በኮቪድ-19 ክትባቶች፣ ክትባት ማስተዋወቂያ፣ የህዝብ ጤና እርምጃዎች እና የፆታ እኩልነት እንዲሁም አካታችነት ላይ የሚያጠነጥኑ የአየርላይ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች (ስፖቶች)

ጤናጤና

Notes to broadcasters

ለሬዲዮ አሰራጮች የቀረበ ማስታወሻ
ኮቪድ-19 ዓለም አቀም የጤና ችግር ሆኖ ቀጥሏል። በአሁኑ ወቅት ክትባቶች ስላሉ አድማጮችዎ እንዲከተቡ
ማበረታታት ትችላላችሁ። እነዚህም፦

  • የኮቪድ-19 ክትባቶችን በተመለከተ የሚኖራቸውን ጥያቄዎችና ግርታዎች በአክብሮት በመመለስ።
  • ስለክትባቶቹ ትክክለኛና ተአማኒ መረጃዎችን በመስጠት።
  • የኮቪድ-19 ክትባቶችን የተከተቡ ሰዎችን ተሞክሮአቸውን እንዲያጋሩ በማድረግ አድማጮቻችሁእንዲከተቡ ማበረታታት።
  • የኮቪድ-19 ክትባቶች ተጓዳኝ ችግር የሌለባቸው እና ውጤታማ መሆናቸውን ለአድማጮች አበክሮ በማሰማት።

የኮቪድ-19 መረጃ እና መልዕክት በጣቢያችሁ በሚተላለፉ የጤና ፕሮግራሞች በአግባቡ መቅረብ አለባቸው!
አድማጮችን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ እንዲረዳ እነዚህን 24 ተከታታይና አጫጭር ማስታወቂያዎችን በየፕሮግራሞቻችሁ እነዚህም በዜና፣ በሙዚቃ፣ በቢዝነስ፣ በስፖርት እና በሐይማኖታዊ ፕሮግራሞች በማስተላለፍ ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች በቀላሉና በአግባቡ ማስተዋወቅ ትችላላችሁ።

ከየጣቢያዎቻችሁ ሁኔታ ጋር ለማዛመድ እነዚህን አጫጭር ማስታወቂያዎችን ማመሳከር ይቻላል። ለምሳሌ የተወሰኑ ማስታወቂያዎች በገበያ ቦታ የሚሰሩ ቢሆንም በስፖርት ግጥሚያ ስፍራዎች፣ በሙዚቃ ዝግጅቶች፣ በቢሮ ውስጥ፣ በእርሻ ስፍራዎች አልያም በፀሎት ቦታዎች መሰራት ይችላሉ።

የሚከተሉትን መንገዶች በመጠቀም የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከማህበረሰቡ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲዛመድ
ማድረግ ይቻላል ፤

  • በማስታወቂያው ያሉ ስሞችን በአካባቢ ስሞች በመቀየር።
  • የሬዲዮ ጣቢያዎቻችሁን ስም በአግባቡ፤ በመጠቀም (ፅሁፉም xxx ሬዲዮ በሚል)።
  • አድማጮቻችሁ በቀላሉ መረዳት የሚችሏቸውን ቃላትን መጠቀም። (ለምሳሌ አድማጮቻችሁ ኮቪድ-19ን “ኮቪድ” ወይም “ኮሮና” ብለው ይገልፁ ይሆናል)።
  • የምታስተላልፉት መልዕክት ከአካባቢው የጤና ኃላፊዎች ጋር የሚናበብ መሆኑን ማረጋገጥ።

ማስታወቂያዎችን በራሳችሁ ለማዘጋጀት አድማጮች የክትባት ተሞክሮአቸውን እንዲያጋሩ መጠየቅና ድምፃቸውን ለመቅዳት ፈቃደኝነታቸውን በመጠየቅ በሂደት ላይ እንዳለ ማስታወቂያ ማሰራጨት። በቃለ መጠይቁ ወቅት ስማቸውን፣ እድሜአቸውን፣ ለምን እንደከተቡና አሁን ምን እንደሚሰማቸው መጠየቅ። እንዲህ ያሉ አዎንታዊ ምስክርነቶች ስለ ክትባቶቹ ጎጂ አለመሆንና ውጤታማነት አድማጮቻችሁን ለማሳመን ረዥም ርቀት መሔድ ይችላሉ።

ስፖት #21 ይህ ስለ "ክትባቱ ማረጋገጫ" ምሳሌ ነው። ታዋቂና እምነት የሚጣልባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ቃለ
መጠይቅ በማድረግ በተከታታይነት ማስተላለፍ።

በተቻለ መጠን ሰፊ የህብረተሰቡ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ አድማጮች በሚናገሯቸው ቋንቋዎች መተርጎም።
በጊዜ ሂደት ፋርም ሬዲዮ ኢንተርናሽናል እነዚህን ማስታወቂያዎች በተለያዩ የአፍሪካ ቋንቋዎች ይተረጉማል። እነዚህ
ማስታወቂያዎች ተተርጉመው ለአገልግሎት ዝግጁ ሲሆኑ በሚከተለው ድረ-ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል፤
https://scripts.farmradio.fm/radio-resource-packs/translations-available/

Script

 

ስፖት 1:
አፍዎንና አፍንጫዎን በጭምብለ ይሸፍኑ፤ ጭምብል አደራረግዎም ትክክለኛ ይሁን

 

ተራኪ:
የኮቪድ-19 ወረርሽኙ እጅግ አታካች ነበር፤ አሁንም አልተቋጨም። ሆኖም ተስፋ አንቁረጥ! ወዳጅ ዘመዶቻችንን እና ማህበረሰቡን ከበሽታው ለመታደግ ስንል መበርታት ይኖርብናል።

ስለዚህ ሙሉ ክትባቱን የተከተቡም ቢሆን አፍና አፍንጫዎን በጭምብል መሸፈኑን አያቋርጡ። ጭንብል ከበሽታ እንዲከላከልሎ ጉንጭዎን፣ ከአፍንጫዎን እና አገጭዎን በደንብ ገጥሞ መሸፈን አለበት። በትክክል ሲለብሱ, ጭምብልዎ ምቾት ሊሰማው ይገባል። ጭምብልዎን ሲያደርጉ ምቾት እንዳይነሳ አድርገው መሆን አለበት።

ልክዎ የሆነ ጭምብል ይጠቀሙ፤ እንዲሁም ይከተቡ።

በጋራ ኮቪድ-19ን መግታት እንችላለን።

 


 

ስፖት 2:
የህክምና ጭምብሎች ከጭርቅ ጭምብሎች በተሻለ መልኩ በሽታን የመከላከል አቅም አላቸው። ሆኖም ግን ጭምብል ከነአካቴው ካለመጠቀም ይልቅ የጨርቅ ጭምብሎችን መጠቀሙ ይመረጣል።

 

ተራኪ:
የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል ከሚረዱን መሃል ጭምብሎች በዋነኝነት ደረጃ ይቀመጣሉ። በድጋሚ ጥቅም ላይ ከሚውሉ የጨርቅ ጭምብሎች ይልቅ ጥራት ያለው፣ ጥቅም ላይ ከዋሉ የተወሰነ ሰዓት ውስጥ የሚጣሉ የህክምና ጭምብሎች እርስዎን ከበሽታ ለመጠበቅ እና የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የበለጠ ውጤታማ ናቸው። ነገር ግን ያስታውሱ፡- ራስዎንም ሌሎችንም ከበሽታ ለመከላከል ጭምብል በትክክሉ የሚሸፍንዎትን ጭምብል መጠቀም አለብዎት።

ለጥቂት ሰአቶች ተጠቅመውበት የሚያስወግዱት ጭምብል ከሌሎት በተደጋጋሚ ሊጠቀሙት የሚችሉትን የጨርቅ ጭምብል መጠቀምዎን ይቀጥሉበት። የጨርቅ ጭምብልን መጠቀሙ ከነአካቴው ጭምብል ካለመጠቀም ይልቅ ይመረጣል።

የሚወዷቸውን። ጭምብል ይጠቀሙ።

 


 

ስፖት 3:
አሁንም ኮቪድ-19ን በሚመለከት መውሰድ የሚገባንን ጥንቃቄዎች መቀጠል አለብን።

 

ተራኪ:
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ረጅም እና ከባድ ነበር፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ደግሞ ገና አልተቋጨም።

ስለዚህ ሁላችንም የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰዱን አጠናክረን መቀጠል አለብን።

አፍዎን እና አፍንጫዎን በትክክሉ የሚሸፍን ጭምብል ማድረግዎን ይቀጥሉበት። የሰውነት ርቀትዎን ይጠብቁ። እጅዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ። መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝውውር መኖሩን ያረጋግጡ። ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍና አፍንጫዎን በክርኖ መሸፈኑን እይዘንጉ።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ክትባቱን ይከተቡ!

ተግተንና ጠንክረን ማህበረሰባችንን ከበሽታው መጠበቃችንን እንቀጥል።

 


 

ስፖት 4:
ኮቪድ-19 ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጤና ላይ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል።

 

ገላጭ ድምጽ:
ከባድ እቃ የማንሳት ድምጽ። ከዛ የማሳል ድምጽ።

ሚስት:
ምነው ኮፊ? ደህና አይደለህም እንዴ?

ባል:
(ከባድ ትንፋሽ) አዎ ደህና ነኝ ውዴ፣ አመሰግናለሁ። ከኮቪድ-19 ካገገምኩ በኋላ ግን እንደድሮዬ አይደለሁም… እሁንም በጣም ትንፋሽ ያጥረኛል፣ ድሮ በቀላሉ እሰራቸው የነበሩት የሰውነት እንቅስቃሴዎች አሁን አሁን ይከብዱኛል።

ሚስት:
ይህ ገን እንዴት ሊሆን ይችላል? ባለፈው ሳምንት ከኮቪድ-19 ነጻ እንደሆንክ ተነግሮናል፣ ብዛ ላይ ደግሞ ጤናማ ወጣት ነህ!

ባል:
እሱስ እውነት ነው ግን ደግሞ ሃኪሙ እንዳስረዳኝ ኮቪድ-19 ዘላቂ የሆነ ጉዳት በሳምባ ልብና ኩላሊት ላይ ሊያስከትል ይችላል። የማሽተትና የመቅመስ አቅምን እንኳን ያሳጣል። የምትሰሪልኝን ምግብ እንኳን ጣዕሙን ከለየሁ ሳምንታት አለፉኝ። በዛ ላይ ሁሌ እንደደከመኝ ነው…

ሚስት:
ውይ የኔ ውድ አዝናለሁ… ቶሎ እንደሚሻልህ ተስፋ አደርጋለሁ። እሁን ሁለታችንም መከተባችን ተመስገን ነው የሚያስብለው።

ተራኪ:
ኮቪድ-19 አይመርጥም። ለሁሉም ሰው አደገኛ ነው። በጤናዎ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል። ክትባቶች ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መተኛትን እና በኮቪድ-19 ሞትን ለመከላከል በጣም አስተማማኝ እና ውጤታማ መንገዶች ናቸው።

ስለዚህ ሳይዘናጉ ዛሬውኑ የከተቡ።

 


 

ስፖት 5:
በኮቪድ-19 ክትባቶች ዙሪያ ላይ ጥርጣሬዎች አለዎ? የሚያስፈልጎትን መረጃ ያግኙ።

 

ወንድ 1:
ኮቪድ-19ን ለመግታት ተከተቡ እየተባልን መሆኑን ማመን እየተሳነኝ ነው። ይህ እኮ መብትና ነጻነቴን የሚጋፋ ነው!

ወንድ 2:
ምን እየተሰማህ እንደሆነ ይገባኛል ወንድሜ። እኔም የኮቪድ-19 ክትባቶቹ ያጠራጥሩኝ ነበር። ስለክትባቶቹ ተጨማሪ መረጃ እንዲኖረኝ ስለፈለኩ እንዲሁም እንዴት እንደሚሰሩ ለማወቅ ስል ሬዲዮ xxx ን በማዳመጥ ያሉኝን ጥያቄዎች ሁሉ ጠየኩ። ከዛ በኋላ ነው ሃሳቤን የቀየርኩት። አሁን የሚሰማኝ ማህበረሰባችንነ እራሳችንም ከበሽታው ለመከላከል ስንል መከተብ እንዳለብን ነው።

ወንድ 1:
አሃሃ… ይህን ሁሉ ጥናት ካደረክበትማ ምናልባት ትክክል ትሂናለህ…

ወንድ 2:
አሪፍ! በል አሁን ኳስ ግጥሚያችንን እንቀጥል። (የማጀቢያ ሙዚቃውን አለስልሶ ማጫወት)

ተራኪ:
በርካታ ሰዎች ኮቪድ-19 ክትባት ዙሪያ ላይ ጥርጣሬ፣ ንዴት ወይም ፍርሃት አላቸው።

ጊዜ ወስደው ስለ ክትባቶቹ ለማወቅ እና ከቤተሰቦችዎ እንዲሁም ጓደኞችዎ ጋር ስለ ክትባቶቹ በመነጋገር የክትባት ሻምፒዮን ይሁኑ።

እውነታዎቹን ይወቁ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 6:
ከክትባቱ በኋላ በበሽታው መያዝ

 

ገላጭ ድምጽ:
ስልክ ይጠራል

ሴት:
ሄሎ፣ ይህ ሬዲዮ xxx ነው። አየር ላይ ነዎት!

ወንድ:
ሄሎ! ኮቪድ-19ን በሚመለከት ጥያቄ ነበረኝ እባክዎ። እንደሰማሁት ከሆነ የተከተቡ ሰዎችም በኮቪድ-19 የመያዝ እና የመታመም እድሉ አላቸው። ስለዚህ መከተቡ ለምን ይጠቅመኛል?

ሴት:
አዎ ክትባቱን ቢከተቡም በኮቪድ-19 ተይዞ የመታመም አልፎ ተርፎም በሽታውን ወደ ሌሎች የማሰራጨት እድሉ ይኖራል። ሆኖም ግን ክትባቱን መከተቡ በበሽታው የመጠቃትም ሆነ የማስተላለፍ እድሉን በእጅጉ ይቀንሰዋል።

ክትባቱ ከከባድ ሕመም፣ ሆስፒታል ከመተኛት አልፎ ተርፎም ከሞት ይጠብቃል። ለዚህም ነው መከተብ አስፈላጊ የሆነው – ለጤናዎ ነው።

ወንድ:
ከተከተቡ በኋላ ኮቪድ-19 ቢይዘኝ ሳልከተብ ከሚይዘኝ የበለጠ ጤናማ እሆናለሁ እያልሽኝ ነው?

ሴት:
በትክክል!

ተራኪ:
የኦሚክሮን ዝርያ በተለየ መልኩ ተላላፊ ነው። ለዚህም ነው ብርካታ ሰዎች ከተከተቡ በኋላ በኮቪድ-19 የሚያዙት። ነገር ግን ክትባቶች ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መተኛትን እና ሞትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት በጣም ውጤታማ ናቸው።

ስለዚህ ነገ ዛሬ ሳይሉ የከተቡ።

 


 

ስፖት 7:
እጅጉን የተጋለጡትን ከበሽታው ለመከላከል ክትባት ይከተቡ።

 

ቢንቱ:
ፋቱ! ሰሞኑን ምነው ገበያ ቦታ አላየሁሽም (አላየሁህም)?

ፋቱ:
ሰላም ቢንቱ። አሁን አሁን ብዙም ወደ ውጭ አልወጣም። የኮቪድ-19 ክትባቱን መከተብ ስለማልችል ጤናዬ እንዲጠበቅ የተለየ ጥንቃቄ መውሰድ አለብኝ።

ቢንቱ:
ውይ! ለምንድነው መከተብ የማትችይው (የማትችለው)?

ፋቱ:
ፈልጌ ነበር እኔማ ጓደኛዬ። ግን የካንሰር ህክምና እየተከታተልኩ ስለሆነ የሰውነቴ በሽታ የመቋቋም አቅም ተዳክሟል ስለዚህ መከተብ አልችልም። ክትባቶቹ አስተማማኝና ውጤታማ እንደሆኑ አውቃለሁ ግን የሰውነቴ በሽታ የመቋቋም አቅሙ እየተከታተልኩ ባለው ህክምና ምክንያት ተዳክሟል።

ቢንቱ:
አዝናለሁ ፋቱ። ለረዳሽ (ልረዳህ) የምችለው ነገር አለ?

ፋቱ:
አዎ—ጓደኞችሽ (ጓደኞችህ) እና ቤተሰቦችሽ (ቤተሰቦችህ) እንዲከተቡ አበረታቺያቸው (አበረታታቸው)! ምንም እንኳን እኔ መከተብ ባልችልም, በዙሪያዬ ያሉ ሁሉም ሰዎች መከተባቸው እኔንም ይረዳኛል። ሁሉም ሰው ሲከተብ እኔም ምናልባት ወደ ገበያ ለመመለስ መተማመን ይሰማኝ ይሆናል።

ተራኪ:
በሽታ የመቋቋም አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት የመታመም ወይም የመሞት እድላቸው ከፍተኛ ነው። ክትባቱን መከተብ ስለማይችሉም አደጋው የበለጠ ነው።

ለበሽታው በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ጨምሮ ማህበረሰብዎን ከበሽታው ይጠብቁ። ክትባቱን ይከተቡ።

 


ስፖት 8:
አዎን፣ ነፍሰ ጡር እናቶች የኮቪድ-19 ክትባትን ያለ ምንም የጤና ላይ እንከን መከተብ ይችላሉ።

 

ሴት 1:
በአዲሱ ጽንስሽ ላይ እንኳን ደስ አለሽ እህቴ! ሌላ ልጅ ወደ ቤተሰብሽ ልትቀላቅይ ስለሆነ መቼስ ደስታ ላይ ነሽ።

ሴት 2:
በጣም ነው ደስ ያለን እንጂ! በዛ ላይ ደግሞ የኮቪድ-19 ክትባትን በመከተቤ በጣም ደህንነት ተሰምቶኛል!

ሴት 1:
(መገረም) ክትባት?? ግን እርጉዝ ሆነሽ የኮቪድ-19 ክትባትን እንዴት ልትወስጂ ቻልሽ?

ሴት 2:
አልሰማሽም እንዴ? ተመራማሪዎቹ ነፍሰጡሮች ክትባቱን ቢከተቡ በራሳቸው ላይም ሆነ በጽንሱ ላይ የሚያስከትለው የጤና እንከን እንደሌለ ተናግረዋል። በተቃራኒው ደግሞ በኮቪድ-19 ብያዝ ለልጄም አደገኛ ነው የሚሆነው። ክትባቱ እኛን ለመጠበቅ ይረዳናል!

ሴት 1:
ይሄማ መልካም ዜና ነው! እሺ ታድያ… ልጅሽ አንቺን ወይስ ባለቤትሽን የሚመስል ይመስልሻል? (ሳቅ እና አጃቢ ድምጽ መቀነስ)

ተራኪ:
ሴቶች፣ ነፍሰጡር ብትሆኑም የኮቪድ-19 ክትባትን ያለ ምንም የጤና እንከን መከተብ ትችላላቹህ። የኮቪድ-19 ክትባቶችን አሁንም በማጥናት ላይ የሚገኙት ተመራማሪዎች ነፍሰጡር ሴቶች መከተብ እንደሚችሉ እየተናገሩ ነው ያሉት።

ስለዚህ አትዘናጊ! ራስሽንም ልጅሽንም ከበሽታው ጠብቂ። ተከተቢ።

 


 

ስፖት 9:
የኮቪድ-19 ክትባት መካንነትን አያስከትልም።

 

ተራኪ:
የኮቪድ-19 ክትባቶች መካን ወይም በግኑኝነት ወቕት አቅመ ቢስ ያደርጋል የሚል ወሬ ሲናፈስ ሰምተህ ይሆናል! ይህ ግን እውነት አይደለም። የኮቪድ-19 ክትባቶች የመራባት ወይም አቅም ማነስ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ምንም ማረጋገጫ የለም።

ሀሰተኛ ወሬዎችን አይመኑ። ክትባቱን ይከተቡ።

 


 

ስፖት 10:
የኮቪድ-19 ክትባቶች ወንድ ላይ መሃንነትን አያስከትሉም።

 

ወንድ 1:
ጓዴ የኮቪድ-19 ክትባት እንዳልተከተብክ ሰማሁ። ለምንድነው?

ወንድ 2:
መከተብ አልችልም — ልጅ መውለድ እፈልጋለሁ!

ወንድ 1:
ኦ ይህማ ወሬ ነው። ባዛ ላይ ሃሰተኛ ወሬ ነው። የኮቪድ-19 ክትባቶች መሃን አያደርጉህም! ክትባቶቹ አስተማማኝ እና ውጤታማ ናቸው። በኮቪድ-19 ምክንያት በጠና ከመታመም፣ ሆስፒታል ከመተኛት ወይም ከመሞት ይጠብቅሃል።

ወንድ 2:
አንተ አንዳልከው አዎ። ግን በምን ማረጋገጥ ይቻላል?

ወንድ 1:
ሬዲዮ XXXን ሳዳምጥ ነበር። የጤና ባለስልጣናትን፣ የአካባቢ ሃኪሞችን እና ክትባቱን የወሰዱ ሰዎችን ጋብዘው ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ ነበር። ሁሉም ተመሳሳይ ነገር ነበር ሲሉ የነበረው። የኮቪድ-19 ክትባቶች ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን መካን አያደርጉም።

ስለዚህ እባክህ ተከተብ። ለራስህም ለማህበረሰቡም ጤንነት ሲባል ክትባቱን መውሰዱ ጥሩ ነው።

ወንድ 2:
(በጥልቅ ሃሳብ በመዋጥ) እሱስ እነዛ ሁሉ ሰወች ተመሳሳይ ነገር መናገራቸው አስተሳሰቤን ይቀይረዋል። ሬዲዮ XXX ላይ ደግሞ እምነት አለኝ። ዛሬ ማታ ወደ ሬዲዮ ጣቢያው እደውላለሁ።

ተራኪ:
ኮቪድ-19 ክትባቶች መሃንነትን አያስከትሉም።

ሃሰተኛ ወሬዎችን አይመኑ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 11:
የኮቪድ-19 ክትባቶች ሴቶች ላይ መሃንነትን አያስከትሉም።

 

ገላጭ ድምጽ:
የገበያ ቦታ ድምጽ። ማጀቢያ ድምጹ ይቀነስ።

ወንድ 1:
አህመድ ሚስትህ የኮቪድ-19 ክትባት እንደተከተበች ሰማሁ። ለምን ግን እንዲህ አደረገች? ሌላ ልጅ መድገም የምትፈልግ መስሎኝ ነበር።

ወንድ 2:
አዎ አብዱል ተከተበች እኔም በመከተቧ ደስተኛ ነኝ። የኮቪድ-19 ክትባት መካን አያደርጋትም። ከከባድ ህመም እና ሞት ይጠብቃታል እንጂ።

ወንድ 1:
በምን አወቅክ?

ወንድ2:
በቢልዮኖች የሚቆጠሩ ሰወች የኮቪድ-19 ክትባትን ተከትበው ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ነው ያሉት፣ ስለዚህ እሷም ደህና እንደምትሆን ጥርጥር የለኝም።

ተራኪ:
ኮቪድ-19 ክትባቶች ሴቶችም ላይ ሆነ ወንዶች ላይ መሃንነትን አያስከትሉም።

ሃሰተኛ ወሬዎችን አይመኑ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 12:
ጡት በማጥባት ላይ ያሉ እናቶች የኮቪድ-19 ክትባት በደህና ሊከተቡ ይችላሉ።

 

ገላጭ ድምጽ:
የህጻን ለቅሶ። ማጀቢያ ድምጹ ይቀነስ።

አሳታ:
ኦ ማሪያማ እንዴት ቆንጅዬ ሴት ልጅ አለችሽ! እንኳን ደስ አለሽ።

ማሪያማ:
አመሰግናለሁ አሳታ፣ እጅጉን ተባርከናል። ደግሞ ያለፈው ሳምንት የኮቪድ-19 ክትባትን ስለተከተብኩ ልጄ ስታድግልኝ እኔም ጤንነቴ ይጠበቃል።

አሳታ:
(መገረም) ክትባት?? ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? በርግጠኝነት ልጅሽን እያጠባሽ ነው ያለሽው አደል? መቼስ ክትባቱ ከጡት ወተትሽ ጋር ተቀላቅሎ እንዲያልፍ አትፈልጊም!

ማሪያማ:
ጓዴ፣ በእርግጥ ጣፋጯ ልጄንማ እያጠባኋት ነው። የኮቪድ-19 ክትባቶች ለሚወስዱ ጡት የሚያጠቡ እናቶች እና ህፃናቶቻቸው ፍጹም ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው እንደውም በክትባቱ በኩል የተወሰነ የኮቪድ-19 መከላከያ ሊተላለፍ ይችላል።

አሳታ:
ውይ እሱማ እፎይታ ነው! ለራስሽ እና ለልጅሽ እንደዚህ አይነት ጥሩ እንክብካቤ እያደረግሽ ስለሆነ ደስ ብሎኛል።

ማሪያማ:
እኔ አሁን እናት ነኝ — በጤንነቴ ላይ ምንም አይነት ድርድር አላደርግም።

ተራኪ:
ሴቶች ጡት እያጠቡ ቢሆንም ኮቪድ-19ን ለመከላከል መከተብ ይችላሉ። የኮቪድ-19 ክትባቶችን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ጡት የሚያጠቡ ሴቶች መከተብ ይችላሉ መከተብም አለባቸው ይላሉ።

ስለዚህ አይዘናጉ! ራስዎን እና ልጅዎን ከበሽታው ይከላከሉ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 13:
ወንዶች! ኮቪድ-19 ወረርሽኙ ባለበት በዚህ ወቅት ለሴቶች ድጋፋችሁን ስጡ

 

ተራኪ:
ወንዶች! በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ብዙ ሴቶች በትጋት እና ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰሩ ናቸው። ልጆች ከትምህርት ቤት ወጥተዋል፣ የቤተሰብ አባላት ታመዋል፣ ሴቶች ደግሞ በእርሻ ቦታ፣ በሥራ ቦታ እና በቤት ውስጥ ካሉት ሃላፊነቶች በተጨማሪ ብዙ ጊዜአቸውን የሚጠይቅ ክንውኖች አሉባቸው!

በህይወትዎ ውስጥ ያሉ ሴቶች እንዲሰቃዩ አይፍቀዱ።

ወንዶች፣ እህቶቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን፣ ሴት ልጆቻችሁን እና እናቶቻችሁን በዚህ በችግር ጊዜ ህጻናትን በመንከባከብ እና ሌሎች የቤት ውስጥ ሥራዎችን በመርዳት ደግፉ።

ሴቶችን ለመደገፍ እና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ሌላ ዋነኛ መንገድም አለ። የኮቪድ-19 ክትባትን ይከተቡ።

 


 

ስፖት 14:
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በፆታ ላይ ተመስርቶ እየተደረገ ያለን ጥቃት እየተጋፈጡ ላሉ ሴቶች ድጋፍ አለ።

 

ተራኪ:
ኮቪድ-19 ሁሉንም ጎድቷል — ከሁሉም በበለጠ መልኩ ግን ሴቶች ላይ ጉዳቱ ያመዝናል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት፣ ብዙ ሴቶች ከቤት መውጣት አልቻሉም ነበር ለዚህም በባሎቻቸው ጥቃት ሲደርስባቸው ተስተውሏል። እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው የሞራል፣ አካላዊ ህክምና፣ ህጋዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ካስፈለገ፣ ይደውሉ። [ጾታዊ ጥቃት እና የቤት ውስጥ ብጥብጥ ሲከሰት ድጋፍ የሚሰጠውን አካል ስልክ ቁጥር እዚህ ያስገቡ]።

ያስታውሱ፦ ብቻዎን አይደሉም።

 


 

ስፖት 15:
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚደርሱ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ይከላከሉ ለተገቢው አካልም ይጠቁሙ።

 

ተራኪ:
አባቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶች እና እናቶች — በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማናቸውንም ጥቃቶችን በመከላከል እና ለተገቢው አካል በማሳወቅ ረገድ ሁላችንም የምንጫወተው ወሳኝ ሚና አለን።

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው የሞራል፣ አካላዊ ህክምና፣ ህጋዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ድጋፍ ካስፈለገ፣ ይደውሉ። [ጾታዊ ጥቃት እና የቤት ውስጥ ብጥብጥ ሲከሰት ድጋፍ የሚሰጠውን አካል ስልክ ቁጥር እዚህ ያስገቡ]።

በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን አልቀበልም ይበሉ።

 


 

ስፖት 16:
ወላጆች! ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች ከልጆችዎ ጋር ያውሩ።

 

ባል:
ውዴ፣ ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች መነጋገር ያለብን ይመስለኛል። ታዳጊ ልጆቻችን አሁን መከተብ ይችላሉ። ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳለብን መወሰን አለብን።

ሚስት:
አዎ ልክ ነህ… ከክትባቴ በኋላ በጣም ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው። ሃኪሙም ክትባቶቹ ከከባድ ሕመም፣ ሆስፒታል ከመተኛት እና ከሞት ጥሩ መከላከያ እንደሚሆኑ ነግረውናል።

ባል:
እውነት ነው… ዛሬ ማታ ከልጆቹ ጋር ቁጭ ብለን እንነጋገር እስቲ። ልጆቻችን የሚከተቡበት ጊዜ ደርሷል።

ተራኪ:
ወላጆች! ከአጋርዎ ጋር በመተባበር የቤተሰብዎን ጤንነትና ደህንነት ይጠብቁ። ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች ከልጆችዎ ጋር ይነጋገሩ፤ ቤተሰብዎን እና ማህበረሰብዎን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲረዳዎ ተገቢውን ምርጫ ይምረጡ።

አይዘናጉ። ጊዜው የመከተቢያ ነው።

 


 

ስፖት 17:
ክትባቶች ለአረጋውያን ብቻ አይደሉም!

 

ሴት 1:
ሁላችሁም ወደ ማህበር ስብሰባችን ዛሬ ማታ እንኳን በደህና መጣችሁ። ዳግም ስለተቀላቀልኳችሁ ደስ ብሎኛል የኮቪድ-19 ክትባቱን ሁለተኛ ዙር ከተከተብኩ በኋላ ደግሞ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው።

ሴት 2:
ግን ለምን ተከተብሽ እመቤት? የኮቪድ-19 ክትባቶቹ ለአረጋውያን ብቻ ናቸው፣ አንቺ ደግሞ ወጣት እና ጤናማ ነሽ።

ሴት 1:
አመሰግናለሁ ግን… እነዚህ ክትባቶች ለሁሉም ነው የተዘጋጁት —ለአረጋዊያንም ለወጣቶችም! ለአርጉዝ ሴቶችም ጭምር።

ሴት 2:
እርጉዝ ሴቶችም?

ሴት 1:
አዎ ለነፍሰ ጡር ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባቱን መከተቡ ፍጹም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። የጤና ባለሙያዎችም እንደሚሉት ክትባት መከተቡ እራስዎን፣ ቤተሰብዎን እና ማህበረሰብዎን ለመጠበቅ የተመረጠ መንገድ ነው።

አሁን ወደ ስብሰባችን እንግባ… (አጃቢ ድምጽ ይቀነስ)

ተራኪ:
ኮቪድ-19 ከሰው ሰው አይለይም። በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያለ ሰውን ሊያጠቃ ይችላል።

የኮቪድ-19 ክትባቶች በሁሉም ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን ከበሽታው ለመጠበቅ አስተማማኝ እና ውጤታማ መንገድ ናቸው።

የመከተቢያ ጊዜው ነው።

 


 

ስፖት 18:
ኮቪድ-19 ከጓደኞችዎ፣ ቤተሰብዎ እና ከስራ ገበታዎ እንዲለይዎ አይፍቀዱለት።

 

ተራኪ:
ከባድ የኮቪድ-19 በሽታ የተከሰተባቸው ሰዎች ለማገገም ስድስት ሳምንታት ወይም ከዚያ በላይ ሊፈጅባቸው ከመቻሉም በላይ ኮቪድ-19 በጤናቸው ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ሊኖረውም ይችላል። ይህ ማለት ደግሞ ከጓደኞች፣ ከቤተሰብ እና ከስራ ገበታ ለመራቅ የሚገደዱበት ጊዜ ማለት ነው።

ነገር ግን ኮቪድ-19 ክትባትን የወሰዱ ሰዎች በጠና የመታመም፣ ሆስፒታል የመተኛት ወይም ለመሞት የመዳረግ እድላቸው በጣም አናሳ ነው። ጤናማና ደስተኛ ኑሮን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን መምራት ይችላሉ።

ስለዚህ አይዘናጉ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 19:
በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወቶዎን አይጡ።

 

ተራኪ:
በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ደግሞ አሰቃቂና አሳዛኝ ክስተት ነው።

ግን እራስዎን ለመጠበቅ ቀላል መንገድ አለ። የኮቪድ-19 ክትባቶች አስተማማኝ እና ውጤታማ ናቸው። መከተብ ከከባድ ሕመም፣ ሆስፒታል ከመተኛት ወይም በኮቪድ-19 ምክንያት ከመሞት ጥሩ የመከላከያ መንገድ ነው።

ህይወትዎን አይጡ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 20:
ኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት ማመንታት ላይ ነዎት? እውነታዎቹን ይረዱ።

 

አማ:
እንደምን አደርሽ (አደርክ) ሲታ! ሱቄ ውስጥ ስላየሁሽ (ስላየሁህ) ደስ ብሎኛል። አምሮብሻል (አምሮብሃል)!

ሲታ:
አመሰግናለሁ አማ። በጣም ደህና ነኝ! የኮቪድ-19 ክትባትን ሙሉ በሙሉ ተከተብኩ። ኡፍ እንዴት ያለ እፎይታ ነው!

አማ:
ኦ ሲታ… እነሱ ክትባቶች ላይስ እምነት የለኝም።

ሲታ:
ስጋትሽን (ስጋትህን) እረዳዋለሁ። ግን ስለክትባቶቹ ማወቅ ሳይሻል አይቀርም። ሁሉም ቤተሰቤ አባላቶች እና የቅርብ ወዳጆቼ ተከትበዋል እና ሁሉም ልክ እንደ እኔ ጤናማ ናቸው።

አማ:
አውነት?

ሲታ:
አዎ። በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶችን በደህና ተከትበዋል። ክትባቶቹ ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መተኛትን እና ሞትን ለመከላከል ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ ናቸው።

አማ:
መልካም ስለነገርሽኝ (ስለነገርከኝ) አመሰግናለሁ። ግን ተጨማሪ ጥያቄዎች አሉኝ። እስቲ የበለጠ ንገሪኝ (ንገረኝ)። ስለ… (አጃቢ ድምጽ መቀነስ)

ተራኪ:
ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ስለሚያሳስቧቸው ጉዳዮች መነጋገር የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆናቸውን ሊያረጋግጥላቸው ይችላል።

ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች እውነታዎቹን ይረዱ፣ ይከተቡ፣ ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ጋር ስለሚያውቁት በመነጋገር የክትባት ሻምፒዮን ይሁኑ።

 


 

ስፖት 21:
የግል የክትባት ማረጋገጫ

 

ተራኪ:
ሕይወት በረከት ነው። እያንዳንዳችን ቤተሰቦቻችንን እና ማህበረሰባችንን ከኮቪድ-19 የመጠበቅ ሃላፊነት አለብን።

(ስም) የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆናቸውን ለማሳወቅ እዚህ ተገኝተዋል። የህይወትን ገጸ በረከቶች ማግኘቱን እንዲቀጥሉ አሁኑኑ እንዲከተቡ አበረታታለሁ።

 


 

ስፖት 22:
የኮቪድ-19 ክትባቶች መደበኛ፣ መለስተኛ የጎንዮሽ ህመሞች

 

ገላጭ ድምጽ:
የስልክ ጥሪ

ወንድ ልጅ:
ሄሎ ቢኒያም ነኝ።

አባት:
ቢኒ! ሰላም ልጄ!

ወንድ ልጅ:
እንዴት ነህ አባዬ?

አባት:
ደህና ነኝ። ግን አንተ ያን ኮቪድ-19 ክትባት መከተብህን ሰማሁ። ምነው እነሱ ክትባቶች እኮ ለህመም ነው የሚዳርጉህ አታውቅም እንዴ?

ወንድ ልጅ:
ኧረ ይሄ ዝም ብሎ ወሬ ነው አባዬ። ክትባቱን ከወሰድኩ በኋላ አንዳንድ መለስተኛ የጎንዮሽ ህመም ተሰምቶኝ ነበር። ክንዴን አሞኝ ነበር፣ እና ትንሽ ደክሞኝ ነበር፣ ህመሙ ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ውስጥ ነው የጠፋው። ልክ እንደ ማንኛውም ሌላ ክትባት ማለት ነው።

እና አሁን ሙሉ ጤንነትና ጥሩ ስሜት ነው የሚሰማኝ። ክትባቶቹ ሰዎችን አያሳምሙም ከበሽታ ይከላከላሉ እንጂ። አንተ እና እማዬም በቅርቡ እንደምትከተቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

አባት:
ጤንነት እየተሰማህ ስለሆነ ደስ ብሎኛል! ክትባቱን እኔና እናትህ ስለመከተባችን ግን እናስብበታለን። በል ደህና ሁን ልጄ፣ ሰሞኑን እደውልልሃለሁ… (ማጀቢያ ድምጽ የቀንስ)

ተራኪ:
የኮቪድ-19 ክትባትን ከተከተቡ በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እንደ ሰውነት መዛል ህመም፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና ቀላል ትኩሳት ያሉ ቀላል የጎንዮሽ ጉዳቶች የተለመዱ ናቸው። እነዚህ የተለመዱ ናቸው የጎንዮሽ ህመም ሲሆኑ ክትባቱ እየሰራ ነው ማለት ነው።

የኮቪድ-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ውጤታማ ነው።

እውነታዎቹን ይወቁ። ይከተቡ።

 


 

ስፖት 23:
ክትባት እንዲከተቡ ለልጆቻችሁ ድጋፍ አድርጉ።

 

ገላጭ ድምጽ:
በር መንኳኳት። በር ሲከፈት ድምጽ።

ሚስት:
መጥቻለሁ አንድራድ!

ባል:
እንዴት ነሽ ውዴ?

ሚስት:
ምነው ፍቅሬ፣ የተጨነክ ትመስላለህ?

ባል:
አዚዝን አውርቸው ነበር… የኮቪድ-19 ክትባት ሊከተብ እንደሆነ ነገረኝ። ሰዎች ክትባቱ አስተማማኝ እንደሆነ እንደሚናገሩ ባውቅም እያሳሰበኝ ነው…

ሚስት:
ለልጅህ መጨነቁ አይቀሬ ነው ውዴ። ነገር ግን ክትባቱን የተከተቡ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ፣ እና ሁሉም ጤናማ እና ደህና ናቸው። ሃኪሜ ክትባቱ ከኮቪድ-19 እንደሚጠብቀኝ ነግሮኛል። ምናልባት ስለ እሱ የበለጠ ማወቅ ይኖርብን ይሆናል።

ባል:
ልክ ሳትሆኚ አልቀረሽም… በዛ ላይ ልጃችን ነው። በስርዓቱ ስላሳደግነው አምነዋለሁ።

ተራኪ:
የኮቪድ-19 ክትባቶች አስተማማኝ እና ውጤታማ ናቸው። ከልጆችዎ ጋር ስለ ክትባቶቹ በማናገር ይደግፏቸው።

አሁን ጊዜው የመከተቢያ ነው።

 


 

ስፖት 24:
ክትባቶቹ አስተማማኝ እና ውጤታማ ናቸው።

 

ተራኪ:
አንዳንድ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶች በፍጥነት የተገነቡ እና አስተማማኝ አይደሉም ብለው ይጨነቃሉ። ግን የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህና እና ውጤታማ ናቸው።

አንዳንድ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት የተዘጋጀው ከመጠን በላይ ፈጥኖ ነው ብለው ስለሚያምኑ የክትባቶቹ አስተማማኝነት ያሳስባቸዋል።

ክትባቶቹ በፍጥነት የተዘጋጁበት ሶስት ምክንያቶች ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡

አንደኛ – ተመራማሪዎች ቾሮናቫይረስን ማጥናት ከጀመሩ አስርታ አመታትን አስቆጥረዋል። በብዙ መንገዶች ኮቪድ-19 ከሌሎች ኮሮናቫይረሶች ጋር ስለሚመሳሰል ተመራማሲዎች ፈጥነው የትኛው አይነት ክትባት ኮቪድ-19ን ሊገታ እንደሚችል ደርሳውበታል።

ሁለተኛ – ኮቪድ-19 ዓለም አቀፋዊ ቀውስ ስለሆነ በርካታ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎች እና መንግስታት የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ክትባት ለመፍጠር ብዙ ገንዘብ አውለዋል። ገንዘቡ የክትባት አምራቾች ከሌሎች ክትባቶች ይልቅ በፍጥነት እና በብቃት እንዲሰሩ አስችሏቸዋል።

ሶስተኛ – የኮቪድ-19 ክትባቶች አስተማማኝና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ሲባል ጥብቅ ሙከራ ተደርጎባቸዋ

፤ አሁንም እየተደረገባቸው ይገኛል። የኮቪድ-19 ብሽታ ተጽዕኖ ከፍተኛ ስለሆነ ተመራማሪዎች ሙከራ መረጃዎቹ እንደወጡ ነው ጥናታቸውን ወዲያው የሚያከናውኑት። ይህ ደግሞ ኩባኒያዎች ክትባቱን በፍጥነት እንዲያዘጋጁ ረድቷቸዋል።

የኮቪድ-19 ክትባቶች አስተማማኝ እና ውጤታማ ናቸው።

ስለዚህ አይዘግዩ። ይከተቡ።

 


 

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጆች፦ቪጄይከደፈርድ፣በፋርምሬዲዮኢንተርናሽናልአስተዳዳሪኤዲተር፣እናሃናቴሊየር፣በፋርምሬዲዮኢንተርናሽናልየሃብትአስተባባሪ

ይህ ግብዓት የተሻሻለው እና የተተረጎመው በካናዳ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ (ወይም ቫክስ) ውስጥ ባለው የስኬል የህዝብ ጤና እና የክትባት ኮሙኒኬሽን አካል በሆነው የካናዳ መንግስት በአለም አቀፍ ጉዳዮች ካናዳ በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡