የቁም ከብት በሽታዎችን ስለመቆጣጠር አጠቃላይ መረጃ :- Coccidiosis በበጎች እና በፍየሎች

የእንስሳት እርባታ እና ንብ ማነብ

Script

መግቢያ

 

ርእሰ ጉዳዩ ለአድማጮቻችን ለምን ይጠቅማል?

 • አርሶ አደሮች ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ በሽታዎችን እንዴት እንደሚከላከሉ እንዲያውቁ
 • አርሶ አደሮች የኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ምልክቶችን ለይተው እንዲያውቁ
 • አርሶ አደሮች የቁም እንስሳት መጠላያዎችን በንጽህና አያያዝ ውጤታማ መንገዶችን እንዲለምዱ
 • አርሶ አደሮች ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ እንዴት እንደሚተላለፉ እንዲውቁ

ጥቂት ቁልፍ መረጃዎቸ?

 • ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ዶሮ ፣ ከብት፣ በግና ፍየልን የሚያጠቁ ዝርያቸው በተለያዩ እንስሳት መካከል ግን የማይተላለፉ በሽታዎች ናቸው
 • ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ እንደ መኖ፣ ውሃ፣ ፋንድያ እና ወተት በመሳሰሉ በተበከሉ ነገሮች አማካኝነት ይተላለፋሉ፡፡
 • አርሶ አደሮች የመመገቢያ እና የመጠጫ ገንዳዎችን በእንስሳቱ ሰገራ እንዳይበከሉ ከመሬት ከፍ ማድረግ አለባቸው
 • vእርጥብ እና ንጽሕናው ያልተጠበቀ ሁኔታ እንስሳቱን ለኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ስለሚያጋልጥ የእንስሳት መጠለያዎች ንጹሕና ደረቅ መሆን አለባቸው፡፡

በሽታዎቹን ለመቆጣጠር የሚያስቸግሩ ዋና ተግዳሮቶች ምነድን ናቸው?

 • አርሶ አደሮች በሽታዎችን ታክመው እንዲድኑ በሚያስችል ደረጃ ቀደም ብለው ለማወቅ ይቸገራሉ፤ ቢታወቁ እንደባለሙያ ምክር አንዳንድ ጊዜ በረጅም ሕክምና ሊፈወሱ ይችላሉ
 • በበሽታዎቹ የተያዙ እንስሳት ሁል ጊዜ ምልክት ስለማያሳዩ አርሶ አደሮች ህክምና ያስፈልጋቸው አንደሆነ ለማወቅ ይቸገራሉ
 • እንስሳት በሚቀመጡበት ቦታ አርሶ አደሮች የንጽሕና ሁኔታዎችን አለመጠበቅ
 • ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ን የሚያስተላለፉ ጥገኛ ሕዋሳት በሚገኙበት አካባቢ እንስሳት ለግጦሽ ሲወጡ
 • አርሶ አደሮች ከልክ በላይ ብዙ የቁም እንስሳት ሲኖሯቸው ለኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ጥገኛ ህዋሳት ሊጋለጡ የችላሉ፡፡
 • ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ የሚከላከል ክትባት አለመኖር፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 1፣ 2 እና 3ን አንብቡ፡፡

ኮክሲዲዮሲስን ለመቀጣጠር የሚረዳ ቁልፍ መረጃ

ይህ በሽታ የሚመጣው በጥገኛ ህዋሳት ሲሆን ዶሮ፣ ከብት እና እንደ በግና ፍየል ያሉ አነስተኛ አመንዣኪ እንስሳትን ያጠቃል፡፡ ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው እንስሳት ብቻ በራሳቸው ዝርያ መካከል በሽታውን ያስተላለፋሉ፡፡

በግና ፍየል

እንደ በግና ፍየል ያሉ ትናንሽ አመንዣኪ እንስሳት በአንጀት ኮክሲዲዮሲስ ይጠቃሉ፡፡ በሽታው ብዙውን ጊዜ ከ4-6 ወር ዕድሜ ያላቸውን ግልገሎች ያጠቃል፡፡ የአንጀት ሕዋሶቻቸውን በመግደል ምግብ ከሰውነታቸው እንዳይዋሃድ ያደርጋል፤ ይህም የደም ማነስ * ያመጣል፡፡

መተላለፍያው

 • በጠባብ ቦታ ብዙ በግና ፍየሎችን ማሳደግ ለኮክሲዲዮሲስ በሽታ አንዲጋለጡ ሊያደርግ ይችላል፡፡
 • ጡት ማስጣል፣ ከባድ የአየር ሁኔታ፣ የምግብ ለውጥ፣ እና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ የኮክሲዲዮሲስ በሽታ ስርጭት መጠን በበግና ፍየሎች መካከል ከፍ እንዲል ያደርጋል፡፡
 • የኮክሲዲዮሲስ ጥገኛ ሕዋሳት በሰገራ አማካኝነት ወደ ግልገሎች ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡
 • ኮክሲዲዮሲስ በተጨማሪ በቆሻሻ መኝታ፣ ንጽህናው ባልተጠበቅ መጠለያ እና በተበከለ ምግብ እና ውሃ አመካኝነት ሊተላለፍ ይችላል፡፡

ምልክቶች

 • ኮክሲዲዮሲስ ያለባቸው የበግና ፍየል ግልገሎች ውሃና ደም ሊያስቀምጣቸው ይችላል፡፡/li>
 • ኮክሲዲዮሲስ የያዛቸው በግና ፍየሎች ጸጉራቸው ጭብርር ይላል፡፡/li>
 • ግልገሎቹ እና ትላልቆቹም ደካማ ሊሆኑና ክብደት ብዙም ላይጨምሩ ይችላሉ፡፡

መከላከል

 • የበግና የፍየል ግልገሎችን በደረቅና ንጽህናው በተጠበቀ ሁኔታ በማሳደግ በበሽታ የመያዝ እድላቸውን ቀንሱ
 • ለግልገሎቹ አስፈላጊውን ምግብ አቅርቡላቸው
 • የበግና የፍየል ጉረኖዎችን በግፊት በሚወጣ የፈላ ውሃ እና ከተገኘ በአሞንያ ጋዝ በመጠቀም ከጀርም አጽዱ፡፡
 • የተለያየ እድሜ ያላቸውን ግልገሎች ለያይታችሁ አሳድጉ
 • የመኖ እና የውሃ ገንዳዎችን በሰገራ እንዳይበከሉ ከመሬት ከፍ አድርጉ
 • በcoccidiosis የመያዝ እድልን ለመቀነስ የግጦሽ ቦታ በፈረቃ ተጠቀሙ፡፡
 • የግልገሎቹ ቆዳ በሰገራ እዳይበከል ተከላከሉ፡፡
 • ሕክምና

 • የኮክሲዲዮሲስ በሽታ ምልክት ከታየ ሁሉንም ግልገሎች አክሙ
 • አርሶ አደሮች በበግና በፍየል የሚከሰተውን ኮክሲዲዮሲስ በሽታ ጸረ-ተህዋሲያን በሆነው ሞኔንሲን፣ ባክቴሪያ በሚገድለው ላሳሎሲድ እና ፕሮቶዞዋ በሚገድለው በዴኮኪኔት ማከም ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 1፣ 2 እና 3ን ተመልከቱ፡፡

ትርጉም
ደም ማነስ :- ይ ህ ሁኔታ የቀይ ደም ሕዋሳት ቁጥር ሲቀንስ ወይም ኦክስጅን የመሸከም አቅማቸው ሲቀንስ ይፈጠራል፡፡ ከባድ ደረጃ ሲደርስ ራስ ማዞር፣ ድካም እና እንቅልፍ እንቅልፍ ማለትን ያመጣል፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከየት ማግኘት እችላለሁ?

 1. Vorster, J.H., and Mapham, P.H., undated, Coccidiosis. http://www.cpdsolutions.co.za/Publications/article_uploads/COCCIDIOSIS.pdf (180 KB).
 2. Khodakaram‐Tafti, A., and Hashemnia, M., 2017. An overview of intestinal coccidiosis in sheep and goats. https://www.revmedvet.com/2017/RMV168_9_20.pdf (2.49 MB).
 3. University of Guelph, 2012. Control of Coccidiosis in Lambs and Kids. In Handbook for the Control of Internal Parasites of Sheep and Goats, pp 55-58. https://www.uoguelph.ca/~pmenzies/PDF/Handbook/Handbook_Coccidia_2012.pdf (246 KB).

Acknowledgements

Contributed by: James Karuga, Agricultural journalist, Kenya
Reviewed by: Sylviah Achieng
Adapted to the Ethiopian context by Dereje Fakadu, Senior Researcher in Animal Nutrition, Holetta Agricultural Research Center, Ethiopian Institute of Agricultural Research, Holetta, Ethiopia

This resource was supported by Elanco Animal Health. The translation of this resource was supported by the International Finance Corporation.