖሬክሲያ (የምግብ ፍላጎት መቀነስ)/Anorexia: የምግብ ፍላጎት ማጣት ወይም መመገብ አለመቻል
አንቲቦዲ/Antibody: በበሽታ መከላከያ ስርአት የሚፈጠሩ እና በሽታ የመቋቋም አቅም የሚፈጥሩ ሞለኪውሎች። የእናት አንቲቦዲዎች ወደ ልጅ ሊተላለፉ ይችላሉ።
ተሸካሚ/Carrier: የበሽታ ምልክት የማያሳዩ ነገር ግን በሽታውን የሚያመጣውን ጀርም የሚሽከሙ እና ወደ ሌላ የሚያስተላልፉ እንሣዎች
ቁንቋን/Dander: ከቆዳ ወይም ላባ ላይ የሚፈጠሩ ቅርፊቶች/ ቅርፋፊዎች
ኦ.አር.ኤስ/Electrolytes: እንደ ሶዲየም፣ ፖታሸም ወይም ክሎራይድ ያሉ ሴሎች ሥራቸውን ለመሥራት እንዲችሉ የሚያስፈልጉ፣ እንደ ተቅማጥ ያሉ እንሥሣትን እነዚህን ንጥረ ነገሮችን እንዲያጡ የሚያደርጉ በሽታዎችን ለማከም የሚሰጡ ንጥረ ነገሮች
ሃገር በቀል/Endemic: በአንድ ጂኦግራፊያዊ አካባቢ ወይም ሕዝብ ውስጥ የሚገኝ
ስር/Follicle: እያንዳንዷን ላባ የሚይዝ ከረጢት
ማንቁርት/Larynx: የአየር ቧንቧ የላይኛው ክፍል፣ የድምጽ ክሮች (vocal cords) ያሉበት ቦታ
የመታመም ምጣኔ/Morbidity (rate): ከእንሥሣዎቹ ውስጥ በበሽታ የሚጠቁት በመቶኛ
የመተንፈሻ/Respiratory: ከመተንፈሻ አካል ጋር ግንኙነት ያለው
ተጓዳኝ በሽታ/Secondary infection: አንድ ኢንፌክሽን ወይም በሽታ ህክምና እየተደረገለት ወይም ተደርጎለት እንዳበቃ ተከትሎ የሚመጣ ኢንፌክሽን
የአየር ቧንቧ/Trachea: የአየር ቧንቧ
ከባድ በሽታ አምጪ/Virulent: ከባድ የሆኑ የበሽታ ምልክቶችን ማምጣት የሚችል