የጋዜጠኞች አሰራር መመርያ: በርቀት ለማሰራጨት የበይነ መረብ መሳርያዎችን መጠቀም

Script

Save and edit this resource as a Word document

ከርቀት ለማሰራጨት እንዲረዳኝ የበይነመረብ መሳርያ ስርአቶችን ለምን መጠቀም ያስፈልገኛል?

የጊዜ እጥረትን ጨምሮ በገንዘብ ወይም የሎጂስቲክስ ምክንያቶች የራዲዮ ጋዜጠኞች ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉላቸውን ሰዎች በአካል ለማግኘት ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አንድን ታሪክ በቦታው በመገኘት መዘገብ ወይም ከሰዎች ጋር ፊት ለፊት መገናኘት ለጋዜጠኞች እና ለሌሎችም ከፍ ያለ አደጋ ሊኖረው ይችላል፡፡ ጥሩው ነገር ግን አሰራጮች ከአርሶ አደሮች ወይም የግብርና ባለሙያዎች ጋር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ፣ የሚሠሩ ታሪኮችን በተመለከተ ስብሰባ ለማድረግ፣ ቀጥታ በሚተላለፉ ወይም አስቀድመው በተቀረጹ የራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የፓነል ውይይት ለማድረግ፣ የማሕበረሰብ አድማጭ ቡድኖችን ለመሰብሰብ እና ሌሎችንም የስርጭት ሥራዎች ለመሥራት መጠቀም የሚያስችሏቸው ብዙ የበይነመረብ መሳርያ ስርአቶች አሉ፡፡ ይህ የአሰራር መመርያ የሚከተሉትን ጨምሮ አንዳንድ በጣም የሚያገለግሉ የመሣርያ ስርኣቶችን ይሸፍናል፡-

  • ዙም
  • ስካይፕ
  • ጉግል ቻት እና ጉግል ሚት (በፊት ጉግል ሃንግአውትስ ይባል የነበረው)
  • ዋትስአፕ
  • ቴሌግራም

እነዚህን የመሳርያ ስርአቶች ከርቀት ለማሰራጨት እንዴት መጠቀም እችላለሁ?

እያንዳንዱ መሳርያ በመጠኑ የተለያዩ ተግባሮች እና ገጽታዎች አሉት (በሚቀጥለው ክፍል እንደተብራራው)፣ ባጠቃላይ ግን የሚከተሉትን ለማድረግ ያገለግላሉ፡-

  • የድምጽ እና/ወይም የቪዲዮ ቃለ መጠይቆችን ለማድረግ
  • ከራዲዮ ጣቢያ ሠራተኞች ጋር አንድ ላንድ ወይም በቡድን ጥሪ ለማድረግ
  • የወርድ እና ፒዲኤፍ ሰነዶችን፤ የስእል እና ቪዲዮ ሰነዶችን በበይነመረብ አማካኝነት ለሌሎች ለመላክ

እነዚህ ሁሉ የመሣርያ ስርአቶች የሚከተሉት ነገሮች ያስፈልጓቸዋል:-

  • የማይቆራረጥ የዋይፋይ ወይም የኢንተርኔት ዳታ (3G ወይም 4G/LTE)
  • ስፒከር እና ማይክሮፎን (አብሮ የተገጠመ፣ በዩኤስቢ ወይም በገመድ አልባ ብሉቱዝ የሚሠራ)
  • የቪዲዮ ካሜራ (አብሮ የተገጠመ፣ በዩኤስቢ ወይም በገመድ አልባ ብሉቱዝ የሚሠራ)

በተለይ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የበይነመረብ መሣርያዎቹን መጠቀም ከመጀመራችሁ በፊት የሚከተሉትን የአሰራር መመርያ ሰነዶች ማንበብ ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡- የራዲዮ ጋዜጠኛ ሆኖ በርቀት መሥራት እና የራዲዮ ጋዜጠኞች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ፡፡

የበይነመረብ የመሳርያ ስርኣቶችን መጠቀም አድማጮቼን የተሻለ ለማገልገል እንዴት ይረዳኛል?

የራዲዮ አድማጮች በራሳቸው ማግኘት የማይችሉትን ወይም በቀላሉ ሊገባቸው በሚችል መንገድ ማግኘት የማይችሉትን አስተማማኝ እና የተረጋገጠ መረጃ እንዲያገኙ የማስቻል ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ይህን ለማድረግ አንዳንዴ ጋዜጠኞቹ ምንጮችን በስልክ፣ በኢሜይል ወይም በቪዲዮ ደውሎ ለማግኘት ተጨማሪ ሥራ መሥራት አለባቸሁ፡፡ እነዚህን የበይነረ መረብ መሳርያዎች በመጠቀም አርሶ አደሮችን፣ ባለሙያዎችን፣ የመንግስት ባለስልጣናትን እና በአካል ማግኘት የማይቻሉ ምንጮችን በማግኘት አድማጮቻችሁ ጠቃሚ እውቀት እንዲያገኙ ማድረግ ይቻላል፡፡

እነዚህ መሳርያዎች የሚፈጥሩት መስተጋብር ፎቶ፣ ቪዲዮ፣ ማስታወሻዎችን እና ሌሎች ሰነዶችን ለመቀያየር ያስችላል፤ ይህን በማድረግ ቀጥታ እየተነጋገራችሁ ባለበት ሰኣት ቃለ መጠይቅ የሚደረግላቸው ሰዎች እያጋሯችሁ ያለው መረጃ ግልጽ እንዲሆን እና ግብረመልስም ማግኘት እንዲቻል ማድረግ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ አንድ የመንግስት ባለስልጣን ስለ አንድ አዲስ የግብርና ፖሊሲ ስታነጋሩ ስክሪን ሼር ካደረጋችሁ /ካጋራችሁ/ ሰነዱን እራሳችሁ ወደላይ ወደ ታች አድርጋችሁ በማየት ነጥብ በነጥብ መነጋገር ትችላላችሁ፡፡ ወይም ካንድ አርሶ አደር ጋር በቪዲዮ እየተነጋገራችሁ ከሆነ ምክር እና ሃሳብ ለነሱ ማስተላለፍ ትችላላችሁ – እግረ መንገዳችሁንም ምናልባት እነዚያን የግብርና ልምዶች ሲተገብሩ ስክሪናችሁ ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡

በዚህ የራዲዮ ጋዜጠኞች መመርያ ውስጥ የተዘረዘሩት የበይነመረብ የመሳርያ ስርኣቶች አድማጮችም የድምጽ መልእክት፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች ወይም የጽሁፍ መልእክቶችን በመላክ እንዲሳተፉ እድል ይፈጥሩላቸዋል፡፡ ለሴቶችም ሳይፈሩና ወንዶች በተቆጣጠሩት ውይይት ተስፋ ሳይቆርጡ ሃሳባቸውን እንዲገልጹ እና ግብረ መልስ እንዲሰጡ እድል ይሰጣሉ፡፡

እንዴት ልጀምር?

  1. እነዚህ የበይነመረብ የመሳርያ ስርኣቶች እንዴት ይሠራሉ?
  2. ዙም
  3. ስካይፕ
  4. ጉግል ቻት እና ጉግል ሚት
  5. ዋትስአፕ
  6. ቴሌግራም

ዝርዝር

1. እነዚሕ የበይነመረብ የመሳርያ ስርኣቶች እንዴት ነው የሚሠሩት? (ስለያንዳንዱ መሳርያ ከስር ያለውን በማንበብ ተጨማሪ እወቁ፡፡)

እነዚህን የመሳርያ ስርኣቶች በሚገባ ለመጠቀም እና ለእናንተ እና ለአድማጮቻችሁ የቱ እንደሚያስፈልጋችሁ ለይታችሁ ለማወቅ የሚከተሉትን መመዘኛዎች መመርመር አለባችሁ፡-

  • ወጭ (ነጻ ወይም በደምበኝነት የሚያስከፍል)
  • የመሳርያ ስርኣቱን ለመጠቀም የሚስፈልግ የሲስተም (ስርኣት) መስፈርት
  • የመሳርያ ስርኣቱ የሚደግፋቸው መጠቀሚያ መሳርያዎች
  • የመሳርያ ስርኣቱ ያሉት ገጽታዎች
  • የመሳርያ ስርኣቱ ውስንነቶች
  • የመሳርያ ስርኣቱን በመጠቀም ማግኘት የምትፈልጓቸው ሰዎች

እነዚህን የመሳርያ ስርኣቶች ፊት ለፊት ለማግኘት የሚያስቸግሩ አርሶ አደሮችን ጭምር (ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን) ለማግኘት እንደ አማራጭ መንገድ ተጠቀሙበት፡፡ እነዚህን መሳርያዎች የማሕበረሰብ አድማጭ ቡድኖች ጋርም ለመገናኘት ልትጠቀሙባቸው ትችላላችሁ፡፡

በስልክ ከመደወል ባለፈ ከአድማጮቻችሁ ጋር በርቀት በመገናኘት ልታገለግሏቸው የምትችሉባቸው መንገዶች ከዚህ በታች አሉ፡፡

  • የድምጽ ማስታዋሻ/የድምጽ ምልክቶችን በመጠቀም ቃለመጠይቅ ማድረግ፡፡ ይህ መንገድ ቃለመጠይቅ የሚደረግለት ሰው ከመጻፍ ይልቅ በደምብ ዘርዘር አድርጎና ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ መልሱን እንዲሰጥ ያስችላሉ፡፡ መጻፍ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው ቋንቋ ራሳቸውን ለመግለጽም ያስችላቸዋል፡፡ የድምጽ ፋይሎችን ከስልክ ወደ ኮምፒዩተር ማስተላለፍ እና ወደ MP3 በመቀየር ኤዲት አድርጋችሁ ቀጥታ በሚተላለፍ የራዲዮ ፕሮግራም ላይ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፡፡
  • አንድ ርዕሰ ጉዳይን ለመነጋገር የእድማጮች እና የባለሙያዎች ቡድን መፍጠር ያስችላል፡፡ ለምሳሌ፣ የጤና እና የግብርና ባለሙያዎችን፣ የአካባቢ ባለሙያዎችን፣ እና ሌሎችም መረጃ ያላቸው ሰዎችን አንድ ላይ አድርጋችሁ የዋትስአፕ ቡድን መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ የመልክት መጥለቅለቅ ችግር እንዳይኖር ሁለት የተለያዩ ቡድኖችን ፍጠሩ፡- አንድ ለእድማጮች ሌላ ደግሞ ለመረጃ ሰጭዎች፤ ከዚያ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የመረጃ ሰጭዎችን መረጃዎች ለአድማጮች አጋሩ – ከአድማጮች የተገኙ በጣም ጠቃሚ መረጃዎችንም ለባለሙዎች ቡድን አጋሩ፡፡ ብዙ ሴቶች እንዲሳተፉ ለማበረታታት እና ሳይፈሩ ወይም በብዙ ወንድ ደዋዮች ሳይጨናነቁ ሃሳባቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ የሴቶች ብቻ ቡድኖች ጠቃሚ ናቸው፡፡
  • <የገበያ እና የአየር ሁኔታ መረጃዎችን ቀጥታ ለአድማጮች ለማድረስ፡- መረጃውን በድምጽ ወይም በጽሑፍ መልእክት መላክ ትችላላችሁ፡፡ አድማጮች ለሌሎች የማሕበረሰብ ክፍሎች እንዲያጋሩ አበረታቱ፡፡

ለአርሶአደሮች ቃለ መጠይ ስለማድረግ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትአርሶአደሮችን ስለጠቃሚ ነገሮች እንዲናገሩ ስለማድረግ (የአርሶአደር ድምጾች እንዲሰሙ ማድረግ) የሚለውን የአሰራር መመርያችንን ያንብቡ፡፡

2. ዙም

መሰረታዊ ገጽታዎቹ

ዙም ቪዲዮ፣ ድምጽ እና ይዘት ማጋርያ እና ቻት ማድረጊያ አገልግሎት ሲሆን ስብሰሰባዎችን፣ የክፍል ትምህርቶችን (ሌክቸር)፣ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት እና ለሌሎችም የሚያገልግል የበይነመረብ አገልግሎት ነው፡፡ ዙምን ለመጠቀም መተግበርያውን በነጻ ወደ ሞባይላችሁ ወይም ኮመፒዩተራችሁ ማውረድ እና የነጻ መለያ መፍጠር አለባችሁ፡፡

ዙም አራት ዓይነት አጠቃቀሞችን ያቀርባል፡- ሦስት ክፍያ የሚያስፈልጋቸው እና አንዱ ነጻ፡፡ አስተናጋጁ የዙም ጥሪ ፕሮግራም ሲያደርግ መሳርያው የስብሰባ መለያ፣ ወደ ስብሰባው መግቢያ አገናኝ፣ የመግቢያ ኮድ እና ለተሳታፊዎች በይፋ ወይም በግብዣ ብቻ የሚለቀቅ የስልክ ቁጥር ያዘጋጃል (ከስር ተመልከቱ)፡፡ ዙም መተግበርያ የሌላቸው ተሳታፊዎች የኢንተርኔት ማሰሻ (ብራውዘር) ወይም የስልክ መስመራቸውን በመጠቀም የዙም ስብሰባውን መቀላቀል ይችላሉ፡፡

በነጻ የሚቀርበው የዙም እቅድ የሚከተሉት ገጽታዎች አሉት፡-

  • ስብሰባዎች፡- ሁሉንም ተሳታፊዎች ማየት፣ መናገር፣ መስማት እና ስክሪናቸውን ለማጋራት የሚያስችል ባለመስተጋብር መሳርያ ነው፡፡ የዙም ስብሰባ ለመጥራት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • ዌቢናር፡- ተሳታፊዎች እርስ በርስ መተያየት አይችሉም፤ አስተናጋጁም ተሳታፊዎችን ማየት አይችልም በቀጥታ ግን ለነሱ ማቅረብ ይችላል፡፡ ስለዙም ዌቢናር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • የይለፍ ቃል፡- ለደህንነት ሲባል ለስብሰባዎች የይለፍ ቃል ማዘጋጀት ይቻላል፤ ነገር ግን ያለ ፓስኮድም ስብሰባ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ አስተናጋጁ ስብሰባ ወይም ዌቢናር አዘጋጅቶ ግብዣ ሲልክ ስርኣቱ የሚከተሉትን አዘጋጅቶ ለሁሉም ተሳታፊዎች ያጋራል፡- የስብሰባው መለያ፣ መግቢያ አገናኝ፣ እና የይለፍ ቃል፡፡ ስለ ይለፍ ቃል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • ስክሪን ማጋራት፡- በዙም ስብሰባ ጊዜ አስተናጋጆች እና ተሳታፊዎች የሞባይል ወይም ኮምፒዩተር ስክሪናቸውን ማጋራት ይችላሉ፡፡ ስክሪነስ ስለማጋራት መረጃ ለማገኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • የቻት አገልግሎት፡- የዙም ስብሰባዎች እና ዌቢናሮች ተሳታፊወች፣ ተወያዮች፣ አስተነጋጆች እና ተባባሪ አስተናጋጀች ጥያቄ በመጠየቅ፣ አስተያየት በመስጠት እና ፋይሎችን በማጋራት እንዲግባቡ የሚያስችል የቻት አገልግሎት አለው፡፡ አስተናጋጁ መልእክቶቹን ለሌላ ጊዜ ለመጠቀም ማስቀመጥ ይችላል፡፡ ስለዙም ቻት አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • መቅረጽ፡- አስናጋጁ የዙም ስብሰባዎችን እና ዌቢናሮችን ዙም ክላውድ ላይ (በበይነመረብ ላይ ባለ ዲጂታ
  • ማጠራሚያ) ወይም ኮምፒዩተሩ ወይም ሞባይሉ ላይ ማስቀመጥ ይችላል፡፡

የተከፈለበት የዙም እቅድ የሚከተሉት ገጽታዎች አሉት፡-

  • ገደብ የሌለው የቡድን ስብሰባ
  • የ30 ሰኣት የስብሰባ ጊዜ ገደብ
  • የክላውድ ማጠራቀሚያ
  • በማሕበራዊ ሜዲያ ቀጥታ ማሰራጨት
  • ወርሃዊ ወይም አመታዊ ክፍያ

አንድ ራዲዮ ጋዜጠኛ ዙምን እንዴት መጠቀም ይችላል?

አንድን እንግዳ በዙም ቃለ መጠይቅ ስታደርጉ ቀርጻችሁ ኤዲት በማድረግ በቀጥታ ራዲዮ ፕሮግራም ላይ ልታጫውቱት ትችላላችሁ፡፡ ወይም በቀጥታ ስርጭት ወቅት እንደ ቃለ መጠይቅ ወይም የፓነል ውይይት የሚያገለግል የዙም ጥሪ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ዋናው ነገር እናንተ እና እንግዶቻችሁ ፕሮግራሙ እስከሚያልቅ ድረስ የማይቋረጥ የኢንተርኔት ግንኙነት ማግኘታችሁ ነው፡፡

የዙም መሳርያ ስርኣት የራዲዮ ጋዜጠኞች በቻት አገልግሎቱ አማካኝነት ማታወሻዎችን፣ ሪፖርቶችን፣ የቃለመጠይቅ ጥያቄዎችን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን እና ሌሎችንም ፋይሎች ለማጋራት እንዲችሉ ያደርጋል፡፡ ጋዜጠኞቹ እነዚህን ፋይሎች ቀጥታ ለዙም ግንኙነት በሚጠቀሙባቸው ስልኮች ወይም ኮምፒዩተሮች ላይ እንዲያስቀምጡ ያስችላል፡፡

ዙም በተጨማሪም ከራዲዮ ጣቢያ ዝግጅት ቡድኖች ጋር የፕሮግራም እቅድ ስብሰባዎችን፣ የስራ አመራር ስብሰባዎችን፣ እና ሌሎች ስራ ነክ ስብሰባዎችን ለማድረግም ይጥቅማል፡፡ አስተናጋጁ ብቻ የዙም መተግበርያ እንዲኖረው ያስፈልጋል፤ ሌሎች በድረገጽ ማሰሻቸው ወይም ቀጥታ በስልክ መስመራቸው አመካኝነት መቀላቀል ይችላሉ፡፡

ልብ በሉ፡- ከላይ የተዘረዘሩተን ሁሉንም የዙም ተግባሮች እና ገጽታዎች ለመጠቀም ነጻ መተግበርያውን ማውረድ ይመከራል፡፡

የዙም አገልግሎት ውስንነት

የዙም የነጻ እቅዱ እስከ 100 ድረስ ተሳታፊዎችን ቢበዛ ለአርባ ደቂቃ ብቻ ምናባዊ (ቨርቹዋል) ስብሰባ እንዲሳተፉ ያስችላል፡፡ የጊዜ ገደቡ ሲደርስ አስተናጋጁ በአዲስ አገናኝ፣ የስብሰባ መለያ እና የይለፍ ቃል አዲስ ስብሰባ ማስጀመር አለበት፡፡ አንድ ለአንድ የሚደረጉ ስብሰባዎችየጊዜ ገደብ የለባቸውም፡፡

የዙም የተከፈለባቸው እቅዶች (ፕሮ፣ ቢዝነስ እና ኢንተርፕራይዝ) ተጨማሪ ገጽታዎች አሏቸው፤ እነዚህም የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡- ለስብሰባዎች ተጨማሪ የጊዜ መጠን፣ ድምጽ መስጠት ማስቻል፣ የተበታተኑ የስብሰባ ክፍሎች፣ በክላውድ መቅረጽ፣ ቀጥታ ትርጉም እና ሌሎችንም ይጨምራል፡፡

ስለዙም ዋጋ እና ዕቅዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

የሥርዓት መስፈርቶች

  • ዊንዶውስ 7 ወይም ከዚያ በላይ (Windows 7 or higher)
  • ማክ ኦኤስ ኤክስ ከማክ ኦኤስ 10.9 ወይም ከዚያ በላይ ጋር (Mac OS X with Mac OS 10.9 or higher)
  • አይኦኤስ 8.0 ወይም በላይ (iOS 8.0 or later)
  • አንድሮይድ ኦኤስ 5.0 ወይም በላይ (Android OS 5.0 or later)

የሚደገፉ መሳርያዎች፡

  • ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር (ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ክሮም ኦኤስ)
  • አንድሮይድ መሳርያዎች
  • አይፎን፣ አይፓድ፣ አይፖድ ተች)
  • ዊንዶውስ ታብሌት

ለዙም መሳርያ መስፈርቶች እና የተደገፉ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ሙሉ ዝርዝር እዚህ ይጫኑ፡፡

3. ስካይፕ

መሰረታዊ ገጽታዎች

ስካይፕ በአለም የትኛውም ክፍል ካሉ ሰዎች ጋር በነጻ የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪ የሚደረግበት መሳርያ ነው፡፡ እሱን ለመጠቀም የሚከተሉት ያስፈልጓችኋል፡- ኢንተርኔት፣ ማይክሮፎን ወይም ሄድሴት (ወይም መሳርያችሁ ላ የተገጠሙትን ማይክሮፎን እና ስፒከር መጠቀም ትችላላችሁ)፣ ስካይፕን ካወረዳችሁ በኋላ ስልካችሁ ወይም ኮምፒዩተራችሁ ላይ የምታዘጋጁት የሥካይፕ መለያ፡፡ አውትሉክ፣ ሆትሜይል ወይም የማይክሮሶፍት መለያ በመጠቀም ወደ ስካይፕ መግባት ትችላላችሁ፡፡

ስካይፕ ላይ ሰዎችን በስም፣ በስልክ ቁጥር ወይም በኢሜይል በመፈለግ የእውቂያ (ኮንታክት) ዝርዝር ማዘጋጀት ትችላላችሁ፡፡

የስካይፕ መሰረታዊ ገጽታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

  • ስብሰባዎች (ከላይ የዙምን ክፍል ተመልከቱ)
  • ስክሪን ማጋራት (ከላይ የዙምን ክፍል ተመልከቱ)
  • ፋይል ማጋራት – ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ የድምጽ መልእክቶችን፣ ፒዲኤፍ፣ ኤክሰል እና ሌሎችንም ፋይሎች
  • የኮንፈረንስ (ጉባኤ) ጥሪ – እስከ 20 የሚደርሱ ሌሎች ስካይፕ ተጠቃሚዎች ጋር ባንድ ጊዜ ጥሪ ማድረግ
  • የመስመር እና የመባይል ስልኮችን ከየትኛውም የዓለም ክፍል መደወል፡፡ ስካይፕን በመጠቀም በክፍያ ወደ መስመር እና የሞባይል ስልኮች መደወል ትችላላችሁ፡፡ ስካይፕን ለዓለም አቀፍ ጥሪዎች ስለመጠቀም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • መቅረጽ፡- ስካይፕ ጥሪዎቹን መተግበርያው ውስጥ እንድታስቀምጡ እና mp4 ቪዲዮ እና mp3 ድምጽ ፋይሎችን እንድታወርዱ ያስችላችኋል፡፡ ልብ በሉ – የተቀረጹት ፋይሎች ካላወረዳችኋቸው የቻት መስኮቱ ውስጥ ለ30 ቀናት ከተቀመጡ በኋላ በራሳቸው ይጠፋሉ፡፡

አንድ የራዲዮ ጋዜጠኛ ስካይፕን እንዴት መጠቀም ይችላል?

ስካይፕ በአካል ለማግኘት የሚቸግሩ ሰዎች ጋር የሚደረጉ ቃለ መጠይቆችን ለመቅረጽ ጠቃሚ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ የገጠር ራዲዮ ጣቢያ ላይ የሚሠራ ጋዜጠኛ እሩቅ ቦታ ላይ የሚኖር የግብርና ባለሙያን ሄዶ በአካል ቃለ መጠይቅ ለማድረግ የትራንስፖርት እና የሆቴል ወጭ የሚሸፍንበት አቅም ላይኖረው ይችላል፡፡ ስካይፕ በመጠቀም ጋዜጠኛው ባለሙያውን ከራዲዮ ጣቢያው ወይም በቅርብ ከሚገኝ የኢንተርኔት ካፌ ሆኖ በመደወል ቃለ መጠይቁን መተግበርያው ውስጥ በቀጥታ በመቅረጽ ለስርጭት ዝግጁ የሆነ ቪዲዮ እና ድምጽ ማስቀመጥ ይችላል፡፡

የስካይፕ ጥቅም ውስንነቶች

ስካይፕ በነጻ እስከ 20 ሰዎችን በአንድ ጥሪ ማገናኘት ያስችላል፡፡ ከዚ በላይ ተጨማሪ ተሳታፊዎችን ከፈለጋችሁ የሚከፈልበትን እቅድ ተጠቃሚዎች መሆን አለባችሁ፡፡ ስለስካይፕ ደምበኝነት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

የሥርኣት/ሲስተም መስፈርቶች፡-

  • ዊንዶውስ 10 ስሪት 1809 ወይም ከዚያ በላይ (Windows 10 version 1809 or higher)
  • ማክ ኦኤስ ኤክስ ከማክ ኦኤስ 10.10 ወይም ከዚያ በላይ ጋር (Mac OS X with Mac OS 10.10 or higher)
  • አይኦኤስ 10 ወይም በላይ (iOS 10 or later)
  • አንድሮይድ ኦኤስ 4.0.4 ወይም በላይ (Android OS 4.0.4 or higher)

ከስካይፕ ጋር ተስማሚ ስለሆኑ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች/ስርኣቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

4. ጉግል ቻት እና ጉግል ሚት (በፊት ሃንግአውትስ ይባል የነበረው)

መሰረታዊ ገጽታዎቸ

ጉግል ቻት እና ጉግል ሚት ጉግል ሃንግአውትስን የተኩ ሁለት መተግበሪያዎች ናቸው፡፡ ጉግል ቻት ቀጥታ መልእክት ለመላክ እና በቡድን ለመነጋገር ያገለግላል፤ ጉግል ሚት ደግሞ ስብሰባዎችን ለማካሄድ እና ለመቅረጽ ያስችላል፡፡

እነዚህ የጉግል ሱይት (ጂ ሱይት) የአግልግሎት ስብስብ አካል ሲሆኑ ሌሎቹ አገልግሎቶች የሚከተሉት ናቸው፡- ድራይቭ፣ ጂሜይል፣ ዶክስ፣ ሺትስ፣ ስላይድስ፣ ፎርምስ፣ ካሌንደር፣ ጉግል+፣ ሳይትስ፣ ሃንግአውትስ እና ኪፕ ናቸው፡፡ እነዚህ መሳርያዎች ጉግል ክሮም ውስጥ ባሉ ቅጥያዎች አማካኝነት ጉግል ቻት እና ጉግል ሚት ውስጥ ማገልገል ይችላሉ፡፡ ልብ በሉ፡- እናንተ ወይም የራዲዮ ጣቢያችሁ እነዚህን አገልግሎቶች ለመጠቀም የጂ ሱይት መለያ ሊኖራችሁ ያስፈልጋል፡፡

ጉግል ቻት ለሚከተሉት አገልግሎቶች ይጠቅማል፡-

  • ቅጽበታዊ መልእክት ለመላክ
  • ፋይል ለማጋራት – ምስል፣ ቪዲዮ፣ የድምጽ መልእክት፣ ፒዲኤፍ፣ ኤክሰል እና ሌሎች ፋይሎች

ጉግል ሚት ለሚከተሉት አገልግሎቶች ይጠቅማል፡-

  • ስብሰባዎችን ለመጥራት እና በቪዲዮ ለመቅረጽ (ከላይ ያለውን የዙም ክፍል ተመልከቱ)
  • ስክሪን ለማጋራት (ከላይ ያለውን የዙም ክፍል ተመልከቱ)
  • ፋይል ለማጋራት – ምስል፣ ቪዲዮ፣ የድምጽ መልእክት፣ ፒዲኤፍ፣ ኤክሰል እና ሌሎች ፋይሎች

አንድ የራዲዮ ጋዜጠኛ ጉግል ቻት እና ጉግል ሚትን እንዴት መጠቀም ይችላል?

ልክ እንደ ዙም እና ስካይፕ ሁሉ በጉግል ሚት መተግበርያም የቪዲዮ ስብሰባን መቅረጽ እና በቀጥታ የራዲዮ ፕሮግራም ለማስተላለፍ ኤዲት ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ወይም ንግ

ሩን በቀጥታ ስርጭት ወቅት ማስተናገድ ትችላላችሁ – ነገር ግን እናንተ እና እንግዶቻችሁ እስከመጨረሻው ድረስ የማይቆራረጥ የኢንተርኔት ግንኙነት ያስፈልጋችኋል፡፡

በሁለቱም መተግበርያዎች ላይ ባለው የቻት አገልግሎት መልእክት ወይም ፋይሎችንም – ማስታወሻዎችን፣ ሪፖርቶችን፣ ቃለመጠይቆችን፣ ምስሎችን፣ ቪዲዮዎችን እና ሌሎችንም – ማጋራት ትችላላችሁ፡፡ የራዲዮ ጋዜጠኞች ፋይሎችን ሞባይላቸው ወይም ኮምፒዩተራቸው ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡

እነዚህ መተግበርያዎች ከራዲዮ ጣቢያ የዝግጅት ቡድን ጋር የፕሮግራም እቅድ ስብሰባዎችን፣ የስራ አመራር ስብሰባዎችን፣ እና ሌሎች ስራ ነክ ስብሰባዎችን ለማድረግም ይጥቅማሉ፡፡ ሁሉም ተሳታፊዎች ግን ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም የጉግል መለያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ልብ በሉ፡- ጉግል ቻት እና ሚት ለመጠቀም ነጻ ሲሆኑ የጥሪ የጊዜ ገደብም የላቸውም፡፡

የጉግል ቻት እና ሚት የአጠቃቀም ውስንነቶች

የጉግል ቻት ወይም ሚት ጥሪ ለመጀመር የጉግል መለያ ያስፈልጋችኋል፤ ጥሪውን መቀላቀል የሚፈልጉ ሰዎች ግን መለያ አያስፈልግም፡፡ ቻት ውስጥ እስከ 150 ሰዎች ይፈቀዳል፣ የቪዲዮ ጥሪዎች ግን በአንድ ጥሪ 25 ሰው ብቻ ይፈቀዳል፡፡ የቪዲዮ እና የድምጽ ጥሪዎቻችሁን ለማስቀመጥ ከፈለጋችሁ በጉግል ድራይቭ ወይም በጉግል ዋን መለያችሁ አማካኝነት ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ መግዛት ያስፈልጋቸኋል፡፡

የስርኣት/ሲስተም መስፈርቶች< እነዚህ መተግበሪያዎች ከሚከተሉት ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች አሁን ካሉት እና ከዚህ በፊት ከነበሩ ሁለት ስሪቶች ጋር ይጣጣማሉ፡-

  • ማክ ኦኤስ ኤከስ
  • ዊንዶውስ
  • ክሮም

ጉግል ቻት እና ጉግል ሚት ከሚከተሉት የድረገጽ ማሰሻዎች ጋርም ይጣጣማሉ፡-

  • ጉግል ክሮም
  • ማይክሮሶፍት ኤጅ
  • ፋየርፎክስ
  • ሳፋሪ 13 ወይም በላይ
  • ማይክሮሶፍት ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 11

የተደገፉ መሳርያዎቸ

  • አይፎን ወይም አይፓድ
  • አንድሮይድ ስልክ ወይም ታብሌት

ስለጉግል ቻት እና ጉግል ሚት (ጉግል ሃንግአውትስ) የስርኣት መስፈርቶች እና ስለሚደገፉ መሳርያዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

5. ዋትስአፕ (የፌስቡክ ንብረት የሆነ)

መሰረታዊ ገጽታዎች፡-

  • ዋትስአፕ ቻት፡- ዋትስአፕን ለመጠቀም በጣም ቀላሉ መንገድ የቅጽበታዊ መልእክት መለኪያ የመሳርያ ስርኣቱን መጠቀም ነው፡፡ ለግለሰቦች ወይም ለቡድን የጽሑፍ፣ ምስል፣ ቪዲዮ፣ ፒዲኤፍ፣ ድምጽ እና ሌሎች አይነት ፋይል ያላቸውን መልእክቶች መላክ ይቻላል፡፡
  • የድረ ገጽ ዋትስአፕ፡- ዋትስአፕን በኮምፒዩተራችሁ ላይ ለመጠቀም መተግበርያውን ስልካችሁ ላይ አውርዱ እና ሜኑ ወይም ሴቲንግስ የሚለውን ተጭናችሁ ዋትስአፕ ዌብ የሚለውን ምረጡ፡፡ ከዚያ እዚህ ያለውን ኪውአር ኮድ በሞባይላችሁ አንብቡ፡፡
  • የድምጽ መልእክት፡- በዋትስአፕ ቻት ውስጥ ከጽሑፍ መጻፍያው ሳጥን ወስጥ በስተቀኝ በኩል ያለውን የማይክሮፎን ምስል ተጭኖ በመያዝ የድምጽ መልእክት መላክ ይቻላል፡፡ ሳይጨነቁ በራስ ቋንቋ ለአድማጮች መልእክት ለማስተላለፍ ይህጥሩ መንገድ ነው፡፡ የድምጽ መልእክቱን ለሌሎች ሰዎች ማስተላለፍ ትችላላችሁ – ለምሳሌ የግብርና መረጃ እያጋራችሁ ከሆነ፡፡
  • የብሮድካስት (ስርጭት) ዝርዝሮች፡- ይህ ገጽታ የእውቂያ (ኮንታክት) ዝርዝሮችን መፍጠር እና ማስቀመጥ እና ለሁሉም አባላት ባንድ ጊዜ መልእክት መላክ ያስችላችኋል፡፡ የስርጭት ዝርዝሮችን ለመጠቀም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

አንድ የራዲዮ ጋዜጠኛ ዋትስአፕን እንዴት መጠቀም ይችላል?

  • የድምጽ ማስታወሻ/የድምጽ መልእክት በመጠቀም ኢንተርቪው ማድረግ፡፡ ይህን ማድረግ ለተጠያቂዎቹ ከመጻፍ በተሻለ ዘርዘር ያለ እና ተፈጥሯዊ የሆነ መልስ ለመስጠት ያስችላል፡፡ ፋይሎችን ከስልካችሁ ወደ ኮምፒዩተር ገልብጣችሁ ወደ MP3 መቀየር እና የቀረጻችሁትን ኤዲት አድርጋችሁ በቀጥታ በራዲዮ ማስተላለፍ ትችላለችሁ፡፡
  • ለአድማጮች እና ለባለሙያዎች ርእሰ ጉዳዮን የሚቀያየሩበት ቡድኖች መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ ለጤና ባለሙያዎች፣ ባካባቢያችሁ ላሉ ባለሙያዎች እና ሌሎች መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ ሰዎች አንድ የዋትስአፕ ግሩፕ መፍጠር ትችላላችሁ፡፡
  • የመልእክት መጥለቅለቅን ለማስወገድ ሁለት የተለያዩ ቡድኖችን ለመፍጠር ሞክሩ፡- አንድ ለአድማጮች እና አንድ ለመረጃ ሰጭዎች፡፡ ከዚያ ከመረጃ ሰጭዎች የተገኙትን በጣም ጠቃሚ መረጃዎች ለአድማጮቻችሁ አጋሩ፤ ከአድማጨቻችሁ የሚገኙትን በጣም ጠቃሚ መረጃዎች ደግሞ ለመረጃ ሰጭዎች አጋሩ፡፡
  • የገበያ እና የአየር ጸባይ መረጃዎችን ቀጥታ ለአድማጮቻችሁ ማድረስ፡፡ መረጃውን እንደ ድምጽ ወይም ጽሑፍ መልእክት መላክ ትችላላችሁ፡፡ አድማጮች ለሌሎች የማሕበረሰብ ክፍሎች እንዲያስተላለፍ አበረታቱ፡፡
  • የፋርም ራዲዮ ኢንተርናሽናል የዋትስአፕ የአገር ቡድኖች በአገራችሁ ውስጥ ካሉ ሌሎች የራዲዮ ጋዜጠኞች ጋር ለመገናኘት እና ሃሳብ፣ ጥቆማ እና ሌሎች መረጃዎችን ለማጋራት ጥሩ መድረኮች ናቸው፡፡ የፋርም ራዲዮ የሃገራችሁን ገጽ ለመቀላቀል ስማችሁን፣ የራዲዮ ጣቢያችሁን/ድርጅታችሁን እና ስልክ ቁጥራችሁን ጠቅሳችሁ ወደ radio@farmradio.org ኢሜይል ላኩ፡፡<
  • የሴቶች ብቻ የዋትስአፕ መስመሮች ለሴቶችም ሳይፈሩና ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ወንዶች ደዋዮች ሳይጨናነቁ ለመሳተፍ እና አስተያየታቸውን በአየር ላይ ለማካፈል ለማበረታታት በጣም ጠቃሚ መንገዶች ናቸው፡፡
  • የብሮድካስት/ስርጭት ዝርዝር ከራዲዮ ፕሮግራሙ የፕሮግራም ቅንጣቢዎችን እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ባንድ ጊዜ ለብዙ ሰዎች ለማካፈል ጠቃሚ መንገድ ነው፡፡

የዋትስአፕ ውስንነቶች ምንድን ናቸው?

ዋትስአፕ በአንድ ጊዜ በአንድ ስልክ ቁጥር እና በአንድ መጠቀሚያ መሳርያ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በዋትስአፕ የተነጋገራችሁትን ወደተለያዩ የመሳርያ ስርኣቶች /ፕላትፎርሞች የማስተላለፊያ መንገድ የለውም፣ ነገር ግን በኢሜይል አባሪ አድርጋችሁ መላክ ትችላላችሁ፡፡ የዋትስአፕ መልእክቶችን ለማስቀመጥ እና ከስልካችሁ ወይም ኮምፒዩተራችሁ ላይ የተያዘ ቦታን ለማጽዳት ከፈላጋችሁ ይህ አስፈላጊ ነው፡፡ በተጨማሪም በዋትስአፕ ለሚላኩ ለሁሉም አይነት ማህደረ መረጃ/ሜዲያ (ፎቶ፣ ቪዲዮ፣ የድምጽ መልእክት) የሚፈቀደው ከፍተኛው መጠን ለአንድ ፋይል18ሜባ ነው፡፡

እስካሁን ድረስ የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪዎችን መተግበርያው ውስጥ መቅረጽ የሚያስችል መንገድ የለውም፡፡ ነገር ግን በዋትስአፕ የምታደርጉትን የስልክ ጥሪ ላውድ ላይ በማድረግ በሌላ መቅረጫ መቅረጽ ትችላላችሁ፡፡

የስርኣት/ሲስተም መስፈርት፡-

  • አንድሮይድ ኦኤስ 4.0.3 ወይም በላይ
  • አይኦኤስ 9 ወይም በላይ
  • ካይኦኤስ 2.5.1 ወይም በላይ (KaiOS 2.5.1 or higher)

የተደገፉ መሳርያዎች፡-

  • አንድሮይድ መሳርያዎች
  • አይኦኤስ መሳርያዎች
  • ጂዮፎን ወይም ጂዮፎን 2

6. ቴሌግራም

መሰረታዊ ገጽታዎች

ቴሌግራም በብዙ ሃገሮች ዝነኛ የሆነ ሌላ የነጻ የተግባቦት አገልግሎት ነው፡፡ የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪዎችን እንዲሁም የቻት አገልግሎትን ትኩረቱን ደህንነት እና ፍጥነት ላይ አድርጎ ይሰራል፡፡ በቴሌግራም የሚላኩ መልእክቶች በከፍተኛ ሁኔታ የተመሰጠሩ እና ከፍተኛ ደህንነት ያላቸው ናቸው፤ ይህም ለአንዳንድ ተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተሻለ የተጠበቀ እና ይበልጥ አስተማማኝ የሆነ የተግባቦት አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡

የቴሌግራም መሰረታዊ ገጽታዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

  • ቻት – ለግለሰቦች እና ለቡድን ተቀባዮች የሚላኩ የጽሑፍ እና የድምጽ መልእክቶችን ይጨምራል
  • የቪዲዮ ጥሪ
  • የድምጽ ጥሪ
  • ያልተገደበ የፋይል ማጋራት፡- ቴሌግራም የማህደረ መረጃ/ሜዲያ እና የቻት መጠን ገደብ የለውም
  • ያልተገደብ የጥሪ አቅም፡- ቴሌግራም በአንድ ቡድን ጥሪ ውስጥ እስከ 200,000 ሰዎችን ማስተናገድ ይችላል
  • የሚስጥር ቻት፡- በሚስጥር ቻት ውስጥ ያሉ ሁሉም መልእክቶች ከጫፍ እስከጫፍ ይመሰጠራሉ፣ ማለትም እናንተና ተቀባዩ ብቻ ናችሁ መልእክቶቹን ማየት የምትችሉት – ለሌላ ሰው ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ይህ ገጽታ መልእክቶቹ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በራሳቸው እንዲጠፉ ማዘዝ ትችላላችሁ፡፡ ስለ ሚስጥር ቻት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡
  • እንከን የለሽ ማዋደድ/ Seamless sync መልእክታችሁን ባንድ ጊዜ በብዙ መገልገያ መሳርያዎች ላይ እንድታዩ እና እያንዳንዳቸው እስከ 2ጂቢ የሚደርሱ ያልተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ፋይሎች ማካፈል ትችላላችሁ፡፡ ስለቴሌግራም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ፡፡

አንድ የራዲዮ ጋዜጠኛ ቴሌግራምን እንዴት መጠቀም ይችላል?

የራዲዮ ጋዜጠኞች ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ላይ እየሰሩ ከሆነ ወይም ውሥን የቴሌኮሙኒኬሽን ነጻነት ባለበት አገር የሚሰሩ ከሆነ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የተግባቦት አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ቴሌግራም ጠቃሚ መተግበርያ ነው፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ ሃገሮች ብዙ ሰዎች ለመግባባት የሚጠቀሙበት መተግበርያ አይደለም፡፡

ከዚህ በተረፈ ቴሌግራም ባብዛኛው ልክ እንደ ስካይፕ፣ ዙም፣ ጉግል ሚት እና ዋትስአፕ ለመድረስ አስቸጋሪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ፣ ፋይሎችን ለማጋራት፣ ለማስቀመጥ እና ለራዲዮ ስርጭት ኤዲት ለማድረግ የሚያገለግል አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የመሳርያ ስርአት ነው፡፡ ተጨማሪ የደህንት ገጽታዎቹ እና ገደብ አልባ የሆነው የፋይል ማጋራት እና የጥሪ አግልግሎቱ ሲታይ በአንዳንድ ሁኔታዎች ከዋትስአፕ ሊሻል ይችላል፡፡

የስርአት/ሲስተም መስፈርቶች፡-

  • አንድሮይድ ኦኤስ 4.0.3 ወይም በላይ
  • አይኦኤስ 9 ወይም በላይ
  • ካይኦኤስ 2.5.1 ወይም በላይ (KaiOS 2.5.1 or higher)

የተደገፉ መሳርያዎች፡-

  • አንድሮይድ መሳርያዎች
  • አይኦኤስ መሳርያዎች

የበይነመረብ የመሳርያ ስርኣቶችን ለራዲዮ ስርጭት ስለመጠቀም ተጨማሪ መረጃ የት ማግኘት እችላለሁ?

Farm Radio International, 2019. Connecting with farmers, journalists and communicators on social media. Barza Wire. https://wire.farmradio.fm/resources/connecting-with-farmers-journalists-and-communicators-on-social-media/

Haburchak, Alan. 2020. Remote video interviews: All you need to know. International Journalists Network. https://ijnet.org/en/story/remote-video-interviews-all-you-need-know

Soon, Alan. 2020. Tips for running an online event in the time of COVID-19. Global Investigative Journalists Network. https://gijn.org/2020/05/05/tips-for-running-an-online-event-in-the-time-of-covid-19/

Tellier, Hannah. 2020. How Ouaga FM creates quality content despite the restrictions of COVID-19, Barza Wire. https://wire.farmradio.fm/spotlights/how-ouaga-fm-creates-quality-content-despite-the-restrictions-of-covid-19/

Acknowledgements

ምስጋና

የጽሑፉ አዘጋጅ፡- ማክሲን ቤተሪጅ-ሞይስ፤ ፍሪላንስ ጋዜጠኛ እና የቀድሞ የፋርም ራዲዮ ኢንተርናሽናል ጋና የብሮድካስተር ሪሶርስስ አማካሪ፡፡

ይህ ጽሑፍ ከካናዳ መንግስት በግሎባል አፌይርስ ካናዳ በኩል በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡