ዳራ ፡ አራቱ የማዳበሪያ አጠቃቀም ስልቶች

የመሬት ጉዳዮች

Script

መግቢያ

ይህ ዳራ የማዳበሪያ አጠቃቀም ስልቶች ላይ በተለየ በማተኮር የስንዴ እና የጤፍ ምርት ገፅታዎችን ያብራራል፡፡* በተጨማሪም ከፆታ ጋር የተያያዙና የአየር ጠባይ-ነክ ልምዶችንም አካቷል፡፡

ይህ ርዕሰጉዳይ ለአድማጮች ለምን ጠቃሚ ሆነ;

ይህ ፅሁፍ በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አድማጮችን ለማሳወቅ ያለመ ነው:-

 • በሰብል ምርት ወቅት ማዳበሪያን የመጠቀም ጥቅሞች
 • የሰብል ምርት ለማሻሻል ምርጥ የማዳበሪያ አጠቃቀም ዘዴዎች
 • የማዳበሪያአጠቃቀምላይፆታዊገፅታዎች
 • የማዳበሪያአጠቃቀምተግዳሮቶች
 • የአየር ጠባይ ለውጥ እና የማዳበሪያ አጠቃቀም
 • የማዳበሪያ አይነቶች (የተፈጥሮ: ሰው ሰራሽ)

ማዳበሪያን የመጠቀም ጠቀሜታዎች

 • ማዳበሪያዎች ሰብሎች ለጥሩ እድገት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች ያቀርባሉ፡፡ ምንም እንኳን አፈር ሰብሎች የሚፈልጉትን አብዛኛዎቹን ንጥረ ነገሮች ብዙውን ጊዜ ቢይዙም አብዛኛው አፈር እነዚህን ንጥረ ነገሮች በአነስተኛ መጠን ነው የሚይዘው በተለይ አፈሩ በአነስተኛ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ለረጅም ጊዜ የታረሰ ከሆነ፡፡
 • ማዳበሪያ መጠቀም ተጨማሪ እና የተሸለ ጥራት ያለው ምግብ እንዲመረት ማረጋገጫ ነው፡፡
 • አርሶ አደሮች አዲስ የእርሻ መሬት ፍለጋ የሚያደርጉትን ደን ምንጣሮ በመቀነስ ማዳበሪያን መጠቀም በአነስተኛ ቦታ ላይ ከፍተኛ ምርት እንዲገኝ ያደርጋ፡፡

ማዳበሪያ አጠቃቀም ላይ ያሉ ትልልቅ ተግዳሮቶች

 • ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን ከእርሻዎች የሚሄደው ንጥረ ነገር የመሬትና ውሀ ስነ-ምህዳሮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች በቀላሉ እና በፍጥነት በዕፀዋት ስለሚመጠጡ ማዳበሪያ ሲጨመር ወይም በመስኖ ወይም በከፍተኛ ዝናብ ወቅት ወደ ከርሰ-ምድር ታጥበው ሊሄዱ ይችላሉ በተለይ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ ካ
 • ዋሉ፡፡
 • ተገቢ ያልሆኑ ናይትሮጂን ላይ የተመሰረተ ማዳበሪያ ለምሳሌ ዩሪያ አጠቃቀም መጠኑ ከፍ ያለ የአሞኒያ ጋዝ እና ናይትሮጂን ኦክሳይድ ልቀትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
 • ማዳበሪያዎችንእንዴትበትክክልመጠቀምእንደሚቻልጋርየተያያዘየግንዛቤእጥረት
 • በአፍሪካ ውስጥ ያለው ከፍተኛ የማዳበሪያ ዋጋ በዋናነት ከወደቦች ወደ እርሻ ማሳዎች /እርሻዎች ለማጓጓዝ የሚወጣው ከፍተኛ የማጓጓዥያ ዋጋ አብዛኞቹ የአፍሪካ አርሶ አደሮች ማዳበሪያን በምክረ-ሀሳቡ መሰረት እንዳይጠቀሙ ይገድባቸዋል፡፡

ፆታ-ነክየሰብልምርትገፅታዎችእናየማዳበሪያአጠቃቀም

በሰብል እና እንስሳት ምርት፤ ክምችት እና ግብይት ላይ ሴቶች ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በግብርናው መስክ ከተሳሳተ አመለካከት የተነሳ የሴቶች ስራ የሚገባውን ዋጋ አልተሰጠውም፡፡ ከአምራችነት ይልቅ እንደ ተጠቃሚነት ይታያሉ፡፡ (19) በተጨማሪም በንፅፅር ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመጠቀምና ለመቆጣጠር ያላቸው አቅም የተገደበ ነው፡፡

 • ሴቶች ለግብርና ስራ ከፍተኛ የሰው ሀይ
 • /ጉልበት የሚያበረክቱ ቢሆንም በሰብል ምርት ላይ በውጤታማነት የመሳተፍ ችሎታቸው: በአብዛኛው ጊዜ ውሳኔ የመወሰኑ እና መሬት እና ፋይናንስን መጠቀም አቅማቸውን በሚገድቡ ባህላዊና ማህበራዊ ምክንያቶች የታጠሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ከሰሀራ በታች በሚገኙ አብዛኞቹ ማህበረሰቦች ውስጥ ባሎች፤ ወንድ የቤተሰብ አባላት እና ወንድ ዘመዶች የመሬት አጠቃቀምን የተመለከቱ ውሳኔዎችን በበላይነት ይወስናሉ፡፡
 • አብዛኛውን ጊዜ የመሬት ባለቤትነት በወንድ የቤተሰብ አባላት የተያዘ ነው፡፡ የመሬት ባለቤትነት መብቶች ከአባት ወደ ወንድ ልጅ ይተላለፋሉ፡፡ በቤተሰቦች ውስጥ የመሬት ባለቤትነት ሰነዶች ብዙውን ጊዜ በባል ስም ናቸው ምንም ”£” ሴቶች የለት ከለት የእርሻ ስራዎች ውስጥ የበለጠ ተሳታፊ ቢሆኑም፡፡
 • የሴቶች የመሬት የመጠቀም እና የማስተዳደር መብቶች ህጋዊ መብቶቻቸውን ጨምሮ ብዙውን ጊዜ በወላጆቻቸው እና በባሎቻቸው ዘመዶች ይጣሳሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ በአነስተኛ የግብርና ስርዓቶች ውስጥ የሚከናወን የሰብል ምርትን በተመለከተ ሴት አርሶ አደሮች ብዙውን ጊዜ ተጎጂ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ውጤታማነታቸው በሚከተሉት ጉዳዮች ስለሚደናቀፍ:-
 • ከደካማ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ቀውስ የተነሳ እንደ ማዳበሪያ እና የተሸሻለ ዘር ያሉ የእርሻ ግብዐቶችን የመግዛት አቅማቸው አነስተኛነት
 • ግብዐቶችን ለመ
 • ዛትየሚያስፈልጉማስያ¹ዎችእጥረትእንደ ብድርለማግኘትየሚያስችልሕጋዊመብት ያለ
 • ከእርሻምርትሽያጭየሚገኝገቢንመጠቀምአለመቻልምክንያቱምይኼብዙውንጊዜ በወንድየቤተሰብአባላትቁጥጥርስርስላለ
 • በተወሰነመልኩከአነስተኛየትምህርትደረጃየተነሳየኤክስቴሽንመረጃተደራሽነትአነስተኛመሆንየሰብልምርታማነትየማሻሻያስልትንጨምሮ
 • ከቤት ወስጥ ሃላፊነት (ለምሳሌ ምግብ ማብሰል እና ልጆችን እና ሌሎች የቤተሰብ አባላትን መንከባበብ) የተነሳ ሙሉ በሙሉ የእርሻ ስራዎችን ለመስራት የተወሰነ ሰዓት መኖር
 • አነስተኛ የገበያ ተደራሽነት መኖር
 • ዝቅተኛ የግብርና ቴክኖሎጂዎች እና ማሽኖች ተደራሽነት

ካልተመጣጠነ የኤክስቴሽን መረጃ አነስተኛ የግብርና ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት እና ዝቅተኛ የመግዛት አቅም የተነሳ አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች አነስተኛ ማዳበሪያ ይጠቀማሉ:: ይኸም በሴት በሚተዳደሩ እርሻዎች ላይ አነስተኛ የሰብል ምርታማነትን ያስከትላል፡፡

የአየርጠባይለውጥናማዳበሪያ

የአይር ጠባይ ለውጥ በአለማቀፍ የአይር ጠባይ ላይ የሚከሰት ከፍተኛ እና ዘላቂ ለውጥ ነው፡፡

የአይር ጠባይ ለውጥን ለመዋጋት ውጤታማ የማዳበሪያዎች አጠቃቀም ሁለት ዋና ዋና ሚናዎችን ሊጫወቱ ይችላሉ::

 1. ማዳበሪያ መጠቀም ምርታማነትን ስለሚጨምር የደን ምንጣሮን ለመከላከል ያስችላል፡፡ የምርታማነት መጨመር ምንጣሮን ይቀንሳል:: በተጨማሪም ጠቃሚ ካርቦን ስለሚዘቅጥ ደንን ለመንከባከብ ይረዳል:፡
 2. በተሻሻለ የካርቦን ቁጥጥር አማካይነት ማዳበሪያ እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ያሉ ጋዞችን ልቀት ሊቀንስ ይችላል ፡፡ ማዳበሪያን ከመጠቀም የሚመጣ ከፍተኛ የሰብል ምርት ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን የስነ-ህይወታዊ አፈር ቁሶችን ሊጨምር ይችላል፡፡(ከምርት ስብሰባ በኋላ የሚገኙ የሰብል ቅሪቶች ፣ የዕፅዋት ሥሮች እና ማሳ ላይ የሚጨመር የተፈጥሮ ፍግ ):: ደደይኸ የግብርና አፈር ካርቦንን በመቆጣጠር የካርቦን ዳይኦክሳይድን ልቀት ይገድባል፡፡(13)\

ማዳበሪያ ምንድነው?

ማዳበሪያበቀጥታየዕፅዎትንዕድገትየሚያፋጥንየአፈርውስጥአልሚምግብአቅርቦትንየሚጨምርተፈጥሮአዊወይምማዕድናዊንጥረነገርነው፡፡ማዳበሪያበሰብልእርሻ/ማሳላይበመጨመርምርታማነትንያሳድጋል፡፡ማዳበሪያለዕፅዋትየሚፈለጉትን”Å ናይትሮÍ=”þሽየምእናፎስፎረስያሉትንዋናዋናአልሚምግቦችንበማካተትአንድ፣ሁለትወይምብዙጠቃሚየማዕድንንጥረነገሮችንየያዘነው፡፡ (1)

ሰው ሰራሽ የንግድ ማዳበሪያዎች አፈር ወስጥ ሲጨመሩ ከሚሟሙ እና በስር ዕፅዋት ጥቅም ላይ ከሚውሉ ከ14ቱ ጠቃሚ ኬሚካላዊ የዕፅዋት የማዕድን ንጥረ ነገሮች ቢያንስ አንዱን የያዘ ነው፡፡ (20)

ተጨማሪ ምርትን ለማረጋገጥ እና ማዳበሪያ በአካባቢ ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቀነስ ማዳበሪያ በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡ ይኸንን ለማሳካት ማዳበሪያን በአግባቡ እና በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል አስፈላጊ ነው፡፡ አራቱ የማዳበሪያ አጠቃቀም ስልቶች (4 Nutrient Stewardship) አራት መርሆዎችን ያመለክታሉ:- ትክክለኛ ምንጭ፣ ትክክለኛ መጠን፣ ትክክለኛ ጊዜ እና ትክክለኛ ቦታ፡፡

ለተሸሻለ ሰብል ምርት የማዳበሪያ ጠቀሜታ (4)

አንድ ሰው ለማደግና ጤናማ ለመሆን የተለያዩ አይነት እና መጠን ያላቸው ንጥረ ነገሮች በምግባችን ውስጥ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለጥሩ እድገትና ምርት ዕፅዋትም የተለያየ አይነት እና መጠን ያላቸው ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይፈልጋሉ ፡፡ ማዳበሪያዎች ጥቅም ላይ ካልዋሉ የሰብል ምርት፣ የግብርና ምርታማነት እና የአፈር ለምነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳሉ፡፡

ማዳበሪያን የመጠቀም ጠቃሚና ጎጂ ጎኖች

ጠቃሚ ጎኖች

 • ማዳበሪያን መጠቀም ተጨማሪ እና ጥራት ያለው ምግብ እንዲመረት ያረጋግጣል፡፡
 • ማዳበሪያን መጠቀም በአነስተኛ የእርሻ ማሳ ላይ ከፍተኛ ምርት እንዲገኝ ያደርጋል:: ከዚህም የተነሳ አርሶ አደሮች አዲስ የእርሻ መሬት ፍለጋ የሚያደርጉትን የደን ምንጣሮ ይቀንሳል::
 • የሰብል ምርትን ይጨምራል:: ዝቅተኛ የአፈር ጥራት ከፍ እንዲል ያደርጋል::
 • ፍግ የአፈር ልስላሴን ያሻሽላል፣ ናይትሮጂን በድጋሚ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ የአፈር አወቃቀርን እና ጥምረትን የማያሻሽሉ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች እንዲመጡ ያደርጋል፣ የአፈር ጥጥረ ነገሮች እና ውሃ በድጋሚ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል (11)::
 • ግጦሽን በማሻሻል እንሰሳት በፍጥነት እንዲወፍሩ/እንዲያድጉ ያደርጋል::
 • ለምነታቸውንና ምርታማነታቸውን ያጡ አፈሮች ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ ይችላል፡:
 • ሰብሎች በፍጥነት እንዲያድጉ ያግዛል በተለይ የተዳቀሉ ዘሮች ጥቅም ላይ ሲውሉ::

ጎጂ ጎኖች

 • ማዳበሪያን መጠቀም ፈጣን የአረም እድገትን ሊያበረታታ ይችላል::
 • ከመጠን በላይ የማዳበሪያን ናይትሮጂን መጠቀም እንደ ስንዴ፣ ጤፍ እና ሩዝ ያሉ ዕፅዋትን ውድቀት ሊያስከትል ይችላል::
 • ከመጠን በላይ እና ተገቢ ያልሆነ የማዳበሪያ አጠቃቀም እንደ ናይትሮጂን ያሉ ንጥረ ነገሮች ወደ ገፅ-ምድር እና ከርሰ-ምድር ውሀ ታጥበው እንዲሄዱ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህም የተነሳ የውሃ ጥራት ሊቀንስ እና አሳ እና ሌሎች የውሃ ውስጥ ፍጥረታት ሊጎዱ ወይም ሊሞቱ ይችላሉ::
 • ተገቢ ያልሆነ የማዳበሪያ አጠቃቀም እንደ ሜቴን እና ናይትረስ ኦክሳይድ ያሉ ጋዞች ወደ አካባቢ አየር በብዛት እንዲለቀቁ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይኸም ከአለማቀፋዊ ሙቀት መጨመር የተነሳ ለሚከሰት የአየር ጠባይ ለውጥ አስተዋፅኦ ሊያበረክት ይችላል::
 • በጥንቃቄ ጥቅም ላይ ካልዋሉ በአንዳንድ ማዳበሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች በአርሶ አደሩ ጤና ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡

4ቱ የማዳበሪያ አጠቃቀም ስልቶች ላይ ዝርዝር መረጃ

አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጲያ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ማዳበሪያን በተመለከተ ምርጥ ተሞክሮዎችን ጥቅም ላይ እንደማያውሉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ይኸ ደግሞ ውጤታማ የሰብል ምርት ከባድ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በውጤታማ የማዳበሪያ አጠቃቀም አካባቢን እና ሃላፊነት የተሞላበትን የእርሻ ልማዶችን ለመጠቀም የሚረዱትን 4ቱን የማዳበሪያ አጠቃቀም ስልቶች መጠቀም ወሳኝ የሆነው፡፡

 1. ትክክለኛ ምንጭ (The right source)(6)

ትክክለኛ ምንጭ ማለት ሰብሎች ለጥሩ ዕድገት እና ጉልምስና የሚያስፈልጋቸው ሁሉንም ንጥረ ነገሮችን የሚያቀርቡትን ትክክለኛ ማዳበሪያዎች ወይም ተፈጥሮአዊ ግብአቶችን መጠቀም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ለእያንዳንዱ የአፈር እና ሰብል ሁኔታ አንድ ትክክለኛ ምንጭ እንዳሌለ ማስታወሱ ጠቃሚ ነው፡፡ ምንጭ በሚመረጥበት ወቅት እያንዳንዱ አፈርና ሰብል የተለያየ¿ ፍልጎቶች እንዳላቸው ግንዛቤ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪም ትክክለኛ ምንጭ በሚመረጥበት ወቅት የአርሶ አደሩ ግቦች ለምሳሌ ለገበያ የሚውል ከፍተኛ ምርት ወይም ለቤት ፍጆታ የሚሆን መካከለኛ ምርት ከግንዛቤ ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡ ለተወሰነ የሰብል ሥርዓት ትክክለኛ ምንጭ ለመወሰን የሚከተሉት ቁልፍ ጉዳዮች ከግንዛቤ መግባት አለባቸው፡-

 • ለተተከለውሰብልበምክረ-ሀሳቡመሠረትየተቀመጠየማዳበሪያአጠቃቀምመጠን
 • በአፈር ውስጥ ቀድሞውን ያሉ ንጥረ ነገሮች(7)
 • በዛ መሬት/ማሳ ላይ በፊት የተተከሉ ሰብሎች
 • እንደተፈጥሮፍግአይነትያሉሌሎችየንጥረነገሮችምንጮች
 • በሰብሉ የሚፈለጉ የንጥረ ነገሮች አይነት እና መጠን የያዙ በአካባቢው የሚገኙ በጣም ወጪ ቆጣቢ ምንጮች
 • በተወሰነ ማዳበሪያ ውስጥ ያሉ ወዲያውኑ ወይም ቆይተው በሰብሉ ጥቅም ላይ የሚወሉ ንጥረ ነገሮች
 • የተጨመሩማዳበሪያዎችንውጤታማነትሊገድቡየሚችሉእንደአሲዳማነትወይምጨዋማነትያሉያፈርሁኔታዎች
 • የሚጠበቀው ጥቅም ላይ የሚውለው የማዳበሪያ መጠን (የተለያዩ ምንጮች ንጥረ ነገሮችን በተለያየ መጠን ይለቃሉ)
 • ማዳበሪያን ለመጠቀም በምክረ-ሀሳብ የተቀመጠው ቦታ (ንጥረ ነገሮች ¾ት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ በመመስረት የተለያዩ ምንጮች ትክክለኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ማዳበሪያው ቅጠል ላይ የሚጨመር ከሆነ ሙሉ በሙሉ የሚሟሙ ባለ አንድ ንጥረ ነገር ማዳበሪያዎች ትክክለኛ ምንጮች ናቸው፡፡

ትክክለኛውን የንጥረ ነገር ምንጭ መምረጥ (6)

ናይትሮጂን (N)

 • ሁሉም የN ማዳበሪያ እንደ አሞኒያ ነው የሚጀምረው:: አሞኒያ በግፊት አማካይነት በቀጥታ ወይም ወደ ተለያዩ ጠጣር እና ፈሳሽ ማዳበሪያዎች በመለወጥ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል::
 • ናይትሬት፣ አሞኒየም እና ዩሪያ በጣም የሚታወቁት የN ምንጮች ናቸው::

ፎስፎረስ (P) እና ፖታሺየም (K)

 • የ “P” እና “K” ማዳበሪዎች ፎስፌት እና ፓታሽ ማዕድናት ክምችት በቁፋሮ የሚገኙ ናቸው፡፡ በቁፋሮ ከተገኙ በኋላ ፎስፌት እና ፖታሽ ወደሚባለው ማዳበሪያዎች ይቀየራሉ::
 • አብዛኛውን ጊዜ “P” በፎስፌት መልክ በዕፅዋት ይወሰዳል::
 • ፖታሺየም ክሎራይድ (የፖታሽ ሙሪዬት ተብሎ የሚጠራው) በማዳበሪያ ምርት ውስጥ በጣም ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል የ “K” ውህድ ነው(18)::
 • ፎስፎረስን የሚያቀርቡ ማዳበሪያዎች ዳፕ፣ ኤን ፒ ኤስ እና ቲሲፒን ያካትታሉ::
 • ፖታሺየምን የሚያቀርቡ ማዳበሪያዎች ኤን ፒ ኬ እና የፖታሽ ሙሪዬትን (MOP) ያካትታሉ፡፡

2. ትክክለኛ መጠን

ትክክለኛ መጠን ማለት ለሰብሎች ጤንነት እና ዕድገት ትክክለኛ መጠን ንጥረ ነÑሮችን ማቅረብ ማለት ነው፡፡ ትክክለኛው ምንጭ አንዴ ከታወቀ በኋላ በትክክለኛ መጠን አማካይነት በቂ ብዛት /መጠን፤ የተመጣጠነ ቅንብር ፤ ያሉ አይነቶች እና ዕፀዋቱ በጣም በሚፈልጉበት ወቅት ንጥረ ነገሮች መቅረብ አለባቸው፡፡

የተለያዩ ሰብሎች የተለያየ መጠን ንጥረ ነግሮችን ይፈልጋሉ፡፡ የሚፈለጉት ንጥረ ነገሮች መጠን በሚፈለገው ምርት እና አፈሩ ንጥረ ነገሮች ማቅረብ በሚችለው አቅም ላይ ይመሰረታል፡፡ ትክክለኛ መጠንን መምረጥ የንጥረ ነገር አቅርxትን ከሚፈለገው የዕፀዋት ፍላጎት ጋር ማጣጣምን ያካትታል፡፡

ትክክለኛ መጠን የማዳበሪያ አጠቃቀምን እንዴት መወሰን እንዲሚቻል

 • የንጥረ ነገር ምንጭ: ጊዜና ቦታ አጠቃቀምን ከግምት ያስገቡ:-
 • የተለያዩ የንጥረ ነገር ምንጮች የተለያየ መጠን ንጥረ ነገር አላቸው፡፡ ለምሳሌ በንፅፅር ሲታዩ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች አብዛኛውን ጊዜ ከሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ያነሰ መጠን ንጥረ ነገር አላቸው፡፡ ስለዚህም የተተለመው የንጥረ ነገሮች መጠን ላይ ለመድረስ አርሶ አደሮች ብዛት ያለው የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች ያስፈልጋቸዋል፡፡
 • የማዳበሪያ መጠቀሚያ ጊዜም ትክክለኛ መጠን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ በዕፀዋት እድገት ወቅት ብዙ ማዳበሪያ መጠቀም ቢያስፈልግ (ስንዴ እና ጤፍን በናይትሮጂን ማዳበሪያ አብዛኛውን ጊዜ በምንጠቀምበት ወቅት) በዘር ወቀት አርሶ አደሮች አነስ ያለ ማዳበሪያ መጠቀም ይችላሉ አንድ ጊዜ ብቻ መጠቀም ከሚያስፈልገው ጋር ሲነፃፀር፡፡
 • የማዳበሪያ መጨመሪያ ቦታም ትክክለኛ መጠን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ በየተወሰ ርቀት ላይ የሚቀመጡ ማዳበሪያዎች በአነስተኛ መጠን ይጨመራሉ:: ይኽ በብተና ከሚጨመረው ያነሰ ነው ም¡ንያ~ም ከብተና ይልቅ በየተወሰ ርቀት ላይ ማዳበሪያ c=ጨመር ንጥረ ነገሮች ወደ ዕፅዋት ስሮች አቅራቢያ እንዲበዙ ስለሚያደር::
 • የዕፅዋት ንጥረ ነገሮች ፍላጎትን ይመርምሩ:-
 • የተለያዩሰብሎችየተለያየመጠንንጥረነገሮችንይፈልጋሉ፡፡ለምሳሌእንደስንዴያሉየእህልሰብሎችበአጠቃላይከፍያለመጠንይፈልጋሉእንደ ሽንብራወይምምስርካሉየጥራጥሬሰብሎችጋርሲነፃፀሩ::
 • የሚፈለጉት የንጥረ ነገሮች መጠን በታለመው ምርት ላይም ይመሰረታል:: ከፍተኛ ምርት ከፍተኛ መጠን ማዳበሪያ ይፈልጋል ምክንያቱም ዕፀዋት ከፍተኛ ምርት ለመስጠት ከፍተኛ መጠን ንጥረ ነገሮችን ማግኛት አለባቸው፡፡
 • የንጥረ ነገሮች መጠን በንጥረ ነገሮች አይነት ላይም ይመሰረታል ፡፡ በአጠቃላይ ዋና ዋናዎቹ ንጥረ ነግሮች (ናይትሮጂን ፡ ፎስፈረስ እና ፖታሺየም) በሁለተኛ ደረጃ ካሉት ንጥረ ነገሮች (እንደ ሰልፈር እና ካልሽየም ወይም ዚንክ እና xሮን) ጋር ሲነፃፀሩ በዕፀዋት ከፍተኛ መጠን ይፈለጋሉ፡፡
 • የአፈር የንጥረ ነገሮችን የማቅረብ አቅም ይመርምሩ፤-
 • ለዕፀዋት እድገት የሚያስፈልጉ አንዳንድ ንጥረ ነገሮች በአፈር አማካይነት ሊቀርቡ ይችላሉ:: ሌሎች በማዳበሪያ አማካይነት ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ በጣም ለም አፈር ንጥረ ነገሮች የማቅረብ በጣም የተሻለ ችሎታ አለው፡፡ እናም አነስተኛ መጠን ማዳበሪያ ነው የሚፈልገው፡፡ የአፈር ለምነትን እና የአፈር ንጥረ ነገሮችን የማቅረብ አቅሙን በፍጥነት ለመመርመር የሚረዱ ዘዴዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
  • የአፈር ምርመራ:- የአፈር ምርመራ ዕፅዋት መውሰድ/መጠቀም የሚችሉትን ያለ የንጥረ ነገሮች መጠንን ይለካል፡፡ ከፍተኛ የዕፀዋት ንጥረ ነገሮች መኖር ከፍተኛ የአፈር ለምነት እና ንጥረ ነገሮች የማቅረብ አቅምን ያመለክታል፡፡
  • የሰብል ምርት ታሪክ ፡- ለብዙ ወቅቶች በአነስተኛ ማዳበሪያ ወይም የፍግ መጠን ሰብሎች የተመረተበት አፈር አነስተኛ ንጥረ ነገሮች የማቅረብ አቅም እንዳለው ሊጠበቅ ይችላል፡፡
  • የአፈር ዓይነቶች፡- አሸዋማ አፈር አብዛኛውን ጊዜ ከሸክላማዎች ሲነፃፀር አነስተኛ የንጥረ ነገሮች ማቅረብ አቅም አለው፡፡
  • የአፈር ስነ-ህይወታዊ ቁስ ይዘት፡ የአፈር ስነ-ህይወታዊ ቁስ ይዘት ለዕፀዋት እድገት የሚያስፈልገውን አብዛኛውን ንጥረ ነገሮች የያዘ ነው፡፡ ከፍተኛ ስነ- ህይወታዊ ቁስ ይዘት ያለው አፈር ንጥረ ነገሮችን የማቅረብ ከፍተኛ አቅም አለው፡፡
  • ግልፅየንጥረ ነገርእጥረትምልክቶች:-የዕፀዋትእድገት፤ጥንካሬ/ጉልበትእናቀለምብዙውንጊዜየአፈርንጥረነገሮችንየማቅረብችሎታን/አቅምንያመለክታል::ለምሳሌእንድበቆሎእናስንዴያሉሰብሎችጠንካራግንድያላቸውዕፀዋትእናጠቆርያሉአረንጓዴቅጠሎችበቂየንጥረነገሮችአቅርቦትንያመለክታሉ፡፡
 • ሁሉንም ያሉ የንጥረ ነገሮች ምንጮችን ይመልከቱ:-ትክክለኛመጠንማዳበሪያንበሚወስኑበትጊዜበእርሻ/ማሳላይያሉትንሌሎችየንጥረነገሮችምንጮችአስተዋፅኦይመልከቱ፡፡ተጨማሪየንጥረነገሮችምንጮች የሚከተሉትንያጠቃልላሉ፡-
 • ብስባሽ /ኮምፖስት እና የእንስሳት ፍግ:- በብዛት ሲጨምሩ ብስባሽ እና የእንስሳት ፍግ በዕፀዋት የሚፈለጉትን አንዳንድ ንጥረ ንገሮች ሊያዋጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ብዛት ያለው ብስባሽ ወይም የእንስሳት ፍግ ማግኘት የሚችሉ አርሶ አደሮች አነስተኛ መጠን ማዳበሪያ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
 • የጥራጥሬሰብሎችእናአረንጓዴፍጎች፡- እንደሽንብራናምስርያሉጥራጥሬሰብሎችናይትሮጂንለአፈርሊያዋጡይችላሉ፡፡እናምከጥራጥሬሰብሎችጋርበፈረቃየሚ²ሩእንደስንዴያሉየእህልሰብሎችላይየሚጨመረውየናይትሮጂንመጠንሊቀንስይችላል፡፡
 • የሰብል ቅሪቶች፡- እንደ ቅጠልና ግንድ ያሉ የሰብል ቅሪቶች ንጥረ ነገሮች አሏቸው፡፡ ከፍተኛ መጠን የሰብል ቅሪቶች ወደ አፈር በድጋሚ የሚመለሱባቸው ማሳዎች ላይ የሚጨመረው የማዳበሪያ መጠን መቀነስ ይችላል፡፡

ለአንድለተወሰነሰብልትክክለኛውየማዳበሪያመጠንከተወሰነበኋላማዳበሪያበእኩልመጠንለመጨመርእንዲያስችልተደርጎልኬቱመስተካከሉንማረጋገጥወሳኝነው፡፡

ትክክለኛው መጠን ለምንድነው ጠቃሚ የሚሆነው;

ትክክለኛ መጠን ማዳበሪያን መጨመር/መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ንጥረ ነገር ከመጠን በታች ወይም ከመጠን በላይ መጠቀም በሰብል ምርት ፤በገቢ እና በአፈር ጤና ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ከመጠን በታች መጠቀም ለአነስተኛ የምርት መጠን፤ ለአነስተኛ የምርት ጥራት እና ለአፈር ለምነት መመናመን ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ ከመጠን በላይ መጠቀም ለአነስተኛ ትርፍ፤ ለአፈር እና ለውሃ ሥርዓቶች መበከልና እንደ ሩዝ፤ ጤፍ እና ስንዴ ባሉ ሰብሎች ላይ ውድቀትን ሊያሰከትል ይችላ፡፡

3. ትክክለኛው ጊዜ

ትክክለኛው ጊዜ ማለት እፀዋት ንጥረ ነገሮችን በጣም በሚፈልጓቸው ጊዜ መስጠት/መጨመር ማለት ነው፡፡ ትክክለኛው ምንጭን እና የሚጨመረውን ንጥረ ነገር መጠን ከወሰኑ በኋላ አርሶ አደሮች እፀዋት ንጥረ ነግሮችን ከሚወስዱበት ጊዜ ጋር አጣጥመው መስጠት አለባቸው፡፡ ይኼ ንጥረ ነገሮች በትክክል ጥቅም ላይ መዋላቸውን እና ጥሩ እድገት እና ከፍተኛ ምርት ለማረጋገጥ ይረዳል ፡፡

ንጥረ ነገር ለመጨመር ትክክለኛ ጊዜን እንዴት መወሰን እንደሚቻል

 • የንጥረ ነገር መጨመሪያ ምንጭን ፤ መጠን እና ቦታን ይመልከቱ:-
 • የተለያዩምንጮችንጥረነገሮቻቸውበሚለቀቁበትፍጥነትይለያያሉ፤ይኼትክክለኛየንጥረ ነገርመጨመሪያጊዜላይተፅዕኖያሳድራል፡፡ለምሳሌእንደፍግያሉየተፈጥሮምንጮችጋርሲነፃፀሩንጥረነገሮችንበዝግታነውየሚለቁት፡፡ስለዚህ የተፈጥሮምንጮችከመዝሪያ/ከተከላወቅትጥቂትሳምንታትቀደምብለውመጨመርአለባቸው፡፡ይኼሰብሎችበሚዘሩበትጊዜንጥረነገሮችመኖራቸውንለማረጋገጥይረዳል፡፡በሌላበኩልየማዕድንምንጮችበተከላወቅትሊጨመሩይችላሉ፡፡
 • የሚጨመረው መጠንም ትክክለኛ የማዳበሪያ መጨመሪያ ሰዓት/ጊዜ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ እንደ ናይትሮጂን ላሉ ከአፈር ውሰጥ በቀላሉ ለሚጠፉ ንጥረ ነገሮች ከፍ ያለ መጠን ከአንድ ጊዜ በላይ መጨመር አሰፈላጊ ነው፡፡ እናም የሚጨመሩትን ንጥረ ነገሮችን ጥቅም ለማረጋገጥ አጠቃላይ የሚጨመረው የንጥረ ነገር መጠን በአነስተኛ መጠን መከፋፈል አለበት፡፡
 • ንጥረ ነገሮች የሚጨመሩበት ቦታም ትክክለኛ ጊዜ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ ንጥረ ነገሮች በዕፀዋት ቅጠሎች ላይ መጨመር ዕፀዋቱ በፍጥነት እንዲወስአቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ስለዚህም አርሶ አደሮች ዕፀዋት ንጥረ ነገሮችን በሚፈልጉበት ትክክለኛ ጊዜ ቅጠሎቹ ላይ መጨመር ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ማዳበሪያ አፈር ውስጥ ሲጨመር ዕፀዋት ንጥረ ነገሮቹን ለመውሰድ ረጅም ጊዜ ስለሚፈልጉ ከሚፈለገው ንጥረ ነገሮች መውሰጃ ጥቂት ቀናት በፊት መጨመር አለበት፡፡
 • የንጥረ ነገሮች መጨመሪያ ጊዜን ከዕፀዋት ንጥረ ነገር ፍላጎት ጋር ያጣጥሙ:- አብዛኛዎቹ ሰብሎች በመጀመሪያ የእድገት ደረጃቸው ወቅት በቀስታ ነው ንጥረ ነገሮችን የሚወስዱት:: የንጥረ ነገሮች ፍጆታቸው ሰብሎች በፍጥነት ሲያድጉ ይጨምራል፡፡ ሲበስሉ ደግሞ ይቀንሳል:: ይኼ በተለይ እንደ በቆሎ፤ ስንዴ እና ጤፍ ላሉ ሰብሎች ጠቃሚ ነው ምክንያቱም የናይትሮጂን አጨማመር ከቁልፍ የእድገት ደረጃዎች ጋር መጣጣም አለበት፡፡ ለምሳሌ በስንዴ እና ጤፍ ላይ በናይትሮጂን የበለፀገ ንጥረ ነገር ከላይ በመጀመሪያ የእርሻ ወቅት መጨመር የእፀዋቱን የ N አወሳሰድ በማፋጠን እና ምርትን ለመጨመር ያግዛል ፡፡ ለሩዝ በ N የበለፀገ ማዳበሪያ ከላይ በመጀመሪያ የእርሻ ወቅት እና አበባ ወቅት ከፋፍሎ መጨመር የ N አወሳሰድን ያፋጥናል ምርትንም ይጨምራል፡፡
 • የንጥረ ነገር መጥፋትን ስጋት ይቀንሱ፡የአፈርንጥረ ነገሮችንመጥፋትስጋትለመቀነስየማዳበሪያመጨመሪያጊዜመታቀድአለበት፡፡ለምሳሌእንደናይትሮጂንያሉንጥረነግሮችበከባድዝናብወቅትየሚጨመሩከሆነበቀላሉይጠፋሉ፤ስለዚህበዚህ ወቅትመጨመርየለባቸውም፡፡
 • ሌሎች ቁልፍ ታሳቢዎች፡ የንጥረ ነገር መጨመሪያ ጊዜ የማሳ እና የአየር ጠባይ ሁኔታዎችንም ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡ ታሳቢ መደረግ ያሉባቸው ጉዳዮች:-
 • የሰው ሀይል መኖር ፡- ያለንን የሰው ሀይል/ጉልበት በትክክል ለመጠቀም እንደ ሌሎች የማሳ ሥራዎች ማዳበሪያ መጨመር ያለበት ከሞላ ጎደል በተመሳሳይ ጊዜ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ በዘር/ተከላ ወቅት የሚፈለግ ማዳበሪያ ዘር በሚዘራበት ወቅት መጨመር ይችላል፡፡ ይኼ በዘር ወቅት ላይ የሚውለውን የሰው ሀይል ባግባቡ ለመጠቀም ያስችላል፡፡
 • የማዳበሪያ በወቅቱ መገኘት:- ንጥረ ነገሮች በትክክለኛ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማስቻል ማዳበሪያ አስቀድሙው ይግዙ፡፡
 • የአየር ጠባይ:- ለምሳሌ የናይትኖጂን ማዳበሪያ ከላይ መጨመር ያለበት አፈር እርጥበት ሲኖረው ነው፡፡ ግን አፈሩ በጣም እርጥብ መሆን የለበትም፡፡ የንጥረ ነገርን መጥፋት ለመቀነስ እና ትክክለኛ የንጥረ ነገር አወሳሰድን ለማረጋገጥ አፈር ደረቅ ሲሆን እና ከባድ ዝናብ ባለበት ወቅት መከናወን የለበትም፡፡

4.ትክክለኛቦታ

ትክክለኛ ቦታ ማለት ሰብሎች በጣም በቀላሉ ሊያገኙት በሚችሉበት ቦታ አፈር ላይ ንጥረ ነገሮችን መጨመር ማለት ነው፡፡ ንጥረ ነገሮችን በትክክለኛ ቦታ ማስቀመጥ/መጨመር ዕፅዋት በወጉ እንዲያድጉና ከፍተኛ ምርት እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡

ለአብዛኞቹሰብሎችትክክለኛውቦታየሥርዞን/ቀጠናወይምእያደገካለውየሥርሥርዓትፊትነው፡፡አብዛኛውንጥረነገርበዕፅዋትየሚወሰደውበሥርሥርዓትአማካይነትነው፡፡እናምንጥረነገሮችንበሥርዞን/ቀጠናውስጥማስቀመጥበዕፅዋትየመመጠጥ/የመወሰድእድሉንከፍያደርገዋል፡፡

በትክክለኛቦታማዳበሪያዎችንለመጨመርእሳቤውስጥመግባትየሚገባቸውጉዳዮችየሚከተሉትናቸው:-

 • ምንጭ፣መጠንእናየንጥረነገርመጨመሪያጊዜ
 • የንጥረ ነገሩ ምንጭ ለትክክለኛው ቦታ አንድምታዎች አሉት፡፡ ለምሳሌ ፍግ በተሻለ መልኩ መጨመር የሚቻለው በብተና እና አፈር ውስጥ በማዋሀድ ነው፡፡ በሌላ መልኩ የማዕድን ማዳበሪያዎች በመትከያ ጉድÕድ አቅራቢያ ቦታን ጠብቆ ለመጨመር በጣም የሚመቹ ናቸው፡፡
 • የሚጨመረው የንጥረ ነገር መጠንም ትክክለኛው ቦታ ላይ ተፅዕና ያሳድራል፡፡ ብዙ መጠን ማዳበሪያ ሲኖር በብተና ሊጨመር ይችላል፡፡ ነገር ግን የማዳበሪያው መጠን አነስተኛ ሲሆን ቦታን ጠብቆ መጨመር ተመራጩ መንገድ ነው፡፡
 • ንጥረ ነገር የሚጨመርበት ጊዜም ትክክለኛው ቦታ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ በበቆሎ ተከላ ጊዜ ሥር ላይ በሚጨመርበት ወቅት ማዳበሪያ ዘሮች መተከል ባለባቸው መትከያ ጉድÕድ አቅራቢያ መጨመር አለበት ፡፡ ነገር ግን ከላይ በሚጨመርበት ወቅት ማዳበሪያ በአነስተኛ ጉድÕድ በተክሉ አቅራቢያ መቀመጥ/መደረግ አለበት፡፡
 • የተክል ሥሮች እያደጉ ያሉበትን ቦታ ታሳቢ ያድርጉ:- የተለያ¿ ሰብሎች የተለያየ የሥር ሥርዓት አላቸው፡፡ ለምሳሌ በቆሎ ጥ
 • ቅ እና ጠባብ ስሮች ሲኖሩት በቄላ አጭር እና በሰፊው የሚያድጉ ስሮች አሉት:: ስሮች በቀላሉ የሚጨመሩትን ንጥረ ነገሮች እንዲወሰዱ ለማረጋገጥ ማዳበሪያ በሚጨመርበት ጊዜ የተክሉን ሥሮች ከግንዛቤ ያስገቡ፡፡
 • የንጥረ ነገሮች የአፈር ውስጥ እንቅስቃሴ:- ትክክለኛ የማዳበሪያ መጨመሪያ ዘዴ እና ትክክለኛ የማዳበሪያ መጨመሪያ ቦታ የንጥረ ነገሮችን በአፈር ውስጥ በቀላሉ የመንቀሳቀስ ሁኔታ ከግምት ማስገባት አለባቸው፡፡ እንደ ፎስፎረስ ያሉ አነስተኛ የመንቀሳቀስ ባህሪይ ያላቸው ንጥረ ነገሮች በተክሉ አቅራቢያ ባሉ ቀዳዳዎች/ጉድÕ ውስጥ በብዛት መጨመር አለባቸው፡፡

አራት አይነት ዋና ዋና የማዳበሪያ አቀማመጥ ወይም አጨማመር ዘዴዎች አሉ፡-

) ብተና (broadcasting) – በማሳ ገፅ/ወለ

ላይወጥየሆነየማዳበሪያአጨማመር

ከብተና ጋር የተያያዙ ቁልፍ እውነታዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡

 • እንደ ስንዴ እና ጤፍ ላሉ ጥቅጥቅ ብለው ለሚዘሩ ሰብሎች ተስማሚ ነው፡፡
 • አጠቃላይ የእርሻ ንብርን የለምነት ደረጃ ለመጨመርም ተስማሚ ነው፡፡
 • በእጅ ወይም በማዳበሪያ መጨመሪያ መሳሪያ ሊከናወን ይችላል፡፡
 • በእጅም ሆነ በመሳሪያ በሚጨመርበት ወቅት በተቻለ መጠን ሥርጭቱ ወጥ መሆን አለበት፡፡
 • ሥር ላይ በብተና በሚጨመርበት ወቅት ማዳበሪያ በቁፋሮ አፈር ውስጥ መዋሀድ /መግባት አለበት፡፡
 • ብተና ለመተግበር ቀላል እና አነስተኛ የሰው ጉልበትን ይጠይቃል፡፡

ለ) አንድ ቦታ በብዛት ማስቀመጥ (banding):-ማዳበሪያንበአንድላይወይምከ5-8 ሳ.ሜ. ጥልቀት/ከአፈርወለልበታችየማስቀመጫዘዴ

ከዚህ ዘዴ ጋር የተያያዙ ቁልፍ እውነታዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡ ይሄ ዘዴ በሰብል መትከያ መስመሮች አቅራቢያ ማዳበሪያ መጨመር አስፈላጊ ሲሆን ተስማሚ የሆነ ዘዴ ነው፡፡

 • ይኼ ዘዴ በንፅፅር ሰፋ ባሉ መስመሮች ለሚተከሉ ሰብሎችም ተስማሚ ነው፡፡
 • ነገር ግን በተክሎች መካከል አነስተኛ ርቀት መኖር አለበት:- ለምሳሌ በቄላ እና ምስር
 • ፎስፎረስን ውጤት አልባ ለሚያደርጉ የአፈር አይነቶች ውጤታማ ዘዴ ነው፡፡
 • ወጥ የሆነ ሥርጭትን በዚህ ዘዴ አማካይነት ለማረጋገጥ በእያንዳንዱ መስመር ውስጥ እኩል መጠን ማዳበሪያን ያስቀምጡ:: ይኼ የሚከናወነው የመትከያ መስመሮችን ለሚጨመረው አጠቃላይ የማዳበሪያ መጠን በማካፈል ለእያንዳንዱ መሥመር የማዳበሪያ መጠንን በመወሰን ነው፡፡
 • ይኼ ዘዴ ሲተገበር በዘሮች እና በማዳበሪያ መካከል ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ እንዳይፈጠር ማዳበሪያ በዘሮች ስር ወይም አጠገብ በመቀመጥ በአፈር መሸፈን አለበት፡፡

) ቦታን ጠብቆ ማዳበሪያ መጨመር፡በተከላወቅትወይምከዛበኋላአነስተኛየማዳበሪያመጠንየመትከያጉድÕድአቅራቢያመጨመር

ከዚህ ዘዴ ጋር የተያያዙ ቁልፍ እውነታዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ:-

 • እንደ በቆሎ ላሉ ራቅ ራቅ ተደርገው ለሚዘሩ ሰብሎች ተስማሚ ነው::
 • ለአነስተኛ መጠን ማዳበሪያ በጣም ውጤታማው ዘዴ ነው፡፡
 • በዚህ ዘዴ አማካይነት ወጥ የሆነ የማዳበሪያ ስርጭትን ለማረጋገጥ በእያንዳንዱ የመትከያ ጉድÕድ ውስጥ እኩል መጠን ማዳበሪያ ለመጨመር የተለያየ መጠን ያላቸውን አነስተኛ ባለ እጀታ ስኒዎችን ይጠቀሙ፡፡
 • እነዚህ የመስፈሪያ ኩባያዎች/ስኒዎች ከሌሉ የጠርሙስ ክዳን ወይም ማንኪያዎን ይጠቀሙ፡፡

) በጥልቀት ማስቀመጥ፡ በእጅ ወይም ለዚህ አላማ ተብሎ በተሰራ የማዳበሪያ መጨመሪያ መሳሪያ የማዳበሪያ ፍሬዎችን በመሬት ወለል ሥር ከ5-10 ሳ.ሜ ጥልቀት ላይ ማስቀመጥ፡፡ ከዚህ ዘዴ ጋር የተያያዙ ቁልፍ እውነታዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡

 • ይኼ ዘዴ ናይትሮጂንን በሩዝ ማሳ ላይ ለመጨመር ውጤታማው መንገድ ነው፡፡
 • የዩሪያ ማዳበሪያዎች ከ 1-4 ግራም መጠን ወደ ትላልቅ ፍሬዎች በመጨፍለቅ በጥልቀት ሊጨመሩ ይችላሉ (ከመደበኛ የማደበሪያ ፍሬዎች ይልቅ)፡፡
 • ማዳበሪያን በጥልቀት ማስቀመጥ/መጨመር ከሌሎች ዘዴዎች ጋር ሲነፃፀር በሚከተሉት ምክንያቶች የበለጠ ውድ ሆኖ ይገኛል፡፡
 • የማዳበሪያፍሬዎችከፍያለዋጋ
 • ከፍተኛ የሰው ጉልበት ፍላጎት
 • ለየት ያለ መሳሪያ ማስፈለጉ

ቁልፍ ብያኔዎች

ለምነት (Fertility):-የአፈርበዘላቂነትለጥሩዕድገትእናከፍተኛምርትበማደግላይባሉተክሎችየሚያስፈልጉትንንጥረነገሮችየማቅረብችሎታ

ማዳበሪያዎች (Fertilizers):- ተክሎችን በቀጥታ የሚጠቅሙ ወሳኝ የዐፈር ውስጥ የዕፅዋት የማዕድን ንጥረ ነገሮች አቅርቦትን የሚጨምሩ የተፈጥሮ ወይም የማዕድን ንጥረ ነገሮች

መሬት ላይ መዘርጋት (Lodging):- የፍሬ ሰብሎች ግንዶች መሬት ላይ መዘረር/መውደቅ:- ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ሁኔታን የሚፈጥርና የምርት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ የሚችል

ንጥረ ነገር (Nutrient):- ለመኖር ለማደግ እና ለመራባት ሕይወት ባለው ነገር የሚፈለግ ነገር

ስነ-ህይወታዊ ቁስ (Organic Matter):- እንደ ዕፅዋት እና እንሰሳት ካሉ ሕይወት ካላቸው ነገሮች ቅሪቶች ከሚገኙ ስነ-ሕይወታዊ/የተፈጥሮ ውህዶች የተዋቀረ ቁስ እና ከተረፈ ምርቶች የአፈር ሰነ-ሕይወታዊ ቁስ የአፈር ተፈጥሮአዊ ቁስ አካል ነው፡፡

P መለኪያ (P Index) (Phosphorous Index):- የፎስፎረስን ከእርሻ ማሣ የመሟሟት አቅምን በቁጥራዊ መረጃ መልክ ለማስላት የሚረዳ የሥጋት መለኪያ መሳሪያ:- ፎስፎረስ በከፍተኛ ደረጃ የሚሟሟበትን ቦታ ላይቶ ትኩረት አድርጎ ለመሥራት ያግዛል፡፡

የፎስፎረስ መሟሟት (Phosphorus-fixation):- አፈር ላይ የሚጨመር ፎስፎረስ ከሌሎች ማዕድናት ጋር በመገኛነት የማይሟሙ ውህዶችን በመፍጠር ለሰብሎች ጥቅም ላይ መዋል የማይችልበት ሂደት

የላይኛው ህብር (plough layer) እርሻ/መሬት በሚታረስበት ወቅት ብዙ ጊዜ የሚዘጋጀው/የሚሰራው የአፈር የላይኛው ክፍል/ህብር

የአፈር ህብር/ስብጥር (soil aggregates):- አፈር የቀዳማይ ቁራጮች ህብር ነው (አሸዋ፣ ደለል እና ሸክላ):- እነዚህ በሕብረት አንድ ላይ በመምጣት የተለያየ መጠን ያሏቸው የአፈር አጀብን ይፈጥራሉ፡፡

የሚሟሟ (soluble):- በተለይ በውሀ ውስጥ መሟሟት የሚችል

ተለዋዋጭነት/መትነን፡ ፈሳሽ ውስጥ የሟሟ ፈሳሽ በትነት ወደ ጋዝነት የሚለወጥበት ሂደት

Acknowledgements

ምሥጋና:

አዘጋጆች፡ ኒዮ ብራውን:- የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ባለሙያ፤ አዲስ አበባ: ኢትየጵያ

ገምጋሚ፡ሳሙኤል ኒዮሮጌ. ፕሮግራም ማናጀር:- 4R ኒውትረንት እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና: ናይሮቢ: ኬኒያ

ቃለ መጠይቆች

ነብዩ የፀዳው ካንትሪ ፕሮጀክት ኦፊሰር:- óርም ሬድዮ ኢንተናሽናል ኢትዮጵያ: ሚያዝያ 10 ቀን 2021 በስልክ

ሸዋዬ ደርብ ወልደዩሐንስ ፕሮግራም ዳይሬክተር ኢትዮዌት ላንድስ ሚያዝያ 23 ቀን 2021 በስልክ

አባይነህ መኮንን:- ወረዳ ፕሮጀክት አስተባባሪ: ምንጃር ሸንኮራ (አማራ ክልል) ሚያዝያ 23 ቀን 2021 በስልክ

Information sources

በዚህ ርዕስ ጉዳይ ሌሎች ማጣቀሻዎችን የት ላገኝ እችላለሁ;

 1. 3M Future Wise, undated. Advantages of applying fertilizers to the land. http://www.3m.com/intl/IE/3MFutureWise/geography-farm-9-2-answers-fertilisers.htm
 2. 4R Learning Module 1 – Right Source
 3. 4Rs Module 2 – Right Rate
 4. 4Rs Module 3 – Right Place & Time
 5. Belay, F., and Oljira, A., 2016. Gender Role in Agricultural Activities in Ethiopia: Country Review. Journal of Culture, Society, and Development Vol. 22. https://core.ac.uk/download/pdf/234691181.pdf
 6. BYJU’S, undated. Fertilizers. https://byjus.com/biology/fertilizers/#:~:text=Fertilizers%20are%20chemical%20substances%20supplied,nitrogen%2C%20potassium%2C%20and%20phosphorus
 7. Farm Radio International, 2020. Backgrounder: Organic fertilizers. https://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/farm-radio-resource-pack-116/backgrounder-organic-fertilizers/
 8. Carlson, C., undated. Potassium Compounds Used In Potash Fertilizer Production On The Rise. FEECO International. https://feeco.com/potassium-compounds-used-in-potash-fertilizer-production-on-the-rise/#:~:text=Potassium%20chloride%20(KCl)%2C%20also,potassium%20compound%20in%20fertilizer%20production
 9. Morris. M, et al, 2007. Fertilizer Use in African Agriculture: Lessons Learned and Good Practice Guidelines. World Bank. https://documents1.worldbank.org/curated/en/498591468204546593/pdf/390370AFR0Fert101OFFICIAL0USE0ONLY1.pdf
 10. Gebre, G. G., et al, 2021. Gender differences in agricultural productivity: evidence from maize farm households in southern Ethiopia. GeoJournal 86: 843-864. https://link.springer.com/article/10.1007/s10708-019-10098-y
 11. Gupta, R. K., et al, 2008. Soil Solution. In Encyclopedia of Soil Science, 8th edition. https://link.springer.com/referenceworkentry/10.1007%2F978-1-4020-3995-9_555
 12. Henin, U., undated. How to create a prescription map for variable-rate seeding. OneSoil. https://blog.onesoil.ai/en/how-to-create-a-variable-rate-seeding-prescription#:~:text=Variable%2Drate%20seeding%20means%20we,rate%20seeding%20is%20financially%20advantageous
 13. Hochmuth, G., Mylavarapu, R., and Hanlon, E., 2018. The four Rs of fertilizer management. University of Florida Extension. https://edis.ifas.ufl.edu/publication/SS624
 14. Hoorman, J. J., undated. Role of Soil Bacteria. Ohioline. https://ohioline.osu.edu/factsheet/anr-36#:~:text=Bacteria%20perform%20many%20important%20ecosystem,particles%20together%20with%20their%20secretions
 15. International Fertilizer Association, undated. Fertilizers and Climate Change. https://www.fertilizer.org/public/fertilizer_Topics/Climate_Change.aspx
 16. Ministry of Agriculture and Natural Resources, 2018. Guideline for Conservation Agriculture (Amharic).
 17. Rogers, E., 2019. The 4R’s of Nutrient Management. Michigan State University Extension. https://www.canr.msu.edu/news/the-4r-s-of-nutrient-management#:~:text=The%204R’s%20of%20nutrient%20stewardship,on%20and%20in%20the%20field
 18. Raimi, A., Adeleke, R., and Roopnarain, A., 2017. Soil fertility challenges and Biofertiliser as a viable alternative for increasing smallholder farmer crop productivity in sub-Saharan Africa. Cogent Food and Agriculture, Vol 3(1). https://www.tandfonline.com/doi/full/10.1080/23311932.2017.1400933
 19. United Nations Environment Programme, 2020. Fertilizers: challenges and solutions. https://www.unep.org/news-and-stories/story/fertilizers-challenges-and-solutions
 20. YARA, undated. Why is fertilizer important for feeding the world? https://www.yara.com/crop-nutrition/why-fertilizer/feeding-the-world/#:~:text=Fertilizers%20replace%20the%20nutrients%20that,absorbed%20and%20used%20by%20crops

ይኼ ፅሁፍ 4R-Nutrient Stewardship Project (4R-NSP) በሚተገበረው Global Affairs Canada (GAC) የገንዘብ ወጪ “Cooperative Development condition Canada and fertilizer Canada” ድጋፍየተዘጋጀነው፡፡