የስንዴ ምርት ልምዶች ዙሪያ ላይ የተዘጋጀ የድህረ ታሪክ መነሻ

የሰብል ምርት

Script

መግቢያ

ይህ ርዕሰ ጉዳይ ለአድማጭች ያለው ጠቃሚነት ምንድን ነው?

ስንዴ እርሻቸው ጥሩ ምርት ማግኘት የሚፈልጉ አርሶ አደሮች ለያውቋቸው የሚገቡ፦

 • በቅድሚያ ዕቅድ ማቀድና የታቀደ የግብዓት ድልድል የማድረጉን ጠቀሜታ።
 • ግብዓቶችን ማደላደል ላይ ውሳኔ ማስተላለፍን ጨምሮ እቅድ አወጣጥ ላይ ሴቶችና መላው ቤተሰብን የማሳተፉ ጠቀሜታ።
 • የግብዓት (ማዳበሪያ፣ ፀረ-ተባይ፣ ዘር) እና ሜካናይዜሽን (ማረስ፣ የተጣመረ ሰብል አሰባሰብ) አገልግሎቶችን እንዴት ማግኘት እና መጠቀም እንደሚችሉ።
 • በትራክተር ማረስን እንዴት መተግበር እንደሚቻል፣ የተሻሻለ በበሬ የማረስ ትግበራን (በርከን ማረሻ እና አይባር ቢ.ቢ.ኤም በመጠቀም) ሰብል ማፈራረቅ (ለምሳሌ የጥራጥሬ ሰብሎችን በማፈራረቅ)፣ እና ምርታማነትን ለማሻሻል በመስመር መዝራት።
 • ቴክኖሎጂዎችን(የምክር አገልግሎቶች) እና ስለ ግብዓቶች ምንጭ መረጃዎችን እንዲሁም ከለርሻ ድህረ ገጽ ላይ የእርሻ ልምዳቸውን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ግብዓቶችን መሸመት።

አንዳንድ ቁልፍ መረጃዎች የትኞቹ ናቸው?

 • ለስንዴ እርሻ ትራክተር ሲጠቀሙ ቺዝል ማረሻን መጠቀሙ ይመከራል። ዲስክ ማረሻዎችን ሲጠቀሙ ዝቅተኛ ማርሽ መጠቀም ይኖርቦታል።
 • አርሶ አደሮች ስንዴን በረድፍ ብእጃቸው የሚዘሩ እንደሆነ በቁፋሮዎቹ መካከል ከ20-30 .ሜ ክፍተት ሊኖር ይገባል። በማሽን የሚዘራ ሲሆን በቁፋሮዎቹ መካከል 20 .ሜ ክፍተት መኖር አለበት።
 • አርሶ አደሮች በሄክታር መሬት ላይ በመስመር ለመዝራት 100-125 .
 • ዘር እና በስርጭት ለመዝራት ደግሞ 150 ኪሎ ግራም ዘር ያስፈልጋቸዋል።
 • በሄክታር የሚጠቀመው የማዳበሪያ መጠን የሚወሰነው የአፈሩን አይነት፣ የአፈሩን ለምነት፣ ቦታውን፣ የአይነት ብዛትን እና የማዳበሪያ አይነትን ከግንዛቤ በመክተት ነው።
 • ስንዴ ከበቀለ 25-30 ቀናት ውስጥና እና ከበቀለ በኋላ 40-45 ቀናት ውስጥ ሁለት ዙር አረም ያስፈልገዋል።
 • አርሶ አደሮች ስንዴን ከበሽታዎች ለመከላከል በየጊዜው መከታተል አለባቸው። ይህም በትክክል ተለይቶ በተገቢው ኬሚካሎች ወዲያውኑ ሊታከም ይገባል
 • አርሶ አደሮች ምርቱን ከመሰብሰባቸው በፊት በጥርስ ወይም በጥፍር በመጫን እየደረቀ ያለ ሰብል ተገቢውን የእርጥበት መጠን ማግኘቱን እንዴት እንደሚለይ ማወቅ አለባቸው። በመከር ወቅት የእርጥበት መጠን 16-18% መሆን አለበት። አዝመራው ከመወቃቱ በፊት አየር እንዲደርቅ መደረግ አለበት
 • መከር ከመጀመሩ በፊት ንጹህ እና ብቁ የሆኑ የማከማቻ ስፍራዎች መመቻቸት አለባቸው።
 • አርሶ አደሮች ኮምባይነሮችን የሚጠቀሙ ከሆነ በጥሩ ሁኔታ የሚሰሩ መሆናቸውን እና የሚያንቀሳቅሱ ባለሙያዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
 • የድህረምርት ብክነትን ለመቀነስ እህሎች ወይም ዘሮች ትክክለኛ የእርጥበት መጠን ሊኖራቸው ይገባልየዕህል ማከማቻ ቦታው ንጹህ መሆን አለበትእንዲሁም አርሶ አደሮች አይጦች እና ነፍሳቶች ላይ ቁጥጥር ማረግ ይኖርባቸዋል።
 • የማከማቻ ስፍራው ጥሩ የአየር ዝውውርእንዲኖረው ያስፈልጋል።
 • የስንዴ ምርትን ለማሻሻል ከባቄላና ሌሎች የቅባት እህሎች ጋር አያፈራረቁ መዝራቱ ጠቃሚ ነው።
 • ተስማሚ ዋጋን ለማግኘት አርሶ አደሮች አርሶ አደሮች የሰበሰቡትን እህል በማከማቸትና ተስማሚ ወቅትን ጠብቀው በመሸጥ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።

የስንዴ ምርትን ገብያ ላይ ከማቅረቡ ረገድ የሚታዩ ተግዳሮቶች ምንድናቸው?

 • መሬቱን ማመቻቸትና አፈሩ ትክክለኛ መጠን እርጥበት እንዳለው ማረጋገጥ።
 • ትክክለኛ ዝርያዎችና በቂ የዘር መጠን ማግኘት።
 • በመስመርመዝራትእናየሚፈለገውንዘርእናማዳበሪያመጠንእንዲሁምማዳበሪያንለመጠቀም አመችውን ወቅትመወሰን።
 • በትክክለኛው ወቅት አረምን ማረም።
 • የተለያዩ የስንዴ በሽታዎችን መከታተል፣ መለየትና መቆጣጠር።
 • የድህረ ምርት ብክነትን መቀነስ።
 • ገበያና ተስማሚ ዋጋ ማግኘት።

ስንዴን ማምረት ሥርዓተፆታ ገጽታዎች

 • በአለም አቀፍ ደረጃ ከተወሰኑ ስፍራዎች ውጭ፣ ሴቶች 43 በመቶ የሚሆነውን የግብርና ስራ ይሸፍናሉ።
 • ለስንዴ መሬትን በማዘጋጀት፣ በበሬ ማረስ እና ሌሎች ምርጫዎችን በሚመለከት ወንዶች የበላይ ሚና ይጫወታሉ።
 • ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች በዋነኝነት የሚሰማሩት አረም ማረምና ሰብል ስብሰባ ላይ ቢሆንም ጥረታቸው ግን እምብዛም እውቅና አይሰጠውም። ሴቶች ግብርና ላይ የሚጫወቱት ሚና ዕውቅና ስለማይሰጠው ሴቶች የመሬት፣ የካፒታል፣ የግብርና ግብአቶች፣ የብድር እና የኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን ጨምሮ የግብአት፣ ተደራሽነት እና ቁጥጥር ላይ ውስን እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
 • በኢትዮጵያ ስንዴ በመስመር ሲዘራ ማንኛውም የቤተሰብ አባል መዝራት ይችላል። በስርጭት የሚዘራ ከሆነ ግን በዋነኝነት ወንዶች ናቸው የሚዘሩት።
 • ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ስንዴ ለማምረት እና ለማስተዳደር በሚወስኑት ውሳኔዎች ላይ በሚሳተፉበት ጊዜ እንዲሁም ግብዓቶች እንዴት እንደሚመደቡ በሚወስኑበት ጊዜ፣ የሚያበረክቱት የሃሳብ ግብዓቶች ሁሉንም የምርት ማቀነባበሪያዎች፣ የግብይት እንዲሁም የፍጆታ ጉዳዮችን በትክክል ለማመዛዘን ይረዳሉ።
 • በማህበረሰብ ውስጥ አንደ ነውር ስለሚታይሴቶችበመስክላይእንዳይሰሩሊያደርጋቸውይችላል።በኢትዮጵያያሉአንዳንድማህበረሰቦችሴቶችመሬቱንቢያርሱዝናብአይዘንብም ብለውያምናሉ።በአብዛኛዎቹማህበረሰቦችውስጥየተከለከለባይሆንምአይበረታታም።
 • ኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች የሚመሩ ቤተሰቦች እንደ ብረት ሲሎስ ያሉ ትክክለኛ የማከማቻ ዕቃዎችን የመግዛት አቅሙ የላቸውም።
 • የፑርዱ የተሻሻሉ የሰብል ማከማቻ ከረጢቶች አቅርቦት እንዲሁም በአጠቃቀማቸው ላይ ስልጠና ከተሰጠ ሴቶች እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው የስንዴ አርሶ አደሮች ኪስን በማይጎዳ አልኩ ሰብላቸውን እንዲያከማቹ ያስችላቸዋል።
 • በኢትዮጵያወንዶችየተሻለመረጃየማግኘትእድላቸውበተለያዩሁኔታዎች ላይ የበላይነታቸውንያንጸባረቃል።

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ ቁጥር 1246፣ እና 7 ይመልከቱ።

ስንዴን ስለማምረት ቁልፍ መረጃዎች

አርሶ አደሮች ከሀገር ውስጥ የግብርና ባለሙያዎች ከሚሰጣቸው ምክር ጋር ጎን ለጎን የሚከተሉትን ተግባራት ከተጠቀሙ ምርትን ማሳደግ ይችላሉ።

የእርሻ መሬትን በበሬ እና/ወይም በትታክተር ማዘጋጀት

 • አርሶ አደሮች ለእርሻ በሬን የሚጠቀሙ እንደሆነ ባህላዊ ማረሻን በመጠቀም አራት ዙር ከሚያርሱ ይልቅ በርከን ማረሻን በመጠቀም 2 ዙር ብቻ እንዲያርሱ ይመከራል።
 • ለእርሻ ትራክተር የሚጠቀሙ ከሆነ ወደ አፈሩ ውስጥ በደንብ ዘልቆ እንዲገባ ከዲስክ ማረሻ ይልቅ ቺዝል ማረሻን እንዲጠቀሙ ይበረታታል።
 • መሬቱ እርጥበቱን ከማጣቱ በፊት ሰብል እንደተሰበሰበ ወዲያውኑ መታረስ አለበት። ሁለተኛ ዙር እርሻ መከናወን ያለበት የመጀመሪያው ዝናብ ከዘነበ በኋላና አፈሩ በውስጡ በቂ እርጥበት ሲኖረው ነው። ይህ አስተራረስ አረምን ለማስወገድ ይረዳል። እንደ አፈሩ ዓይነት፣ የዝናብ መጠን እና የአረሙ መጠን ላይ በመመርኮዝ ተጨማሪ እርሻ ሊከናወን ይችላል። የመጨረሻው ማረስ መከናወን ያለበት ልክ ዘር ከመዘራቱ በፊት ነው።
 • በጥልቀት ማረሱ ወደ አፈሩ ዘልቆ የሚገባውን የውሃ መጠን እንዲጨምር ከማረጉም በላይ የተሻለ ስርወ እድገትን ያመቻቻል።
 • በጥልቀት ለማረስ ትራክተሮችን መጠቀሙ ይበረታታል ምክንያቱም የስሮችን መብዛት በማገዝ ከፍተኛ መጠን ያለው ንጥረ ነገሮች እና ውሃ ወደ አፈሩ እንዲገቡና ምርታማነት እንዲጨምር ያደርጋሉ። ገልብጦ የሚያርስ ማረሻ ባለው ትራክተር የሚጠቀም በጥልቀት ይቆፍራል፣ በደንብ ያቀላቅላል፣ አብዛኛዎቹን የአረም ዘሮችን እንዲሁም ቀድመው እየበቀሉ ያሉ እንክርዳዶችን ይቀብራል።

የተሻሻሉ ዘሮች

 • ባለፉት አመታት ከመቶ በላይ ያሚሆኑ የስንዴ ዝርያ አይነቶች ተዘጋጅተዋል። ከቅርብ ወቅት ጀምሮ እየተሰራጩ የሚገኙት 33 የዳቦ ስንዴ ዝርያዎች እና 12 የዱረም ስንዴ* ዝርያዎች ይካተቱበታል።
 • በአርሲ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ ከሚውሉት የተሻሻሉ ዘሮች ለምሳሌ ኦጎልቾ፣ ዋኒ፣ ሂዳሴ፣ ኪንግበርድ፣ ዳንዳአ እና ሳናቴ ይገኙበታል።
 • ምርታማነትን ለቀንስ ስለሚችል የተሻሻሉ ዘሮችን ከሌሎች ዘሮች ጋር አይቀላቅሉ።
 • የሚፈለገው የዘር መጠን በተለያዩ ምክንያቶች ሊለያይ ስለሚችል ባለሙያዎችን ማማከር ያስፈልጋል።
 • የተሻሻሉ ዘርን በመስመር የሚዘሩ ከሆነ በሄክታር ከ100-125 .ግ የተሻሻሉ ዘሮችን ይዝሩ።
 • የተሻሻሉዘርየሚያቀርቡየእርሻአገልግሎትማዕከላት፣የዘርአምራችኅብረትሥራማህበራት፣የመንግሥትዘርኢንተርፕራይዞችእናየግልየዘርኩባንያዎችይገኙበታል።
 • በአካባቢ በቅርበት የሚገኙ የዘር ምንጮች ደግሞ የአርሶ አደሮች የራሳቸው ዘሮችና ሌሎች አርሶ አደሮች ናቸው።

ማዳበሪያዎች

 • የማዳበሪያው መጠን እንደየ አካባቢው፣ የአፈሩ አይነት፣ የአፈሩ እርጥበት፣ የአፈሩ ይዘት፣ የማዳበሪያው አይነት፣ ሰብል እና ልዩነት ይለያያል። ለምሳሌ በአፈሩ አይነት ላይ ተመርኩዞ የሚመከሩ ማዳበሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፦
  • ለቀላል አፈር፦ ለተክሉ ጥሩ ጅምር እንዲሆነው 100 ኪሎ ግራም ኤን.ፒ.ኤስ እና 67 ኪሎ ግራም (ወይም አንድ ሶስተኛ) ዩሪያን በመዝራት ላይ ይተግብሩ። ከተተከለ 30-35 ቀናት በኋላ 133 ኪሎ ግራም ዩሪያ ይጠቀሙ (መጀመሪያ ዙር አረም ከታረመ በኋላ)።
  • ለከባድ አፈር፦ በሚዘራበት ጊዜ 100 ኪሎ ግራም ኤን.ፒ.ኤስ እና 83 ኪሎ ግራም (ወይም አንድ ሶስተኛ) ዩሪያን ይጠቀሙ። ከተተከለ ከ30-35 ቀናት በኋላ (መጀመሪያ ዙር አረም ከታረመ በኋላ) 167 ኪሎ ግራም ዩሪያን ይጠቀሙ።
 • ሳይንሳዊ ምርምር የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ለምሳሌ ፍግ፣ ብስባሽ) መጠንን በሚመለከት ያስቀመጠው ነገር የለም። ለጊዜው አርሶ አደሩ 100 ኪሎ ግራምየተፈጥሮ ማዳበሪያን ከኬሚካል ማዳበሪያ ጋር አድርጎ መጠቀም ይችላል።

አረም ማረም

 • ትክክለኛ አስተራረስ አረሞችን ያስወግዳል።
 • ንጹህ እና ጤናማ ዘሮችን መጠቀም ሰብልን በመዝራት ወቅት አረምን አብሮ ከመዝራት ይታደጋል።
 • ሰብሉ በበቀለ ከ25-30 ባሉት ቀናቶች ውስጥ የመጀመሪያ ዙር አረም መታረም ሲኖርበት በጸደቀ 40-45 ቀናቶች ውስጥ ደግሞ ሁለተኛ ዙር አረም መታረም አለበት።
 • ስንዴን የማይጎዳ ተገቢ የሆነውን ፀረ አረም ይጠቀሙ። ፀረ አረሙን ከመጠቀምዎ በፊት ምን ጊዜም በሽፋኑ ላይ ያሉትን መመሪያዎች አንብበው ይተግብሩ።
 • ጸረ ተባይን ለመጠቀም በቂ ስልጠና ያለው ባለሙያ ቢሆን ይመከራል።

የስንዴ በሽታዎችና ተባዮች

 • የተለመዱ የስንዴ በሽታዎች መሃል ዋግ፣ ሴፕቶሪያ፣ ታን ስፖት፣ እና ስካብ ይገኙበታል።
 • ዋግ የሚያጠቃው የተክሉን ቅጠል፣ ግንድ እና ቡቃያዎችን ሲሆን ቀይ፣ ቡናማ እና ቢጫ ነጠብጣቦችን በቡቃያዎቹ አንደኛው ወይም በሁለቱም በኩል ላይ ይከስታል።
 • ሴፕቶሪያ የሚተላለፈው በበሽታው ከተጠቃ ዘር ሲሆን በቅጠሎቹ ላይ ነጠብጣቦችን ያስከስታል።
 • ታን ስፖት በቅጠሎች ላይ ቡናማ ነጠብጣቦችን ያስከስታል።
 • ክትትል እና ቅጥጥር ካርተደረገበት በሽታው ሙሉ ሰብሉን ሊያጠፋው ይችላል።
 • አርሶ አደሮች የተለየ የበሽታ ምልክት ባያገኙም በሳምንት አንዴ መከታተላቸውን መተው የለባቸውም። አርሶ አደሮች በሽታውን ያገኙ እንደሆነ ተጨማሪ የበሽታውን ምልክቶች ለመለየት በየቀኑ ክትትል ማድረግ ይኖርባቸዋል።
 • በሽታውን በትክክሉ መለየቱ አርሶ አደሮች ተገቢውን መድሃኒት ገዝተው እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል።
 • በንፋስ የሚዛመተውን የዋግ በሽታ ምልክት (ቢጫ ግንድ፣ ወይም ቅጠል ላይ ያለ ዋግ) ከመቶ በአምስት ቅጠሎች ላይ ያገኙ እንደሆን አርሶ አደሮች በፍጥነት በሽታውን ለመቆጣጠር መስራት ይኖርባቸዋል።
 • በሽታን የሚያስከትሉ ተህዋሲያን ካለፈው የእርሻ ወቅት በተበከሉ ዘሮች አማካኝነት ወይም ዕጽዋቶች በተለይ በእርሻው ላይ በሚበቅሉ ሳራማ አረሞች በኩል ሊተላለፉ ይችላሉ።
 • ከተለመዱ የስንዴ ተባዮች መካከል ክሽክሽ፣ መሰክ፣ እና ተምች ይገኙበታል።

ተባይ ቁጥጥር

ክሽክሽ

 • የመከላከልና የመቋቋም አቅም ያላቸውን ዝርያዎች ይጠቀሙ።
 • ወረርሽኙ ከባድ ከሆነ በተመከረው መጠን እና ጊዜ ፀረ ተባይ መድኃኒቶችን ይጠቀሙ።

መሰክ

 • መሰክ መከላከል የሚችሉ የስንዴ ዝርያዎችን ይጠቀሙ።
 • ሰብሎችን እያቀያየሩ ይዝሩ። ተባዮቹ በህይወት የሚቆዩት ስንዴና ገብስ በመመገብ በመሆኑ ከስንዴ በኋላ ሌላ አይነት ሰብል መዝራት የተባዮቹ ብዛት እንዲቀንስ ይረዳል።
 • ተባዮቹ ሰብሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የማድረስ አደጋን የሚጋርጡ እንደሆነ ዘሩን ከመዝራት በፊት እውቅና ባለውና በተመዘገበ የተባይ መድሃኒት ያክሙ።

ተምች

 • እንደ ወፎች፣ ጥንዚዛዎች፣ ተርቦች፣ የተወሰኑ የዝንብ አይነቶች ያሉ የተፈጥሮ አዳኞች ተምች ለማጥፋትና ተራብተው እንዳይባዙ ከፍተኛ አስተዋጾእ ያበረክታሉ።
 • በእርሻው ላይ እና በዙሪያው ያሉ ሳርማ አረሞችን በማስወገድ ወይም በመቆጣጠር ተምች ወረርሽኝ አደጋን መቀነስ ይቻላል።
 • አባጨጓሬዎች በጣም ብዙ ካልሆኑ በእጅ በመልቀም ሳሙና ያለው ውሃ ውስጥ ያስወግዱ
 • በመጀመሪያ ደረጃ ተምች ሊያስወግዱልን የሚችሉትን ከላይ የተጠቀሱትን ጠቃሚ የተፈጥሮ አዳኞችን ሊጎዳ የሚችል ጎጂ ጸረ ተባይ መድሃኒቶችን ከመጠቀም በተቻለን መታቀብ ይኖርብናል።

ጸረተባይ መጠቀም

 • የተቀናጀ የተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን (አይ..ኤም) ይጠቀሙ። ፀረተባይ መድሃኒቶች አስፈላጊ ሲሆኑ ብቻ ነው ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው
 • ኬሚካሎችን ለማከም መጠቀም ያለብዎት ኬሚካሎቹ ለታቀዱለት ሽታዎች እና ተባዮች ማከሚያነት ብቻ ነው።
 • ፀረተባይ መድሃኒቶችን በጣም አብዝቶ ወይም በጣም አሳንሶ መጠቀሙ በሽታውን ካለመቆጣጠሩም በላይ ስንዴው ላይ እንዲሁም የሰው ጤና እና አካባቢ ላይ ጉዳት ስላሚያደርስ ፀረተባይ መድሃኒት የአምራቾች የሚያስቀምጧቸው መመሪያዎችን በጥብቅ ይከተሉ።
 • የእራስዎ እና ቤተሰብዎ ጤና ላይ ሊከሰት የሚችል አደጋን ለመቀነስ ኬሚካሎችን በሚረጩበት ጊዜ እራስዎን ይጠብቁ። ርጭቱን የሚያከናውን ባለሙያ ሰው ይቅጠሩ።
 • የጸረ ተባይ መድሃኒት ርጭቱ ከተከናወነ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ በተጨማሪ መታከም ሊያስፈልገው ስለሚችል ሰብሉን በቅርበት ይከታተሉ።

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ ቁጥር 1289፣ እና 11ን ይመልከቱ።

በረድፍ መዝራት

 • በእጅ የሚዘራ ከሆነ በረድፎቹ መሃል ከ20 እስከ 30 .ሜ ክፍተት ሊኖር ይገባል እንዲሁም ዘሮቹ ከ3-4 .ሜ ጥልቀት ውስጥ ሊዘሩ ይገባል።
 • ማሽን በመጠቀም የሚዘሩ ከሆነ በረድፎቹ መሃል 20 .ሜ ክፍተት ሊኖር ይገባል እንዲሁም ዘሮቹ ከ3-4 .ሜ ጥልቀት ውስጥ ሊዘሩ ይገባል።

አለማየሁ የረድፍ አዘራር ቴክኖሎጂ (.አር.)

አለማየሁ የረድፍ አዘራር ቴክኖሎጂ ከመጠቀምዎ በፊት (ከስር ያለውን ምስል ይመልከቱ) መሬቱ በደንብ እንዲታረስና እንዲዘጋጅ ይመከራል።

አለማየሁ የረድፍ አዘራር ቴክኖሎጂ ሶስት አካላት አሉት:-

 1. ከታረሰ በኋላ እና የስንዴ ዘር ከማሰራጨቱ በፊት ሸንተረሮችን እና ቡርቡሮችን የሚያወጣ ረድፍ መስሪያ።
 2. ስንዴ እና ከስንዴ ነፃ የሆኑ መሬቶቹን ለመፍጠር የሚረዳ እና በረድፍ መዝራት የሚያስችል ልኬት ማውጫ።
 3. በረድፎቹ መካከል የሚበቅሉ አረሞችን የሚያጠፋ አካል።

ለረድፍ አዘራር የሚረዱ የአለማየሁየረድፍአዘራርቴክኖሎጂ ደረጃዎች፦

 • ረድፍ ያዘጋጁ (ሸንተረር እና መቦርቦር)
 • ዘሩን ያሰራጩ።
 • ስንዴ እና ከስንዴ ነፃ የሆኑ መሬቶቹን ለመፍጠር እንዲሁም በረድፍ መዝራት እንዲያስችል ልኬት ማውጫመለካት።

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 5ን ይመልከቱ

ሰብል ማፈራረቅ

ተባይና በሽታን ለመከላከልና ምርታማነትን ለማሻሻል አርሶ አደሮች ስንዴንና ባቄላን መቀያየር አለባቸው።

 • ሌሎች ከስንዴ ጋር መቀያየር የሚችሉ ሰብሎች አተር፣ ሽምብራ እና የተለያዩ የቅባት እህሎች ይገኙበታል።

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ ቁጥር 1 እና 2 ይመልከቱ።

የድህረመኸር ክንውኖች

የሚመከሩ የድህረ መኸር አሰራሮችን በመከተል ከምርት በኋላ የሚደርሰውን የስንዴ ብክነት በተለይ በኢትዮጵያ በአማካይ በሄክታር 5.6 ኩንታል (560 ኪሎ ግራም) ድረስ የሚደርስን ብክነት በእጅጉ መቀነስ ይቻላል።

ከምርት በኋላ የሚደርሰውን ኪሳራ ለመቀነስ አርሶ አደሮች የሚከተሉትን ተግባራት ምርጥ ተሞክሮዎች መጠቀም አለባቸው፦

መውቃት እና ማጽዳት

 • ሰብሉ በእርሻ አከባቢ ሳይወቃ በሚቆይበት ወቅት ለአይጥ፣ ለወፍ እና ለነፍሳት ጥቃት የተጋለጠ ስለሚሆን የምርት እና የጥራት ኪሳራን ለመቀነስ ሲባል ከመኸር በኋላ ወዲያውኑ መወቃት አለበት።
 • መውቃት በእጅ ወይም በእንስሳት (ዝግተኛ በሆነ ሂደት) ወይም በተንቀሳቃሽ መውቂያዎች እና ኮምባይነር በመጠቀም ሊከናወን ይችላል። ሜካናይዝድ መውቂያዎችን መጠቀም መዘግየቶችን ለማስወገድ ይረዳል።
 • ማበጠር፣ መልቀም/መንፋት ወቅት ጥሬውን በደንብ ማጽዳቱ ከተባዮች፣ ከሻጋታ እና ያልተፈለገ ጣዕም እና ቀለምን ከማምጣት ይከላከላል።

ማከማቻ

 • አየር የማያስገባ ማስቀመጫዎችን ይጠቀሙ።
 • የኬሚካል ጭስ ማሰራጫዎችን ማከማቻ ቦታዎች ላይ ይጠቀሙ ነገር ግን ይህን ሲጠቀሙ በዘር እና በሰው ጤና ላይ ጉዳት የማድረስ እድል እንደሚኖረው ይገንዘቡ። የሀን መንገድ መጠቀሙ ከጊዜ ቦኋላ ተባዮች ጸረ ተባዩን እንዲላመዱት ሊያደርጋቸውና ዳግመኛ ብክለትን ሊያስከስት ይችላል። እነዚህ አደጋዎች የበለጠ የሚባባሱት አርሶ አደሮች የመድኃኒት መጠን እና የመርጪያ ጊዜን ጨምሮ የሚመከረው የአተገባበር ስርዓት ላይ እውቀቱ ስለሌላቸው ነው።

መጓጓዣ

 • ጥሩ የመጓዣ መንገዶች መፍሰስና ብክለትን ይቀንሳሉ።
 • የእህል መበላሸት ወይም የመጥፋት እድልን ለመቀነስ በማጓጓዝ ወቅት ሰብሉ የሚጫንበት እና የሚወርድበትን ጊዜ ብዛት ይቀንሱ።
 • በሚጓጓዝበት ጊዜ መፋሰስን ለመከላከል ጥሩ ጥራት ያላቸውን ከረጢቶች ይጠቀሙ።

ለበለጠ መረጃ ሰነድ 10 እና 11ን ይመልከቱ

ድህረመኸርብክነትንመከላከል

የሚከተሉት ክንውኖች የድህረ-ማኸር ብክነትን ለመከላከል ይረዳሉ።

 • መረጃና ስልጠና የሚሰጥባቸው፦
  • ከአያር ንብረት ጋር መላመድ (በተለይ በመኸር ወቅት)
  • የእርጥበት መጠንን እንዴት መለካት እንደሚቻል፣
  • የተሻሻሉ የማከማቻ ስፍራዎችን መጠቀም (የብረት ሲሊሎ፣ አያር የማያስገቡ ከረጢቶች፣ የተሻሻሉ ባህላዊ ማከማቻ ስፍራዎች፣ ወዘተ…)
  • የተሻለ የማከማቸት ስልቶች (በማከማቸት ወቅት የተባይ መድሃኒት መጠቀምንም ያካትታል)፣ እና
  • ስለ ገበያ የተሻለ መረጃን ማግኘት።
 • የሴቶችን በእርሻ ላይ መሰማራት እንደ ነውር የሚያዩ አስተሳሰቦችን ድል መንሳት።
 • ትክክለኛ ማከማቻ የሌላቸው በእማወራዎች የሚመሩ ቤተሰቦችና አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ለመደገፍ ሲባል በአካባቢያቸው የሚገኙ ማከማቻዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ እንዲሁም ምርቶቻቸውን የገበያውን ሁኔታ ሳያጠኑ በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡና በአነስተኛ ዋጋ እንዲሸጡ አለማስገደድ።
 • በብድር እና በኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች አባልነት እና በአካባቢው የገበሬዎች ማህበራት አማካኝነት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የተሻሻሉ የማከማቻ ስልቶችን (ለምሳሌ የብረት ሲሎስ) ለመጠቀም ማበረታቻ እና ድጋፍ ማድረግ።

ለበለጠ መረጃ ሰነድ 4ን ይመልከቱ

ለርሻ

ለርሻ (https://www.lersha.com) በመረጃ መረብ ላይ የሚገኝ አነስተኛ አርሶ አደሮች የእርሻ ግብዓቶችን እንዲያዙ የሚያስችል እና የሜካናይዜሽን እና የምክር አገልግሎት በጥሪ ማእከላት፣ በለርሻ ወኪሎች ወይም በለርሻ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ በኩል እንዲጠይቁ የሚያስችል መድረክ ነው።

የለርሻ አተገባበር

 • የሰለጠኑ የለርሻ ወኪሎች በመንደሮች ወስጥ በአካል ይገኛሉ።
 • የጥሪ ማዕከሉ የአርሶ አደሮችን ጥሪ በመቀበል በተለያዩ ቋንቋዎች ያስተናግዳል።
 • የለርሻ መተግበሪያን በእጅ ስልካቸው በመጠቀም አርሶ አደሮች ግብዓቶችን ማዘዝ ይችላሉ።
 • አርሶ አደሮች እንደ ሜካናይዜሽን እና የምክር አገልግሎትን ለመገልገል ይችላሉ።
 • የእርሻ አገልግሎት ማእከላት አውታር የአርሶ አደሮችን ትዕዛዝ ተቀብሎ በሳምንት 7 ቀናት በቀን ለ24 ሰአት ያቀርባል።
 • በለርሻ በኩል አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን ለሽያጭ ማቅረብ ይችላሉ።
 • አርሶ አደሮች የለርሻን አገልግሎቶች ለመጠቀም ከመረጃ መረብ ወይም ከጥሪ ማእከላት፣ ከወኪሎች፣ እና የአቅርቦት አገልግሎቶች በኩል ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ www.lersha.com

የቃላት ፍቺዎች

ዱረም ስንዴ፦ ዱረም ስንዴ ፓስታ ወይም መኮረኒ ስንዴ በመባልም የሚታወቅ ሲሆን፣ በከፍታና መካከለኛ ከፍታ ቦታዎች ላይ የተዘራ እና ፓስታ ለማምረት የሚያገለግል ደረቅ ስንዴ ነው።

Acknowledgements

ምስጋና:

አዘጋጅ፦ አየነው ሃይለስላሴ፣ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሞያተኛ፣ ኢትዮጵያ

ሃያሲ፦ ዶ/ር ታደሰ ደሳለኝ፣ አማካሪ፣ የስንዴ እሴት ሰንሰለት፣ የግብርና ምርታማነት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም፣ ለግብርና እና ምግብ ዘርፍ የአረንጓዴ ፈጠራ ማዕከሎች- ኢትዮጵያ፣ ጂ.አይ.ዜድ

ይህ ስራ የአረንጓዴ ፈጠራ ማዕከልን ፕሮጀክት ለመተግበር .አይ.ዜድ በሰጠው ድጋፍ አማካኝነት የተዘጋጀ ነው።

Information sources

የመረጃ ምንጮች

 1. ጂ.አይ.ዜድ። ጥቅምት 2013። በአማራ ክልል ለስንዴና ባቄላ አምራች አካባቢዎች አፈራርቆ በማምረት ላይ የተመረኮዘ የተሻለ የእርሻ ስራ አተገባበር
 2. በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር። ስኔ 2010። የሰብል አመራረት ፓኬጅ
 3. Belay, F. and Oljira, A., 2016. Gender Role in Agricultural Activities in Ethiopia. Journal of Culture, Society, and Development, Volume 22. https://core.ac.uk/download/pdf/234691181.pdf
 4. Dessalegn, T., et al. 2017. Post-harvest wheat losses in Africa: An Ethiopian case study. In: Achieving sustainable cultivation of wheat, Volume 2 (pp.85-104). https://www.researchgate.net/publication/318879047_Post-harvest_wheat_losses_in_Africa_an_Ethiopian_case_study/link/59bf87d0458515e9cfd506d6/download
 5. Hirpa, D., et al. 2019. Evaluating the impacts of using Alemayehu row seeding technology (ART) on wheat production as compared to manual row seeding: the case of selected six Woredas of Arsi Zone.
 6. Kumar, D. and Kalita, P., 2017. Reducing Postharvest Losses during Storage of Grain Crops to Strengthen Food Security in Developing Countries. Foods, 6(1): 8. https://www.ncbi.nlm.nih.gov/pmc/articles/PMC5296677/
 7. Lersha website: www.lersha.com
 8. Atlaw, A., Kaske, K., and Haile, M, 2014. Wheat Production: Manual for Quality Seed Production. Ethiopian Institute for Agricultural Research. http://publication.eiar.gov.et:8080/xmlui/bitstream/handle/123456789/140/Wheat%20Manual.pdf?sequence=1&isAllowed=y
 9. Seyoum, A., 2019. Good Agricultural Practices (GAP) Intervention through Crop Rotation Based On-Farm Demonstrations (RoBOFD) in Arsi Zone.
 10. Federal Democratic Republic of Ethiopia Ministry of Agriculture, 2014. Wheat Sector Development Strategy (Working Document 2013-2017).