ለቃለ መጠይቅ የሚመከሩ ጥያቄዎች: ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ

ጤና

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ለስርጭት ባለሙያዎች ማስታወሻ

እነዚህ ጥያቄዎች የተነደፉት የስርጭት ባለሙያዎች ስለ ሥር የሰደደ COVID-19፣ ወይም ረዥም የሚቆይ ኮቪድ፣ ወይም ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ላይ ባለሙያዎችን ወይም በሽታው ደርሶባቸው የሚያውቁን ሰዎች ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እንዲረዳቸው ነው። ጥያቄዎቹ የተነደፉት ስለ ሥር የሰደደ የኮቪድ-19 ወይም የረዥም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ-19 ምልክቶች፣ መንስኤዎች እና የረጅም ጊዜ ተጽዕኖዎች መረጃ ሰጪ ውይይቶችን ለማዘጋጀት እንዲያግዝዎት ነው። እነዚህን ጽንሰ-ሀሳቦች በጥልቀት ለመመርመር እና ለተመልካቾችዎ የሚፈልጉትን መረጃ ለመስጠት የተወሰኑ ወይም ሁሉንም ተከታታይ ጥያቄዎች ይጠይቁ። እነዚህን ጽንሰ-ሀሳቦች በጥልቀት ለመመርመር እና ለአድማጮችዎ የሚያስፈልጋቸውን ዝርዝር መረጃ ለመስጠት የተወሰኑ ወይም ሁሉንም ተያያዥ ጥያቄዎች ይጠይቁ።

ስለዚህ ርዕስ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመሸፈን ከፈለጉ በጉዳዩ ተመሳሳይ እውቀትካለው ሌላ እንግዳ ጋር ወይም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት መናገር ከሚችሉ ተጋባዥ እንግዶች ጋር ተከታታይ ቃለ ምልልሶችን ያዘጋጁ። ውጤታማ ቃለ መጠይቅ ከመለያዎቹ መሃል በጥሞና ማዳመጥ እና ተያያዥ ጥያቄዎችን መጠየቅ እንደሚገኙበት ያስታውሱ። እነዚህን ጥያቄዎች ለውይይትዎ እንደ መመሪያ ይጠቀሙ ነገር ግን በማንኛውም ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ተያያዥ ጥያቄዎችን ለመጨመር ወይም ለማስወገድ ይዘጋጁ።

በእነዚህ ውይይቶች ወቅት ተደጋጋሚ አባባሎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊነሱ ይችላሉ። ከእንግዳዎ በሚያደርጉት ውይይት በማህበረሰብዎ ውስጥ ያሉትን እነዚህን የተዛቡ አመለካከቶች በበቂ ሁኔታ መሸፈንዎን እና እንዲወገዱ የበኩልዎን ያበርክቱ።

በመጨረሻም፣ በውይይትዎ ወቅት የሚነሱት ፅንሰ ሀሳቦች ቴክኒካል ወይም ሳይንሳዊ ሊሆኑ ይችላሉ። ማንኛውም አድማጭ ሊረዳው በሚችልበት ግልጽ እና ቀላል ቃላት እንዲያብራሩላቸው ቃለ መጠይቅ እየተደረገላቸው ያሉ እንግዶችን ሁልጊዜ ይጠይቁ። እንግዶች የተወሳሰበ ወይም ቴክኒካል ቃላቶችን ከተጠቀሙ እርስዎ ሃሳቡ ቢገባዎትም እንግዳው ግልጽ አርገው እንዲያብራሩ ይጠይቋቸው።

Script

ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድን አስመልክቶ ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄዎች

 

1. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ምንድን ነው?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ መንስኤው ምንድን ነው?

a.ii. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

a.iii. አንድ ሰው ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ብሎ ካመነ ምን ሊያደርግ ይገባል?

a.iv. አንዳንድ ሰዎች ሥር በሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ በሚቆይ ኮቪድ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው? ያብራሩ።

2. በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው የረዥም ጊዜ የጤና ችግሮች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. በኮቪድ-19 በተጠቁ ሰዎች እና ሥር በሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ኮቪድ በተያዙ ሰዎች መካከል ያለው የረጅም ጊዜ የጤና ተጽኖዎች ምንድናቸው?

3. ከኮቪድ-19 ወይም ሥር ከሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ ከሚቆይ ኮቪድ የሚያገግሙ ሰዎች ጤንነታቸውን እንዴት መንከባከብ ይንፖርባቸዋል?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ይችላሉ?

a.ii. የኮቪድ-19 ክትባት ሥር የሰደደ ኮቪድ-19ን ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድን ይከላከላል?

a.iii. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች በበሽታው ከተያዙ በኋላ ሰውነታቸው በሽታውን የመከላከል አቅሙ ይዳብራል?

a.iv. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች እንደ ጭንብል መልበስ ያሉን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መቀጠል አለባቸው? መልሱ አዎ ከሆነ ለምን?

a.v. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ ያለባቸው ሰዎች ራሳቸውን ከሌሎች ማግለል ይኖርባቸዋል?

 

የድህረ ኮቪድ-19 ወይም የረጅም ጊዜ የኮቪድ-19 ምልክቶች ላለባቸው ሰዎች የተዘጋጁ ጥያቄዎች

 

1. በኮቪድ-19 መያዞትን መቼ ነው ያወቁት?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ምን ምልክቶች ነበረብዎት?

a.ii. በኮቪድ-19 ከተያኡበት ጊዜ አንስቶ ባለው ጊዜ በጤናዎት ላይ ያለው ለውጥ ምን ይመስላል?

a.iii. የማያቋርጡ የበሽታው ምልክቶች አለዎት?

a.iii.1. መልሱ አዎ ከሆነ የትኛዎቹ ምልክቶች ናቸው?

2. የሕመም ምልክቶችዎ ለምን ያህል ጊዜ ቆይተዋል?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. የበሽታ ምልክቶችዎ ከተለመዱት የኮቪድ-19 ምልክቶች የተለዩ መሆናቸውን መቼ ነው የተረዱት?

a.ii. ሥር በሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ በሚቆይ ኮቪድ እየተሰቃዩ እንደሆነ ሲረዱ ምን አደረጉ?

a.iii. ሐኪምዎን አነጋግረዋል?

a.iii.1. በአሁኑ ጊዜ ለዚህ የጤና ጉድለት ህክምና እያገኙ ነው? ይህ ህክምና ምንን ያካትታል?
a.iii.2. ይህ ህክምና የበሽታውን ምልክቶች በሚገባ ያክማል?

a.iv. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረጅም ጊዜ የሚቆይ ኮቪድ-19 በህይወቶ ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?

a.iv.1. ሥር የሰደደ ኮቪድ-19 ወይም ረዥም ጊዜ የሚቆይ የኮቪድ ምልክቶችን እንዴት ተቆጣጥረዋል?

a.v. አሁን ከኮቪድ-19 ያገገሙ ይመስልዎታል?

a.v.1. መልስዎ አዎ ከሆነ ካገገሙ ምን ያህል ጊዜ ሆነዎት?
a.v.2. መልስዎ አይ ከሆነየማገገም ስሜቱ መቼ እንደሚሰማዎት መገመት ይችላሉ? መቼ ሊያገግሙ እንደሚችሉ የጤና a.v.3. ባለሙያዎች ግምታቸውን ነግረዎታል?

3. የኮቪድ-19 ክትባቱን ተከትበዋል?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. መልስዎ አዎ ከሆነ እንዲከተቡ ያነሳሳዎት ምንድን ነው?

a.ii. መልስዎ አይ ከሆነ ለምን?

4. ከህመሙ አገግመው ከሆነ በህመምዎ ወቅት ራስዎን እንዴት ነበር ሲንከባከቡ የነበረው ወይም ሌሎች እንዴት ነበር ሲንከባከብዎት የነበረው?

a. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. የመቅመስ ህዋስዎን መልሰው አግኝተውታል? የማሽተትስ?

a.i.1. በህመምዎ ወቅት የማሽተት እና/ወይም ጣዕም የመለየት ችሎታዎን ማጣትዎን በምን መልኩ ተቋቋሙት?

a.ii. ሃኪምዎ ምን መከሩዎት?

a.iii. ከስር ሰደድ ኮቪድ-19 ወይም ረዥም ጊዜ ከሚቆይ ኮቪድ አሁን እያገገሙ ባሉበት ወቅት ቀጣይ እርምጃዎችዎ ምንድን ናቸው?

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጅ፦ አሪስቲዴ ሶሚዬ-አባሎ ካወሌ፣ የመልቲሚዲያ ጋዜጠኛ እና ጦማሪ፣ ሶቶዩቡዋ፣ ቶጎ

ይህ ግብአት በካናዳ የአለም ጉዳዮች ካናዳ መንግስት በኩል በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ የህይወት አድን፣ የህዝብ ጤና እና የክትባት ኮምዩኒኬሽን ከሳህራ በታች ባሉ አፍሪካ (ወይም ቫክስ) ፕሮጀክት አካል ነው።