የቤት ውስጥ ጥቃት፦ መንስኤ እና ውጤቱ

Notes to broadcasters

ለብሮድካስተሮች ማስታወሻ

በማሊ ውስጥ በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን አስመልክቶ በ2013 ዓ.ም. የወጣ ሪፖርት እንደጠቆው 38% የሚሆኑት ጥቃቶች ወሲባዊ ጥቃትን ያካትታሉ። 23 በመቶው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፅሟል። እነዚህ ጥቃቶች ሁሌም በጥንዶች መሃል ወይም ጥንድ ባልሆኑ ሰዎች በሴቶች ላይ የተፈጸሙ ናቸው።

የቤት ውስጥ ጥቃት ከሁለቱ አንዱ የፍቅር አጋር ከሚያሳዩት የባህሪ፣ ድርጊት እና አመለካከት ይመነጫል። እነዚህ ድርጊቶች አንዱ ሌላውን ለመቆጣጠር፣ ጫና ለመፍጠር ወይም የበላይነት ለማሳየት ያለሙ ናቸው። የቤት ውስጥ ጥቃት ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ሲሆን፤ በንግግር፣ በአካላዊ፣ ፆታዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥሰቶችን፣ ዛቻዎችን አልያም ጫናዎችን ያካትታል። ጥቃት የደረሰባቸውን ቤተሰቦችና ዘመዶች እንዲሁም የጥቃቱ ፈፃሚን የሚጎዳ ሲሆን በተለይም ህፃናት የበለጠ ተጎጂ ያደርጋቸዋል።

ከህግ አንፃር ሲታይ የቤት ውስጥ ጥቃት ወንጀል ነው። ሆኖም ከማህበራዊ ባህል ከሚመነጩ ተግዳሮቶች የተነሳ በማሊ የሚገኙ የጥቃት ሰለባዎች በአጥቂዎቻቸው ላይ ክስ አይመሰርቱም። በዚህ ረገድ በማሊ የሚገኙ በርካታ ማህበራት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፆታዊ ጥቃትን የተመለከተ ህግ እንዲወጣ ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

ይህ የሬዲዮ ስክሪፕት የቤት ውስጥ ጥቃት መንስኤዎችን እንዲሁም የጥቃት ሰለደረሰባቸው እና ቤተሰቦቻቸውን እንድትረዱ ያግዛችኋል። በእውነተኛ ቃለ መጠይቆች ላይ የተመሰረተ ሲሆን እነሱም የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባት፣ በፆታዊ ጥቃት ላይ የምትሰራ የህግ ባለሙያ እና መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ባልደረባን ያካተተ ነው።

ይህን ስክሪፕት በሬድዮ ጣቢያችሁ ለማዘጋጀት በድምፅ የሚተውኑ ባለሙያዎች እያንዳንዱን ሰው ሆነው እንዲተውኑ ማድረግ ትችላላችሁ። በድምፅ የሚሰሙት ባለታሪኮቹን አስመስለው የሚደመጡ ባለሙያዎች መሆናቸውን አስቀድማችሁ ለአድማጮቻችሁ ማሳወቅ ይኖርባችኋል። በተመሳሳይ ርዕስ በመመስረት በአካባቢያችሁ ያሉ ባለታሪኮችን በማናገር የራሳችሁን የሬድዮ ፅሁፍ ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ለምሳሌ ያህል ቃለ መጠይቅ የምታደርጉላቸውን የሚከተሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችላላችሁ፤

  • የቤት ውስጥ ጥቃት ምንድነው?
  • የቤት ውስጥ ጥቃት የሚከሰተው በምን ምክንያት ነው?
  • የቤት ውስጥ ጥቃት እንዴት ይገለፃል?
  • የቤት ውስጥ ጥቃት ምን አይነት ችግር ይዞ ይመጣል፤ ጥቃት የደረሰባቸውስ እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?

ማጀቢያ ሙዚቃን፣ መግቢያና መውጫውን ጨምሮ የሬዲዮ ፅሁፉ ከ30 ደቂቃ መብለጥ የለበትም።

 

Script

የፕሮግራም መሪ፦
ጤና ይስጥልኝ ውድ አድማጮች፣ እንኳን ፕሮግራማችንን ለማድመጥ መረጣችሁ።.

ዛሬ ከእንግዶቻችን ጋር ስለ የቤት ውስጥ ጥቃት ነው የምንነጋገረው። እንግዶቻችን ስለ ቤት ውስጥ ጥቃት መስነኤዎችና ውጤቶች፣ እንዲሁም በተቋማትና ግለሰቦች ስለተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ጨምረው ይነግሩናል። ጥቃቶችን ለመከላከል ከተቀመጡ ህግጋት ተግባራው ከማድረክ አንፃር በማህበራትና በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተወሰዱ ተግባራትም ጨምረው ይነግሩናል።

በዚሁ ጉዳይ ሶስት ሰዎችን እናነጋግራለን። የመጀመሪያዋ ወ/ት አሚና ትራውሬ ስትሆን፤ ።የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባት ስትሆን ሴጎ ግዛት ጆሮ በተባለ ስፍራ በሚገኝ አንድ የግል ትምህት ቤት ውስጥ መምህርት ናት። ይህ ጥቃት እንዴት እንደደረሰባት ታብራራልናለች።

ቀጥለን በቤት ውስጥ ጥቃትን ላይ ትኩረቷን አድርጋ የህግ ድጋፍ አገልግሎት የምትሰጠውን ከወ/ት ማርያም ትራውሬ ጋር እንወያያለን። እሷም ተሞክሮዋንና ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚደገፉባቸውን ዘዴዎች ታካፍለናለች። በመጨረሻም የስነ ልቦና ባለሙያና የጤና አማካሪ እንዲሁም የማሊ ስነ ልቦና ባለሙያዎች ማህበር አባል የሆኑትን አቶ ሰኜ ሳንጋሬን ጋብዘን እንወያያለን። ከአቶ ሳንጋሬ ጋር በተመሳሳይ ጉዳይ የምናወያያቸው ቢሆንም በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚደርሱ የቤት ውስጥ ጥቃቶች ከስነ ልቦና አንፃር ያላቸውን ጉዳት ያካፍሉናል።

የፕሮግራም መሪ፦
ወ/ት አሚናታ ትራኦሬ እንኳን ወደ ፕሮግራማችን መጣሽ!
አሚናታ ትራኦሬ፦
ስለጋበዛችሁን አመሰግናለሁ።
የፕሮግራም መሪ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት እንደደረሰባት ሴት ስለ ሁኔታው ብትነግሪን።

አሚናታ ትራኦሬ፦
የቀድሞ ባለቤትን ከሃያ አመታት በፊት ነው የማውቀው። በዛን ጊዜ ሁለታችንም ተማሪዎች ነበርን። ጥሩ ባህሪ ያነበረው ሰው ስለሆነባቸው ያለቤተሰቦቼ ይሁንታ ነበር ያገባሁት። ከመጀመሪያው ጀምሮ ለምን ጓደኞቼ አይሆኑም ሌሎች ወንዶችን ሳወራ ካየ በጣም ይቀና ነበር። በዚህ የተነሳ ለብዙ ቀናት ያኮርፈኝ ነበር። ለንዴቱ መወጣጫ በቀበቶ ይገርፈኝ ነበር። ሲናገረኝ እንኳን ድምፄን ከፍ አድርጌ የመለስኩለት እንደሆነ ይመታኝ ነበር። ከስራው ሲሰናበት ደግሞ ነገሮች እየባሱ መጡ። የአምስት ዓመት ልጅ ወልጄለት ስለነበር ሁሉንም ችዬ መቀመጥ ነበረብኝ። ሆኖም ቤተሰቦቼ ቀድሞም ጋብቻችንን ይቃወሙ ስለነበረ ስለሚያደርስብኝ ጥቃት አላወራላቸውም ነበር። አንድ ቀን የእጨት ወንበር አንስቶ መታኝ። ደም በደም ሆንኩ ሰውነቴ ሁሉ ቆሳሰለ። እንደዛ ጎድቶኝም ቢሆን ግን የወሲብ ፍላጎቱን እኔ ላይ ሳያረካ አይተኛም ነበር። ለቅሶዬ እንደሚያስደስተው ማስተዋል ቻልኩ። አንድ ቀን ይለወጣል ብዬ ተስፋ ባደርግም እየባሰበት እንጂ ሊሻሻል አልቻለም።

ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሁለተኛ ልጄን አረገዝኩ። ሆኖም ምንም የሚሻሻል ነገር አልነበረውም። በባለ በሚደርስብኝ ሁሉም አይነት ጥቃት ለዓመታት ተሰቃየሁ። በገንዘብም አይረዳኝም ነበር። በማስተማር በማገኛት ደሞዝ የልጆቼንና የእሱን የህክምናና የምግብ ወጪ ስሸፍን ቆየሁ። ባጭሩ የማሊ የጋብቻ ህግ ለሱ በሚሰጠው ግዴታ ይልቅ እኔ የሱን ሚና ስወጣ ኖርኩ። ህጉ ባል ሚስቱን መመገብና መጠበቅ አለበት ይላል።

በነዚህ ጊዜያት ሁሉ አንዴ እንኳን ስራ ለመስራት አልሞከረም። ሸክሙን መቋቋም ባቃተኝ ጊዜ ደግሞ ይመታኛል ይሰድበኛል። ለዓመታት የተሸከምኳቸው ፆታዊ፣ የንግግር እና አካላዊ ጥቃቶች የአዕምሮ ጤናዬን ክፉኛ ጎዱት በዚህም የተነሳ ለጭንቀት፣ ለድባቴ፣ ለብስጭት የዳረገኝ ሲሆን ለወንዶች ሁሉ ጥላቻ እንዲኖረኝ አድርጓል።

የፕሮግራም መሪ፦
ይህን ስቃይ ለዚህ ያህል ግዜ ለምን ተቋቋምሽው?

አሚናታ ትራኦሬ፦
ቤተሰቦቼ ስለቀድሞ ባለቤቴ ስላስጠነቀቁኝ በከፊሉ ራሴን እወቅስ ነበር። ቀድመው አስጠንቅቀውኝም ስለነበር ለወላጆቼ ችግሩን መናገር አልቻልኩም። በዛ ላይ ደግሞ በማሊ አንዲት ሴት ጠበኛ የሆነችውን ባሏን ትታ መሄዱ ቀላል አይደለም ምክንያቱም በተለይ ሴቶች ታጋሽ እንዲሆኑ እና ጽኑ እንዲሆኑ የባህል ጫና ስላለ ነው።

የፕሮግራም መሪ፦
ልጆችሽ ይህንን ወቅት በምን መልኩ አሳለፉት?

አሚናታ ትራኦሬ፦
ከፍቺው በፊት የ16 ዓመቱ ወንዱ ልጄ ለእኔ ኃላፊነት እንዳለበት ይሰማው ነበር። በአባቱ እና በእኔ መካከል ቆሞ እኔን እንዳያጠቃኝ ለማስቆም ይሞክር ነበር። ይህ ደግሞ በጣም ያስፈራኝ ነበር ምክንያቱም ልጄ እኔን ለማዳን ሲል በአባቱ ላይ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል፤ ይህ ደግሞ በህብረተሰባችን ውስጥ በጥብቅ የተከለከለ ቢሆንም። በአይኖቼ እንባ ሞልተው ለልጄ አባቱ ሲመታኝ ምንም እንዳያደርግ እነግረው ነበር። ሴት ልጄ ደግሞ እያለቀሰች ወደ መኝታ ክፍሏ ትገባ ነበር። በትምህርት ቤት ልጄ ጓደኞቹን ያጠቃ ነበር። ጥቃቅን ነገሮች ሁል ጊዜ ያበሳጩታል፣ ሴት ልጄ ደግሞ ሁሌም በፍርሃት እንደተዋጠች ነበር።

የፕሮግራም መሪ፦
ፍቺውን እንዴት ለመፈጸም ቻልሽ?

አሚናታ ትራኦሬ፦
ብዙ ጊዜ እንደምንለው፤ ይበቃል! ብሎ ብሎ ከቤት ሰራተኞቼ እና ከጎረቤቶቻችን ሴት ልጆች ጋር መዳራት ጀመረ። እንዲያቆም ስጠይቀው በጥፊ መታኝ፤ እጄን እስኪሰበር ድረስ በዱላ መታኝ። በዚያ ቅጽበት ንብረቶቼን ሁሉ ይዤ ወደ ወላጆቼ ቤት ሄድኩ። ስለጠላሁት ከእሱ ጋር ለመለያየት የወሰንኩት ያኔ ነበር። የደረሰብኝን ለጓደኞቼ ስነግራቸው ለጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችን የሚደግፉ ማህበራትን በማነጋገር ቅሬታ እቅርቤ ፍቺ እንድጠይቅ መከሩኝ። በፍርድ ቤት ልከተላቸው የሚገቡትን ሂደቶች ስለማላውቅ ቀላል አልነበረም። ሆኖም እንደ ዊልዳፍ (WiLDAF) ባሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ጓደኞቼ እርዳታ ፍቺ ልፈጽም ቻልኩ። አሁን የራሴን መኖሪያ እስካገኝ ከልጆቼ ጋር በወላጆቼ ቤት እየኖርኩ ነው።

የፕሮግራም መሪ፦
ለሴቶች ምን ምክር አለሽ?

አሚናታ ትራኦሬ፦
ሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል መሆናቸውን እና ማንም ሰው ሌላውን የመጉዳት መብት እንደሌለው ለሴቶች መንገር እፈልጋለሁ። ሰው ትዳር ውስጥ የሚገባው ደስተኛ ለመሆን እንጂ ለትዳር ጓደኛ ባሪያ ለመሆን አይደለም። አንዲት ሴት ህይወቷን ስታጣ ልጆቿ የመጀመሪያዎቹ ተጎጂ ናቸው። ሳይዘገይ ውሳኔ ማድረግ ያስፈልጋል። ከነበርኩበት ሁኔታ ለመውጣት በመቻሌ እኔ እድለኛ ነኝ። ግን ስንት ሴቶች ህይወታቸውን አጥተዋል? ቆራጥ ውሳኔ ማድረጉ አስፈላጊ ነው፣ አለበለዚያ ቀጣይ ተጠቂ ልትሆኚ ትችያለሽ።

የፕሮግራም መሪ፦
አመሰግናለሁ አሚናታ ትራኦሬ። የዊልዳፍ የቤት ውስጥ ጥቃት ጠበቃ እና ልዩ ባለሙያ ከሆኑት ወ/ሮ ማርያም ትራኦሬ ጋር ደግሞ ቆይታ እናድረግ። ዊልዳፍ ማሊ ወደ ሃያ የሚጠጉ ማህበራት እና ሃምሳ አባላት ያሉት ጥምረት ሲሆን የሴቶች እና ህጻናት መብቶች ለማስጠበቅ እና ለማስከበር ያለመ ተቋም ነው።

ግብዣችንን ስለተቀበልሽ እናመሰግናለን። የቤት ውስጥ ጥቃት ምንድን ነው ማርያም?

ማሪያም ትራኦሬ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት የአጋር ወይም የቀድሞ አጋር ባህሪ፣ድርጊት እና አመለካከት ሲሆን ይህም አጋርን ለመቆጣጠር እና የበላይ ለመሆን ያለመ ነው። ይህ ጥቃት የቃላት፣ የአካል፣ ጾታ ላይ የተመሰረተ ወይም ኢኮኖሚያዊ ማስፈራሪያዎችን የያዘ ነው።

የፕሮግራም መሪ፦
በማሊ የዚህ ዓይነቱ ጥቃት ሁኔታ ምን ይመስላል?

ማሪያም ትራኦሬ፦
እንደሌሎች ሃገራት ሁሉ በማሊም የቤት ውስጥ ጥቃት አሳሳቢ ሆኖ ቀጥሏል። የምንኖረው የወንዶች የበላይነት በሚንጸባረቅበት ማህበረሰብ ውስጥ ነው። ባልየው የቤተሰብ አስተዳዳሪ ሆኖ ይታያል። የቤተሰቡን ሸክም በዋነኝነት የሚሸከመው እሱ ነው። ሚስትን በተመለከተ ደግሞ ባሏን መታዘዝ እንዳለባት ይጠበቃል። ይህ የኃይል አለመመጣጠን ብዙውን ጊዜ የቤት ውስጥ ጥቃትን ያስከትላል።

ለምሳሌ አንዳንድ ሴቶች በባሎቻቸው ተቃውሞ የተነሳ ትምህርታቸውን ወይም ሙያዊ ሥራቸውን ለመቀጠል ሲቸገሩ አስተውለናል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት በማሊ ውስጥ ከ15 እስከ 49 ዓመት ከሆናቸው ከሁለት ሴቶች መካከል በአንዷ ቢያንስ አንድ ጊዜ በሕይወቷ አካላዊ፣ ስሜታዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት ደርሶባታል። በተመሳሳይ በዚሁ የእድሜ ክልል ባሉ ሴቶች ከአጋራቸው በሚለያዩበት ወቅት ከሁለት ሴቶች መካከል በአንዷ ስሜታዊ ወይም አካላዊ ጥቃት ይደርል።

እንደ አለመታደል ሆኖ፤ አብዛኛውን ጊዜ ሴቷ ለዚህ ጥቃት አጋሯን እንድትታገስ አልፎ ተርፎም ይቅር እንድትል የማህበራዊ ዓውድ ያስገድዳታል። ቤታቸውን ጥለው የሚሄዱት ሴቶች ደግሞ በህብረተሰቡ ዘንድ መገለል ይደርስባቸዋል። ነገር ግን ሁከት፣ በሌላው የትዳር ጓደኛ ላይ የሚደርሰው ስቃይ፣ የጋብቻን ህይዎት ስምምነት ከማበላሸት በተጨማሪ የጥንዶቹን ልጆች እጣ ፈንታ ያጨልማል።

በማሊ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የቤት ውስጥ ጥቃትን በሁሉም መልኩ ያወግዛሉ። ነገር ግን ተደጋጋሚ የተሃድሶ ጥሪዎች ቢኖሩም፣ ይህን መሰል ጥቃት በዘዴና በብቃት ለመፍታት እየተገኘ ያለው ለውጥ አነስተኛ ነው።

የፕሮግራም መሪ፦
በማሊ የቤት ውስጥ ጥቃት መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

ማሪያም ትራኦሬ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት ብዙ ምክንያቶች አሉት። የትምህርት ምክንያት አለ። ልጆች በትምህርት ቤትም ሆነ በቤተሰብ ውስጥ ሁሉም ችግሮች በኃይል በሚፈቱበት አካባቢ ውስጥ ሲያድጉ ይህንን ባህሪ ይኮርጃሉ።

በማሊ ማህበረሰብ ውስጥ እናቶችን፣ እህቶችን እና ሴት ልጆችን የማያካትት ግን ሚስቶችን በሚመለከት የማይጠቅሙ ብዙ አመለካከቶች አሉ። ለምሳሌ እናቴን እወዳታለሁ፣ እህቴን እወዳታለሁ፣ ልጄን እወዳታለሁ፣ ግን ባለቤቴን ማመን የለብኝም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አድልዎ አስከትሎ የሚከሰት ነው። በማሊ ማህበረሰብ ውስጥ ወንዱ በተለምዶ በጣም አስፈላጊ ነው ተብሎ ይታሰባል ምክንያቱም ሴቷን የሚያገባው፣ ቤተሰቡን የሚመግብው እና የሚንከባከበው እሱ ነው ተብሎ ስለተፈረጀ ነው። በቤተሰብ ንብረት መከፋፈል እንኳን በልማዳችን መሰረት፤ ወንዱ የሴቷን ሁለት እጥፍ ነው የሚቀበለው። ስለዚህ ወንዶች ሴቶች የበታች ናቸው ብለው ካሰቡ ወይም ሴቶች ከወንዶች እኩል ስልጣን የላቸውም ብለው ካሰቡ ሴቶቹ የመጠቃት እድላቸው የሰፋ ነው። በመሠረቱ የቤት ውስጥ ጥቃት የማህበራዊ ኢፍትሃዊነት ውጤት ነው።

የፕሮግራም መሪ፦
ከጥቃት የተረፉ ሴቶችን ለመርዳት ድርጅትዎ ምን እየሰራ ነው?

ማሪያም ትራኦሬ፦
በርካታ የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከቤት ውስጥ ጥቃት ለተረፉ ሴቶች የህግ እና ማህበራዊ ድጋፍ ይሰጣሉ። እኛ እራሳችን በጭንቀት ውስጥ ላሉ ሴቶች እና ህጻናት መጠለያ አለን። በተመሳሳይ፤ ሴቶች ብሶታቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ የሚረዱ የህግ አውደ ጥናቶች አሉ። ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚያዳምጧቸው እና የሚያረጋጋቸው የስነ-ልቦና ባለሙያዎች እርዳታ የሚያገኙበትም አኳኋን ይኖራል። ከዚያም የሴቶችን መብት በተመለከተ እና ሴቶችን ከቤት ውስጥ ጥቃት በሚከላከሉ ህጎች ላይ የስልጠና፣ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና መረጃ ማግኛ ዐውደ ጥናቶችን እናዘጋጃለን።

የፕሮግራም መሪ፦
በማሊ የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚቃወሙ ህጎችን ለማስከበር አስቸጋሪ የሚያደርገው ምንድን ነው?

ማሪያም ትራኦሬ፦
ብዙ የቤት ውስጥ ጥቃት ፈጻሚዎች ህጉ በትዳራቸው ጣልቃ መግባት የለበትም ብለው ያምናሉ። የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባቸው ደግሞ የተፈጠረው በራሳቸው ስህተት ምክንያት እንደሆነ ስለሚያምኑ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል። ለዚህም ነው በየዕለቱ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች ድርጊቱን የሚደብቁት፣ የሚያሳንሱት ወይም ጊዜያዊ ነው ብለው የሚያምኑት። ​​ይዋል ይደር እንጂ አጥፊው ተለውጦ ከድርጊቱ ይቆጠባል ብለው ብለውም ስለሚያምኑ ነው።

ከቤት ውስጥ ጥቃት የተረፉ ሴቶች ጥቃቱ እንዲቆም ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ በአጥቂው ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አይፈልጉም። በተጨማሪም በልጆች ወይም በሁለቱም ቤተሰቦች የሚደርሰው ማኅበራዊ ጫና፤ አጥቂው ተጎጂዋን ጥሎ ሲሄድ፣ ሲዘልፋት ወይም ሲደበድባት የትዳር ጓደኛዋ ላይ ሕጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ሊቆጥባት ይችላል። የማሊ ሴቶች ከትዳር ህይወታቸው እና ከልጆቻቸው የወደፊት ህይወት ጋር በጣም የተቆራኙ ስለሆኑ ለብዙ አመታት የቆየ የትዳር ህይወታቸውን ለማፍረስ ከመወሰናቸው በፊት አጋሮቻቸውን ከመጠን በላይ መታገስ እንዳለባቸው ያስባሉ።

የፕሮግራም መሪ፦
የቤት ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል ህጎችን ለማስከበር ምን ያስፈልጋል?

ማሪያም ትራኦሬ፦
ህገ መንግስታችን በወንዶችና በሴቶች መካከል እኩል እድል እንዲኖር አድርጓል። አንዳንድ የአካል እና ወሲባዊ ጥቃቶች በህግ ይቀጣሉ። የቤት ውስጥ ጥቃት የሚያስከትለውን መዘዝ በተመለከተ ግንዛቤን የሚጨምሩ ተግባራትን በመጨመር ህግን ማስከበር ያስፈልጋል። እንዲሁም የቤት ውስጥ ተጠቂዎችን ለመጠበቅ እና የቤት ውስጥ አጥቂዎችን በጥብቅ ለመቅጣት አገራዊ ማዕቀፍ መፍጠር አለብን።

ለምሳሌ የልጃገረዶች የትምህርት ተደራሽነት መሻሻል፣ የሴቶች የገቢ ማስገኛ እድሎች እና የሴቶች የተሻለ ውክልና በሁሉም የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የአመራር ቦታዎችን ጨምሮ ፋይዳ ይኖረዋል። ወንዶች ሊያደርጉ የሚችሉትን ማንኛውንም ነገር ሴቶች በሥራ ቦታም ሊሠሩ ይችላሉ። ሴቶችና ወንዶች ለሀገር ልማት በጋራ መስራት አለባቸው።

የፕሮግራም መሪ፦
በጣም አመሰግናለሁ ማርያም። አሁን ደግሞ የሥነ ልቦና ባለሙያ፣ የጤና አማካሪ እና የማሊ ሳይኮሎጂስቶች ማኅበር አባል የሆነውን ሳንጋሬ ሰኝን እናገኛለን።

አቶ ሳንጋሬ፣ አንዳንድ ወንዶች በአጋሮቻቸው ላይ ጥቃት እንዲያደርሱ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?

ሳንጋሬ ሰኝ፦
አንዳንድ ወንዶች በተፈጥሯቸው ግልፍተኛ ስለሚሆኑ ጠበኛ የመሆን እድላቸው ከፍተኛ ነው። በማሊ ባህል አንድ ሰው ሚስቱን የበላይ ሆኖ መግዛቱ “የተለመደ” እንደሆነ ያስባል። ታዛዥ ካልሆንች ወደ መስመር ያስገባታል። እነዚህ ወንዶች ሚስቶቻቸውን ሲመቱ ዓላማው ተገዢ እንድትሆን ማድረግ ነው። ሚስትየዋ እምቢ ካለች፤ ለሷ አስቸጋሪ እና እንዲያውም ለሞት ልትዳረግ ትችላለች። ሆኖም የቤት ውስጥ ብጥብጥ መንስኤዎች የተለያዩ ናቸው። ከአስተዳደጋችን፣ ማህበረሰቡ ለሴቶች ካለው ጭፍን አስተሳሰብ እና በማህበረሰባችን ውስጥ ለወንዶች ተዳልቶ ከተሰጡ ጥቅሞች ሊመነጭ ይችላል።

የፕሮግራም መሪ፦
ለምንድነው የተበደሉ ሴቶች የትዳር አጋሮቻቸውን ጥለው ለመሄድ የማይፈልጉት?

ሳንጋሬ ሰኝ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ከቤት ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ የማይሆኑባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ። በመጀመሪያ፣ ህብረተሰቡ ሴቶች ልጆቻቸው በህይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ መሰቃየት አለባቸው ብሎ ያምናል። ሌሎች በርካታ ምክንያቶችም አሉ። ተጠቂዎች ብዙ ጊዜ ያፍራሉ፣ በደለኛ እና አቅመ ቢስ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ሌሎች አይረዱኝም ወይም ታሪኬን አያምኑም ብለው ይሰጋሉ። ወንዱ ጸባዬን አሻሽላለሁ ብሎ ቃል ስለሚገባ ብቻ ሊለወጥ ይችላል ብለው ያምናሉ።

የእሱ ዛቻ እና የልጆቻቸው የወደፊት እጣ ፈንታ ያስጨንቃቸዋል። እሱን ጥለው ቢሄዱ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ያስፈራቸዋል። ለብዙ ዓመታት የገነቡት ህይወትን እንዳያጡት ይሰጋሉ። ብቻቸውን መወጣት እንደማይችሉ ያምናሉ። ቤተሰብን “ለመፍረስ” መንስኤ መሆናቸው ያሳስባቸዋል። የሚጠብቃቸውን ሕጎች ችላ ይላሉ ወይም ሕጎቹ ከለላ ሊሆኗቸው እንደማይችሉ ያምናሉ። ባሎቻቸውን ቢወዷቸውም አስነዋሪ ባህሪያቸውን ግን አይወዱላቸውም።

ስለዚህም በሚያምኑት ብቻ ሳይሆን በአመለካከታቸው ጭምር ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል።

የፕሮግራም መሪ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች እና ልጆቻቸው ምን መዘዝ ይጋፈጣሉ?

ሳንጋሬ ሰኝ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት አንዳንድ ሴቶች በራሳቸው የመተማመን ስሜታቸውን ያዳክማል። እነዚህ ሴቶች ከአሁን በኋላ ብቻቸውን ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ እና በማንኛውም ጊዜ የግድ መመራት እንደሚያስፈልጋቸው ተደርጎ ይወሰዳል። ውርደት እና ግራ መጋባት ይሰማቸዋል። በእንቅልፍ እጦት ይቸገራሉ፤ በባላቸው ጫና ምክንያት በማህበራዊ ሁኔታዎች ይሰቃያሉ።

ይህ ሁኔታ ደግሞ በልጆች ላይ የበለጠ ውስብስብ ያደርገዋል። በገዥነት እና በጥቃት ላይ የተመሰረተ አውድ ውስጥ ይኖራሉ። በወላጆቻቸው መካከል ለመምረጥ ስለሚገደዱ በጭንቀት ይኖራሉ። ከዚህ በተጨማሪ በቤተሰብ ውስጥ ስለ ጥቃት እምብዛም በግልጽ አይወራም። በአጠቃላይ በነዚህ ሁኔታዎች ዙሪያ ያለው ዝምታ እና እገዳ ልጆቹ ለሚመለከቷቸው እና ለሚያደርጉት ድርጊት ማብራሪያ አይሰጣቸውም ማለት ነው። ስለዚህም ስሜታቸውን የመግለጽ ወይም የመጽናናት እድል የላቸውም። በጭንቀት እና በድንጋጤ ውስጥ ከቀሩ ደግሞ እነዚህ ልጆች እድገታቸው ላይ ተጽእኖ የሚፈጥሩ ስሜታዊ እና የባህርይ ችግሮችን ሊጋፈጡ ይችላሉ።

የፕሮግራም መሪ፦
የእናንተን አገልግሎት የሚፈልጉ የቤት ውስጥ ተጠቂዎች በየትኛው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሴቶች ናቸው?

ሳንጋሬ ሰኝ፦
በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች አሉ። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ከአምስት ዓመት በላይ በአጋርነት የቆዩ ሴቶች ናቸው። እስካሁን የኔን አገልግሎት ካገኙት በዕድሜ ትልቋ ለ ለ45 ዓመታት በአጋርነት የቆዩት የ63 አመቷ ሴት ናቸው። የአካል ጥቃት ሰለባ ነበሩ።

የፕሮግራም መሪ፦
ይህንን ቃለ ምልልስ ለመደምደም ምን ይላሉ?

ሳንጋሬ ሰኝ፦
የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች ሌት ተቀን ልንደግፋቸው ዝግጁ እንደሆንን መናገር እፈልጋለሁ። ምንም እንኳን በማሊ ውስጥ ያሉትን ህጎች ለማስከበር አስቸጋሪ ቢሆንም፤ የምንኖርበት ማህበረሰብ ለእነሱ በጣም ምቹ ባይሆንም፤ በማህበራቱ እና በመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኩል አሁንም ተስፋ አለ። ሁል ጊዜም ቢሆን ሴቶቹ እና ህጻናት ሰምተው የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ።

የፕሮግራም መሪ፦
አቶ ሳንጋሬ ስለሰጡን ማብራሪያ እናመሰግናለን።

ወ/ሮ አሚናታ ትራኦሬ ወ/ሪት አሚናታ ትራዕሬ እና ወ/ሪት ማርያም ትራኦሬም ለአበክቶዋቸው እናመሰግናለን።

በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አካላዊ ጥቃትን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ፣ ጾታዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃትንም ያካትታል። ሁሉንም ማህበረሰቦች፣ ያደጉ ወይም በማደግ ላይ ያሉ፣ እና ሁሉንም ማህበራዊ መደቦች ይነካል። መዘዙ በአጠቃላይ ህብረተሰቡን አጥፊ ነው።

የቤት ውስጥ ጥቃት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች፤ ያደጉ ወይም በማደግ ላይ ያሉ፤ መደቦችን ይነካል። መዘዙ በአጠቃላይ ህብረተሰቡን አጥፊ ነው።

የዛሬው ፕሮግራማችን ማገባደጃ ላይ ደርሰናል። ለሁሉም እንግዶቻችን እና ለአድማጮቻችን ሁሉ እናመሰግናለን። በቅርቡ በሌላ ፕሮግራም እንመለሳለን።

Acknowledgements

ማጣቀሻዎች

የደህንነት ጥናት ተቋም ባወጣው ሪፖርት (https://issafrica.org/fr) ከ15 እስከ 49 የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የማሊ ሴቶች ውስጥ ከሁለቱ አንዷ የአካል ወይም ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባታል።

This resource was produced through the “HÉRÈ – Women’s Well-Being in Mali” initiative, which aims to improve the sexual and reproductive health well-being of women and girls and to strengthen the prevention of and response to gender-based violence in Sikasso, Ségou, Mopti, and the district of Bamako in Mali. The project is implemented by the HÉRÈ – MSI Mali Consortium, in partnership with Farm Radio International (RRI) and Women in Law and Development in Africa (WiLDAF) with funding from Global Affairs Canada.

Information sources

ቃለ መጠይቆች:

ወ/ሪት አሚናታ ትራኦሬ፣ ከጾታ ላይ የተመሰረተ ተጠቂዎች እና የግል ትምህርት ቤት መምህር በሴጉ ክልል፣ ጆሮ። እ.ኤ.አ ግንቦት 26 ቀን 2022 ዓ.ም. የተደረገ ቃለ መጠይቅ።

ወ/ሮ ማርያም ትራኦሬ፣ በዊልዲኤፍ ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት ልዩ ባለሙያተኛ። እ.ኤ.አ ሰኔ 15 ቀን 2022 ዓ.ም. የተደረገ ቃለ መጠይቅ።

አቶ ሴኝ ሳንጋሬ የስነ-ልቦና ባለሙያ፣ የጤና ተግባራት አማካሪ እና የማሊ ሳይኮሎጂስቶች ማህበር አባል ናቸው። እ.ኤ.አ ሰኔ 13 ቀን 2022 ዓ.ም. የተደረገ ቃለ ምልልስ።