በኢትዮጵያ ጥራጥሬ ምርት ላይ ጥሩ የግብርና ልምዶች፡ ባቄላ ላይ ያተኮረ

Script

Save and edit this resource as a Word document

መግቢያ

 

ይህ ርዕሰ ጉዳይ ለአድማጮች ለምን ይጠቅማል?

ጥራጥሬ ማምረት ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮችና ሌሎች የሚከተሉትን ማወቅ ስላለባቸው፦

  • ለአነስተኛ አርሶ አደሮች፣ ሸማቾችና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ከምግብ ዋስትና አንጻርና ከገቢ ምንጭነት ጥራጥሬዎች ያላቸው ጥቅም።
  • የጥራጥሬዎች የተመጣጠነ ምግብ ይዘት።
  • አንደ ባቄላ ያሉ ጥራጥሬዎች ለአፈር ምርታማነት የሚያበረክቱት አስተዋዕጾ።
  • ስለ ተሻሻሉ የግብርና አሠራሮች እና ግብዓቶች ጥራት ያላቸው የዘር ዝርያዎችን እና መረጃን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል።
  • ባቄላን የሚያጠቁ በሽታዎችንና ተባዮችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል።
  • የእርሻ መሬትን አግባብ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማዘጋጀትና ባቄላ ዘር የመዝሪያ ትክክለኛው ወቅት።
  • ብክነትን በሚቀንስ መልኩ ባቄላ ምርት ለመሰብሰብ የሚመከሩ መንገዶች።
  • አለማየሁ የመስመር አዘራር ቴክኖሎጂ ጥቅሞች።
  • የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከሎች ጥቅም።
  • የሜካናይዜሽን አገልግሎቶች።

በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ጥራጥሬ ምርት ዋና ዋና ነጥቦች

  • ኢትዮጵያበዓለምላይካሉት አሥርምርጥየጥራጥሬአምራችአገራት መሃል አንዷነች፣ከቻይናቀጥሎበባቄላምርት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፣ በሽምብራ አምራችነቷ ደግሞ አምስተኛወይምስድስተኛደረጃ ላይ ትገኛለች።
  • ጥራጥሬዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ከታረሰው መሬት 13% ገደማ የሚይዙ ሲሆን ለአነስተኛ ገበሬዎች ኑሮ ገቢ ወሳኝ ናቸው።
  • ጥራጥሬዎች ለተለያዩ ምክንያቶች ይመረታሉ፦
    • ለቤት ውስጥ ፍጆታነት እንዲውሉ
    • ለቤተሰብ ገቢ እንዲያስገኙ
    • የአፈርን ጤንነት ለማሻሻል
  • ጥራጥሬዎች ወጪ ቆጣቢ የፕሮቲን ምንጮች ናቸው።
  • ጥራጥሬዎች የአየር ንብረት ለውጥን በቀላሉ መላመድ የሚችሉ ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመጣውን ውጤት ለመቋቋም ይረዳሉ።
  • በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ አስር የሚጠጉ የጥራጥሬ አይነቶች በዋነኝነት ይበቅላሉ። ባቄላ ከምርት ብዛትና ከሚዘራበት ቦታ ይዞታ አኳያ አንደኛ ሲሆን ቀጥሎ በስፋት የሚመረቱት አተር፣ ሽምብራ፣ እና ምስር ይገኙበታል።
  • ጥራጥሬዎች ከፍተኛ ከአካባቢና ከአመጋገብ አኳያ ከፍተኛ ጥቅም ቢኖራቸውም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደ ዋነኛ ሳይሆን እንደ ሁለተኛ ደረጃ ሰብል ነው የሚታዩት። በዚህም ለጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ገብስ፣ ማሽላና የመሳሰሉት እህሎች የሚሰጠው የኢንቬስትመንትና ፖሊሲ ትኩረት ለጥራጥሬዎች አይሰጣቸውም። ይህ የኢንቨስትመንት እና የፖሊሲ ትኩረት ማጣት ለጥራጥሬዎች የመሬት ምደባ በሚደረግበት ወቅት አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

በኢትዮጵያ ስለ ባቄላ ቁልፍ መረጃዎች

  • ባቄላ በኢትዮጵያ ካሉ ጥራጥሬዎች መሃል ዋነኛው ነው። በሃገሪቱ በአጠቃላይ የጥራጥሬ ምርት 14% ሲሆን ከዛ ውስጥ የባቄላ ምርት 1.5% ይይዛል።
  • ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባቄላ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል። ከፍተኛ ምርታማነቱ በአምራቾች እንዲመረጥ ሲያደርገው፣ ሸማቾች ደግሞ ለከፍተኛ ፕሮቲን ይዘቱና ተመጣጣኝ ዋጋው ሲሉ ይመርጡታል።
  • ባቄላበኢትዮጵያበአብዛኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ለምግብነት ከሚውሉ ሰብሎች ውስጥ ዋነኛው ስለሆነ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው። ባቄላን በፉል፣ ንፍሮ፣ አሹቅና ሽሮ ወጥ መልክ በባህላዊ መልክ መመገብ የተለመደ ነው።
  • የተለያዩ ተግዳሮቶች የባቄላ ምርትና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ ያደርጋሉ፣ ከነዚህም መሃል አሁን ጎልቶ እየታየ ያለው የባቄላ በሽታ ይገኝበታል።
  • በኢትዮጵያ የባቄላ ምርት ሙሉ ለሙሉ በዝናብ ላይ የተመረኮዘ ነው።
  • በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች ባቄላ ለአርሶ አደሮች ዋነኛው የገቢ ምንጫቸው ነው።
  • ባቄላበአፈርውስጥ የሚገኝናይትሮጅንን የማስተካከልና የአፈርን ለምነት የማሻሻል አቅም ስላለው ለአርሶአደሮችየሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።
  • በኢትዮጵያ ባቄላ የሚያመርቱ አነስተኛ አርሶ አደሮች በአጠቃላይ ባህላዊ የአስተራረስ ልምድን የሚጠቀሙ ናቸው። ባቄላ በአርሶ አደር ቤተሰቦች ዘንድም የሚዘወተር ምግብ ስለሆነ ከምርቱ ላይ ለገበያ የሚቀርበው አምራቾቹ ቤተሰቦች በአመት ለምግብነት ተጠቅመው ከሚተረፋቸው ላይ ነው።

በኢትዮጵያ የጥራጥሬ ምርትን አስመልክቶ የሚታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች

  • አርሶ አደሮች በቂ የምርጥ ዘር እና እንደ ማዳበሪያ፣ ፀረ-ተባይና ሌሎች ዕጽዋትን ለማከም የሚጠቅሙ ግብዓቶች እጥረት አለባቸው።
  • ከፍተኛ ምርት የሚያስገኙ እና በሽታዎችን የመቋቋም አቅም ያላቸው የዘር ዓይነቶች በቂ ሁኔታ ተደራሽ አለመሆናቸው።
  • ለጥራጥሬ ምርት እና ተያያዥ አገልግሎቶች በቂ ትኩረት አለመስጠት።
  • ምርት ከተሰበሰበ በኋላ ለሚደርስ ብክነት አርሶ አደሮች ተገቢውን ትኩረት አለመስጠታቸው።
  • ረጅሙየገበያአሰራር ሂደትገበሬዎችበሚያገኙትዋጋላይተጽዕኖያሳድራል።በአርሶአደሮችእናበመጨረሻውየምርቱመድረሻመካከልበተለይምለውጭ ገበያ ለሚቀርቡሰብሎችበርካታመካከል ላይ የሚገኙ አስፈጻሚዎችይገኛሉ።
  • የመስኖ እጥረት።

የአየር ንብረት ለውጥ በባቄላ ምርት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

  • የአየርንብረትለውጥበባቄላእርሻላይየሚያሳድረውዋነኛተፅዕኖከሌላው ጊዜ ያጠረ የእድገትወቅትእናየድርቅመጠን መጨመርነው።
  • ከሌላው ጊዜ ያጠረ የእድገትወቅት የሰብልአበቃቀል ላይ ተጽኖ አድርጎ ሙሉ ለሙሉ ሊያከሽፈው ይችላል።
  • አርሶ አደሮች ትክክለኛ የአየር ሁኔታ ትንበያዎች የማግኘት እድላቸው አነስተኛ ስለሆነ መትከል ያለባቸውን ቀን በትክክሉ መወሰን ይከብዳቸዋል።
  • ድርቅአበቃቀልን፣ማበብንእናምርታማነትንበመቀነስየባቄላእድገትንያደናቅፋል።
  • ድርቅ የዕፅዋትን ቁመት እና ክብደት፣ እርጥብና ደረቅ እምቡጥ ክብደትን፣ የቅጠሉን ስፋት እና በእጽዋቱ ውስጥ ያለውን የክሎሮፊል* መጠን የመቀነስ አዝማሚያ አለው።
  • ከመጠን በላይ የሆነ ሞቃት የአየር ሁኔታ ድርቅን እና ጥነትን ያስከትላልይህምመሬት ውስጥ ያለውን የውሃመጠን እጥረትንያስከትላል።ደረቅመሬት ደግሞ ለማረስ እስቸጋሪ መሬቱን ለእርሻ ለማዘጋጀት ብቻ ከፍተኛ የጉልበትና የዋጋ መስዋዕትነት ይጠይቃል።
  • በድርቅ ምክንያት ባቄላ ሰብል ልይ ቸኮሌትስፖት በሽታ፣አፊድ-ቬክተርድበሽታና የባቄላዝገትበሽታ በወረርሽኝ መልክ በተደጋጋሚ ሊከሰት ይችላል።

በኢትዮጵያ የጥራጥሬ ምርትና የስርዓተ ጾታ

  • የሜካናይዜሽን መስፋፋት ሴቶች በጥራጥሬ ምርት ውስጥ የበለጠ የተሳትፎዋቸው አስፈላጊነት እንዲጎላ ያደርጋል።
  • የሴቶች ተሳትፎ በምርት ሥራው ጉልህ ነው፣ በእርሻም ሆነ በመከር ወቅት አብዛኛው የእርሻ ሥራን ያከናውናሉ።
  • ለበርካታ አመታት የመሬት ይዞታ እና ውሳኔን ማስተላለፍ በሚመለከት ወንዶች በሰፊው ወንዶች ተቆጣጥረውት ኖረዋል። ሆኖም ግን ባሁኑ ወቅት በህጉ መሰረት ሴቶች ከወንዶች እኩል የመሬት ድርሻ አላቸው።
  • ጥራጥሬምርትናግብይትጋር በተያያዘ ከጥራጥሬጋርየተዛመዱቴክኖሎጂዎችንማስተዋወቅ፣ማሳየትእናመውሰድበዋነኝነት በወንዶችየበላይነትየተያዘነው።
  • ወንዶች እውቀትና ችሎታቸውን የሚያዳብሩበት ስልጠናዎች መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እና በመንግስት፣ በመንግስት ወስጥና በግል ባሉ ባለሙያዎች በሚሰጡ ማብራሪያዎች፣ በጉብኝቶች እና ይፋዊ ካልሆኑ ምንጮች በሚያገኙት መረጃ ነው። በተቃራኒው ሴቶች እውቀትና ችሎታቸውን ለማዳበር በዋነኝነት የሚመረኮዙት ይፋዊ ባልሆኑ ምንጮች በኩል በሚያገኟቸው መረጃዎች ላይ ነው። በዚህም ምክንያት የትኞቹን የዘር አይነቶችና የቶቹን ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዳለባቸው በበላይነት የወስናሉ።
  • ባቄላን በማምረት ረገድ ሴቶችና ወንዶች እኡል የስራ ጫና አላቸው። ወንዶች በዋነኝነት የሚወስዱት የስራ ድርሻዎች ለእርሻ መሬት ማዘጋጀት፣ ለዘር መረጣ፣ መዝራት እና መሰብሰብ ናቸው። ሴቶችም ዘር መዝራት ላይ በሳተፉም ዘር ምርጫ ላይ ግን ዕውቀቱ እና ክህሎቱ ይጎድላቸዋል። ሴቶች ወንዶችን በመሬት ዝግጅትና እርሻ ላይ ሲያግዟቸው አረም በማረምደግሞ በዋነኝነት ሰፊውን የስራ ድርሻ ይይዛሉ።
  • በዋነኝነት ሴቶችየመውቃት፣የማጨድእናየማከማቸትኃላፊነትአለባቸው።
  • በወንዶችእናበሴቶችየሚሸጡትየባቄላመጠንእንደየቤተሰቡ ይለያያል።ሴቶችበየወቅቱአነስተኛ መጠን የሆነ እስከ20 ኪሎ
  • ራምሊሸጡሲሸጡ ይህንንም ሽያጭ የሚያከናውኑት በቤትውስጥጥሬገንዘብሲያስፈልግ ሲሆንወንዶችደግሞ ከ100-600 ኪሎ
  • ራምሸጠውየተገኘውንገቢ ሙሉ ለሙሉይቆጣጠራሉ።
  • ለቤት ውስጥ ፍጆታ በሚተርፍ ባቄላ ላይ ሴቶች በዋነኝነት ያስተዳድራሉ።
  • በአብዛኛው የባቄላ ምርት ደረጃዎች ላይ ያለውን የስራ ጫና ወንዶችና ሴቶች እኩል የሚጋሩ ቢሆንም ገብያ ላይ ከወጣው የባቄላ ምርት ላይ የሚገኘው ጥቅም ላይ ሴቶች ያላቸው መብት ውስን ነው።

ስለ ባቄላ ምርት ቁልፍ መረጃዎች

ለባቄላ የሚሆን ምቹ መሬት መረጣ

  • ለባቄእርሻየሚመከረውዓመታዊየዝናብመጠን በዓመት700-1000 ሚ.ሜድረስ ነው።ሰብሉ በማደግላይበሚሆንበትወቅትዝናብበተከታታይመሰራጨትአለበት።
  • ፋባባቄላከባህርጠለልበላይከ1800 እስከ3000 ሜትርከፍታላይበስፋትይመረታል።ከ1800 ሜትርበታችከፍታላይሰብልበድርቅናበበሽታሊጠቃይችላል።ከ3000 ሜትርበላይከሆነ ደግሞበከፍተኛ ቅዝቃዜ ምክንያትሰብሉ ላይ ጉዳትሊደርስበትና የምርትማሽቆልቆል ሊደርስይችላል።
  • ባቄላ ሲተከል ሙቀት ባለው አፈር ውስጥ መሆንአለበት።
  • ባቄላ በጣም አሲዳማ ወይም ጨዋማ ካልሆነ በስተቀር በአብዛኛው የአፈር ዓይነቶች ላይ ሊበቅል ይችላል። በደንብ የተዋቀረ የሸክላ አፈር እንዲሁም አሸዋማ የሸክላ አፈር ወይም ከ15-35% ድረስ የሸክላ ይዘት ያለው አፈር ተስማሚ ነው።
  • ከአበቃቀልእንስቶ እስከ ማበብ ድረስ ያለውየአፈርሙቀትበአማካይከ20-25 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መሆንአለበት።
  • ለስንዴእናገብስምርትተስማሚየሆነ የአየርንብረትእናአፈርለባቄላምርትምተስማሚሊሆንይችላል።

መሬት አዘገጃጀት

  • በተፈጥሮ የባቄላ ስሮችየተጠቀጠቀ እና ጥልቅ አፈርን መግባት አይችሉም።
  • በአካባቢው በተለመደው ማረሻ ከ1-2 ጊዜ ይረሱ ወይም አንድ ጊዜ በዲስክ ማረሻ ካረሱ በኋላ ሁለቴ ደግሞ አፈሩን በዲስክ ያለስልሱ።
  • የመሬትዝግጅትንቀደምብሎመጀመርየአረሞችእንዲበቅሉያበረታታልስለዚህበቀጣይእርሻ ወቅትአረሞቹን ማጥፋት ይቻላል።
  • ቀደም ብሎ የነበረው ሰብል ሙሉ ለሙሉ ከተሰበሰበና መሬቱ ከተጸዳ በኋላ በተቻለ መጠን በፍጥነት መታረስ አለበት። ባቄላ ከመትካሎ በፊት መበስበስ እንዲችሉ የተራረፉ ሰብሎችን ማካተቱ ይመከራል።
  • አፈር የለሰለሰና ደቃቅ ቢሆን ይመረጣል። ውሃ የታቆረ እንደሆነ አርሶ አደሮች ውሃው አንድ ቦታ ተቋጥሮ እንዳይቀር የፍሳሽ ማስተላለፊያ ዘዴ መጠቀም አለባቸው።
  • ድርቅ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ሸንተረሮች* የአፈርን እርጥበት በመቆጠብ የውሃ ትነትን ይቀንሳሉ።
  • በአፈር ውስጥ የውሃማጣራትንእናየአፈር ውስጥ ያለንአየርዝውውር ለማሻሻልእንዲሁምየአፈርንእርጥበትማጣትለመቀነስተገቢ የሆነየመሬትዝግጅትወሳኝነው። መሬትን በትክክሉ ማዘጋጀት አበቃቀል፣ የሥር እድገት፣ የአረም ቁጥጥርን እና በአፈር ወለድ በሽታዎች እና ተባዮች የመጠቃት እድልን ሊቀንስ ይችላል።

አርሶ አደሮች የሜካናይዜሽን አገልግሎቶችን የሚያገኙበት መንገድ

  • በኢትዮጵያየግብርናሜካናይዜሽንን መጠቀም ዝቅተኛደረጃ ላይ ነው።
  • በዋነኝነት አቀላቅለው እህል የሚሰበስቡ አርሶ አደሮች ከኢኮኖሚ ቁጠባ አንጻር እና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ሜካናይዜሽንበጣምተስማሚበሆኑየስንዴአብቃይአካባቢዎችውስጥእየተለመደ ነው።
  • አብዛኞቹ የንግድ እርሻዎች በደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ይህም የማሽን ኪራይ ገበያ እንዲሻሻል አበረታቷል።
  • ቀላቅለው ሰብል ለሚሰበስቡ በተለይየንግድአገልግሎትአቅራቢዎችይፋ እየሆኑ ይገኛሉ።
  • በአብዛኛው ትራክተሮችን የሚጠቀሙት ትላልቅ የንግድ አርሶ አደሮችና የመንግስት እርሻዎች ቢሆኑም፣ አሁን አሁን አርሶ አደሮች በተለይ የስንዴ አርሶ አደሮች ሜካናይዜሽን በጥቅም ላይ በሰፊው እያዋሉ ይገኛሉ።
  • ማረስ፣ማረምእናመሰብሰብአገልግሎቶችን እያስከፈሉ የሚያቀርቡ ነጋዴዎች በሰፊው እየታዩ ይገኛሉ።
  • ከአነስተኛ አስተራረስና አርሶ አደሮች የተበታተኑ የእርሻ መሬቶችን ጥቅም ላይ ከማዋላቸው ጋር በተያያዘ ሜካናይዜሽን ላይ ማነቆዎች አሉ። የኢትዮጵያ ረግረጋማ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ እና በመስኮች ውስጥ ድንጋዮች በብዛት መገኘታቸው ሜካናይዜሽን ተጠቅሞ ማረስን ያወሳስበዋል።

መዝራት

  • በትክክለኛው ወቅት ላይ ዘር መዝራት ወሳኝ ነው። አፈሩ እርጥብ በሆነበት ወቅት መዝራት አስፈላጊ ነው። ከወቅቱ ቀድሞ መዝራት ባቄላው በዝናብ እንዲጎዳ ያደርጋል። ዘሮቹ ከደረሱ በኋላ ዝናብ የሚቀጥል ከሆነ በቡቃያዎቹ ውስጥ መብቀል ሊገምሩ ይችላሉ። ከወቅቱ ዘግይቶ መዝራት የዝናብ እጥረት ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ዘር ለመዝራት ተስማሚው ወቅት የሰኔ መጨረሻ ወይም የሃምሌ መጀመሪያ ነው።
  • አፈሩ በበቂ ሁኔታ ያልረጠበ እንደሆነ ዘር ላይበቅል እና ምርት ለቀንስ ይችላል።
  • አፈርወለድበሽታዎችንእናተባዮችንለመቆጣጠርተገቢበሆነፀረ-ፈንገስእናፀረ-ተባይመድሃኒትዘር ከመዝራትዎ በፊት ያክሙ።የሰብልማሽከርከርእናሰብሉንማግለልእንደአማራጭየባዮሎጂቁጥጥርአማራጭአማራጭነው።ለተወሰኑበሽታዎችመቋቋምየሚችሉዝርያዎችንመትከልአስፈላጊነው። የሰብል አይነቶችን አያቀያየሩ መዝራትና ሰብሎችን መለየት አማራጭ የባዮሎጂ ቁጥጥር ናቸው። የተወሰኑ በሽታዎችን የመቋቋም አቅም ያላቸውን ዝርያዎች መትከል አስፈላጊ ነው።
  • የመትከያ ጉድጓድ ጥልቀት ወሳኝ ነው። የዘሩ ትልቀት መጠን፣ የአፈሩ አይነት እና የ አየር ንብረቱ ሁኔታን ከግምት በማስገባት ዘሮች ከ2-6 ሳ.ሜ ጥልቀት ባለው ጉድጓድ ውስጥ ሊተከሉ ይገባል።
  • በሞቃታማ፣ደረቅየአየር ሁኔታዎችወይምዝናብመዝነብ አለመዝነቡን እርግጠኛ በማይሆንበት ወቅት ዘሮቹን ከጸሃይ ለመከላከልና ካፊያ ባለበት ወቅት ዘሩ ያለወቅቱ እንዳይበቅልጥልቀትባለው ጉድጓድ መዝራት ይኖርበታል። ጥሩ የዝናብ መጠን በሚዘንብበትና ከበድ ያለ አፈር ወስጥ ግን ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መዝራት የሰብሉን የመብቀል አቕም ያመናምነዋል።
  • የባቄላዘሮችንበረድፍ ውስጥ ከ4-10 ሳ.ሜርቀት በመካከላቸው ኖሮ ረድፎቹ ደግሞ በመካከላቸው 40 ሳ.ሜ ርቀት ሊኖር ይገባል።
  • እንደ ዘሩ አይነትና መጠን፣በአንድ ሄክታር መሬት ላይ የሚዘራው የትናንሽ ዘር መጠን ከ150-170 ኪሎ ግራም ሲሆን ለትላልቅ ዘሮች ደግሞ ከ200-250 ኪሎ ግራም ድረስ ይደርሳል።

ምርጥ ዘር ማግኛ መንገዶች

  • ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጥ ዘር የሚሰራጨው በመንግስት፣ የግል፣ ዘር ተኮር የህብረት ስራ ማህበራትና ዘር አምራች የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው።
  • በኢትዮጵያውስጥየመንግሥትናየግልየዘርኩባንያዎችለምግብነት የሚውሉ የሰብልዘሮችንከ10% በላይ አያቀርቡም።
  • የቀጥታየዘርገበያ- ይህየሚያመለክተውአርሶአደሮችበወረዳውግብርናጽ/ ቤትበኩልየተረጋገጠዘርለመቀበል የሰብል መትከያወቅቱከመጀመሩበፊትበልማትወኪል(ኤክስቴንሽንወኪል) እንዲመዘገቡየሚጠበቅበትንየዘርመዳረሻሥርዓትነው።
  • ምርጥ ዘር ያላቸው አርሶ አደሮች ለሌሎች አርሶ አደሮች ለሸጡ ይችላሉ።
  • ለሰብል ምርት እንደ እንቅፋት ሆነው ከሚጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ የዋጋ ማሻቀብ እና የምርጥ ዘር በተገቢው ወቅት አለመቅረብ ይገኙበታል።

በረድፍ ወይም በመስመር መዝራት

  • መረድፎች መሃል ያለውን የሚመከረውን ርቀት መጠበቁ በአፈር ውስጥ ያለውን አየር፣ እርጥበት፣ ጸሃይ እና ንጥረ ነገር በማስቀመጥ ምርታማነትን ያረጋግጣል።
  • በብታና ዘር ማሰራጨት ከረድፍ ተከላ ጋር ሲወዳደር ብታና ስርጭቱ በርከት ያለ ዘርን ይጠይቃል አንዲሁም ምርታማነትን ይቀንሳል።
  • የብተና ዘር ስርጭት ላይ በእጅ አረም ማረምና ኩትኮታ ከባድ ይሆናል ባዛ ላይ ደግሞ በአረሞች ምክንያት ሰብሎች እድገታቸው ላይ ተጽኖ የፈጠራል።
  • በኢትዮጵያበከብትየሚሳቡወይምበትራክተርየተጫኑዘሮችን በረድፍ የመትካሉ ስራ እምብዛም አልተለመደም።
  • የረድፍ ተከላን ለማስተዋወቅ ጥረት ቢደረግም በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ በዋነኝነት ግን የመንግስት የዘር ድርጅቶች እየተገበሩት ይገኛሉ፦
  • በትራክተር ላይ የረድፍ ዘሮችን ለመዝራት በተከታታይ መሳሪያውን ለማስተካከልና ለማሰናዳት ቢያንስ የቴክኒክ ክህሎትና ልምድ ይጠይቃል።
  • ትራክተር ላይ ከተገጠሙ የረድፍ መዝሪያዎች ጋር ሲነጻጸር በእጅ የረድፍ መዝሪያዎቹ በቁጥር አነስተኛ ናቸው አገልግሎት ላይም የሚውሉት ዝቅተኛ ቁጥር አላቸው።
  • በእጅ በረድፍ መዝራት ከፍተኛ ጉልበት የሚጠይቅ እንዲሁም የቤተሰብ እርዳታ ወይም የጉልበት ሰራተኛ አለመኖር ተግዳሮት ስለሚሆን አስቸጋሪ ይሆናል።

አለማየሁበረድፍመዝራትቴክኖሎጂ

  • አለማየሁየረድፍአዘራርቴክኖሎጂአለማየሁወንደፍራሽበተባለ ሰው የተዘጋጀ የፈጠራ ስራ ሲሆን በጥንድበሬዎች በሚሳብ የእርሻ መሳሪያ በረድፍ ዘር የሚዘራ ነው።
  • አለማየሁየረድፍአዘራርቴክኖሎጂ ሶስት ክፍሎች አሉት፦ መስመር (ረድፍ) መቆፈሪያ (ማውጫ)፣ የውሃ ልክ ማውጫ ጣውላ እና ማረሻ።
  • ሦስቱም ክፍሎች የሚሠሩት በአካባቢው በቀላሉ ከሚገኙ ቁሳቁሶችና መሣሪያዎች ነው።
  • ረድፍመቆፈሪያው ዘርከማሰራጨቱበፊትቀዳዳዎችንለመሥራትያገለግላል።
  • ዘሩ ከተሰራጨ በኋላ አርሶ አደሮቹ ውሃልክ ማውጫ ጣውላውን በመጠቀም ዘር ያለው እና የሌለው ክፍሎችን አመጣጥነው የረድፍ አዘራርን ያከናውናሉ።
  • በመጀአሪያዎቹ የእርሻ ወቅቶች ላይአርሶ አደሮች ማር4አሻውን በመጠቀምረድፎች መሃል ያሉትን አረሞች ለመንቀልይጠቀማሉ።
  • አለማየሁ የረድፍ አዘራር ቴክኖሎጂ ዘርን እና ጉልበትን ይቆጥባል ምርትንም ይጨምራል።
  • አለማየሁየረድፍአዘራርቴክኖሎጂበእጅ ማረምን እና መንቀልን ያቀላል።

አረም ማረም እና መድሃኒት ርጭት

  • ባቄላን በተለይ በመጀመሪያዎቹ የእድገት ወቅት አረሞች በቀላሉ ያዳክሙታል። ሰፊ ቅጠል ያላቸው አረሞች በቀላሉ ባቂላ ላይ ተጽኖ ስለሚኖራቸው በተለይ ከጸደቀ ከ3-6 ሳምንታት ባሉት ጊዜያቶች ውስጥ በተከታታይ አረም መታረም አለበት። ከ3-4 ቅጠሎች ካበቀለበት ጊዜ አንስቶ እስከማበብ ደረጃ ድረስ እስኪደርስ ሰብሉ ከጸደቀ በኋላ የሣር አረም ዝርያዎችን ለመቆጣጠር የአረም ማጥፊያ መድኃኒቶችን መርጨት ይመከራል።
  • ባቄላ ሰብል ማሳ ላይ አረምን ዘግይቶ ማረም ባቂላው ላይ ጉዳት ስለሚያደርስ ምርታማነትንም ይቀንሳል።
  • ባቄላን በረድፍ መዝራቱ የአረም ማረም ስራን ያቃልላል።
  • በመጀመሪያዎቹ የእድገት ቀናቶች (መብቀል ከጀመረ 15 ቀናቶች በኋላ) አረም ማረም ተክሉ መብቀል ከጀመረ ከ10-15 ቀናት እና ከ30-35 ቀናት ሁላቴ ከማረም ጋር ሲወዳደር ውጤታማ ምርታማነትን አስመዝግቧል።
  • ማበብ እንደጀመረ ወዲያው ማረሙ ያበባን መጨናገፍ፣ የበሽታ መስፋፋትና የተክል ጉዳትን ስለሚያስከትል አይመከርም።
  • ባቄላከመድረሱበፊትዘግይተውብቅየሚሉአረሞችንያስወግዱ።የሳርቤተሰብውስጥያሉአረሞችንለዚሁዓላማበተዘጋጁየአረምማጥፊያዎችመቆጣጠርይቻላል።
  • አረም ማረም የሚከተሉትን ያካትታል፦
    • የማሽን ማረሻ በመጠቀም በእጽዋት የመጀመሪያ የእድገት ደረጃ ወቅት በየረድፎቹ ሁላቴ ማረስ፣
    • አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በኋለኛው የዕጽዋቱ የእድገት ወቅት ላይ በእጅ ማረም፣ እና
    • መድሃኒት ርጭት ማከናወን።

ማዳበሪያ አጠቃቀም

  • በዋነኝነት ምርታማነትን ከሚቀንሱ ምክንያቶች ውስጥ የኬሚካል ማዳበሪያዎችን በሰፊው አለመጠቀም፣ ባማካኝ በአንድ ሄክታር መሬት 25 ኪሎ ግራም በተለይ እህል ዘር ላይ ማዋሉ የገኝበታል።
  • በኢትዮጵያ ያሉ አርሶ አደሮች በተለምዶ ሁላት አይነት ማዳበሪያዎችን ይጠቀማሉ፦ ተፈጥሮአዊ ማዳበሪያዎች (ለምሳሌ ዩሪያ እና ዳይ አሞኒየም ፎስፌቶች) እንዲሁም የፍግ እና ቅራሞክል ማዳበሪያዎች።
  • በጥራጥሬ ላይ የኬሚካል ማዳበሪያዎች የመጠቀም ልምድ ውስን የሆነው ከግንዛቤ እጥረትና የብድር ተደራሽነት ውስን መሆን እንዲሁም ከውጭ የሚገባው የፎስፌት ማዳበሪያ እጥረት ነው።
  • ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ማዳበሪያዎች ከውጭ ሃገር በውድ ዋጋ የሚገቡ ስለሆነ በቀላሉ አይገኙም።
  • ማዳበሪያዎች ለአርሶ አደሮች የሚዳረሱት በህብረት ስራ ማህበራት እና በአርሶአደሮች አንድነት ማህበራት በኩል ነው።
  • እንደ አፈሩ ለምነት በአንድ ሄክታር 100 ግራም ዲ ኤ ፒ (DAP) እና በአንድ ሄክታር ከ50-100 ግራም ዩሪያ ማዳበሪያን መጠቀም ይመከራል። ቀላል በሆኑ የአፈር አይነቶች ላይ ደግሞ 100 ግራም ኤን ፒ ኤስ (NPS) በሄክታር ለባቄላ ምርት ይመከራል።
  • የባቄላአርሶ አደሮችዘሮችንበሬዝዞቢየምኢንኮላንትእንደባዮማዳበሪያዘሮችን እንዲያለብሱይመከራል።ይህበስሮች አማካኝነት የከባቢአየርናይትሮጅንእንዲስተካከልያደርጋል፣በዚህም ምክንያትየአፈርለምነትንእናምርትይጨምራል።

ለአፈር ጥራት ጥራጥሬዎች የሚያበረክቱት ጥቅሞች

ጥራጥሬዎችን ማብቀል የሚከተሉት ውጤቶች ይኖሩታል፦

  • የአፈር ለምነትን መጨመር።
  • የአፈር አስራጊነት* መሻሻል።
  • ከፍታኛ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋልና በተሻለ ሁኔታ አፈር ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መገኘት።
  • የተሻለ ቅጣፈር።
  • አነስተኛ የአፈር ፒ ኤች መጠን።
  • የአፈርን ንጥረ ነገር መልሶ የመጠቀምና በበቂ ሁኔታ እንዲኖር የሚያደርጉ እንዲሁም በሽታን መቆጣጠር የሚያስችሉ በርከት ያሉ የተህዋሲያን አይነቶች መኖር።
  • የእህልሰብሎችንናወደጥራጥሬዎችን እያፈራረቁ በመዝራትየበሽታእናየአረምችግሮችይቀንሳሉ፣ምክንያቱምሰብሎችን ማፈራረቅየበሽታተህዋሲያንእናየአረምመብዛትን ይቀንሳል።

ሰብል መሰብሰብ (መከር)

  • ሰብሉለደረቅዘርነት የተፈለገ እንደሆነሙሉበሙሉሲደርስ ለሰበሰብ ይገባል።እንደአትክልትምግብነት እንዲውል ከተፈለገ ቀለሙአረንጓዴበሚሆንበትጊዜይሰብሰብ።
  • በኢትዮጵያበብዛትየተለመደውየመከርዘዴሰብሉንበእጅነቅሎ መውቃትነው።
  • ባጠቃላይ እንደ ባቄላ አይነቱና የአየር ንብረቱ ሁኔታ ባቄላ በተዘራ ከ90-220 ቀናቶች ውስጥ ይደርሳል።
  • እንደደረቅባቄላጥቅምላይየሚውልከሆነ፣የታችኛውቡቃያእስኪበስልእናየላይኛውሙሉበሙሉእስኪያድግድረስሰብሉመቆረጥየለበትም።
  • የላይኛውቡቃያእስኪበስልድረስእህሉ ሳይሰበሰብ ከቆየ ቡቃያው ተፈረካክሶ ለከፍተኛኪሳራይዳርጋል።
  • ሰብሉን በሚቆርጡበት ወቅት ደመናማ ቀናት ላይ ወይም አመሻሽ ላይ ያከናውኑ።
  • አርሶአደሮችዘግይተውየሚሰበሰቡከሆነ፣በዝናብ ብክንያት ቡቃያዎቹ ተከፋፍለው የፈንገስበሽታንሊከሰትይችላል።
  • ባቄላመከርንእና መውቃትን በአንድ ላይ አቀናጅቶ ለመስራት አያመችም። ነገርግንበእጅመሰብሰብበቂ የጉልበት ሃይል ባለበት ወቅት በተለይ ገንዘብ ቆጣቢ ነው።

አውድማእናማከማቻ

  • አግባብባልሆነመንገድየተወቁዘሮችሲታዩ ምንም ያልሆኑ እና ጤነኛ ሊመስሉ ቢችሉምባማደግ ላይ ያሉ ችግኞች እድገታቸው ተደናቅፎ አንዲጫጩ ወይም እንዲሞቱ የሚያደርጓቸውትናንሽስንጥቆችወይምውስጣዊጉዳቶችሊኖራቸውይችላል።
  • በአግባቡየተፈወሰዘርከጥቃቅን ስንጥቆች ሊታደገው የሚችል በቂ እርጥበት በውስጡ ቢይዝምበፅንሱላይየውስጥጉዳትንለመከላከልየሚያስችል በቂየእርጥበትመጠን ግን የለውም።
  • የአወቃቅ ዘዴው ከሚወቃው ዘር ብዛት እና ከሚገኙት መሣሪያዎች ጋር ይዛመዳል። ለዚህም ነው አነስተኛ መጠን ያለው ዘር በሚወቃበት ወቅት በእጅ መውቃቱ ተስማሚ ዘዴ ነው።
  • ቡቃያዎቹ ሁለት ቦታበእጅሊከፈሉወይምበፕላስቲክገንዳሊቀመጡእናበእጅ መታሸት ይችላሉ፣በዚህጊዜጓንትማድረጉይመከራል።
  • ዘሮቹእርጥበትእንዳይይዙና ከተባይነፃ እንዲሆኑ በደረቅ ቀዝቃዛስፍራ ከወለል ቢያንስ30 ሴ.ሜከፍ ብለውመቀመጥአለባቸው።
  • ዘሮችንለክምችት ምቹ እንዲሆኑበተገቢውኬሚካልመታከምአለባቸው።ዘሮችን ለዚያዓላማባልተመደቡፀረተባይመድኃኒቶችማከምበአበቃቀላቸው ላይ ደካማእንዲሆኑ ያደርጋል።

ሰብል መቀያየር

  • የእህልና የጥራጥሬ ሰብሎችን እየቀያየሩ ማምረት የአፈርን ለምነት ይጨምራል እንዲሁም የተለያዩ በሽታዎችን፣ አረሞችንና ተባዮችን ይከላከላል።

በኢትዮጵያበአብዛኛው የሚታዩየባቄላበሽታዎች

  • የባቄላየባቄላ ቆርምድ በሽታከ30-100%ኪሳራሊያስከትልይችላል።የዘርማልበስእናቅጠላፈንገስመድኃኒቶችበባቄላሐሞትላይየተወሰነውጤትአላቸው። እንደ የቅጠል ፈንገስ መድሃኒት ያሉ በሽታውን በመጠኑም ቢሆን የመከላከል አቅም አላቸው።
  • የባቄላ ዝገት በሽታ እስከ 30% የሚደርስ ብክነት ያስከትላል።የባቄላ ገለባ በማቃጠል ወይም በመቅበር እንዲሁም ሰብሎችን እያቀያየሩ በመዝራት የባቄላ ዝገት በሽታ የመከሰት እድሉን መቀነስ ይቻላል። የባቄላ ዝገት በሽታ በሰፊው በሚታይበት ስፍራ የመድሃኒት ርጭት በማድረግ በሽታውን መቆጣጠር ይቻላል።
  • ቸኮሌት ነጠብጣብ የተባለው በሽታ ባቄላን በሰፊው የሚያጠቃ ሲሆን እስከ 60% የሚሆነውን የሰብሉን ክፍል ያጠፋል።
  • ቸኮሌት ነጠብጣብ በሽታን ለመቆጣጠር የበሽታ ቁጥጥር መርሆች ተግባራዊ ሊሆኑና የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይጋባል፦
    • ሰብሎችን እያቀያየሩ መዝራት እና ከአምናው የባቄላ ሰብል ትርፍራፊ ቢያንስ በ500 ሜትር ሊርቅ ይገባል፣
    • በሽታ የመቋቋም አቅም ያላቸውን አይነቶች ማብቀል፣
    • ንጹህ ዘርና የፈንገስ መድሃኒት መጠቀም፣
    • ይስመዝሪያ ጊዜውን በመለዋወጥ የሰብል ከለላውን ማመቻቸት፣
    • ባለሙያዎች የሚመክሩትን የዘር መጠንና በረድፎች መሃል ለደረግ የሚገባውን ባዶ ስፍራ ስፋት መጠቀም፣
    • መደበኛ የሰብል ክትትል፣
    • በእርሻው ላይና ከእርሻው ውጪ ከፍታኛ ንጽህናን መተግበር እና፣
    • ፎሌር የፈንገስ መድሃኢትን በስልታኢ መንገድ መጠቀም።
  • የቸኮሌትነጠብጣብ ወይም ቸኮሌት ስፖት በሽታንየመቋቋምእድሉከፍተኛበሆነባቸውአካባቢዎችውስጥበሽታውን መቋቋምየሚችሉዝርያዎችለተከሉ ይገባል።ዘር ከመዝራትዎበፊትሁሉንምየባቄላተረፈ ምርትእናእራስ በቀልእፅዋቶችንሙልኩ ለሙሉ በማጥፋት፣እና በባለሙያዎች ምክር መሰረትከበሽታነፃየሆነዘርበመዝራትእንዲሁምየሰብሎችን እያፈራረቁ በመዝራትሰብሎች ለበሽታውተጋላጭነትያላቸውን እደጋ መቀነስ ይቻላል።
  • አየር ወለድ የፈንገስ በሽታዎች በምርት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እንደየወቅቱ እና እንደየክልሉ ይለያያል። አንዳንድ በሽታዎች በሃገሪቱ ውስጥ ትልቅ ፋባ በሚያመርቱ አካባቢዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ እናም በጥራት እና በብዛት ከፍተኛ ኪሳራ ያስከትላሉ። አንዳንድ በሽታዎች በሀገሪቱ በስፋት ባቄላ በሚያመርቱ አካባቢዎች ላይ ተጽዕኖ በማሳደር በጥራትና በብዛት ከፍተኛ ኪሳራ ያስከትላሉ።

የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከል

  • የአርሶአደሮችማሰልጠኛማዕከላት ከስር የተዘረዘሩትን ጨምሮ መጠነ ሰፊ አገልግሎቶች ይሰጣሉ፦
    • በተሻሻሉየእርሻቴክኒኮችላይየሥልጠናእናየኤክስቴንሽንአገልግሎቶችበኮርሶች፣በኤግዚቢሽኖች፣በማሳያእርሻዎች፣በመስክእናከአርሶአደር ወደአርሶ በደርማስተላለፊያ።
    • ገበያተኮርመረጃእናየምክርአገልግሎት።
    • ስብሰባና መረጃ መለዋወጫ ቦታዎች።
    • አትክልት፣ ፍራፍሬና የመኖ አዳዲስ ዘሮችና ችግኞች አቅርቦት።
  • የመንግስትበጀትአነስተኛስለሆነ መንግስትለሠራተኞችደመወዝከከፈለበኋላለመደበኛሥራዎችበጣምዝቅተኛገንዘብነው የሚተርፈው።ይህ ሁኔታየሥልጠናማዕከላቱ ማከናወን ከሚችሉትየሥራዓይነቶችይገድባቸዋል።

የቃላትፍችዎች

ክሎሮፊል፦በእፅዋትውስጥየሚገኘውአረንጓዴቀለም።ዕፅዋትምግብለመሥራትክሎሮፊልእናብርሃንይጠቀማሉ።

አስራጊነት፦አፈር ውስጥ የሚገኝ ክፍት ቦታ መጠን፣ በጠጣር ያልታያዘው እና በአየር ወይም ውሃ የተያዘው የአፈሩ ክፍል።

ሸንተረሮች: በቦይ ውስጥ አርገው ከፍ ያለ የእርሻ መሬትን አቋርጠው የሚያልፉ መስመሮች (ትስስር የሚባሉት)።

 

በዚህ ርዕስ ላይ ሌሎች ግብዓቶችን የት ማግኘት እችላለሁ?

  1. Africa RISING, 2015. Adding value in a changing world: Mechanizing small scale faba bean processing in Ethiopia. https://africa-rising.net/mechanizing-faba-bean/
  2. Alemayehu, N., 2010. Farmer training centres and the IPMS programme in Ethiopia.
  3. Ayele, S., 2021. The resurgence of agricultural mechanisation in Ethiopia: rhetoric or real commitment? The Journal of Peasant Studies. https://www.tandfonline.com/doi/full/10.1080/03066150.2020.1847091
  4. Berhane, G., et al., 2017. The rapid – but from a low base – uptake of agricultural mechanization in Ethiopia: Patterns, implications and challenges. https://www.ifpri.org/publication/rapid-%E2%80%93-low-base-%E2%80%93-uptake-agricultural-mechanization-ethiopia-patterns-implications-and
  5. Bioversity International & CIAT, CGIAR CCAFS, and GIZ. 2020. Adapting Green Innovation Centres to Climate Change: Analysis of value chain adaptation potential. Wheat, Faba Beans, and Honey Value Chains in Arsi Zone, Ethiopia. https://cgspace.cgiar.org/bitstream/handle/10568/111337/ETHIOPIA_2021.pdf?sequence=1&isAllowed=y
  6. Ethiopian Institute of Agricultural Research, 2018. Faba bean Production Guideline Using Rhizobial Bio-fertilizer Technology. Downloadable at: http://publication.eiar.gov.et:8080/xmlui/handle/123456789/3133
  7. Grains Research and Development Corporation (GRDC). 2017. Fungal disease management strategies. https://grdc.com.au/__data/assets/pdf_file/0030/369147/GrowNote-Faba-Bean-West-9-Diseases.pdf
  8. Hirpa, D. et al, 2019. Evaluating the impacts of using Alemayehu row seeding technology (ART) on wheat production as compared to manual row seeding: the case of selected six Woredas of Arsi Zone.
  9. Kebede. E., 2020. Grain legumes production and productivity in Ethiopian smallholder agricultural system, contribution to livelihoods and the way forward. Cogent Food & Agriculture,6:1,1722353.https://www.tandfonline.com/doi/pdf/10.1080/23311932.2020.1722 353
  10. Seyoum, A., 2019. Good Agricultural Practices (GAP) Intervention through Crop Rotation Based On-Farm Demonstrations (RoBOFD) in Arsi Zone.
  11. United States Department of Agriculture, 1998. Legumes and Soil Quality. Technical Note No. 6. https://www.nrcs.usda.gov/Internet/FSE_DOCUMENTS/nrcs142p2_053276.pdf
  12. Van den Broek, J., et al, 2014. Legume Value-Chains in Ethiopia—Landscaping Study. https://gatesopenresearch.org/documents/3-116
  13. Yitayih, G., and Azmeraw, Y., 2017. Adaptation of faba bean varieties for yield, for yield components and against faba bean gall (Olpidium viciae Kusano) disease in South Gondar, Ethiopia. The Crop Journal 5(6), 560-566. https://www.sciencedirect.com/science/article/pii/S2214514117300582
  14. Yurga, C., and Rashid, S., 2010. Pulses Value Chain in Ethiopia: Constraints and opportunities for enhancing exports. https://www.researchgate.net/publication/282730151_Pulses_Value_Chain_Potential_in_Ethiopia_Constraints_and_opportunities_for_enhancing_exports

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጅ፡ ነፃነት ኃይሉ፣ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያ።

ሃያሲ: ደሳለኝ ሞላ, አማካሪ, ጥራጥሬዎች ቫልዩ ቼይን, የግብርና ምርታማነት ፕሮግራም ማስተዋወቅ፣ለግብርና እና ለምግብ ዘርፍ የአረንጓዴ ፈጠራ ማዕከል – ጂ.አይ.ዜድ ኢትዮጵያ።

ይህ ስራ የአረንጓዴ ፈጠራ ማዕከልን ፕሮጀክት ለመተግበር ጂ.አይ.ዜድ በሰጠው ድጋፍ አማካኝነት የተዘጋጀ ነው።