ምግብን ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ማቆየት

የድህረ-መከር እንቅስቃሴዎችግብርና

Script

መግቢያ:

በኮቪድ-19 የተነሳ የእንቅስቃሴ እቀባ በተጣለባቸው በርካታ ከሳሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት የትኩስ ምግቦች ገበያዎች ተዘግተዋል ወይም ተወስነዋል፡፡ ይሄ በነጋዴዎች እና በሸማቾች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ እስካሁን ድረስ የጥራጥሬ እና የሰብሎች አይነቶችን ብዙ ባይነካም፣ ሸማቾች እንደ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የወተት እና የሥጋ ውጤቶች የመሳሰሉ ትኩስ ምግቦችን ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ እነዚህ ምግቦች ቶሎ የሚበላሹ ሲሆን ትኩስ እንደሆኑ የሚያቆይ መንገድ ከሌለ ቶሎ ይበሰብሳሉ፡፡ ከምግብ ጋር በሚኖር ንክኪ የኮቪድ-19 የመተላለፍ እድል ዝቅተኛ ነው፤ ነገር ግን የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሃገሮች የወሰዷቸው እርምጃዎች እነዚህን ምግቦች በቀላሉ ለማግኘት እና አንዳንዴም በክልሎች መካከል ለማጓጓዝ ችግር ፈጥረዋል፡፡

ወረርሽኙ (ኮቪድ-19) የመግዛት እና አምርቶ የማከፋፈል አቅምን በመቀነስ የምግብ አቅርቦት እና ፍላጎት ላይ ባሳደረው ተጽእኖ የምግብ ስርኣቱን አናግቷል፡፡

የጉዞ እገዳዎች የምግብ እንቅስቃሴ ላይ ያሳደሩት ተጽእኖ ምሳሌዎች:-

 • በናይጄሪያ የተደረገው የጉዞ እቀባ አነስተኛ የምርት ነጋዴዎችን ለኪሳራ ዳርጓቸዋል፡፡ የሃገሪቱ የዳቦ ቅርጫት በሆነችው ቤኑዌ ግዛት የምርት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም ነጋዴዎች ምርታቸውን ታቅፈው ቁጭ ብለዋል፡፡
 • ኬንያ ውስጥ መንግስት በከተሞች መካከል የምግብን እንቅስቃሴ ወሳኝ አገልግሎት ብሎ በመወሰኑ የምግብ ዋጋ ላይ የታዬ የጎላ ጭማሪ የለም፡፡
 • ኬንያ ውስጥ አነስተኛ እርሻ ያላቸው ገበሬዎች ሰው በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ ምርታቸውን ከመኪና ላይ እየሸጡ በኮቪድ-19 ቀውስ ወቅት ኑሯቸውን ለመደጎም ይታትራሉ፡፡
 • የጭነት መኪና አገልግት የሚሰጥ አንድ ድርጅት በናይጄሪያ፣ ኬንያ፣ ቶጎ፣ ጋና እና ኡጋንዳ ካሉት የጭነት መኪናዎች 30% የሚሆኑት መንግስታት አስፈላጊ ማጓጓዝ የሚሉት ምን እንደሆነ ግልጽ ስላልሆነ ያለሥራ ቆመዋል ይላል፡፡.
 • የአፍሪካ ሃገሮች ጉዞ ላይ የጣሉት እቀባ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገሮች የምግብ ቀውሱን ሊያባብሰው እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት ይተነብያል፡፡

ትኩስ ምግቦችን መመገብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ በዋጋቸው እርካሽ የሆኑ የኃይል ሰጭ ምግብ፣ ገንቢ ምግብ፣ ቫይታሚን እና ማዕድናት ምንጮች ናቸው፡፡ የምግብነት ጠቀሜታቸው በትኩስነታቸው ከፍተኛ ሲሆኑ አብዛኞች ፍራፍሬ እና አትክልቶች በቶሎ በተገቢ ሁኔታ ካ

ተቀመጡ በስተቀረ ትኩስ ሆነው የሚቆዩት ላጭር ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ትኩስ ምግቦች በዓመት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በሚገኙባቸው ሃገሮች ትኩስነታቸውን ጠብቀው ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆዩ ለማድረግ ሰዎች የተለያዩ ዘዴዎችን ፈጥረዋል፤ ይህንን በማድረግ አቅርቦት ዝቅተኛ በሚሆንባቸው ጊዜያት እነዚህ ምግች ለም

ብነት እንዲውሉ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ዘዴዎች ለአርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች እና አቀነባባሪዎች ጠቃሚ ናቸው፡፡ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅትም በተደረገው የጉዞ ዕቀባ ምክንያት ትኩስ ምግብ ማግኘት ያልቻሉ ሸማቾችም ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ፡፡ እነዚህ ዘዴዎች በአየር ንብረት ለውጥ እና አፈር መራቆት የተጎዱ አርሶ አደሮች ከብዙ የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ለማገገም ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ፡፡

ትኩስ ምግቦች ካ

ተቀነባበሩ ወይም በልዩ ሁኔታ ካልተቀመጡ ይበላሻሉ፡፡ የሚበላሹትም በጀርሞች ምክንያት ነው፡፡ የሚበላሹበትን ፍጥነት ለመቀነስ ፕሪዘርቫቲቭ መጠቀም ወይም ሳይበላሹ በሚያቆይ ማጠራቀሚያ ውስጥ መቀመጥ ወይም ምግቦቹን ማቀነባበር ይቻላል፡፡

ፍራፍሬ እና አትክልቶች ከእርሻ በተሰበሰቡ ከ4 እስከ 48 ሰዓት ውስጥ ባለው ጊዜ ውስጥ እንዳይበላሹ መዘጋጀት አለባቸው፡፡ ጊዜ ባለፈ ቁጥር የመበላሸት እድላቸው ይጨምራል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 2 እና 11ን ተመልከቱ፡፡

ምግብን ትኩስ እንደሆነ ከማቆየት ጋር የተያያዙ መረጃዎች ምንድን ናቸው?

 • በብዙ ድሃ ሃገሮች ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የቫይረሱ ኢኮኖሚዊ መዘዞች ከራሱ ከበሽታው በላይ የከፉ ሊሆን ይችላል፡፡ የትኩስ ምግቦች እጥረት የምግብ ዋስትና እና የአመጋገብ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በዚህም እርጉዝ እና የሚያጠቡ እናቶች በዋናነትና ባጠቃላይ ግን መጨረሻ ላይ ስለሚመገቡ እና የተሻለ ጥራት ያላቸው ምግቦችን ስለማያገኙ ሴቶች በጠቅላላው ለጉዳት ይጋለጣሉ፡፡
 • ቤት ውስጥ በሚደረጉ የማቀነባበር ስራዎች ቶሎ የሚበላሹ ምግቦችን አድሜ ማራዘም ይቻላል፡፡
 • ኬሚካላዊ እና የተፈጥሮ የፈንገስ መግደያ ዘዴዎችን በመጠቀም እንደ አፕል፣ ሙዝ እና ሎሚ በመሳሰሉ ምግቦች ላይ በሚገኙ ሻጋታ እና ባክቴሪያዎች አማካኝነት የሚፈጠረውን መበስበስ ማቆም ይቻላል፡፡
 • ፍራፍሬ እና አትክልቶች ከታጠቡ በኋላ በማድረቅ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ማድረግ ይቻላል፡፡
 • ትኩስ ስጋን በጨው በማሸት እና በጢስ በማጠን እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል
 • ፍራፍሬ እና አትክልትን በማድረቅ አነስተኛ አርሶ አደሮች ኪሳራቸውን መቀነስ እና ከምርት ወቅት ውጭ ባሉ ጊዜያት ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • አነስተኛ አርሶ አደሮች ማንጎ፣ ፓሽን ፍሩት፣ ቲማቲም፣ የተለያዩ የአፍሪካ የአትክልት ምግቦችን (የዱባ ቅጠል፣የቃጫ ተክል (Sunn hemp) ፣መለኩያ/ኩድራን ( Jute mallow)፣ የላም አተር ቦለቄ መሰል ጥራጥሬ(Cowpea) እና የቤት አካቢ ማስጌጫ ተክል(Spider plants)በጸሃይ ማድረቅ ይቻላል፡፡ በዚህ መልክ በማድረቅ የተትረፈረፈ ምርት በሚኖርበት ጊዜ ወይም እንደ ኮቪድ-19 ባለ ወቅት እንቅስቃሴ እና ገበያ በመንግስት ሲታገድ ሳይበላሹ እንዲቆይ ማድረግ ይቻላል፡፡
 • በደንብ የደረቀ ፍራፍሬ እና አትክልት እስከ አንድ ኣመት ሊቆይ ይችላል፤ ይህ እንዲሆን ግን በቀዝቃዛ፣ ጥላ ባለበት እና ደረቅ ቦታ መቀመጥ አለበት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 3፣ 4፣ 10፣ 11፣ 13 እና 14ን ተመልከቱ፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ምግቦችን ሳይበላሹ ማቆየት ላይ ያለው ተጽእኖ

 • የአየር ንብረት ለውጥ የምግብ እጥረት እያስከተለ ባለበት ሁኔታ አነስተኛ አርሶ አደሮች የምግብ እጥረት ሲያጋጥማቸው የሚስፈልጋቸውን ምግብ እንዲያገኙ በትርፍ ምርት ጊዜ የሚኖራቸውን ምግብ ሳይበለሽ ማቆየት ማወቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ በምግብ አቅርቦት እና የቤት ውስጥ የምግብ ልማዶች ላይ የሚፈጠሩ ለውጦች ሴቶች ላይ የጎላ ተጽእኖ ያሳድራሉ፣ ተጨማሪ የሥራ ጫናም ይፈጥራሉ፡፡
 • በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተፈጠረ ያለው የሙቀት መጨመር በቀላሉ የሚበላሹ ምግቦችን እድሜ እያሳጠረ ነው፡፡ እድሜያቸውን ለማራዘም ቀዝቃዛ ቦታ ውስጥ እና ፍሪጅ ውስጥ በማስቀመጥ ወይም ቶሎ ማቀነባር ያስፈልጋል፡፡
 • የውሃ እጥረት ሲኖር በደረቁ በማቀነባር እና በማብሰል ትኩስ ምግቦችን ማቀነባር እና ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
 • እንደ ድርቅ እና ወቅት ያልጠቀ ዝናብ የመሳሰሉ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ተጽእኖዎች ትኩስ ምግቦን ጨምሮ ሁሉም አይነት ምግቦች ላይ የጎላ መቀነስ እንዲታይ ሊያደርጉ ይችላ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 1፤ 5፣ እና 6ን ተመልከቱ፡፡

ምግብን ሳይበላሽ በማቆየት ሥራ ዙርያ የሚታየው ጾታዊ ሚና

 • በብዙ ሃገሮች ሴቶች፣ ህጻነት እና አረጋውያን ትኩስ ምግቦችን በማይበላሹበት ሁኔታ ለማስቀመጥ የማጠብ፣ የመለየት እና የመላጥ ዋነኛ ሃላፊነቶችን ይወጣሉ፡፡
 • ትኩስ ምግቦችን ማቀነባር ለሴቶች የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉበት እና ለማህበረሰብ እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርጉበት እድል ይፈጥርላቸዋል፡፡ ይህም በቤተሰባቸው ላይ የገንዘብ፣ ማህበራዊ እና የአመጋገብ ለውጥ ያመጣላቸዋል፤ የበለጠ ነጻ እንዲሆኑ፣ ለቤተሰባቸው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማቅረብ እንዲችሉ እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ያላቸውን ደረጃ ከፍ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሴቶች ለፍተው የሚያመርቷቸው ምርቶች ላይ የመወሰን አቅም ላይኖራቸው ይችላል፣ ተጨማሪው ሥራም ትርፉ ለነሱ ድካም ማብዛት ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡
 • በገጠራማ የሱዳን ክፍሎች የሚኖሩ ሴቶች የምግብ እጥረት በሚፈጠር ጊዜ እንዲጠቀሙበት የሚያስፈልጋውን ትኩስ አትክትልት፣ ፍራፍሬ እና ወተት የማቀነባበር ሃላፊነት ብቻ አላቸው፡፡ ሴቶች እንደ ማድረቅ እና ማብላላት (ፈርመንቴሽን) ያሉ የማቀነባበርያ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡
 • እማወራ ቤተሰቦች ለምግብ እጥረት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፤ ሴቶችም ልጆቻቸውን ስለሚያስቀድሙ በቂ ምግብ ያለማግኘት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 9 እና 20ን ተመልከቱ፡፡

ምግብን ሳይበላሽ ስለማቆየት የተሳሳቱ መረጃዎች እና ግንዛቤዎች

 • ሁሉም እንዳይበላሹ የተደረጉ ምግቦች ረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ኬሚካ
 • ያስፈልጋቸዋል
 • የምግብ ማቆያ ዘዴዎች በሙሉ የምግብነት መቀነስ ያስከትላሉ
 • ምግብ ሳይበላሽ ትኩስ እንደሆነ እንዲቆይ ውድ መሣርያ ያስፈልጋል፡፡ የገጠር አርሶ አደሮች የምግብ ማቆያ መሣርያዎችን እንደ እንጨት ከመሳሰሉ በአካባቢያቸው ከሚገኙ ነገሮች መሥራት ይችላሉ፡፡

ምግብን በትኩስነቱ ስለማቆየት ቁልፍ መረጃዎች

የሸክላ ድስት ማቀዝቀዣ

አትክልት እና ፍራፍሬዎች ትኩስ ሆነው እንዲቆዩ ይህ ቀላል እና ርካሽ ዘዴ ነው፡፡ አሌክትሪክ አያስፈልገውም፣ በሞቃት እና ደረቅ አካባቢዎች በጥሩ ሁኔታ ይሠራል፣ የሚጠቀመውም በትነት የማቀዝቀዝ ዘዴን ነው *፡፡ እለታዊው ከፍተኛ ሙቀት ከ30 – 45 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሚደርስባቸው ሞቃት እና ደረቅ የአየር ንብረቶች በሸክላ ውስጥ የተቀመጠ ምግብ ከ13-22 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነ ሙቀት ይቆያል፡፡ ይሄ የምግቡን እድሜ ከሦስት እስከ አራት እጥፍ ያራዝማል፡፡

የሸክላ ድስት ማቀዝቀዣ ሁለት የተለያየ መጠን ካላቸው ድስቶች፣ ከእርጥብ አሸዋ እና ከጨርቅ ይዘጋጃል፡፡ ማቀዝቀዣውን ለመሥራት ትንሹን ድስት ትልቁ ድስት ውስጥ ጨምሩ እና በሁለቱ ድስቶች መካከል ያለውን ቦታ በአሸዋ ሙሉ፡፡ አሸዋውን ውሃ ጨምሩበት እና የትንሿን ድስት አፍ በእርጥብ ጨርቅ ክደኑ፡፡

ሸክላው ጥቃቅን ማስተላለፊያ ቀዳዳዎች ያሉት ስለሆነ አሸዋው ውስጥ ያለው እርጥበት ወደ ሸክላው ይዘልቃል፡፡ ይህ ሂደት ከሽክላው ውስጥ ያለውን ሙቀት በማስወገድ ያቀዘቅዘዋል፡፡ ውሃን ለማትነን ከዙርያው ኃይል ይወስድ እና የአየሩ ሙቀት እንዲቀዘቅዝ ያደርጋል፡፡ ከስር ያለውን ስዕል ተመልከቱ፤ በተጨማሪም በማትነን የሚያቀዘቅዘውን የፋርም ራዲዮን Zero Energy Cooling Chamber አንብቡ፡፡ Ceramic refrigerators (የሰራሚክ ማቀዝቀዣ) እና clay refrigerators (የሸክላ ማቀዝቀዣዎች) በተመሳሳይ መንገድ ይሠራሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 11ን ተመልከቱ፡፡

ማድረቅ

ትኩስ ምግቦችን በተለያየ መንገድ አድርቆ ማቆየት ይቻላል፡፡ ምግብ ውስጥ ያለው የእርጥበት መጠን ቀንሶ 10-15% ሲደርስ ምግብን የሚያበሰብሱ ጀርሞች መራባት ስለማይችሉ ማድረቅ ምግብን ሳይበለሽ ማቆየት ያስችላል፡፡ ከዚያ በላይ እርጥበትን መቀነስ አያስፈልግም፣ ከቀነሰ ምግቡ ስብርብር ሊል ይችላል፡፡

ማድረቅ ከባድ አይደለም፡፡ ምግቦች የውሃ ይዘታቸው ሲቀንስ ክብደታቸው ይቀንሳል፣ ለማንቀሳቀስ እና ለማጓጓዝም ቀላል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ቫይታሚን ያጣሉ፣ መልካቸውም ይቀየራል፡፡ በጣም የተለመደው ማድረቂያ ዘዴ ምግብን በአየር ማድረቅ ነው፡፡ አየር ውሃ ይስባል፤ሞቃት ሲሆን ደግሞ ብዙ እርጥበት ይስባል፡፡ ስለዚህ ጥሩ ውጤት ለማግኘት አየሩ ሞቃት፣ ደረቅ እና ነፋሻ ሲሆን ጥሩ ነው፡፡ የተዘጋ ቦታ ከሆነ አዲስ አየር ቶሎ ቶሎ እንዲገባ መደረግ አለበት፤ አለበለዚያ ከምግቡ የሚስበው እርጥበት ይጠራቀማል፤ ጥሩ ማናፈሻ እንዲኖር ይመከራል፡፡ በትክክለኛ ለማድረቅ የአየሩ የእርጥበት መጠን ከ65% በታች መሆን አለበት፡፡ ከዚያ በላይ ከሆነ ፍራፍሬ እና አትልክልት ብለው ብለው መድረቃቸው አይቀርም ግን በትክክል አይደርቁም፡፡ የጸሃይ ብርሃን ካለ ብዙ ጊዜ አርጥበቱ ከ 65%, በታች ይሆናል፣ በደመናማ እና ዝናብ ወቅት ግን የአርጥበት መጠኑ ይጨምራል፡፡ ስለዚህ የጸሃይ ብርሃን በጣም ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ምክንያት በአመቱ ውስጥ ካሉ ወቅቶች ለዚህ ዘዴ ተስማሚ ያ

ሆኑ አሉ፡፡

ለመድረቅ የሚመረጡ ፍራፍሬ እና አትክልት ጥሩ ጥራት ያላቸው መሆን አለባቸው፣ ሰለዚህ የበሰበሱትን እና የተጎዱትን አስወግዱ፡፡ የምግብ ጥራት መቀነስን ለመከላከል ከእርሻ ተሰብስቦ እስከሚደርቅ ድረስ ለውን ጊዜ አሳጥሩ፡፡ ከማድረቃችሁ በፊት ሙሉ በሙሉ አጥባችሁ ካስፈለገ ቆራርጧቸው፡፡ ጠጣር ፍራፍሬን እና የሥራ ሥር አትክ

ቶችን ከማድረቃችሁ በፊት ረዘም ያለ ጊዜ መቆየት ይቻላል፤ ለስላሳ እና ቅጠላማ እንደሆኑት አትክለቶች አያጣድፍም፡፡ ከእርሻ ተሰብስበው ለምግብነት እስከሚውሉበት ድረስ ያለው ጊዜ ማድረቅ ለመጀመር የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ጊዜ ለመገመት ይረዳል፡፡

ምርቶቹ ከደረቁ በኋላ እንዳይበላሹ እርጥበት በሌለበት ቦታ መቀመጥ አለባቸው፡፡

የአደራረቅ አይነቶች

 • በንፋስ ማድረቅ፡- ይሄ ቀላል እና እርካሽ ዘዴ ነው፣ ከጸሃይ ብርሃን እና ከነፋስ ውጪ ለማድረቂያ የሚወጣ ወጭ የለውም፡፡ ሊደርቁ የሚፈለጉትን ምርቶች በትሪ ወይም በጥቁር ምንጣፍ ላይ ዘርዘር አድርጋችሁ አስጡ፡፡ ትሪዎቹ ብዙ ጊዜ ከእንጨት ተሰርተው ከላያቸው ላይ ላስቲክ ወይም የብረት ወንፊት ይለበጥባቸዋል፡፡ አቧራ ምግቡን እንዳያገኘው እና የጸሃይ ብርሃን በደምብ እንዲያርፍበት ትሪውን ከመሬት አንድ ሜትር ያህል ከፍ አድርጋችሁ ጠፍጣፋ ማስቀመጫ ላይ አስቀምጡት፡፡ ካስፈለገ ትሪውን ዝናብ፣ አቧራ፣ ወፎች፣ ነፍሳት እና ሌሎች ተባዮች እንዳያርፉበት መሸፈን ትችላላችሁ፡፡ ከተባይ ለመከላከል የወባ መከላከያ አጎበር መጠቀም ጥሩ ነው፡፡ ፍራፍሬውና አትክልቱ እኩል እንዲደርቁ በየጊዜው አገላብጡ ወይም ትሪውን ቀስ አድርጋችሁ ወዝውዙ፡፡ ቲማቲም ለማድረቅ ለሁለት ቆርጣችሁ ሳትደራርቡ ትሪው ላይ ደርድሩ፡፡
 • የተሻሻለ የጸሃይ አደራረቅ፡- የመስታውት ሽፋን ባለው ማድረቂያ እቃ ውስጥ ምርቶቹ ሲቀመጡ እቃው ሙቀቱን ይዞ በማስቀረት ከ60-75°C የሚደርስ ሙቀት በመፍጠር ቶሎ እንዲደርቁ ያደርጋል፡፡ አየር እንዲገባ እና እንዲወጣ በማድረግ ግለት እንዳይፈጠር አድርጉ፡፡ አየር ካልገባ እና ካልወጣ በተለይ አድርቃችሁ ልትጨርሱ አካባቢ ሙቀቱ ከ90-100°C ሊደርስ ይችላል፡፡ አየር እንዲገባ እና እንዲወጣ በማድረግ መስታውቱ ጤዛ እንዳይይዝ ማድረግ ይገባል፡፡

በጸሃይ ማድረቅ

አትክልት እና ደርቀው የሚበሉ ነፍሳት መጀመርያ ለጥቂት ደቂቃ ጨው ባለበትና በሚፈላ ውሃ ውስጥ ለጥቂት ደቂቃ ከተነከሩ በኋላ ለሦስት ቀናት ያህል በጸሃይ ሊደርቁ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ በቀዝቃዛ፣ ደረቅ እና ብርሃን በሌለት ቦታ አስቀምጡ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 11ን አንብቡ፡፡

በጨው ማሸት

እንደ ስጋ እና ቲማቲም ያሉ በቀላሉ የሚበላሹ ምግቦች ጨው ተጨምሮባቸው በደረቅ ቦታ ከማቀዝቀዣ ውጭ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ የደረቀ ቲማቲም ለብ ባለ ወሃ ተዝፍዝፎ እንደ ድልህ ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሊቀመጥ ይችላል፡፡

ለተጨመሪ መረጃ ሰነድ 8 እና 18ን ተመልከቱ፡፡

የጸሃይ ማድረቂያ ሳጥን መጠቀም

አነስተኛ አርሶ አደሮች በዝቅተኛ ዋጋ አትክልትና ፍራፍሬ ማድረቂያ ሳጥን ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡ ሳጥኑ ከእንጨት የተሠራ አራት ማእዘን ሲሆን በጥቁር ጨርቅ ይሸፈናል፡፡ አትክልቶቹን በአራት ማእዘን እንጨት ላይ በተገጠመ ወንፊት ላይ አስቀምጧቸው፡፡ ወንፊቶቹን ጥቁሩ ጨርቅ ላይ አስቀምጡና በሚያሳይ ላሳቲክ ሸፍናችሁ ጸሃይ ላይ አስጡ፡፡

 • ጥሩ ጥራት ያላቸውን የበሰሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎች አንድ በአንድ ምረጡ
 • ከተጠቀማችሁ በኋላ የጸሃይ ማድረቂያ ሳጥኑን እና ማስቀመጫ ወንፊቶቹን በበረኪና አጽዱ
 • የተመረጡ አትክልትና ፍራፍሬዎቹን እጠቡ እና በንጹህ እቃ አስቀምጡ
 • አትክልቶቹን የሚያበሰብሱት ኢንዛየሞች እንዲመክኑ አትክልቶቹን በእንፋሎት አሙቋቸው፤ ይህን ማድረግ አትክልቶቹ የምግብ ይዘታቸውን እንዳያጡ እና በሚደርቁበትም ጊዜ እንዳይጠባበቁ ያደርጋቸዋል
 • ፍራፍሬዎቹን ከማድረቂያው በንጹህ እቃ በማንሳት እንዳይበከሉ አድርጉ
 • ፍራፍሬዎቹን በቀጭኑ ቆራርጡ – ከማድረቂያው ጋር እንዳይጣበቁ ግን በጣም ቀጭን አታድርጓቸው
 • የተቆራረጠ ፍራፍሬ በጸሃያማ ሁኔታ ከሁለት ቀን በኋላ ይደርቃል፡፡ በደንብ ካልደረቀ ለተጨማሪ አንድ ወይም ሁለት ሰዓት አድርቁ፡፡
 • በደረቀ ፍራፍሬ ውስጥ ያለው የመጨረሻው የእርጥበት መጠን 10 በመቶ መሆን አለበት፡፡

ሰው ሰራሽ ማድረቂያ፡- በደምብ ለማድረቅ የውጩ ሙቀት በትንሹ ከፍ እንዲል ማድረግ ይበቃል፡፡ ለምሳሌ በ30°C ዝናብ ሲኖር አየሩ ቢያንስ ወደ 37°C እንዲሞቅ መደረግ አለበት፡፡ ከዚያ በላይ ማሞቅ ምርቱ የሚደርቅበትን ጊዜ ያፈጥነዋል፡፡ አየሩን በጸሃይ ሙቀት ወይም እሳት በማንደድ ማሞቅ ይቻላል፡፡ የተለያዩ ምግቦች ለመድረቅ የተለያየ የሙቀት መጠን ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሙቀት ከታለፈ የደረቀው ምግብ ጥራት በፍጥነት ይቀንሳል፣ ስለዚህ እንዳያልፍ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሌላው በከፍተኛ ሙቀት ማድረቅ የማያስፈልገው ደግሞ ምግቡ ከውጭ ቶሎ ይደርቅና ውስጡ እርጥብ ስለሚሆን ነው፡፡

የማድረቅ ሂደቱ የሚያልቀው መቼ ነው?

ምርቱ በሚገባ መድረቁን ለማረጋገጥ እስኪቀዘቅዝ ድረስ ጠብቁ፡፡ ሞቅ ያሉ ምርቶች ለስለስ ያሉ ሲሆን በውስጣቸውም ውሃ ይኖራቸዋል፡፡ የደረቁ ፍራፍሬዎች ከ12-14% ውሃ ይይዛሉ፤ አትክልቶች ከዚ ደረቅ የሚሉ ሲሆን ከ4-8% ውሃ ይኖቸዋል፡፡ ማድረቂያ ምድጃ ወይም እርጥበት መለኪያ ከሌለ የእርጥበት መጠንን መለካት ከባድ ቢሆንም የሚከተሉትን መመርያዎች መጠቀም ይቻላል፡-

 • ፍራፍሬ ከደረቀ ስትጨምቁት ውሃ መውጣት የለበትም
 • ፍራፍሬዎች የማድረቂያው ትሪ ላይ ሆነው የሚንኮሻኮሽ ድምጽ እስከሚያወጡ ድረስ መድረቅ የለባቸውም
 • ፍራፍሬዎች በእጅ ለመጨፍለቅ አስቸጋሪ መሆን የለባቸውም፣ ነገር ግን እርስ በርስ መጣበቅም የለባቸውም
 • የደረቁ አረንጓዴ አትክልቶች ስብርብር የሚሉ እና ሲታሹ በቀላሉ ወደ ዱቄት የሚቀየሩ መሆን አለባቸው

የደረቁ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ማሸግ እና ማስቀመጥ

የማድረቅ ሂደቱ ካለቀ በኋላ እንደ እንጨት ያሉ ባእድ ነገሮችን እና በደምብ ያልደረቁ ክፍሎችን አስወግዱ፡፡ የደረቁ አትክልቶች በቀላሉ ከአካባቢ እርጥበት ስለሚስቡ ደረቅ ክፍል ውስጥ መታሸግ አለባቸው፡፡ ያየሩ ሙቀት ከፍተኛ እና የእርጥበት መጠኑ ዝቅተኛ በሆነበት ሰዓት አሽጎ መጨረስ ይመከራል፡፡ የደረቁ ምርቶችን ጥላ ላይ አድርጋችሁ አቀዝቅዙ እና በዚህ ሂደት ንጽህናቸውን ከጠበቃችሁ ወዲያውኑ ማሸግ ይቻላል፡፡ ማሸጊያ እቃው ውሃ፣ አየር እና ነፍሳት የማያስገባ መሆን አለበት፡፡ የደረቁ ምርቶች ሳይበላሹ የሚቆዩት በደረቅ ቦታ እና ነፍሳት ሳያገኛቸው ከተቀመጡ ነው፡፡ በደምብ የታሸጉ የፕላስቲክ ከረጢቶች ለተወሰነ ጊዜ ሊያገለግሉ ይችላሉ፤ አየር እና ውሃ ፈጽሞ እንዳይገባ የማድረግ አቅማቸው ግን ፍጹም አይደለም፡፡

የደረቁ ምግቦችን መመገብ

የደረቁ ምርቶችን በሳሃን ውስጥ ጥቂት ውሃ እድርጋችሁ ዘፍዝፉ፡፡ ለሁለት እጅ የደረቀ ፍራፍሬ ሁለት ሦስትኛ ውሃ አድርጋችሁ ከ8 – 12 ሰኣት ያህል ዘፍዝፉ፡፡ የደረቁ አትክልቶችን ለሁለት እጁ ከሁለት አምስተኛ (2.5) እስከ አራት አምስተኛ (4.5) እጅ ውሃ ጨምራችሁ ዘፍዝፉ፡፡ በዱቄት መልክ ያሉ ምርቶች ለጥቅም ከመዋላቸው በፊት መዘፍዘፍ አያስፈልጋቸውም፡፡ ከዘፈዘፋችሁ በኋላ ምርቱን ከ10-15 ደቂቃ ያህል አብስሉ፡፡ አንዳንድ ፍራፍሬዎች በአጭር ጊዜ ሲበስሉ አንዳንዶቹ ረዘም ያለ ጊዜ ይፈልጋሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 3፣ 10፣ 11፣ 12 እና 13ን ተመልከቱ፡፡

ጎመን እና ሌሎች የአፍሪካ የቅጠላቅጠል አትክልቶችን ሳይበላሹ ማቆየት

በዝናባማ ወቅት አትክልቶች በብዛት ሲበቅሉ፣ በደረቅ ወቅት ደግሞ አቅርቦታቸው ያንሳል፡፡ የደረቁ አትክልቶች ለመብሰል አጭር ጊዜ ብቻ የሚወስድባቸው ሲሆን ጣእማቸውም ልክ እንደ ትኩስ አትክልት ነው፡፡

 • ሰባት ኪሎ የአፍሪካ ቅጠላ ቅጠል አትክልቶች አንድ ኪሎ ደረቅ አትክልት ይወጣቸዋል
 • ኬንያ ውስጥ አንድ አርሶ አደር አንድ ኪሎ የደረቀ አትክልት በ600 ሺሊንግ (6 የአሜሪካን ዶላር መሸጥ ይችላል)
 • ንጹህ፡- ለእርሻ የተሰበሰበውን አትክልት ግንድ ቁረጡ፡፡ የደረቁ ቅጠሎችን እና ባእድ ነገሮችን አስወግዱ፡፡ ከዚያ አትክልቶቹን በብዙ ውሃ እጠቡ፡፡
 • በሙቅ ውሃ መንከር፡- ውሃ አሙቁ፡፡ ለአንድ ሊትር ውሃ አንድ የሻይ ማንኪያ ጨው ጨምሩ እና ውሃው እየሞቀ በደምብ ቀላቅሉ፡፡ አትክልቱን በጥጥ ጨርቅ ጠቅልሉና የሚፈላው ውሃ ውስጥ ጨምራችሁ ለአምስት ደቂቃ ገልበጥ ገልበጥ በማድረግ ሙሉ በሙሉ በውሃ እንዲዳረስ አድርጉ፡፡
 • አለቅልቁ፡- አትክልቶቹን በንጹህ ቀዝቃዛ ውሃ አለቅልቁ እና በጸሃይ ማድረቂያ ትሪዎች ወይም ማንኛውም ጠፍጣፋ እቃ ላይ አስቀምጧቸው፡፡ እንደ አየሩ ጸባይ ከ2-5 ቀን ተውት፡፡ ሲደርቁ ከማሸጋችሁ በፊት በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ላይ አስቀምጡ፡፡
 • ማሸግ፡- አትክልቶቹን መቶ መቶ ግራም እያደረጋችሁ ክርችም ብሎ ቢዘጋ የፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ አሽጉ፡፡ አየር በማይስገባ እቃ አድርጋችሁ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ አስቀምጡ፡፡ በዚህ ሁኔታ ከተቀመጡ አትክልቶቸ ቢያንስ ለስድስት ወር ሳይበላሹ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

ጎመን

ከእርሻ የተሰበሰበውን ትኩስ ጎመን በእርጥብ ወረቀት ጠቅልላችሁ በትልቅ የፕላስቲክ ከረጢት ውስጥ አድርጋችሁ ፍሪጅ ውስጥ ከ14-21 ቀን አስቀምጠት፡፡ ጎመኑ ዝልፍልፍል እንዳይል ከማስቀመጣችሁ በፊት አትጠቡት፡፡ በቂ የአየር ዝውውር ባለበት ቦታ አስቀምጡት፡፡

 • በአምስት ሊትር ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ አንድ ሻይ ማንኪያ ጨው አድርጉ እና ጎመኑን ለአንድ ደቂቃ ዘፍዝፉት
 • ጎመኑን አንጠፍጥፋችሁ እንደ አየሩ ሁኔታ ከ2-3 ቀን ጥላ ላይ ዘርዘር አድርጋችሁ አስጡት
 • የደረቀ ጎመን እስከ ስድስ ወር ሊቀመጥ ይችላል

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 4፣ 10፣ 11 እና 13ን አንብቡ፡፡

የአረንጓዴ ሙዝ ዱቄት

ቤት ውስጥ ሸጠው ወይም ተመግበው ከሚጨርሱት በላይ ብዙ ምርት ሲኖራቸው እና ሰአት እላፊ ሲታወጅ እና ከቤት መውጣት ሲከለከል አጋዥ ምግብ እንዲሆናቸው የገጠር አርሶ አደሮች ከአረንጓዴ ሙዝ ዝቅተኛ ግሉቴን ያለው ዱቄት ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡ ከአረንጓዴ ሙዝ በሚከተለው መንገድ ዱቄት ማዘጋጀት ይቻላል፡-

 • ሙዞቹን ከዛላው ገነጣጥሉ
 • የሚያጣብቀው ሙጫ እንዲቀንስ፣ ከለሩ እንዲሻሻል እና ለመላጥም እንዳያስቸግር ለ10 ደቂቃ ያህል በእንፋሎት አሙቁ
 • ላጡና በትናንሹ ክተፉት
 • ቁርጥራጮቹን ለ30 ደቂቃ ያህል በ5% የሲትሪክ አሲድ ውህድ ውስጥ ዘፍዝፉ
 • የሙዙ እርጥበት መጠን 10% እስከሚሆን ድረስ በፕላስቲክ መደርደርያ ላይ አድርጋችሁ አድርቁ፡፡ የአርሶ አደር ማሕበሮች ባንድ ላይ የእርጥበት መለኪያ መሣርያ መግዛት ይችላሉ፡፡ እንደ አማራጭ የሙዙ ቁርጥራጮች ሙሉ በሙሉ መድረቃቸውን በቀላሉ በመሰባበራቸው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
 • የደረቀውን ሙዝ ፍጩ እና ዱቄቱን ንፉ
 • የሙዙን ዱቄት አሽጋችሁ በዝግ፣ ቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ አስቀምጡ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 7ን ተመፐልከቱ፡፡

በማሞቅ እንዳይበላሽ ማድረግ

ፍራፍሬዎች እና አትክልት እንዳይበላሹ ለማድረግ በጣም የተለመደው እና ውጤታማው ዘዴ አየር በማያስገባ እቃ ውስጥ አስቀምጦ እቃውን ማሞቅ ነው፡፡ ከፍተኛው ሙቀት ጀርሞችን ይገድላል፣ መበስበስ ለማምጣት የሚያግዙ ኢንዛየሞችንም ያመክናል፡፡ ለፍራፍሬ የሚደረገው የማሞቅ መንገድ ከአትክልት ይለያል፡፡ ፍራፍሬዎችን በሚፈላ ውሃ ውስጥ (100° C) ማሞቅ ይቻላል፣ አትክልት ግን የፒኤች መጠናቸው ከፍተኛ ስለሆነ በዚህም ምክንያት በባክቴሪያ ለመበከል ተገላጭ ስለሆኑ ከ100° C በላይ መሞቅ አለባቸው፡፡

በሙቀት ሳይበላሹ ማቆየት የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፡-

 • ብዙዎቹ ጀርሞች ስለሚጠፉ የመበላሸት እድል ይቀንሳል
 • ከጀርም ጸድቶ ከተቀመጠ በኋላ ምግቡ ለረጅም ጊዜ ሳይበላሽ ይቆያል፡፡

ጉዳቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

 • በሙቀት እንዳይበላሹ ማድረግ የሚከተሉትን ወጭዎች ያስከትላል፡- ሙቀት የሚቋቋሙ እንደ ጣሳ እና ጠርሙስ ያሉ መያዣ እቃዎች፣ በእንፋሎት የሚያሞቁ እቃዎች እና ነዳጅ
 • ሥራው አድካሚ ነው
 • ብዙ ንጹህ ውሃ ይፈልጋል
 • በዚህ መልክ የተዘጋጁት ፍራፍሬዎች እና አትክልት የምግብ ይዞታቸው ይቀንሳል፣ ጥፍጥናቸውም እንደ ትኩስ አትክልት አይደለም፡፡ ቢሆንም ግን የምግብ ይዞታቸው መቀነስ ያን ያህል የጎላ አይደለም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሰነድ 11ን ተመልከቱ፡፡

በቤት የሚሠሩ ማቀዝቀዣ ዘዴዎች

ትኩስ ምርት በእጃቸው ያላቸው እና ወዲያው ወደገበያ ማቅረብ የማይችሉ አነስተኛ አርሶ አደሮች በአካባቢያቸው የሚገኙ እቃዎችን በመጠቀም ማቀዝቀዣ ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ማቀዝቀዣ የሽቦ ወንፊት ግርግዳ ያለው እና በከሰል በተደመደመ የእንጨት ሳጥን ይሠራል፡፡ ትናንሽ ቀዳዳዎች ያሉት ቱቦ በከሰሉ ላይ ተጋድሞ ውሃ ያንጠባጥባል፡፡ ሳጥኑ በውስጡ በኩል ቀዝቃዛ ስለሚሆን ከውስጥ የተቀመጡት ፍራፍሬ እና አትክልት ከውጭ ሙቀት ቢሆንም ቀዝቅዘው ይቆያሉ፡፡

ለተጨማ መረጃ ሰነድ 3ን ይመልከቱ፡፡

ዋና ዋና ትርጉሞች

በፈላ ውሃ መንከር:- ይህ ሂደት ወደ ማቀዝቀዣ ለመጨመር በፊት በእንፋሎት ወይም በፈላ ውሃ መገሸር ማለት ነው፡፡ የምግብን ቃና፣ ቀለም እና አካላዊ ገጽታ የሚያሳጡትን ኢንዛየሞች በመገሸር ማቆም ወይም ቀስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከአትክልት ላይ ያለውን ቆሻሻም ያጸዳል፣ ቪታሚን ይዘታቸውም እንዳይቀንስ ይረዳል፡፡ አትክልት ሲገሸሩ ስለሚዝለፈለፉ ለማሸግ ሥራ ያቀላል፡፡ ልክ እንደ አትክለቱ ዓይነት መገሸር ከ10 ሰከንድ እስከ 10 ደቂቃ ይወስዳል፡፡

በትነት የማቀዝቀዝ ዘዴ፡- ይህ የማድረቅ ዘዴ ዝቅተኛ እርጥበት ያለው አየር እርጥብ አካል ላይ ሲያልፍ እርጥበቱን ከእርጥቡ አካል ላይ በትነት መልክ ሲስበው የሚፈጠር ነው፡፡ የትነት ፍጥነቱ ፈጣን ሲሆን ቅዝቀዘቄው በፍጥነት ይፈጠራል፡፡ የዚህ ዘዴ ውጤታማነት በዙርያው ባለው የአየር እርጥበት መጠን ይወሰናል፡፡

ተደራራቢ ጓሮ፡- እንደዚህ ዓይነት ጓሮ ክብ ቅርጾች ከላይ ወደታች በተርታ ተደራርበው የሚሠራ ነው፡፡ ከሥር የደረቀ ጥቁር ፕላስቲክ ተነጥፎ አፈሩን ይይዛል፡፡ በነዚህ ጓሮዎች የሃበሻ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ድምብላል፣ ቲማቲም እና ስትሮውቤሪ የመሳሰሉ አትክልትና ፍራፍሬዎች ይበቅላሉ፡፡

ማምከን፡- በዚህ ዘዴ በጠርሙስ ወይም በጣሳ የታሸገ ምግብ ከ100 – 121°C ባለ ሙቀት እንዲሞቅ ይደረጋል፡፡ ይህ ሂደት ጀርም ይገድላል፤ ምግቡም ሳይበላሽ እስከ አንድ ኣመት እንዲቆይ ያደርጋል፡፡ ስፖሮችን ወይም እራሳቸውን በመከላከያ ሽፋን የሸፈኑ ጀርሞችን ግን አይገድላለቸውም፤ እነዚህ ጀርሞች ጣሳው ሲከፈት መልሰው መራባት ይጀምራሉ፡፡

 

Acknowledgements

ምስጋና

የጽሑፉ አዘጋጅ፡- ጄምስ ካሩጋ፣ የግብርና ጋዜጠኛ፣ ኬንያ

የጽሑፉ ገምጋሚ፡- ዲነስ ኬጆ፣ የግብርና ምርምር መኮንን (ሰብኣዊ ስነምግብ) ፣ የታንዛንያ ግብርና ምርምር ማዕከል – ቴንጌሩ

ይህ ጽሑፍ በግሎባላ አፌይርስ ካናዳ በኩል ከካናዳ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡

Information sources

 1. AgriProFocus, Verbos, and Food & Business Knowledge Platform, 2018. What is climate smart in Africa’s horticulture? https://images.agri-profocus.nl/upload/post/190207_report-businessdrivers-csa-horticulture-compressed1549554309.pdf (1.47 MB).
 2. Bagnetto, L. A., 2020. African street vendors feel the squeeze under strict Covid-19 measures. Radio France International. http://www.rfi.fr/en/africa/20200408-african-street-vendors-feel-the-squeeze-under-strict-covid-19-measures-food-traders-markets-coronavirus-lockdown
 3. Feed the Future-USAID, 2018. Drying Fruits and Vegetables with the Chimney Solar Dryer, chapter 2 in Chimney Solar Dryer Manual. https://horticulture.ucdavis.edu/sites/g/files/dgvnsk1816/files/extension_material_files/drying-fruit-vegetables-chimney-solar-dryer.pdf (654 KB).
 4. Food and Agriculture Organization, 2011. Preserving green leafy vegetables and fruits. http://www.fao.org/3/CA2556EN/ca2556en.pdf (683 KB).
 5. Food and Agriculture Organization, 2009. Climate Change in Africa: The threat to agriculture. https://www.uncclearn.org/sites/default/files/inventory/fao34.pdf (215 KB).
 6. Food and Agriculture Organization, 2008. Climate Change and Food Security: A Framework Document. Intergovernmental Working Group on Climate change. http://www.fao.org/3/k2595e/k2595e00.pdf (750 KB).
 7. Food and Fertilizer Technology Center (FFTC), 2005. Processing of banana flour. https://www.fftc.org.tw/htmlarea_file/library/20110716233724/pt2005019.pdf (377 KB).
 8. Global Forum on Food Security and Nutrition, 2013. Indigenous methods of food preparation: what is their impact on food security and nutrition? Food and Agriculture Organization of the United Nations. http://assets.fsnforum.fao.org.s3-eu-west-1.amazonaws.com/public/files/90_indigenous_knowledge/summary_89_EN_indigenous_methods.pdf (189 KB).
 9. Ibnouf, F. O. 2012. The Value of Women’s Indigenous Knowledge in Food Processing and Preservation for Achieving Household Food Security in Rural Sudan. Journal of Food Research, Volume 1(1), pages 238-253. http://citeseerx.ist.psu.edu/viewdoc/download?doi=10.1.1.473.5547&rep=rep1&type=pdf (557 KB).
 10. Infonet-Biovision, undated. Drying of Fruit and Vegetables.https://www.infonet-biovision.org/PlantHealth/Drying-fruit-and-vegetables
 11. James, I.F., and Kuipers, B., 2003. Preservation of fruit and vegetables. Agrodok #3. Agromisa Foundation.http://ubblab.weebly.com/uploads/4/7/4/6/47469791/03-preservation_of_fruit_and_vegetables.pdf (1.25 MB).
 12. Mnkeni, A. P., Soundy, P, and Brutsch, M. O., 2008. Solar drying of fruit and vegetables. Department of Agriculture, Republic of South Africa. http://www.daff.gov.za/docs/Infopaks/Solardrying.pdf (1.52 MB).
 13. Okoko, N., Pole, F., and Katama, C. K., 2008. How to preserve African leafy vegetables for use in dry periods. Kenya Agricultural Research Institute (KARI). https://kalro.org/fileadmin/publications/brochuresII/How_to_preserve_African_leafy.pdf (4.52 MB).
 14. Paltrinieri, G., undated. Handling Of Fresh Fruits, Vegetables and Root Crops: A Training Manual For Grenada. Food and Agriculture Organization of the United Nations. http://www.fao.org/3/a-au186e.pdf (1.52MB).
 15. Smallholder Horticulture Empowerment and Promotion Project-JICA, 2016. Kale Production. https://www.jica.go.jp/project/english/kenya/015/materials/c8h0vm0000f7o8cj-att/materials_11.pdf (1.8 MB).
 16. Ukulima Tech, 2016. Vertical Garden Technology. https://www.youtube.com/watch?v=rG4h8TFYnvcVideo.
 17. UNHCR-BMZ, 2008. Multi-Storey Gardening: Training Manual. https://www.unhcr.org/4b7becf99.pdf (3.18 MB).
 18. United States Department of Agriculture Food Safety and Inspection Service, 2016. Jerky and Food Safety. https://www.fsis.usda.gov/wps/wcm/connect/32da4779-ba5e-4d7b-ad5a-2ad8a13aad1e/Jerky_and_Food_Safety.pdf?MOD=AJPERES(526 KB).
 19. University of California Division of Agriculture and Natural Resources, undated. Pickling: Vinegar and Fermentation. https://ucanr.edu/sites/MFPOC/files/239033.pdf (7.45 MB).
 20. Weiser, S., 2018. Food Insecurity and Poor Health In Sub-Saharan Africa. Power Point presentation at The Fifth Annual Global Health Economics Colloquium: The Economics of Vulnerable Populations, at Home and Abroad. https://globalhealthsciences.ucsf.edu/sites/globalhealthsciences.ucsf.edu/files/sheri-weiser.pdf (57.2 MB).