Radio spots on COVID-19 from your fellow broadcasters: Preventative measures, misinformation, vaccines, and the impacts of COVID-19

ጤናጤና

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

Save and edit this resource in Oromo

This series of spots was written by broadcasters at the Amhara Media Corporation, Oromia Broadcasting Network, and South Mass Media Agency in Ethiopia.

The spots have been edited for clarity and length. Take some time to review these spots and adapt them to your community’s context by:

  • Changing the names of the characters to local names.
  • Using familiar terms that are easily understood by your listeners (for example, your listeners may refer to COVID-19 by another name such as “COVID” or “corona”).
  • Ensuring that the information you share is consistent with advice from your local health authorities.

Remember: Information and messaging on COVID-19 information should not be limited to your station’s health program! You can easily and effectively promote COVID-19 vaccines by airing this series of 17 spots on many of your programs—including your news, music, business, sports, and religious programs—to reach as many listeners as possible.

Work with your colleagues to edit these spots so they match the different types of programs on your station. For example, some spots take place in a market, but could easily happen at a sports match or musical concert, in the office, in a farmer’s field, or at a place of worship.

To reach as many people as possible, translate these spots into the languages spoken by your listeners.

These spots are also available in English and Oromo. To access these translations, go to:
https://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/translations-available/

Script

 

Spot 1:
ጥንቃቄ የጎደለውንክኪ

 

SFX:
የመስኖዉሃ ድምፅ፡፡

አበበች:
በመስኖበሚለሙማሳቸውዉሃያጠጣሉ፡፡

ፋጤ:
እንደምን አለሽ አበበች የመስኖ ስራው በደምብ ይዘሽው የለ እንዴ፡፡

አበበች:
እንደምን አለሽ ፋጤ፤ እንዴታ ጠፋሽሳ ነይ እስኪ ሳሚኝ፡፡

ፋጤ:
እረሳሽውእንዴ፣መሳሳም፣መጫባበጥናመነካካትእኮለኮረናያጋልጣልተብለዋል፡፡

አበበች:
አረ ተይኝ እቴ ሰው እንዴት ነው ወዳጁንና ወገኑን ከመጨባበጥና ከመሰሳም ተከልክሎ የሚኖረው መቼስ ነው እንምንገላገለው ከዚህ ችግር፡፡

በይበይለቤተሰባችንምለራሳችንምስንልመጠንቀቅይኖርብናል፡፡

መውጫ:
መጨባበጥና በአጠቃላይጥንቃቄ የጎደለውመነካካት ለኮረና ሊያጋልጥ ስለሚችል ጥንቀቄእናድርግ፡፡

 

 


 

Spot 2:
አካላዊ ርቀት

 

አቶ ለሜሳ:
እንዴት ነህ ወዳጄ፡፡

አቶ ከበደ:
አምላክ ይመስግን ደህና ነኝ፡፡

አቶ ለሜሳ:
ምነው ራቅ አልከኝ ጠጋም አትለኝም እንዴ፡፡

አቶ ከበደ:
አሃ እሱማ ኮቪድ ከመጣ ወዲህ ቀረ እኮ፡፡

አቶ ለሜሳ:
አልተረሳም እንዴ እሱ ነገር፡፡

አቶ ከበደ:
አረ ስንቱ እየተጎዳ ነው፤ ይኼ እስኪጠፋ ድረስ ፍቅራችን በልባችን አደርገን ሰላምታችን እንለዋወጥ፡፡

መውጫ:
አካላዊ ርቀትዎን በሁለት የአዋቂእርምጃ በመጠበቅ ራስችንንም ሆነ ቤተሰባችንን ከኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ እንጠብቅይህ፡፡

 


 

Spot 3
: የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ

 

አቶ ጫላ:
አቶ ደሴን ወደየት እየሄድክ ነው፡፡

አቶ ደሴ:
በቀበሌው በቲማቲም ምርት ላይ በተዘጋጀው የመስክ በዓል ቀን ልሳተፍ ነው ፡፡

አቶ ጫላ:
በል እንሂድ እኔም ወደዛው ነኝ፡፡ በል እንግዲህ ከሰው ጋር ስለምንቀላቀል መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

አቶ ደሴ:
አሁንእኮደህናነውየጠፋመስሎኝ፡፡

አቶ ጫላ:
ኤሄሄ መቼ ኮረና ጠፋና እንዲያውም ብዙ ሰው እየተያዘ ነው ወዳጄ፡፡

መውጫ:
በማንኛውምጊዜናቦታየአፍናየአፍንጫመሸፈኛማደረግኮረናንለመከላከልያስችላል፡፡

 


 

Spot 4:
የእጅ ንጽህና መጠበቅ

 

ተራኪ:
ንጹህ ባልሆነ እጅ ዓይን፣ አፍና አፍንጫችንን በመነካካት በቀላሉ ለኮረና ባይረስልንጋለጥ እንችላለን፡፡

እጃችንንበውሃናሳሙናአዘወትረንእንታጠብ፡፡

ውሃናሳሙናበማይኖርበትጊዜየእጅማጽጃፈሳሾችንእንጠቀም፡፡በአቅራቢያችንየሚገኙየንጽህናመጠበቂያአማራጮችበመጠቀምእጃችንንእናጽዳ፡፡

 


 

Spot 5:
ማስክ ማድረግ

 

በለጠ:
አስራት ሰላም ነህ ወደየት እየሄድክ ነው፡፡ (መንገድ ላይ … የመንገድ ላይ ድምፆች ይካተታሉ)

አስራት:
እንዴ እንዴት ነህ፡፡ እዚሁ ፀሎት ላደርግ እየሄድኩ ነው፡፡

በለጠ:
ምነው ታዲያ ማስክ አድርገህ?

አስረት:
እንዴ ምነው ችግር አለው እንዴ?

በለጠ:
አይይ ብዙ ሰው ስለማያደርግ እንዲያው ሰው እንዳይታዘብህ ብዬ ነው ማስክ ማድረግህን ሲያዩ …

አስራት:
ማስክ በማድረጌ እንዴት ሊታዘበኝ ይችላል … ደግሞ ለምን ይታዘበኛል ብለህ ነው፡፡

በለጠ:
አይ እንዲያው ምትታመንበት አምላክ ከዚህ ከተራ በሽታ አይደለም ከሌላስ ይጠብቅ የለም እንዴ ብዬ ነው …

አስራት:
ምን ነካህ ፈጣሪ እኮ ምታምኑብኝ ከሆነ አትጠንቀቁ አላለም፡፡ ባለመጠንቀቅስ ፈጣሪን ለምን በከንቱ እፈታተነዋለሁ፡፡ በሰጠኝ ዕውቀትና ጥበብ ራሴን ከክፉ መጠበቅ ግዴታም አለብኝ እኮ፡፡ያንግዜ ፈጣሪም ይረዳኛል፡፡

ስለዚህየጤናባለሙያዎችንትዕዛዝተከትዬለራሴምለሌለውምስልእጠነቀቃለሁ፡፡

መውጫ:
የኮሮና የጥንቃቄመከላከያ መንገዶችን መተግበር ከእምነት አስተምህሮጋር ፈፅሞ የሚጋጭአይደለም፡፡

 


 

 

Spot 6:
የጉንፋንና መሰል ምልክቶች ከታዩ ከሌሎች ሰዎች መራቅና እየተባባሰ ከመጣ ወደ ሕክምና ማዕከላት መሄድ

 

አቶ
በለው:
ያስላል፣ ያቃስታል፡፡

አቶ
አደም:
ደህና ነህ አቶ በለው ምነው አመመህ እንዴ፡፡

አቶ
በለው:
አረ ተወኝማ ወንደሜ ይኸው ትኩሳቱን አልቻልኩትም፣ ያስለኛል፣ ራሴን ያመኛል፣ ይቆረጥመኛል፡፡

አቶ
አደም:
አረ ያ የዘመኑ (ኮረና) እንዳይሆን፡፡

አቶ
በለው:
ምን አውቄ አንተው፡፡

መውጫ:
ራስህመም፣ ድካም፣ትኩሳት፣ ሳልናቁርጥማትካለዎት፣ የኮረናምልክቶችሊሆኑስለሚችሉወደሌሎችእንዳያስተላልፉአፍናአፍንጫይሸፍኑ፣ራስዎንከሌሎችያርቁበቤትዎይቆዩእረፍትያድርጉ፡፡ወደጤናተቋምበመሄድምርመራያድርጉ፡፡

 


 

Spot 7:
ክትባት

 

ሚስት:
ሳልታስላለች፡፡

ባል:
ምድነው እሄ ሳል፣ ተደጋገመብሽ አኮ፡፡

ሚስት:
(ሳል) ምን አንደሆንኩ አላቅም (ሳል) በርትቶብኛል፡፡

ባል:
በይ ይሄ የኮሮና ምልክት ሊሆን ይችላል፣ ቶሎ አንመርመር፡፡ እኔ አላማረኝም ፡፡

ተራኪ:
የምርመራውዉጤትተነገራቸው፡፡ከምርመርበሁዋላኮቪድተገኘባቸው፡፡

ባል:
ይሄዋ የኔ ውድ፣ያልኩት ደረሰ፡፡ አኔ የተከተብኩ ጊዜ አብረን አነከተብ ስልሽ ቸል ማለትሽ አኮ ነው፡፡ ብትክተቢ ኖሮ ይሄ ሁሉ ሳል አይበረታብሽም ነበር፡፡ አንደኔ አልጠናብሽም ነበር፡፡

ሚስት:
ሳልሳል፡ምነዋአብዬአጎናፍርአንዲሁኮረናተብሎአንድሁለትቀንአስሎአቸውቢተዋቸውተዘናጋሁ፡፡አንደውሞኝነተነውፈጣሪይማረኝአንጂስድንሶስትወርሲሞላኝወደጤናጣቢያሄጄክትባቱንወስዳለው፡፡

መውጫ:
የኮሮና ቫይረስ ክትባትን መከተብ ህመሙ እንዳይፀናብንና ለሆስፒታል እንደንዳረግ ያደርጋል፡፡

 


 

Spot 8:
ሁለተኛ ዙር ክትባትን

 

ሰው 1:
አያ ገብረ አንዴት ሰነበትክ፡፡

ሰው 2:
አንዴት ሰነበትክ አቶ ገምዙ፡፡

ሰው 1:
ሰሞኑን የት ጠፋህሳ፡፡

ሰው 2:
ከልጄ ዘንድ ወርጄ አዛው ዋል አደር አልኩኝ፡፡

ሰው 1:
አኔ ምልህ፣ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ክትባታችንን ዘነጋሄው አንዴ፡፡ ባለፈው ሐሙስ አኮ ነበር ጤና ጣቢያ የቀጠሩን፡፡

ሰው 2:
አይይይ የኔ ነገር ለካ ሁለተኛ ዙር ስቱወስዱ ነው የተሟላ ክትባት የሚባለው ብለው አስረድተውን ነበር፡፡ግድ የለም ሰሞኑም ሂደን አነከተባለን፡፡

ሰው 1:
አረ ሰሞኑን አትበል አያ ገብሩ፣ ለምን ነገ ማልደን አንዘልቅም?

ሰው 2:
አንገዲያውስ ባልተቤቴንም ልጄንም እነግራቸውና ደርሰን አንመጣለን፡፡

ሰው 1:
አንደውም ነገ የተፋሰስ ልማት ስራ ስልጠና በሁዋላ ወደ ክትባቱ አንሂድ፡፡

ሰው 2:
አሱስ አኔም ይመቸኛል፡፡ ዋናው ጤና አደል?

መውጫ:
ለሁለተኛ ዙር ክትባት ቀጠሮ የተሰጠንሁሉ በቀተሮአቺን ቀን ሄደን እንከተብ፡፡

 


 

Spot 9:
የተሳሳቱ አመለካከቶች

 

ሴት1:
አማዋይ እኔ ምልሽ፣ የዘመኑን በሽታ ለመከላከል አጃችሁን ታጠቡ፣ አንድ ላይ አትሰባሰቡ የሚሉት አሁንም አለ ይሆን? ወይስ መላ ተገኘለት፣ ሰምተሻል?

ሰው2:
ኮሮና ማለትሽ ነው ሺታዬ፡፡ አሱንማ ምነው ክትባቱ ይከላከላል አየተባል አደል አንዴ፣ ክትባት መጥተዋል አኮ፡፡

ሴት1:
የምን ክትባት አመጣሺብኝ እቴ ፣ ለሱማ መድሃኒቱ ተገኝቶለታል፡፡ አገር በቀሉ መድሃኒታችን የት ሄዶ፡፡ ፈጦዋን፣ ዝንጅብሏን፣ ነጭ ሽንኩርቷን መውሰዱ ፍቱን ነው፡፡

ሴት2:
እና ክትባቱ ይቅርብን ነው ምተይው ሺታዬ፡፡

ጤና
ባለሞያ:
ደሕና ዋላችሁ አማ ሺታዬ፣ ምን አያወጋቺሁ ነው?

ሰው2:
አይይ አንደው ኮሮና ነው ምንድነው ስለምትሉት በሽታ አያወጋን ነው፡፡

ጤና
ባለሞያ:
ጎሽ መወያየታቺሁማ መልካም ነው፡፡ ባህላዊ ምግቦቺን መጠቀማቺሁ ክፋት የለውም፡፡ ግን ደግሞ ክትባቱ የተሻለው አማራጭ ነው፡፡ በየአካባቢው ተከተቡ አየተባለ ስለሆነ፣ ዛሬ ነገ ሳትሉ ከነቤተሰቦቻችሁ የክትባቱ ተጠቃሚ ሁኑ፡፡

ሴት1:
ደህና ደህና፣ ከባለቤቴ ጋር ተማክሬን አንከተባለን፡፡

መዝጊያ:
በሌሎቸም የ ኮቪድ መከላከያ መንገዶች ላይ ማስታወስ ባህላዊ ሕክምና፡፡

ወይዘሮሽ X :
ለኮሮና መድሃኒት ምን ልጠቀም አባክሽ?

ወይዘሮ1:
ሎሚ በዝንጅብል አርገሽ ከመተኛትሽ በፊት ጠጭበት ወልቅ ብሎ ነው ምጠፋው፡፡

ወይዘሮ2:
ዳማከሴ በኑግ ቸፍጭፈሽ ጠጭበት፣ በንጋታው ሌላ ሰው ሆነሽ ነው ምትነሽው፡፡

ወይዘሮ3:
አንዴ፣ አድሜ ለነጭ ሽንኩርት፣ ከትንሽ ማር ጋር ከላቅለሽህ ዋጭበት፣ ድራሹን ነው ምያጠፋው፡፡

ወይዘሮ4:
ትኩስ ቡና በ ቂቤ አርገሽ ጠጭበት፣ ፍቱን ነው እሱ፡፡

የጤና
ባለሞያ:
ኮሮና ቫይረስ በሃኒት የለውም፡፡ ባህላዊ መንገድ አስካልጎዳን ድረስ መጠቀሙ ችግር የለውም፡፡ ሆኖም ኮቪድን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው፡፡

መውጫ:
ያልተረጋገጡመላ ምቶቺን ተከትለን ከምንሳሳት በባለሞያ የሚ መከሩ ሃሳቦችን በትክክል በመተግበር አራሳችንን አና ቤተሰቦቻችንን ከኮቪድወረርሺኝ አንከላከል፡፡

 


 

Spot 10:
ከክትባት በሁዋላም ማስክ ማድረግ

 

SFX:
የመንገድ ላይ ጫጫታ፣ የታክሲ ጥሪ፡፡

የማስክ
ነጋዴ:
ማስክ ማስክ፡፡

ተሳፋሪ1:
ታክሲ ውስጥ ያስለዋል፡፡

ተሳፋሪ2:
ምነው አባ ማስክ አድርግ አንጂ፣ አንዴት ያለማስክ ትሳፈራለህ፡፡ አንኩዋን ታክስ ውሥጥ የትም አኮ ማረግ ይኖርብናል፡፡

ተሳፋሪ1:
አይይ እኔ እንኳን በሁለት ዙር የተሰጠውን ክትባት ወስጃለው ፡፡ ብዙ አያሳስበኝም፡፡

ተሳፋሪ2:
አኔ ባጋጣሚ የጤና ባለሞያ ነኝ አንኳን ተገናኝን፡፡

ተሳፋሪ1:
እንዴት?

ተሳፋሪ2:
የኮቪድ 19 ክትባትን መውሰድ ማለት አኮ በቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ አንያዝም፣ ወደሌሎችም አናስተላልፍም ማለት አደለም፡፡ እናም በየትኛውም ቦታ ስንገኝ አንደ ማንኛውም ሰው ማስክ ማረግ አለብህ፡፡ አንተም ሁለተኛ የላማስክ አትሂድ፡፡

ተሳፋሪ1:
አሺበጣምአመሰግናለው፡፡ተከትበያለሁናበኮሮናአልያዝምወደሌሎችምአናስተላልፍምማለትየተሳሳተአመለካከትነው፡፡ማስክእንጠቀም፣በባለሞያዎችየሚሰጡትንምክሮችናጥንቃቀዎችምተግባራዊአናድርግ፡፡

 


 

Spot 11:
የተሳሳተ የማስክ አጠቃቀም

 

ሰው1:
እትዬ አስካለ እንዴት ሰነበትሽ፣ ምነው በገበያ ቀን እንደኔው አረፋፈድሽ፡፡

ሰው2:
እንዴት ነሽ አየሉ፣ ምኑን ከምኑ ላድርገው ብለሽ አንዱን ሳወጣ አንዱን ሳወርድ እንዲሁ ይረፍድ የለ፡፡

ሰው1:
ይሁን ይሁን ደግነቱ ዛሬ ይቺ የመንደራችን ኩር ኩር አላመለጠችንም፡፡

ሰው2:
እኔ የምልሽ አየሉ አረ ወደ ገበያ ተሳፍራችሁ በምትሄዱበት ጊዜም ሆነ በምትገበያዩበት ጊዜ አፍና አፍንጫችሁን መሸፈን አትዘንጉ እየተባለ ነው፡፡ኮረና የሚሉት እኮ አሁንም አልጠፋም፡፡

ሰው1:
አረ ተይኝ እቴ፣ መቼ ይሆን ከስጋት የምንገላገል? ግን ደግሞ አንዳንዱ ሰው የሚመከረውን ከልቡ ያደመጠ አይመስልም፡፡

ሰው2:
አንዴት በዪ፡፡

ሰው1:
ማስክ ነው ምን የምትሉትን አንዳንዱ እኮ ለስሙ ነው ከጆሮው የሚያደርገው፣ ሌላውም ካንገቱ ስር ነው የሚለጥፈው፡፡ይሄው እዚህ ከተሳፈርነው ውስጥ እንኳን ተመልከቺ፡፡

ሰው1:
ግዴለም በኛ በኩል ሰው ስለተሳሳተ መሳሳት የለብንም ስንጎጎዝም ሆነ በገበያ ቦታ ስንገኘ ማስኩን፣ ካልሆነ ደግሞ ያንገት ልብስ በመሀረብም ሆነ ፎጣ መሸፈን እንዳለብን የጤና ባለሙያዎቹ መክረውናል፡፡

ሰው2:
እውነት ብለሻል፣ በጀ፡፡

መውጫ:
አፍና አፍንጫችንን በአግባቡ በመሸፈን ከኮረና ወረርሽኝ ራሳችንንና ቤተሰቦቻችን እንጠብቅ፡፡

 


 

Spot 12:
አላስፈላጊ ጥግጊት

 

መግቢያ:
ሲሳሳሙ ወይም በመሳሳም ሰላምታ ሲለዋወጡ (እሙፓ እሙፓ)፡፡

ካራክተር 1ና2:
ሰላምታ ይለዋወጣሉ፡፡ (chorus)

አቶ ከበደ:
የፈጣሪ ያለህ፡፡ እናንተ ምን መሆናችሁ; ምን እያደረጋችሁ ነው፡፡ እንዴ በዚህ ኮሮና ባለበት ዘመን እንዲህ ያለ ሰላምታ ምን ይሉታል; ኮሮና በመነካከትና በትንፋሽ የሚተላለፍ በሽታ መሆኑን ዘነጋችሁት እና ነው፡፡

ካራክተር1:
ጋሼ ምነው መዓት የሚጠሩብን፡፡ስለምን ኮሮና ነው ሚያወሩብን? እኛ ጋ ኮሮና የለም፣ ጠፍቷል፡፡

ካራክተር2:
ኮሮና ቢኖርም እኛን ፈጣሪ ስለሚጠብቀን ግድ የለም ለኛ አያስቡ ፡፡

ጋሼ:
እናንተን አሊያዝምና ጠፍቷል ልትሉ እንደም ደፈራችሁ? የእድራችን ዳኛ … የመስጂዳችን ሼህ ባለቤት … ያ እወንዝ ማዶ ያለው ታጣቂው ልጅስ ቢሆን የገደላቸው ምን ሆነና፡፡ ለራሳችሁ ባታስቡ ለቤተሰቦቻችሁና ለወዳጆቻችሁ አስቡ እንጂ፡፡ ኮሮና አልጠፋም ተብሎ ሚለፈፈውን አትሰሙም፡፡ ተው እንጂ ልጆቼ! ተው ግድ የላችሁም፡፡ መጠንቀቅ ደግ ነው፡፡

መውጫ:
አንዳንዴ እያወቅን በድፍረት የምንሰራቸውጊዜውን ያልዋጁ ድርጊ ቶች መዘ ዛቸው ይከፋል ይሆናል፡፡ ለፍቅር የሳምነውንወዳጃችንን ለበሽታእንዳንዳርገው እንጠንቀቅ፡፡ኮሮናን በጋራ እንከላከል፡፡

 


 

Spot 13:
አባቶቻችንን የሚያሳጣ በሽታ ነው

 

ውድነሽ:
ውይ ውይ ውይ … የእድራችን ዳኛ አረፉ?!፡፡ ጉድ ጉድ ጉድ ነው ዘንድሮስ፡፡

ብሪቱ:
ውድነሽ ምንድነው? የምን ሞት ነው ምታወሪው??

ማርታ:
የእድራችን ዳኛ አረፉ እኮነው ምትለው፡፡

ብሪቱ:
ውይ ውይ በሞትኩት … ምነው? ምን አገኛቸው፤ እንዴ ባለፈው ሳምንት የደርቤ ሰርግ ላይ ሽማግሌም አልነበሩ እንዴ፡፡ ያኔ ሳያቸው ደህና ናቸው፡፡

ውድነሽ:
እኛስ መች ገምተን፡፡ ይህ መከረኛ ኮሮና ነው አሉኝ፡፡ ወይኔ ወይኔ!

ማርታ:
አይ ፈጣሪ ምን ዓይነት በሽታ መጣብን ደግሞ፤ መካሪና ዘካሪዎቻችንን የሚነጥቅ፡፡ አቤት ጉድ፤ፈጣሪ አንተ ጠብቀን፡፡

ብሪቱ:
ለወጣቱስ፣ለልጆችስ፣ለእኛስቢሆንካልተጠነቀቅንመችይመለሳልብለሽነው፡፡እኛምተጠንቀቁሲባልአልሰማአልና፣አልሰማአልን፡፡ማነሽትንሽዋ(አቤትእማየሚልየሴትድምፅይኖራል) ነጠላዬንአቀብይኝእስኪ፡፡

መውጫ:
የኮሮና ቫይረስ ዕድሜና ፆታን የማይለይ … መካሪ … ዘካሪ … ተቆጪና አስታራቂ፣ እንዲሁም አዛንውቶቻችንንና እህት ወንድሞቻችንን የሚያሳጣ ገዳይ በሽታ መሆን አውቀን መጠንቀቅ የብልህነት መገለጫ ነው፡፡

 


 

Spot 14:
ተጋላጭነት ኖሯቸው ምልክት ባለማሳየት የሚያስተላልፉት በሽታ ነው፡፡

 

ግርማ:
አንተ … ተፈራ የኮሮና ቫይረስ ተያዘ የሚባለው እውነት ነው??

ብርሀኑ:
አዎ ባክህ፡፡ ደግሞ እኮ እሱ ብቻ አይደለም ወንድሙም ተይዟል፡፡

ግርማ:
ማን ሀይሉ …

ብርሀኑ:
አዎ፡፡

ግርማ:
እንዴ ምን እያልክ ነው… ትናንት ቀን ሙሉ አብረን ነበረ ያሳለፍነው፡፡ እንዲያውም ዛሬም አብረን ነበርን፡፡ እንዴት አልነገረኝም፡፡

ብርሀኑ:
እሱሆዬምልክቱስላልታየበትአልያዘኝምአያለያስወራልአሉ፡፡ደግሞምእኮጭራሽከሁሉምጋርሲጨባበጥናሲነካካነውእሚውለው፡፡

ብርሃኑ:
ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱን የሚያስተላልፉ ብዙዎች ናቸው እየተባለ …

ግርማ:
በል ከሱ ጋር ስለተነካካህ ወንድዓለም ሁለታችንም መመርመር ይኖርብናል፡፡ በል ተነስ ተመርምሮ አስፈላጊውን ጥንቃቄ መድረግ ለሌላውም መጠንቀቅ ነውና ወደ ጤና ተቋም፡፡

መውጫ:
በኮሮና ቫይርስ የተያዘ ሰው ጋር የተገናኘ ሰው ምልክቱ ባይታይበትም በቫይረሱ የመያዝ እድልዎ ሰፊ ስለሚሆንና ወደሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ስለሚችሉ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በማምራት መመርመርና መጠንቀቅ ይኖርብዎታል፡፡

 


 

Spot 15:
ኮሮና ቫይረስ ቤተሰብ እንደሚበትን

 

መግቢያ:
የለቅሶ ድምፅ፡፡

አበበ:
ምንዓይነትጊዜነውእናንተዬ … የዛሬዓመትከመንፈቅነውአይደልእንዴ … ሚስታቸውንበዚሁወርርሽኝያጡት፡፡ይኸውደግሞልጆቹንአሳዳጊአሳጣቸው፡፡

መከተ:
እኔ የምልህ አበበ እንደው ቤተዘመድም አላቸው ይሆን …

አበበ:
እኔምያሳሰበኝይኸውአይደል፡፡ቤቱመፍረሱነው፡፡እኚህምልጆችሜዳላይመውደቃቸውነው፡፡ለቤተሰብዎደህንነትናአብሮነትሲሉራስዎንከኮሮናቫይረስይጠብቁ፡፡ይጠንቀቁ፡፡

 


 

Spot 16:
አቶ መብራቱ በተደጋጋሚ ያስላቸዋል፡፡

 

SFX:
አቶ መብራቱ በተደጋጋሚያስላቸዋል፡፡

ኢያሱ:
አቶ መብራቱ ምንድነው? ከሃኪም ቤት እሚወስድ ሳይሆን አይቀርም፡፡

መብራቱ:
አይይ እንዲሁ የሰሞኑ ቅዝቃዜ ይሆናል፡፡ ሚቆረጣመኝም ድካም ድካም የሚለኝ፡፡

ኢያሱ:
እንጃ አይመስለኝም፡፡ ሰሞንኛው ወረርሺኝም እንዲህ ነው ሚያደርገው ብለው ሀኪሞች ሲሉን አልነበረም እንዴ፡፡ ለእኔ ግን ከሀኪም ዘንድ ብትሄድ ሚበጅህ ይመስለኛል፡፡

መብራቱ:
እህህህ ( … ማቃሰት ያለበት … ) እሱው ይሆን እንዴ አነተዬ? ብታይ ቁርጥማቱ … ትኩሳቱ … አቤት ራስምታቱስ ብትል ጭንቅላቴን ሊያፈነዳው ምን ቀረው፡፡ ደግሞ ሳልና ማስነጠሱ ሳይንስ መንፈቅ ሙሉ ያረሰ ይመስል ድካሙ ብርክ ያስይዛል …

መውጫ:
ትኩሳት፣ተደጋጋሚማሳልማስነጠስ፡ራስምታትየድካምስሜት፡እንዲሁምየመገጣጠሚያህመምስሜትየኮሮናቫይረስምልክቶች፡

 


 

Spot 17:
የገጠሩ ማህበረሰብ የእጁን ንፅህና በመጠበቅ ራሱን ከኮቪድ 19 ይከላከላል

 

ተራኪ:
ከዘመናት ቀደም ብሎ … ባባቶቻችን ተረቅቆ የጀመረ ድንቅ እሴት ያለን … እጃችን ከማሳው መዳፋችን ከእርፍኙ አርፎ ሲመለስ …

በውሃተዳብሶበእጅተዳስሶበእንዶዱም፣በዘመኔውሳሙናምታሽቶናተፈትጎበንፅህናገበታእምንቀርብ …

ለአብሮነታችንክብርያደፈእጃችንንለወዳጅየማንዘረጋ … ከዚያይልቅእጅየምንነሳድንቅህዝቦችነን፡፡እጅንበማፅዳትእጅንምበመንሳትህይወትእንታደጋለን፡፡

መውጫ:
ኮሮና ቫይረስ ንፅህና ባልጠበቀ እጅና በአካል ንክኪ የሚተላለፍበሽታ በመሆኑ የእጃችንን ንፅህና በመጠበቅ መከላከል እንችላለን!!

 


 

Acknowledgements

Contributed by: Broadcasters at Amhara Media Corporation, Oromia Broadcasting Network, and South Mass Media Agency.

This resource is funded by funded by the Participatory Small-scale Irrigation Development Programme II of the International Fund for Agricultural Development as part of the Interactive Radio for Providing Response and Building Resilience of Farming Communities on COVID-19 (IPRFC) project.