ስለ... የሬዲዮ ስክሪፕቶችን እያነበብክ ነው። ግብርና
የቁም ከብት በሽታዎችን ስለመቆጣጠር አጠቃላይ መረጃ :- Coccidiosis በበጎች እና በፍየሎች
መግቢያ ርእሰ ጉዳዩ ለአድማጮቻችን ለምን ይጠቅማል? አርሶ አደሮች ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ በሽታዎችን እንዴት እንደሚከላከሉ እንዲያውቁ አርሶ አደሮች የኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ምልክቶችን ለይተው እንዲያውቁ አርሶ አደሮች የቁም እንስሳት መጠላያዎችን በንጽህና አያያዝ ውጤታማ መንገዶችን እንዲለምዱ አርሶ አደሮች ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ እንዴት እንደሚተላለፉ እንዲውቁ ጥቂት ቁልፍ መረጃዎቸ? ኮክሲዲዮሲስ እና ማይኮፕላዝሞሲስ ዶሮ ፣ ከብት፣ በግና ፍየልን የሚያጠቁ ዝርያቸው…
የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የመጤ ተምች መንጋን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ መጤ ተምቹ
ኒዮ ብራውን፡- እንደምን አደራችሁ (ዋላችሁ/አመሻችሁ)! ዛሬ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የመጤ ተምች መንጋን ለመከላከል እንዴት እየጣሩ እንደሆነ እና ማሳቸው ላይ ትልቅ ጉዳት ከማድረሱ በፊት እንዴት እየተከላከሉት እንደሆነ እናወራለን፡፡ የድምፅ ግብአት፡- ኒዮ ብራውን፡- በኢትዮጵያ በልግ አየተባለ የሚጠራው ደረቅ ወቅት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሰሜን ምዕራብ እና ሰሜን መካከለኛ ክፍል ወደሚገኘው የአማራ ክልል ተጓዝኩ፡፡ በአማራ ክልል ከ85 ከመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ…
የዕቀባ እርሻ
መሸጋገሪያ ድምፅ አቅራቢ 1: ጤና ይስጥልኝ ! ወደ አርሶ አደር ፕሮግራምዎ እንኳን በሰላም መጡ ! የዛሬ ፕሮግራማችን የዕቀባ እርሻ እና የአነስተኛ የእርሻ ድግግሞሽ ጠቀሜታ ላይ ያተኩራል፡፡ የትዮጵያ አርሶ አደሮች ምርትን ይጨምራል ብለው በመተማመን ማሳዎቻቸውን ደጋግመው የማረስ ዝንባሌ አላቸው፡፡ አነስተኛ የእርሻ ድግግሞሽ ከማሳዎቻቸው ማግኘት የሚችሉትን የምርት መጠን እንዳያገኙ ምክንያት እንደሚሆንባቸው ያምናሉ፡፡ በእርግጥ አይደለም አንዴ፣ ሁለቴ፣ ለብዛኛዎቹ ሰብሎቻቸው…
ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምችን በአንክሮ መከታተል: የቦቆሎ ምርትዎን እንዳያወድም ተምቹን መቆጣጠር
አቅራቢ: ጤና ይስጥልኝ አድማጮች ፡፡ በዛሬው ፕሮግራማችን የቦቆሎ ሰብሎቻቸው በፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች እንዳይጠቃ ጥረት እያደረጉ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ የኢትዮጵያዊ ሴት አርሶ አደር ወይዘሮ አይናዲስ ተመኩሮን እናካፍላችኋለን፡፡ ወይዘሮ አይናዲስ እባክዎትን ስምዎን ለአድማጮቻችን ያስተዋውቁልኝ፡ ወይዘሮ አይናዲስ: አመሰግናለሁ፡፡ ስሜ አይናዲስ ጥላሁን እባላለሁ፡፡ የምኖረው በጎጃም ዞን በምትገኝ አብደጎማ ጣቢያ ነው፡፡ ዕድሜዬ 45 ዐመት ሲሆን…
መነሻ: የገብስ ምርት በኢቲዮጵያ
ይህ ርዕሰ ጉዳይ ለአድማጮች አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ምንድነው ? ገብስ በኢትዮጵያ ባህላዊ ሰብል ነው፡ ፡ በአገሪቱ ለተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች በመዋል ጥልቅ ታሪክ አለው፡፡ የብቅል ገብስ ምርት በጣም አጭር ታሪክ ያለው ሲሆን አመራረቱም ከ1920ዎች መጀመሪያ ጀምሮ በኢትዮጵያ የጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ መቋቋም ጋር ተያይዞ በዋናኛት ከቢራ ዝግጅት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ በደጋማ አካባቢዎች የብቅል ገብስንማምረት በኢንድስትሪ ግባአትነቱ…
ተባይ መከላከያ ኬሚካልን በጥንቃቄ መጠቀም፡የአዲሱ ተምች ሁኔታ በኢትዮጵያ
የመግቢያ ድምፅ 1ኛ አቅራቢ : ጤና ይስጥልኝ እንኳን ወደ አርሶ አደር ፕሮግራማችሁ በሰላም መጣችሁ፡፡ ዛሬ ፀረ ተባይ ኬሚካሎችን እንዴት ተጠንቅቀን መጠቀም እንደምንችል እንነጋገራለን፡፡ በርካታ አርሶ አደሮች እንደነ ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ያሉ አደገኛ ተምቾችን ለመቆጣጠር ኬሚካል እንደሚጠቀሙ እናውቃለን፡፡ ሆኖም ግን ኬሚካሎችን መጠቀም የራስዎን፣ የቤተሰብዎን፣ እና የደምበኞችዎን ጤና ይጎዳል፡፡ 2ኛ አቅራቢ: ነገር ግን አደጋዎቹን የምንቀንስባቸው ዘዴዎችም አሉ፡፡…
መነሻ: በዕቀባ እርሻ ቋሚ የመሬት ሽፋንን መጠቀም
ይህ ርዕሰ ጉዳይ ለአድማጮች አስፈላጊ የሚሆነበት ምክንያት ምንድነው ? ይህ ርዕሰ ጉዳይ ለአድማጮች አስፈላጊ የሚሆነበት ምክንያት ምንድነው ? መሬትን መሸፈን ለአፈር ጤናማነት እንዴት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ፤ የተለያዩ የመሬት አሸፋፈን ዘዴዎች፤ መሬትን ለመሸፈን የሚጠቅሙ የሰብል ዓይነቶች እና በበለጠ የሚጠቅሙ ተረፈ ምርቶች ፤ የሚያስፈልገው የመሸፈኛ መጠን (በዕቀባ እርሻ ቢያንስ 30 በመቶ በተረፈ ምርት መሸፈን እንዳለበት ይመከራል፡፡) ማሳ ላይ…
ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች
A. መግቢያ ስፖዴፕቴራ ፈራጂፔርዳ በሚል ሳይንሳዊ ስያሜው የሚታወቀው ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች የምግብ ሰብሎች ዋነኛ ተምች ነው፡፡ እጩ (የሳትእራቶች ) የበቆሎ ከፍ ያሉ ቡቃያዎች መመገብን ይመርጣሉ፡፡ ሆኖም ግን ዳጉሳ ፣ ማሽላ ፣ ሩዝ ፣ ስንዴ፣ ሽንኮራ አገዳ ፣ እና አትክልቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ሰብሎችንም እንደሚመገብ ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡ ተምቹ የመነጨው በሰሜናዊ እና ደቡባዊ የአሜሪካ ሞቃታማ እና…
በደቡብ ወሎ አርሶ አደሮች ማሽላን በመንከባከብ ኑሮአቸውን እያሻሻሉ ነው
ነፃነት ኃይሉ፡ ጤና ይስጥልን፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የደቡብ ወሎ ዞን አርሶ አደሮች የማሽላ ምርታቸውን ተንከባክበው እንዴት ኑሮአቸውን እንዳሻሻሉ እንመለከታለን፡፡ የድምፅ ግብዓት፡- የመኪና ድምፅ እና የዝናብ ድምፅ፣ ከስር በትንሹ ይሰማል ነፃነት ኃይሉ፡ ወሩ ነሓሴ ነው፡፡ ይህ ወቅት በአብዛኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች ዝናባማ የክረምት ወቅት ነው፡፡ መሬቱ ረጥቦ አካባቢው አረንጓዴ ለብሷል፡፡ መላከዓ ምድሩ ማራኪ ነው፡፡ በመንገዳችን ላይ…
የመሬት አዘገጃጀት ለባቄላ
አቅራቢ: እንኳን ወደ (የሬድዮ ፕሮግራሙ) በደህና መጡ፡፡ ዛሬ ከርዕሰ መዲናችን አዲስ አበባ ወጣ ብለን በአማራ ክልል የበቃሎ ቀበሌ ማህበረሰብን እየጎበኘን ነው፡፡ በባቄላ ዙሪያ እንነጋገራለን፡፡ ሰኔ ወር የመጀመሪያው ሳምንት ነው፡፡ የባቄላ ዘር የሚዘራበት ወቅት ደርሷል ማለት ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከ ዮሃንስ ከሊለ እና ከአስካለ ካሳየ ጋር መሬታቸውን እንዴት እያዘጋጁ እንደሆነ እያነጋገርኳቸው ነው ፡፡ ይህ መሬቱ እና…
- « Previous
- 1
- 2
- 3
- Next »