የእግድ እብደት፡ ጾታዊ ጥቃት በኮቪድ-19 ወቅት

ማህበራዊ ጉዳዮችየጾታ እኩልነት

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ማስታወሻ ለአሰራጩ

ጾታዊ ጥቃት በእንድ ሰው ጾታ የተነሳ የሚደርስ አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ኢኖሚያዊ ወይም ወሲባዊ ስቃይ ወይም ጉዳት የሞያደርስ ድርጊት ወይም የድርጊት ዛቻ ነው፡፡

የጋና ፖሊስ አስተዳደር እያደገ በመጣው አካላዊ እና በጋብቻ ውስጥ የሚፈጸም ጥቃት ሪፖርት ምክንያት በ1998እአአ የሴቶች እና ወጣቶች ክፍልን አቋቋመ፤ ይህ ክፍል አሁን የቤት ውስጥ ጥቃት እና ተጎጂዎች ድጋፍ ክፍል ሲባል ሴቶች እና ሕጻናት ላይ አተኩሮ የሚሠሩ ወንጀሎችን ይከታተላል፡፡ በ2007 የጸደቀው የቤት ውስጥ ጥቃት ሕግ እና በ2016 የወጣው ማስፈጸሚያም በጋና የሚፈጠሩ የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር ረድተዋል፡፡

የጥቃት ክፍሉ በፖሊስ ቢቋቋምም እንኳን ማሕበራዊ አገልግሎት፣ ትምህርትና የጤና አገልግሎቶች እጥረት ስላለ ጋና አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቤት ውስጥ ጥቃት ሪፖርት ይደርሳታል፡፡ ለምሳሌ የቤት ውስጥ ጥቃት ተጎጂዎች ነጻ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ቢጠበቅም እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ የቤት ውስጥ ጥቃት እና ተጎጂዎች ድጋፍ ክፍል በዲስትሪክት እና ማህበረሰብ ደረጃ ያሉት ውስን ቢሮዎች እና ሠራተኞች ነው፤ ለተጎዱ ሴቶች ያሉት መጠለያዎች አናሳ ናቸው፤ ስለቤት ውስጥ ጥቃትም ያለው የእውቀት ማነስ በአንዳንድ ሁኔታዎች አጥፊዎች ሳይጠየቁ እንዲያልፉ ያደርጋል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አስቀድሞ የነበረውን ጾታዊ መበላለጥ እና የኃይል ተዋረድ አባብሶታል፡፡ የቫይረሱን ሰፊ ስርጭት ለመከላከል ሲባል የእንቅስቃሴ እና ከቤት መውጣት እግድ ተደርጓል፣ እንዲሁም ሕዝባዊ ስብሰባዎች ተከልክለዋል፡፡ እነዚህ እርመጃዎች ለሕዝብ ጤንነት አስፈላጊ ቢሆኑም በማሕበረሰቡ ውስጥ እና ለጥቃት ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች መካከል ወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃት እንዲበረክት አድርገዋል፡፡
እንደመጠለያ እና የቀጥታ ስልክ መስመሮች ተደራሽነት ውስን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በብዙ የጋና ማሕበረሰቦች ውስጥ ጾታዊ ጥቃት ቀጥሏል፡፡ በነዚህ ተግዳሮቶች የተነሳ የተጠቁ ሰዎች ስላሉ አገልግሎቶች እንዲያውቁ እና እራሳቸውን ነጻ ለማውጣት እና ፍትህ ለማግኘት እንዲችሉ በጋና ያሉ ሰዎችን ስለ ጾታዊ ጥቃት ማስተማር በዚህ ልቦለዳዊ ድራማ ውስጥ ፎሪዋ እና ልጆቿ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ሥራውን ያጣው ባለቤቷ ዳንኤል ብስጭቱን በነሱ ላይ በመወጣት በደል እያደረሰባቸው ነው፡፡

እድሜዋ ያልደረሰችውን ሴት ልጁን ለጋብቻ አሳልፎ ገንዘብ ለማግኘት ይሞክራል፤ ከቤት የመውጣት እግዱን ተጠቅሞም ሚስቱን ይበድላል፡፡ ይህ ድራማ በቤት ውስጥ ያለውን ጥቃት አስፈሪነት፣ በሕጻናት ላይ ያለውን ተጽእኖ እና በደል በሚፈጸምባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ ጥፋተኞችን ሪፖርት የማድረግ አስፈላጊነትን ያሳያል፡፡

ድራማው እያንዳንዳቸው ከ4-7 ደቂቃ የሚረዝሙ አምስት ክፍሎች አሉት፡፡

Script

ክፍል 1

መቼት:
የፎሪዋ ቤት

ገጸ-ባህርያት:
ፎሪዋ፣ ዳንኤል፣ ልጆች (ሴርዋ፣ ቤቢ እና ፓፓ)

የድምጽ ኢፌክት:
ሙዚቃ

ዳንኤል:
ውዴ መነጋር አለብን፡፡ ራዲዮውን ቀንሽውና ወደዚ ነይ፡፡

ፎሪዋ:
እሺ ውዴ፡፡

ዳንኤል:
እየውልሽ ቤት ውስጥ ስላለንበት ሁኔታ ሳስብ ነበር፤ እንዴት እንደምንኖር በጣም ጨንቆኛል፡፡ ይሄ ኮቪድ-19 የሚሉት ነገር ከመጣ ወዲህ ሕይወታችን በፍጥነት ከጥሩ ወደ መጥፎ ተቀይሯል፤ እየባሰበት ነው፡፡ አሁን በሃገሪቱ ባለው አጠራጣሪ ሁኔታ ምክንያት አስተማሪዎች የደሞዛቸውን ግማሽ ብቻ ሊከፈላቸው እንደሆነ ከትምህርት ቤት ተነግሮኛል፡፡

ፎሪዋ:
ባለቤቴ ይህን በመስማቴ አዝናለሁ፡፡ ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፣ ግን እናልፈዋለን፣ ይህንን ወረርሽኝ እናልፈዋለን፡፡

ዳንኤል:
አዎ እናልፈዋለን፣ የምናልፈው ግን ዝምብለን ቁጭ ብለን ምንም ሳናደረግ አይደለም፡፡

ፎሪዋ:
እና ምን እናድርግ ትላለህ? የዉበት ሳሎኔን ከቤት መውጣት ከታገደ ወዲህ ከፍቼው አላውቅም፡፡ በአሁን ሰኣት ለጸጉር ሠሪ መደ ሥራ መመለስ አደገኛ ነው፡፡ ቫይረሱ በቀላሉ ከደምበኞቼ ሊተላለፍብኝ ይችላል፡፡

ዳንኤል:
አውቃለሁ፣ ለዚያም ነው ሳይረፍድ ህልውናችንን ማረጋገጥ ያለብን፡፡ ሴርዋ አሁን ወጣት ሴት ናት፤ ጥሩ አድርገን አሳድገናታል፡፡

ፎሪዋ:
[አፏን ከድና ትስቃለች] አዎ ጥሩ አድርገን አሳድገናታል፡፡ ብልህ እና ሃላፊነት የሚሰማት ልጅ በመሆኗ ኩራት ይሰማኛል፡፡

ዳንኤል:
በትክክል፤ ደሞ ስታምር …

ፎሪዋ:
እና ይሄ አሁን ካለንበት ችግር ጋር ምን ያገናኘዋል?

ዳንኤል:
ሁሉም ነገር … ባባን ታስታውሽዋለሽ?

ፎሪዋ:
ሃብታሙ ጓደኛህ?

ዳንኤል:
አዎ፡፡ ልጃችሁን ዳሩልኝ ብሎ ጠይቋል፡፡ ጥሩ ሰዓት ላይ ነው የጠየቀን፡፡ ልጃችንን ብንድርለት ይሄ ሰውይ ቤታችንን በምንፈልገው ነገር ሁሉ ሊሞላን ዝግጁ ነው፤ በየወሩም ጥሩ ድጋፍ ሊደርግልን ተስማምቷል!

ፎሪዋ:
አይሆንም! በፍጹም … ወይ ዳኒ፡፡ ለዚያ … ለዚያ ሰውዬ ልጃችንን ለመስጠት እንዴት ታስባለህ! በጣም ሽማግሌ እኮ ነው፤ በዚያ ላይ ሚስት አለው!

ዳንኤል:
ሚስቱኮ አምና ሞተች፣ እና ልጃችን ጥሩ ሚስት እንደምትሆነው ያምናል! ውዴ አስቢበት …

ፎሪዋ:
አላደርገውም፡፡ ሴርዋ በጣም አዋቂ ወጣት ናት፡፡ ትምህርቷን መጨረስ እና ዩኒቨርሲቲ መግባት አለባት፡፡ ብሩህ ተስፋ ያላት ልጅ ናት!

ዳንኤል:
ሃብታም ወንድ ከማግባት በላይ ምን ብሩህ አለ? አለምን በሙሉ ይሠጣታል፡፡

ፎሪዋ:
ውሸት፡፡ እንዳንተ ያለ መምህር እንዲህ ሊያስብ ይችላል ብዬ ማሰብ አልችልም! እንዲዚህ ባለ ጊዜ ልጅህን ለአንድ ሃብታም በትዳር ለመሸኘት እንዴት ማሰብ ቻልክ? ሴርዋ ገና ልጅ ናት እኮ በፈጠረህ!

ዳንኤል:
ምን ልጅ ናት!

ፎሪዋ:
አስራ ሰባት አመቷ ነው፡፡

ዳንኤል:
አዎ ደርሳለች፡፡

ፎሪዋ:
በፍጹም፡፡ እኔ በዚህ አልስማማም! ልጄን ለማይታወቅ ሰው እንድትድራት አልፈቅድም፡፡ እዚህ ከተማ እንኳ የሚኖር ሰው አይደለም እኮ፡፡ ቢያንገላታትስ፣ ቢጎዳትስ?

ዳንኤል:
አያደርገውም፡፡

ፎሪዋ:
እንዴት አወክ?

ዳንኤል:
በጣም ይወዳታል፡፡ ደሞ የማይታወቅ አይደለም፣ ጓደኛየ ነው፡፡

ፎሪዋ:
ድንቄም ጓደኛ፡፡ እኔ ሞቼ ነው ልጄን ለባእድ የምትድራት!

ዳንኤል:
[በጥፊ ይመታታል፣ ትጮሃለች] ካልሽ ይሁና! እንዴት ነው የምትመልሽልኝ እባክሽ! እዚህ ቤት ውስጥ ያለሽን ቦታ ረሳሽ እንዴ? ሚስቴ ነሽ!! አንቺ ከኔ እኩል አይደለሽም!! ሁለተኛ መልስ እንዳትሰችኝ!

የድምጽ ኢፌክት:
በሩን ጓ ያደርገዋል፤ ፎሪዋ ከቁጥጥር ውጭ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች

 

ከፍል 2

መቼት:
የፎሪዋ ቤት

ገጸባህርያት:
ፎሪዋ፣ ዳንኤል፣ ልጆች (ሴርዋ፣ ቤቢ እና ፓፓ)

የድምጽ ኢፌክት:
በር ሲጥጥ ብሎ ይከፈታል

ፎሪዋ:
ሴርዋ! ቀኑን ሙሉ የት ነው የዋ

ሽው? ስታስጨንቂኝ ዋልሽ እቦ!

ሴርዋ:
ይቅርታ እማማ፡፡ ተኝተሸ ስለነበር ልቀሰቅስሽ አልፈለኩም፡፡ እንኪ ትንሽ ምግብ እና ሳንቲም አምጥቼልሻለሁ፡፡

ፎሪዋ:
እንዴ ከየት አገኘሽው?

ሴርዋ:
ቤት የሰራኋቸውን ማስኮች ሸጥኳቸው፡፡

ፎሪዋ:
ውነት! እጄን ላፍታታበት ነው ስትይኝ አልነበረም፡፡

ሴርዋ:
አዎ ግን ስጨርሳቸው አሪፍ ሆኑልኝ፡፡ ቤት ገንዘብ እንደሚያስፈልገን ስላወኩኝ ሸጥኳቸው፡፡

ፎሪዋ:
ወይ ሴርዋ ምን ላድርግሽ፡፡ ኮርቼብሻለሁ፡፡

ሴርዋ:
አመሰግናለሁ እማማ፡፡ አንቺ እና አባባ ኑሮ እንደከበዳችሁ አውቃለሁ፡፡ ሁለት ልጆች ትመግባላችሁ፡፡ ሸክም መሆን አልፈልግም፡፡ … እኔን ከቤት ለማስወጣት ስላልተስማማሽ አመሰግናለሁ፡፡

ፎሪዋ:
ሽሽሽ … ዝም በይ፡፡ እንዳይሰማሽ፡፡

ሴርዋ:
ይቅርታ …

ፎሪዋ:
ምንም አይደለም፡፡ [ጉሮሮዋን ታጠራለች] ነጠላ ጫማሽን ውጭ አድርጊና ቀጥ ብለሽ ወደ ሽንትቤት ሂጂ፡፡ ውጭ ወጥተሸ እንዳልተዘናጋሽ ተስፋ አደርጋለሁ …

ኮረስ:
ኮቪድ-19 በትክክል አለ!

ሴርዋ:
አውቃለሁ እማ፤ ተጠንቅቄ ነበር፡፡ ማስኬን ቀኑን ሙሉ ሸፍኜ ነበር፡፡ ከደምበኞቼም የአንድ ሜትር እርቀት ጠብቄ ነበር፡፡

ፎሪዋ:
ሁለት ሜትር ካደረግሽው እረጋጋለሁ፡፡

ሴርዋ:
አይ እማ ከገዢዎቼ ሁለት ሜትር ከራኩኝ እንዴት አድርጌ ምርቴን ልሸጥ በው?

ፎሪዋ:
የራስሽ ጉዳይ … ሳኒታይዘርሽ የታለ?

ሴርዋ:
ይሄው …

ፎሪዋ:
ጎሽ፡፡ በይ ወደ ሽንት ቤት ሂጂ፡፡

ሴርዋ:
እሺ እማማ፡፡

ፎሪዋ:
ደሞ እባክሽ ልብስሽን በሞቀ ውሃ ዘፍዝፈሽ በሳሙና አሁኑን እጠቢው!

ሴርዋ:
አሺ እማማ!

ዳንኤል:
(ድምጹ መሰማት ይጀምራል) ያቺ ልጅሽ መጥታለች?

ፎሪዋ:
(ታንሾካሹከላች) ተሎ በይ ወደ ሽንት ቤት ሂጂ!

የድምጽ ኢፌክት:
በር ሲጥጥ ብሎ ይከፈታል፡፡

ዳንኤል:
ለምንም አትጠቅምም ብየሻለሁ፡፡ ፍቅረኛዋን ለማግኘት ሄዳ ነበር፣ አይደለም …?

ፎሪዋ:
አይደለም፡፡ የሰራቻቸውን ማስኮች ለመሸጥ ሄዳ ነበር፡፡ ይሄውልህ ገንዘብ ይዛልን መጣች፡፡ ጥሩ ልጅ ናት ብየሃለሁ፡፡ እባክህ ዳንኤል ሴርዋን እንደግፋት፣ አንድ ቀን ታኮራናለች፡፡

ዳንኤል:
ጥፊ ከፊቴ፤ ሁለታችሁም ታስጠሉኛላችሁ፡፡

ፎሪዋ:
ዳንኤል፣ ምን አድርጌሃለሁ እንደዚህ የምታደርገኝ? ሴርዋ ብቸኛዋ ሴት ልጃችን ናት፣ እሷን …

ዳንኤል:
ውጭልኝ አልኩሽ እኮ! (ደጋግሞ ሲመታት በህመም ታለቅሳለች፡፡ ሕጻኑ ማልቀስ ይጀምራል፡፡)

ፓፓ:
አባባ … ዳዳ … ተው (እየተንሰቀሰቀ ያለቅሳል)

ዳንኤል:
ዝም በል፣ ምን ታውቃለህ? (ፎሪዋን እንደገና ይመታታል፤ እሷም ትጮሃለች)

ሴርዋ:
አባባ!

ዳንኤል:
አንቺ ደሞ ሴርዋ!

ፎሪዋ:
እባክህ አትምታት … እባክህ …

ዳንኤል:
ባል አግቢና ከዚህ ቤት ውጭልኝ፤ እኛ የምናበላው ብዙ ልጅ አለን፡፡ አንቺ ትልቅ ነሽ ከጫንቃችን ውረጅ፡፡ ሂጅ እቃሽን አዘጋጂ፣ እዚህ ቤት የምትኖሪበት ጊዜ ሊያበቃ ትንሽ ቀን ነው የቀረሽ!

ፎሪዋ:
እባክህ አትምታት እባክህ …

ዳንኤል:
ከፊቴ ጥፉ … ሁላችሁም፡፡ (በሩን በሃይል ይዘጋዋል)

የድምጽ ኢፌክት:
ልጆች ጮኸው ያለቅሳሉ፤ እናት ተንሰቅስቃ ታለቅሳለች፡፡

ሴርዋ:
ይቅርታ እማማ ይቅርታ!

ፎሪዋ:
ያንቺ ጥፋት አይደለም፤ ሁላችሁም አላጠፋችሁም፡፡ አባታችሁ ስለጨነቀው ነው፡፡ ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል፡፡

 

ክፍል 3

መቼት:
የፎሪዋ ቤት

ገጸባህርያት:
ፎሪዋ፣ ዳንኤል፤ ልጆች (ሴርዋ፣ ቤቢ እና ፓፓ)

የድምጽ ኤፌክት:
መግቢያ ሙዚቃ

ሴርዋ:
እማ … እማማ! ይሄን ፕሮግራም መስማት አለብሽ፡፡ በጣም አስተማሪ ፕሮግራም ነው፡፡

ፎሪዋ:
ስራ ይዣለሁ ሴርዋ፡፡ ራዲዮውን ወደ ማድቤት ይዘሽው ነይ፡፡

ሴርዋ:
እሺ፡፡ (ቆም ትላለች)

የድምጽ ኢፌክት:
ሙሲቃ ይጫወታል

ሴርዋ:
አዳምጪ የራዲዮ ኤክስ ሳምንታዊ መልእክት ነው፡፡ በየሳምንቱ የተለያዩ ርእሶችን ያቀርባሉ፡፡ በጣም አስተማሪ ነው፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
[የራዲዮው ድምጽ ይመጣል] ይህ የራዲዮ ኤክስ ሳምንታዊ ስርጭት ነው፡፡ ሰላም ውድ አድማጮቻችን፡፡ ይህ መልእክት በሴቶች የፍቅር እና አገልግሎት ፋውንዴሽን ቀርቦላችኋል፡፡ በጥንቃቄ አድምጡ ራሳችሁንም ጠብቁ፡፡

የአንድ ሰከንድ ሙዚቃ፣ ከዚ የሚከተለው መልእክት ይተላለፋል

በዚህ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሰዎች በአንድ ቦታ ለረጅም ጊዜ ስለሚቀመጡ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች የመፈጠር እድላቸው ይጨምራል፣ ነገር ግን በወዳጆቻችን ላይ ጉዳት ከማድረስ መታቀብ አለብን፡፡ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ተጎጆዊች ላይ ብዙ ስቃይ እና ጉዳት ያድረሳሉ፣ የሰውን የማንነት ክብር ያጠፋሉ፣ በአካ እና በአይምሮ እንዲሽመደመዱ ደርጋሉ፡፡

ውድ አድማጮቻችን መደፈር፣ ያለእድሜ ጋብቻ፣ የሴቶች ግርዛት፣ ተገዶ መዳር እና አካላዊ አእመሯ ዊ እና ስሜታዊ በደሎች ሁሉም ጾታ መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አይነቶች ናቸው፡፡ በሕግ የሚያስቀጡ እና አጥፊዎቹ ታስረው የሚከሰሱባቸው የበደል አይነቶች ናቸው፡፡

ማንኛውም አይነት ጾታዊ ጥቃት እየደረሰበት ያለ የሚያውቁት ሰው ካለ እባኮትን ዝም አትበሉ፡፡ እንዲዚህ ያሉ ጉዳዮችን በቅርብ ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ይጠቁሙ ወይም በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ፡- *3390# ወይም *12i4፡፡ (የኤዲተሩ ማስታወሻ፡- እነዚህ ትክክለኛ ቁጥሮች አይደሉም፡፡ በአካባቢያችሁ ያለ ትክክለኛ እርዳታ የሚገኝበት ስልክ ቁጥር ባለቤቱን ፈቃድ ጠይቃችሁ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡)

እናቶች፣ አያቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶች፣ ጎረቤቶች ሁላችንም እርስ በርስ እንጠባበቅ፡፡ በአካባቢችሁ ያሉ ተጠቂዎችን ድረሱላችው፡፡ ውድ ጉዳት የደረሰባችሁ ሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ አትፍሩ፡፡ በቤት ውስጥ ቆዩ፣ ደህንነታችሁን ጠብቁ፣ ለተደበቀው ወረርሽኝ ማለትም ለጾታዊ ጥቃት እጅ አትስጡ!

የፕሮግራሙ መለያ ሙዚቃ ይጫወታል

ፎሪዋ:
እሱን ነገር አጥፊው፣ ራዲዮውን አጥፊው! ስለዚህ ጉዳይ እንደሚያወሩ አውቀሽ ነበር?

ሴርዋ:
እማማ …

ፎሪዋ:
አውቀሽ ነበር ወይ?

ሴርዋ:
አላወኩም … ባለፈው ሳምንት ሰምቼው በኮቪድ-19 ምክንያት በታወጀው ከፊል የእንቅስቃሴ እግድ ጊዜ እንዴት እራሳችንን መጠበቅ እንደምንችል አስተምረውን ነበር፡፡ የዛሬው መልእክት ምን እንደሆነ አላወኩም ነበር፡፡ (ቆም ትላለች) እማማ ደና ነሽ?

ፎሪዋ:
አዎ!

ሴርዋ:
ታዲያ ለምንድን ነው ጠረጴዛውን በቢላ የምትወጊው? (ፎሪዋ ቢላውን ትጥለዋለች)

የድምጽ ኢፌክት:
ቢላዋው ወደ መሬት ሲወድቅ ሴርዋ የታፈነ ጩኸት ታሰማለች፡፡

ሴርዋ:
እማማ … (በቀስታ)

ፎሪዋ:
ይህንን ፕሮግራም ስንሰማ አባትሽ ቢያገኘን ምን እንደሚያደርግ ታውቂያሽ?

ሴርዋ:
ግን አልሰማም እኮ፣ ስለዚህ ለኛ ጥሩ ነው፡፡ እማማ እርዳታ መጠየቅ አለብን፡፡ ለፖሊስ እንናገር ወይም …

ፎሪዋ:
ሽሽሽ ማንም ወደ ፖሊስ አይሄድም፡፡ አብደሻል? አባትሽን እንዲያስሩት ትፈልጊያሽ?

ሴርዋ:
ግን እማማ ለማናውቀው ሰው ሊድረኝ ይፈልጋ፡፡ እማማ ገና ሕጻን ልጅ ነኝ፣ እኔን እንዲድረኝ ሕጉ አይፈቅድለትም፡፡ ባሌ አርብ እንደሚመጣ ነግሮኛል፡፡

ፎሪዋ:
ምን አለሽ???

ሴርዋ:
አዎ እማ፡፡ እንዳልነግርሽ ቃል አስገብቶኛል፡፡ አንቺ ብትስማሚም ባትስማሚም እኔን ሊድረኝ ቆርጧል፡፡

ፎሪዋ:
አይሆንም!

ሴርዋ:
እና ምን እናድርግ እማማ?

ፎሪዋ:
አላውቅም …

ሴርዋ:
ግንኮ እማማ…

የድምጽ ኢፌክት:
ሕጻን ልጅ ያለቅሳል

ፎሪዋ:
ሂጅልኝ እና ወንድምሽን ጠብቂ፡፡ ተይኝ፡፡ ላስብበት፡፡

ሴርዋ:
እሺ፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
ፎሪዋ ምርር ብላ ታለቅሳለች

 

ክፍል 4

መቼት:
የፎሪዋ ቤት

ገጸባህርያት:
ፎሪዋ፣ ዳንኤል፣ ልጆች (ሴርዋ፣ ቤቢ እና ፓፓ)፣ ባባ፣ ፖሊስ፣ ቪቪየን

የድምጽ ኢፌክት:
የጭነት መኪና ድምጽ

ዳንኤል:
ያው መጣ፡፡ ና እዚጋ አቁም፡፡ እንኳንም አገኘሁህ ውድ ጓደኛዬ፡፡ በከፊል እግዱ ምክንያት የምትመጣ አልመሰለኝም ነበር፡፡ የፖሊስ ኬላዎችን እንዴት አለፍካቸው?

BABA:
ሃሃሃሃ፣ ለቤት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመግዛት ሄድኩኝ፡፡ ይሄን ሁሉ ምግብ ለምስክርነት ተሸክሜ ማን እንዳላልፍ ሊከለክለኝ ነው?

የድምጽ ኢፌክት: ትልቅ የሳቅ ድምጽ

ዳንኤል:
ሰራህላቸው፣ ጓደኛየ፡፡ (ቆም ይላል) ፎሪዋ ነይና እነዚህን ነገሮች አስገቢ፡፡

ፎሪዋ:
አቤት?

ዳንኤል:
ጀሮሽ አይሰማም፡፡ ነይ ሄንን አስቤዛ አስገቢው አልኩሽ!

ፎሪዋ:
እሺ፡፡ (ትጣራለች) ሴርዋ …

ዳንኤል:
ሴርዋ አታስፈልግም፣ ባሏን ለመገናኘት እየተዘጋጀች ነው፡፡ ጥሎሽ እስክንስማማ እና የተለመደውን አረቂ እስክንቀበል ድረስ ሊያያት አይገባም፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
ወንዶች በጣም ይስቃሉ፡፡

ባባ:
ልክ ብለሃል ጓደኛዬ፡፡ (ይስቃል)

ፎሪዋ:
ዳንኤል አንዴ ቤት ላነጋግርህ … እባክህ?

ዳንኤል:
ባባ ቁጭ ብለህ ጠብቀኝ፤ አሁን እመለሳለሁ፡፡ ፓፓ ለባባ የሚጠጣ ውሀ ስጠው እስኪ፡፡

ፎሪዋ:
ፓፓ ማስክህን አድርግ፡፡ ከእንግዶቹም ቀርበህ አትቁም፤ ውሃውን ጠረጰዛው ላይ አድርግላቸውና ወደ ቤት ግባ፡፡

ፓፓ:
እሺ እማማ፡፡

ዳንኤል:
ይህ ሁሉ ምን ለማለት ነው?

ፎሪዋ:
ልጆቼን ከኮሮናቫይረስ መጠበቅ አለብኝ፡፡

ዳንኤል:
ለምን? ባባ ስታይው በሽተኛ ነው?

ፎሪዋ:
አላ ኩም፣ ነገር ግን ኮቪድ-19 ኖሮብህ ምንም ምልክት ላታሳይ እንደምትችል ሰምቻለሁ፡፡ ኋላ ከማዘን መጠንቀቅ ይሻላል፡፡

ዳንኤል: የራስሽ ጉዳይ! ምን ፈለግሽ አሁን፣ ጓደኞቼን ማስጠበቅ አልፈልግም፡፡

ፎሪዋ:
ዳንኤል እባክህ ተረጋግተህ አስበው፡፡ ልጅህን አስገድዶ መዳር ሕገ ወጥ ነው፡፡ ሴርዋ እድሜዋ አልደረሰም፡፡ ልትታሰር ትችላለህ፡፡ ውዴ እባክህ አዳምጥ …

ዳንኤል:
ምን! እኔ የማይሰማኝ ወይም እብድ አደረግሽኝ?

ፎሪዋ:
እንደሱ ማለቴ አይደለም፡፡ እኔ …

ዳንኤል:
ከጉዳዬ ውስጥ ውጪ ሴትዮ፡፡ [አንቆ ይዞ በያዳንዱ ቃል ይመታታል] እኔ – በልጄ- የፈለኩትን-አደርጋለሁ፡፡

ፎሪዋ:
ኡኡኡ ድረሱልኝ ኡኡኡ

ሴርዋ:
አባባ እባክህ ተው … አንገቷን ልቀቃት፣ ትገላታለህ፡፡ እባክህ አቁም … ድረሱልን …

የድምጽ ኢፌክት:
በሩ ሲጥጥ ብሎ ይከፈታል

ባባ:
እንዴ ጓደኛዬ ምን እያደረክ ነው? ሚስትህን ልትገላት ትፈልጋህ እንዴ? ልቀቃት!

ፓፓ:
ዳዳ፣ ዳዳ፣ ፖሊሶች ውጭ ቆመዋል!

ዳንኤል:
ምን? ፖሊስ? ማነው ፖሊስ የጠራው? ፎሪዋ፣ አንቺ ነሽ ፖሊስ የጠራሺው?

ፎሪዋ:
አይደለሁም … [ትስልና በእንባዋ መሃል ለመናገር ትሞክራለች] ውነቴን ነው ፖሊስ አልጠራሁም፡፡ ምናልባት ጎረቤቶቻችንን ፈልገው ይሆናል፡፡

ዳንኤል:
አዎ እዚህ ግቢ የምንኖር እኛ ብቻ አይደለንም፡፡ አሁን ሁላችሁም እንድትረጋጉ እፈልጋለሁ፣ ትሰማላችሁ?

የድምጽ ኢፌክት:
ለቋት ሄድና በሩን ከፍቶ ወደ ውጭ ይወጣል፡፡

ቪቪየን:
እንደምን አደርክ ጌታየ፡፡ ቪቨየን ላምፕቴይ እባላለሁ፡፡ ከሴቶች የፍቅር እና አገልግሎት ፋውንዴሽን ነው የመጣሁት፡፡ አንዲት ወጣት የጭንቀት ጥሪአስተላልፋልን ነበር፤ ወደዚህ ግቢ የመራችኝ እሷ ናት፡፡

ዳንኤል:
እሺ፣ ሊሊያን ልትሆን ትችላች፡፡ የሚቀጥለው ቤት ጠይቂ፡፡

ቪቪየን:
አሁን ያለሁት ትክክለኛው ቦታ ላይ ይመስለኛል፡፡ አቶ ዳንኤል ነዎት?

ዳንኤል:
አዎ እኔ ነኝ፡፡ እኔ ደውዬ ነበር??

ቪቪየን:
አይ አልደወሉም፡፡ የደዋዩን ስም መግለጽ አንችልም፡፡ ግን በቂ መረጃ አለን፡፡ እድሜዋ ያልደረሰችውን ልጆትን ለመዳር እንዳሰቡ እናውቃለን፡፡ ይህ የአገሪቱን ሕግ የሚጥስ ሲሆን በህግ የሚያስቀጣ ጥፋት ነው፡፡

ዳንኤል:
ፎሪዋ (ቆም ይላል) አንቺ ነሽ አይደል? ደወልሽላቸው? (ይዝታል) አንቺ ምስጋና ቢስ ሴት፣ እኔ … …

ሴርዋ:
አቁም አባባ! እናቴን ትገላታለህ … እኔ ይህን ሽማግሌ ሰውየ ማግባት አልፈልግም፡፡ እትዬ እባክሽ እርጅን፡፡

ዳንኤል:
ሴርዋ!

ፎሪዋ:
ልጄን ለቀቅ አድርግ፤ እኛ ምንም አላደረግንም፡፡ ውነቴን ነው! እኔ አልደወልኩላቸውም!

ዳንኤል:
ዝጊ ሴትዮ! (ፎሪዋን በሃይል ይይዛታል)፡፡ ንገሪኛ ታዲያ እነዚህ ሰዎች እዚህ ምን እያደረጉ እንደሆነ፡፡ (ፎሪዋ በፍርሃት ትጮሃለች)

ፖሊስ:
እንዳትነካት፡፡ ኮንሰታብል ብራይት ቢልሰነ እባላለሁ፡፡ ልጅህን ያእድሜዋ ለመዳር በመሞከር እና ሚስትህን በመደብደብ ታስረሃል፡፡ ዝም የማለት መብት አለህ፤ የምታደርገውም ሆነ የምትነገረው ነገር ሁሉ በፍርድ ቤት መረጃ ሆኖ ይቀርብብሃል፡፡ የህግ አማካሪ የማግኘት መብት አለህ፡፡

ዳንኤል:
ምን? አይሆንን … ልጄ 18 ዓመቷ ነው፣ እድሜዋ ደርሷል፤ ለማግባትም ተስማምታለች፡፡ ባለቀ ሰኣት ነው ሃሳቧን የቀየረችው፣ ለኔ እንዴት እንደምትነገረኝ ጠፍቷት ነው፡፡ ለዚያ ነው የምትዘላብደው … ባለቤቴም ምንም አልሆነችም፡፡ እይዋት ምንም አልሆነችም፡፡

ቪቪየን:
እንደዛ ነው? ታዲያ የሚስትህ ፊት የበለዘው ምን ሆኖ ነው?

ፎሪዋ:
ኧረ ወድቄ ነው፡፡

ዳንኤል:
ሰማሻት አይደል ሚስቴን፡፡ ወድቃ ነው፡፡ ቤቴ መጥተሸ በሃሰት ልትከሽኝ መብት የለሽም፡፡

ቪቪየን:
አሜቴ ምንም መፍራት አያስፈልግሽም፡፡ እባክሽን ውነቱን ንገሪን፡፡ ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል፣ አትፍሪ፡፡ ይህ የዜጎች መብት ጉዳይ ስለሆነ አንቺም ልጅሽም ባልሽም ቢሆን የሚያስፈልጋችሁን ድጋፍ እንታገኙ እናደርጋን፡፡ ባለቤትሽ ይህን ጉዳት ካደረሰብሽ ችግር ሊኖርበት ይችላል፡፡

ሴርዋ:
እማማ እባክሽ ውነቱን ንገሪያቸው … እርጅኝ እማማ፡፡ አባባም እርዳታ ያስፈልገዋል …

ቪቪየን:
እመኝኝ፣ ቤተሰብሽን ለመርዳት ትክክለኛው መንገድ ይሄ ነው፡፡ ባልሽ ለሰራው ወንጀል በሕግ ይጠየቃል፣ ነገር ግን እሱም እራሱን እንዲያሻሽል እና ምርጫዎቹ ላይ በደንብ እንዲያስብ ይህ የተሻለው መንገድ ነው፡፡ እንዲዚህ መርዛማ በሆነ ከባቢ ልጆችሽን ማሳደግ የለብሽም፡፡

ሴርዋ:
እማማ እባክሽ… እባክሽ

ዳንኤል:
ፎሪዋ … እባክሽ …

ፎሪዋ:
አዎ እሱ ነው፡፡ ሁል ጊዜ ጉዳት ያደርስብኛል፡፡ እየባሰበት ነው የሄደው፡፡ የእንቅስቃሴ እገዳ ተደርጎ ቤት መዋል ከጀመርን በኋላ የበለጠ መጥፎ ሆኗል፡፡ ለልጆቼ ሁለቱ ወንዶች ልጆቼ እና ቆንጆዋ ልጄ ሴርዋ ሁልጊዜ እፈራለሁ፡፡ በጣም አዋቂ ልጅ ናት፡፡ ይሄን አሮጌ ቂል ማግባት አይገባትም፡፡ [ታለቅሳለች]

ባባ:
ማነው አሮጌ ቂል? አምቻሽ ነኝ፣ ንቀት አታሳይኝ!

ቪቪየን:
ኮንስታብል ይህንንም ሰውየ እሰረው፤ እድሜዋ ያ

ደረሰች ልጅ ለማግባት ነው የመጣው፡፡

ፖሊስ:
ጌታየ አንተም ከኔ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ አለብህ፡፡

ባባ:
አይሆንም፣ አይሆንም፣ አይሆንም …

ፖሊስ:
ቃልህን ጣቢያ ስንደርስ እንቀበልሃለን፡፡ ዝም የማለት መብት አለህ፤ የምታደርገውም ሆነ የምታነገረው ነገር ሁሉ በፍርድ ቤት መረጃ ሆኖ ይቀርብብሃል፡፡ የህግ አማካሪ የማግኘት መብት አለህ፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
በር ተክፈቶ ይዘጋል፡፡ ቆም ይልና እንደገና ይከፈታል፡፡

ፎሪዋ:
የልጄ የልደት ሰርቲፊኬት ይሄው፡፡ ዕድሜዋ እንዳልደረሰ ማረጋገጫ ነው፡፡

ዳንኤል:
ፎሪዋ፣ እባክሽ፡፡ እመቤቴ ይቅርታ፡፡ እስኪ እንነጋገር፡፡ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ከመታገዱ በፊት የእለት እንጀራችንን ለማግኘት እየሞከርኩ ነበር፡፡ ከስረናል … ትምህርት ቤት ስለተዘጋ የደሞዛችንን ግማሹን ብቻ ነው እየከፈሉን ያለው፡፡ እኔ ገንዘብ የሚያስፈልገኝ የጨነቀው አባት ነኝ፡፡

ቪቪየን:
ሚስትህን ለመደብደብስ ምክንያትህ ምንድን ነው? እያት እስኪ – ፊቷ ካንተ ዱላ የተነሳ አብጧል፡፡

ዳንኤል:
ይቅርታ፤ ልጎዳት ፈልጌ አይደለም፡፡ ስለጨነቀኝ ነው፡፡

ቪቪየን:
መጨነቅ የትዳር ጓደኛህን ወይም የምትወዳቸውን ሰዎች እንድትበድል ፈቃድ አይሰጥህም፡፡ መሮጥ፣ ስፖርት መሥራት፣ በጽሞና ማሰብ ወይም ሌሎች ጤነኛ ነገሮችን በማድረግ ጭንቀትህን ማስወገድ ትችላለህ፤ አንተ ግን ሌሎችን ለመጉዳት ወሰንክ፡፡

ፖሊስ:
እንሂድ!

ዳንኤል:
እባክህ [ማልቀስ ይጀምራል]፡፡ ይቅርታ፣ ይቅርታ፡፡

ቪቪየን:
ከመጣን ጀምሮ በግልጽ ስለነገርሽን አመሰግናሁ ሴርዋ፡፡ በጣም ጀግና ነሽ፡፡ በሮቻችን ላንቺ ክፍት ናቸው፡፡ በርቀት የምክር አገልግሎት ልንሰጥሽ እንችላለን፤ ሕይወታችሁ እስከሚስተካከልም ድረስ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንችላለን፡፡ ካርዴን እንኪ፡፡ በማንኛውም ጊዜ ልትደውይልኝ ትችያለሽ፡፡

ፎሪዋ:
[እንደማለቃቀስ እያች] አመሰግናለሁ፡፡

ፖሊስ:
እመቤቴ አንቺ እና ልጅሽ ቃላችሁን ለመስጠት ከኔ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያ መምጣት አለባችሁ፡፡ እሷ እድሜዋ ስላልደረሰ አንቺ ፈቃደኝነትሽን መግለጽ አለብሽ፡፡

ፎሪዋ:
እሺ አንመጣለን፡፡

ቪቪየን:
እኔ በመኪና አመጣቸዋለሁ፡፡ በኮቪድ-19 ምክንያት የፖሊሱ መኪና አሁን ሞልቷል፡፡

ፎሪዋ:
አመሰግናለሁ፡፡ በጣመ ባለውለታ ነን፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
ዳንኤል ሳግ እየተናነቀው ማ

ቀስ እና መለመን ይቀጥላል፡፡

 

ክፍል 5

መቼት:
ፖሊስ ጣያ

ገጸባህርያት:
ቪቪየን፣ ፎሪዋ፣ ዳንኤል፣ ፖሊስ

የድምጽ ኢፌክት:
የእግር ኮቴ

ፎሪዋ እና ቪቪየን:
እንደምን አደሩ ኮንሰታብል

ፖሊስ:
እንደምን አደራችሁ፤ እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ ምን ልርዳችሁ?

ፎሪዋ:
እምምም ደህና ነኝ፡፡ ማለቴ ባለቤቴን … እእእ… በዋስ ለማስወጣት ፈልጌ ነበር የመጣሁት፡፡

ፖሊስ:
አቶ ዳንኤልን ነው? ቆይ ቆይ አንቺ ፎሪዋ አይደለሽም?

ፎሪዋ:
አዎ፣ ፎሪዋ ነኝ፣ ባለቤቱ፡፡

ፖሊስ:
ስልደበደበሽ ወደ ቤትሽ ተጠርተን መጥተን ነው ያሰርነው፡፡ እና አሁን በዋስ ልታስፈቺው ነው? [አፉን ከድኖ ይስቃል]

ፎሪዋ:
ኮንስታብል … ሊያስገርም ይችላል፣ ግን ባለቤቴ ነው … ደሞ ብዙ ጭንቀት ነበረበት! ምን እንደሚያደርግ አላወቀም ነበር፡፡ እባኮት አሁን ባሌን በዋስ ላስፈታ ነው የመጣሁት፡፡

ቪቪየን:
ኮንስታብል እባኮትን አቶ ዳንኤልን ያስጠሩልን፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
የእስር ቤት ክፍል በር ሲጥጥ ብሎ ይከፈትና ይዘጋል፡፡

ቪቪየን:
ፎሪዋ ተረጋጊ፡፡ እንደፈራሽና እንደተጠራጠርሽ አውቃለሁ …

ፎሪዋ:
አዎ፣ ባሌን እዚህ መተው አልፈልግም …

ዳንኤል:
ፎሪዋ፣ መጣሽ እንዴ!

ፎሪዋ:
እንዳትነካኝ፡፡

ዳንኤል:
ይቅርታ ፎሪዋ፤ እባክሽ ይቅር በይኝ፡፡

ቪቪየን:
ዳንኤል፣ ይህን ያህል የምትወድህ ሚስት አለችህ፣ አንተ ግን እንደዚያ ታንገላታታለህ፡፡ [አፏን ከድና ትስቃለች]

ዳንኤል:
እስኪጠፋብሽ ድረስ ያለሽን ነገር አታውቂውም፡፡ ሕምም፡፡ ጓደኛዬ ባባስ እንዴት ነው፤ አሁንም እዚህ ነው?

ፖሊስ:
ሦስተኛ እና አራተኛ ሚስቶቹ ነን ያሉ ሁለት ሴቶች በዋስ ሊያስፈቱት መጥተው ነበር!

ፎሪዋ:
ሦስተኛ እና አራተኛ ሚስቶች? ዳንኤል ሚስቱ ሞታበታለች አላልከኝም ነበር?

ዳንኤል:
ውሸቴን ነበር፡፡ ይቅርታ፣ ፎሪዋ፡፡ ባደረኩት ተጸጸቻለሁ፤ ከአንግዲህ አይሆንም፡፡

ፎሪዋ:
ወይ አምላኬ! ይህንን አውቄ ቢሆን ኖሮ አንተን በዋስ ለማስወጣት አልመጣም ነበር፣ አንተ ውሸታም! ቪቪየነ ዋስ እንዲገኝ ያደረግሽ ለምንድን ነው? ንጹኋን ልጄን አምስተኛ ሚስቱ ለማድረግ በመፈለጉ የእጁን ሳያገኝ እንዲወጣ አልፈልግም፡፡

ቪቪየን:
አይዞሽ ፎሪዋ፡፡ የሥራውን ያገኛል፡፡ ዕድሜዋ ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በመሞከሩ በቅርብ ችሎት ፊት ይቀርባል፡፡ ባልሽም እንዲሁ፡፡

ዳንኤል:
እመቤቴ በራሴ በጣም እፍሪያለሁ .. ቢምቢ በሞላው እስር ቤት ውስጥ ያሳለፍኳቸው ሁለት ቀኖች እንዳስተውል አድርገውኛል፡፡ ፎሪዋ በነዚህ ፖሊሶች ፊት አንቺንም ስርዋንም ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ ቤተሰቤን ለማስተዳደር ያለው ጫና እንዲህ ናላየን እንዲዞረው እንዴት እንደፈቀድኩለት አላውቅም፡፡ አይምሮየን ነው ያጠፋው፡፡ አንዳንድ ወንዶች እኔን ጨምሮ ከሁሉ ነገር በላይ የሆንን ይመስለናል … (ቆም ይላል) ሕጉ እስኪይዘን ድረስ የማንነካ ይመስለናል፤ ያኔ ከህጉ በተቃራኒ ጎን መገኘት እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ እናያለን፡፡ ከልቤ አዝናለሁ፡፡ ነገሮችን ማስተካከል እፈልጋለሁ፡፡ አንቺም ልጆቻችንም ላይ ከዚህ በኋላ እጄን አላነሳም፡፡ አንቺንም ልጆቼንም የሚያስከፋ ቃል ላለመጠቀም እሞክራሁ፡፡

ቪቪየን:
አቶ ዳንኤል፣ ወሬ ቀላል ነው በድርጊት ካ

ተደገፈ፡፡ እንካ ይሄ ደብዳቤ ወደቤት ውስጥ ጥቃት እና ተጎጂዎች ማዕከል እንድትመጣ ግብዣ ነው፡፡ ባለቤትህ ቅሬታዋን ልካለች፣ ስለዚህ ከአንድ የቤተሰብ አባል ጋር ቢቻል ሽማግሌ ሰው አብረህ መምጣት ይጠበቅብሃል፡፡

ዳንኤል:
ይቅርታ አልኩኝ እኮ… ፎሪዋ?

ቪቪየን:
ይሄ ለሁለታችሁም አስፈላጊ ደረጃ ነው፣ ዳንኤል፡፡ ሕጉ ታሪክህን መመዝገቡን የምናራጋግጠው በዚህ መንገድ ነው – ምናልባት ድጋሚ ተመሳሳይ ስህተት ከሠራህ!

ዳንኤል:
ሁለተኛ አይደገምም ፎሪዋ፡፡ ሁለተኛ አልመታሽም፣ እባክሽ፣ እስር ቤት መግባት አልፈልግም …

ፎሪዋ:
በቤታችን ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ቤተሰቦቻችን ማወቃቸው ለኔ አስፈላጊ ነው፡፡

ፖሊስ:
አዎ በማእከሉ የአጥቂ እና ተጠቂ ቤተሰቦች ለምስክርነት ይጠራሉ፡፡ በዚህ መልክ ለነሱም ለሕጉም ተጠያቂነት ይኖርሃል፡፡

ቪቪየን:
ወረርሽኙ ሰዎች የትዳር ጓደኞቻቸውን እንዲጠቁ ቀላል አድርጎላቸዋል፡፡ ይህ አስጨናቂ ሁኔታ ነው፡፡ አንተና ሌሎችም አጥፊዎች ኮቪድ-19 ወንጀል ለመፈጸም እና የትዳር ጓደኞቻችሁን ለመበደል አጋጣሚ እንዳ

ሆነ እና ሁሉም አጥፊ በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን እንደምታውቁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ከተያዝክ ህጉ በሙሉ ኃይሉ ያርፍብሃል፡፡

ዳንኤል ይህ ደብዳቤ የእስር ፍርድ አይደለም፡፡ በማእከሉ ይህንን ሁኔታ ከቤተሰብህ ጋር ተነጋረህ ለመፍታት እድል ይሰጥሃል፤ ካልሆነ እንደጥፋቱ መጠን ጉዳይህ ወደ አማራጭ የክርክር መፍቻ ማዕከል ይተላለፋል፡፡ ይሄ እንግዲህ ሚስትህ ሁለተኛ እድል እንደምትሰጥህ እና እንደማትሰጥህ ታይቶ ይወሰናል፡፡ ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሚስትህ ለመክሰስ ወሰነችም አልወሰነችም በህግ እንደምትጠየቅ መገንዘብ አለብህ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ በኋላ በጣም ጥሩ ጸባይ ማሳየት አለብህ፡፡

ፎሪዋ:
ጥሩ ሰው እንደሆንክ አውቃለሁ፤ ሌላ እድል ልሰጥህ እፈልጋለሁ … በትግስት እና በጽናት ይህንን የወረርሽኝ ወቅት እናልፈዋለን፡፡ ይህንን ግን በህጋዊ መንገድ ማድረግ አለብን፣ ሁለተኛ እንዳሻህ ልታደርግብኝ አትችልም፡፡

ዳንኤል:
አመሰግናለሁ ፎሪዋ፣ ይገባኛል … አሁን ወደ ቤት እንሂድ፡፡

ፎሪዋ:
ዳንኤል፣ አሁን ወደ ቤት ለመሄድ ዝግጁ አይደለሁም፡፡ (ቆም ትላለች) ሴርዋም ዝግጁ አይደለችም፡፡ ብትናፍቃትም በጣም ግራ ተጋብታለች፡፡

ዳንኤል:
ይገባኛል፤ ግን የት ትቆያላችሁ?

ቪቪየን:
አንተን በዋስ ለማስፈታት ስንስማማ ወደ መጠለያችን አምጥተናቸዋል፡፡

ዳንኤል:
መጠለያ?

ቪቪየን:
አዎ፡፡ የሴቶች ፍቅር እና አገልግሎት ፋውንዴሽን መጠለያ፡፡ አይዞህ እየተንከባከብናቸው ነው፡፡ የቫይረሱን ስርጭት ለመገበደብ እና መጠለያችንን ጤናማ ለማድረግ ሁልጊዜም የማሕራራዊ መራራቅ ደምቦችን እንፈጽማለን፤ የዓለም ጤና ድርጅት እና የጋና ጤና አገልግሎት ያወጧቸውን መመርየዎችም እንከተላለን፡፡ በሳምንት አንድ ቀን ከነሱ ጋር እንድትገናኝ ይጠበቅብሃል፣ በጉብኝትህም ወቅት ተቆጣጣሪ ይኖራል፡፡ የአይምሮ ሕክምና ባለሙያዎቻችን አንተና ቤተሰብህ እየራሳችሁን እንድትገነዘቡ እና ፍርሃቶቻችሁን እንድታሸንፉ፣ ንዴታችሁን እና ጭንቀታችሁን መቆጣጠር ትችላላችሁ፡፡ ይህ ሂደት ካበቃ በኋላ ዱላ እና ሌሎች አጠራጣሪ እርምጃዎችን ሳትጠቀም ቤተሰብህን ለመንከባከብ የተሻለ ብቃት እንዲኖርህ የእርቀት ስብሰባዎችም ይኖራሉ፡፡

ዳንኤል:
ህምምም …

ቪቪየን:
ልጅህን ለገንዘብ ብለህ መዳር ደስታዋን እና እድገቷን ያሳጣት ነበር፡፡

ዳንኤል:
አዎ አይኖቼ ተገልጸዋል፤ ትምህርቴን ተምሪያለሁ፡፡ ልጄ ሙሉ እና ደስተኛ ህይወት እንድትኖር የሚያስፈልገውን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡

ፎሪዋ:
አዎ ዳኒ፡፡ ገንዘብ ማለት ሁሉም ነገር አይደለም፡፡ ዋናው ነገረ ትእግስት እና የመኖር ቁርጠኝነት ነው፡፡ በየቀኑ ሕይወት እየተሻሻለ ይሄዳል፡፡

ፖሊስ:
ጥሩ ተናግረሃል ዳንኤል፤ ነገር ግን አሁን ምግባርህ ይናገር፡፡ የሃገሪቱ ሕግ በዝምታ ይከታተልሃል፤ ድጋሚ እስከምትያዝ ድረስ እንከታተልሃለን፡፡ ደግመን እስከምንገናኝ ቻው …

ዳንኤል:
ኧረ በፍጹም እኔ ፖሊስ ማቆያ ውስጥ ድጋሚ አልገባም፤ እንደገና ተወልጃለሁ! [ሁሉም ይስቃሉ]

ቪቪየን:
እሱን መስማታችን ደስ ይላል፤ ካልክ አይቀር ግን ከልብህ ይሁን፡፡ አመጽ በፍጹም መልስ አይሆንም!

ፎሪዋ:
ደና ሁን ዳንኤል፤ በቅርብ እንገናኛለን፡፡

ዳንኤል:
ደና ሁኝ ፎሪዋ፡፡ ሁሉንም ስብሰባ እመጣለሁ … ቃ

እገባልሻለሁ፡፡

ፖሊስ:
ስብሰባ መምጣትህ ጥቅሙ ለራስህ ነው ዳንኤል፡፡ ካልመጣህ የባሰ ክስ ሊቀርብብህ ይችላ

፡፡ ደና ሁን፡፡

ዳንኤል:
(በሀሳብ ተውጦ) እሺ ፖሊስ፤ ድህና ሁኑ፡፡

ቪቪየን:
በቤተሰብ ወይም በግንኙነት ስም የፍቅር አጋሮቻቸውን፣ ሴት ልጆቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ወንድሞቻውን፣ ልጆቻውን እና የወንድም እና የእህቶቻቸውን ልጆች መበደል እንችላለን ብለው ለሚያስቡ ለአንተ እና ለሌሎም ወንዶች ይሄ እንደዚያ ሊሆን እንደማይችል ማሳያ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ማንም ከህግ በላይ አይደለም፡፡ እንደሥራህ ይፈረድብሃል – ከተበዳዩ ጋር ያለህ ዝምድና ነጻ አያወጣህም፡፡

ይህ እየተበደሉ ላሉ ሰዎችም ልመና ነው … እባካችሁ ዝም አትበሉ፡፡ አጥፊዎች ከናንተ ጋር ያላቸው ግንኙነት ምንም ቢሆን ሪፖርት አድርጉ፡፡ እንደዚህ ካለ ጭቆና ነጻ የምትወጡበት ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ ሁላችንም የየራሳችን ጠባቂዎች መሆን አለብን፤ ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅርም በመካከላችን እንዲዳብር ማድረግ አለብን፡፡

የድምጽ ኢፌክት: ማጠቃለያ ሙዚቃ

Acknowledgements

ምስጋና

የጽሑፉ አዘጋጅ፡- አቤና ዳኖሳ ኦፎሪ አማንክዋ፤ በኢግልስ ሮር ክሪኤቲቭስ ስክሪፕት ጸሃፊ እና ዳሬክተር፡፡

የጽሑፉ ከላሽ: ሊሊያን ብሩስ፣ ዴቨሎፕመንት ኤንድ ላንድ ሶሉሽንስ ኮንሰልትስ (ዳልስ ኮንሰልት) ኤግዜኪዩቲቭ ዳይሬክተር፤ አክራ፣ ጋና

 

ቃለ መጠይቆች:

Caroline Montpetit, Regional Program Manager, West Africa, & Gender Equality Advisor, Farm Radio International, June 2020.

Lillian Bruce, Executive Director, Development and Land Solutions Consults (DALS Consult), Accra, Ghana, June 2020

Nana Awindo, Ghanaian journalist and advocate on gender issues and domestic violence, June 2020.

Stephanie Donu, Project Officer, Solidaridad Ghana, June 2020.

Lois Aduamuah, Programme Officer, Women in Law and Development (WILDAF) in Ghana, August-September, 2020.

Joseph Howe Cole, Ghana Police Service, June and August, 2020.

Mrs. Josephine Kwao, Police Officer, Odorkor DOVVSU Division, August, 2020.

Resources:

Jeltsen, M., 2020. Home Is Not A Safe Place For Everyone. Huffington Post, March 12, 2020. https://www.huffingtonpost.ca/entry/domestic-violence-coronavirus_n_5e6a6ac1c5b6bd8156f3641b?ri18n=true

Landis, D., 2020. Gender-based violence (GBV) and COVID-19: The complexities of responding to “the shadow pandemic.” A Policy brief: May 2020. CARE. https://reliefweb.int/report/world/gender-based-violence-and-covid-19-complexities-responding-shadow-pandemic-may-2020

Laouan, F. Z., 2020. Rapid Gender Analysis – COVID-19: West Africa–April 2020. CARE. https://insights.careinternational.org.uk/media/k2/attachments/CARE-West-Africa-Rapid-Gender-Analysis-COVID-19-May-2020.pdf  

SD Direct, 2020. Why we need to talk more about the potential for COVID-19 to increase the risk of violence against women and girls. http://www.sddirect.org.uk/news/2020/03/why-we-need-to-talk-more-about-the-potential-for-covid-19-to-increase-the-risk-of-violence-against-women-and-girls/

UNFPA (United Nations Fund for Population Activities), 2020. Developing Key Messages for Communities on GBV & COVID-19: Preliminary Guidance from the GBV AoR, updated 7 April 2020. https://gbvaor.net/sites/default/files/2020-04/GBV%20AoR_key%20messages_Covid%20%26%20GBV.pdf

Wangqing, Z., 2020. Domestic Violence Cases Surge During COVID-19 Epidemic. Sixth Tone. http://www.sixthtone.com/news/1005253/domestic-violence-cases-surge-during-covid-19-epidemic

Yasmin, S., 2016. The Ebola Rape Epidemic No One’s Talking About. Foreign Policy. https://foreignpolicy.com/2016/02/02/the-ebola-rape-epidemic-west-africa-teenage-pregnancy/  

 

ይህ ጽሑፍ ከካናዳ መንግስት በግሎባል አፌይርስ ካናዳ በኩል በቀረበ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡