ለቃለ መጠይቅ የሚመከሩ ጥያቄዎች፦ ወረርሽኙ በሴቶች እና በሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰቡ ክፍሎች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

ጤና

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ለስርጭት ባለሙያዎች ማስታወሻ

እነዚህ ጥያቄዎች የተነደፉት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በማህበረሰብዎ ውስጥ ያሉ ስድስት የተለያዩ ተጋላጭ ወይም የተገለሉ የህብረተሰቡ ክፍሎችን ህይወት እንዴት እንደነካ ቃለ መጠይቅ እንዲያደርጉ ለማገዝ ነው፦ ሴቶች እና ልጃገረዶች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ፣ ስደተኞች፣ ተፈናቃዮች፣ ልዩ እንክብካቤ የሚሹ ወይም አካል ጉዳተኛ ሰዎች ናቸው። ለእያንዳንዳቸው ከአራት እስከ ስምንት ጥያቄዎችን ዘርዝረናል።

ከእነዚህ ተጋላጭ ህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር በቀጥታ የመሥራት ልምድ ላላቸው ሰዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዴት ተጽኖ እንዳደረገባቸው እንዲናገሩ እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ያስፈልግዎታል። እንደዚህ አይነት ሰዎች ለሴቶች ማህበር፣ የወጣት ማኅበራት፣ እንደ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል፣ ፕላን ኢንተርናሽናል እና ገርል ኢፌክት ላሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የአገር ውስጥ ጽሕፈት ቤቶች ወይም ከእነዚህ ስድስት የህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር በቀጥታ በሚገናኙ የመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሊያገኟቸው ይችላሉ። የእያንዳንዳቸውን ቡድን ልምድ ለመቓኘት ከአንድ በላይ ቃለ መጠይቅ ተደራጊ ያስፈልግዎታል።

ለአንዱ የህብረተሰቡ ክፍል የጠየቁት ውስኖቹ ወይም ሁሉም ጥያቄዎች ለሌላውም የህብረተሰብ ክፍል ሊያገለግል እንደሚችል ያስታውሱ። ስለዚህ፣ ለቃለ መጠይቆችዎ በሚዘጋጁበት ጊዜ፣ በዚህ ሰነድ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ጥያቄዎች መከለስዎን ያረጋግጡ። ሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ለምሳሌ ለወጣቶች ወይም ለአረጋውያን እንዴት ሊተገበሩ እንደሚችሉ ግምት ውስጥ ያስገቡ።

ስለዚህ ርዕስ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመሸፈን ከፈለጉ ከአንድ ተጋባዥ እንግዳ ጋር ወይም በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን በጥልቀት ማጋራት ከሚችሉ ሰዎች ጋር ተከታታይ ቃለመጠይቆችን ያዘጋጁ። የዚህ ተከታታይ ክፍሎች አካል አድርገውሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎችን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተገናኘ ያላቸውን ልምድ እንዲያካፍሉ ማነጋገር ይችላሉ።

ጥሩ ቃለመጠይቆች የሚባሉት ተናጋሪውን በንቃት በማዳመጥ እና ጥሩ ተያያዥ ጥያቄዎች በማንሳት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ያስታውሱ። እነዚህን ጥያቄዎች ለውይይትዎ እንደ መመሪያ ይጠቀሙ ነገር ግን ውይይቱ የሚያመራበትን ለመከተል እንዲረዳ በነዚህ ብቻ አይወሰኑ።

በእነዚህ ውይይቶች ወቅት ተደጋጋሚ አባባሎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊነሱ ይችላሉ። ከእንግዳዎ በሚያደርጉት ውይይት በማህበረሰብዎ ውስጥ ያሉትን እነዚህን የተዛቡ አመለካከቶች በበቂ ሁኔታ መሸፈንዎን እና እንዲወገዱ የበኩልዎን ያበርክቱ።

በመጨረሻም፣ በውይይትዎ ወቅት የሚነሱት ፅንሰ ሀሳቦች ቴክኒካል ወይም ሳይንሳዊ ሊሆኑ ይችላሉ። ማንኛውም አድማጭ ሊረዳው በሚችልበት ግልጽ እና ቀላል ቃላት እንዲያብራሩላቸው ቃለ መጠይቅ እየተደረገላቸው ያሉ እንግዶችን ሁልጊዜ ይጠይቁ። እንግዶች የተወሳሰበ ወይም ቴክኒካል ቃላቶችን ከተጠቀሙ እርስዎ ሃሳቡ ቢገባዎትም እንግዳው ግልጽ አርገው እንዲያብራሩ ይጠይቋቸው።

Script

 

ሴቶችና ልጃገረዶችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

 

1. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ላይ ተጽዕኖ ነበረው?

ሀ. መልሱ አዎ ከሆነ፣ እንዴት?

a.i. በምግብ እና በሌሎች የቤት እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሴቶች እና የቤተሰቦቻቸውን የምግብ ዋስትና ላይ ጉዳት አለው? ከሆነ እንዴት?

a.ii. ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ንግዳቸውን ለመዝጋት የተገደዱ ሴቶች ንግዳቸውን እንደገና ለመጀመር ሲሞክሩ ወይም አዲስ ሲከፍቱ ምን ተግዳሮቶች እያጋጠሟቸው?

a.iii. ሴቶች ንግዶቻቸውን መልሰው ለማቋቋም ሲጥሩ ገንዘብ ከማግኘት አንጻር ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች ነበሩ? አዎ ከሆነ፣ እነዚህ ፈተናዎች ምንድን ናቸው?

a.iv. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የስራ ቦታቸው መዘጋት ምክንያት በሴቶች በእራሳቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ምን ተጽእኖ አሳድሯል?

a.v. እነዚህን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለማሸነፍ ሴቶች ምን እያደረጉ ነው?

2. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሴቶችን በማህበራት ያላቸውን ተሳትፎ፥ ለምሳሌ የብድርና ቁጠባ ማህበር፣ የሸማቾች ማህበር እና ሌሎች ማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ማህበራት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ላይ በምን መልኩ ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል?

ሀ. ይህ በሴቶች ህይወት እና በማህበረሰባቸው ውስጥ ባሉ ሰዎች ህይወት ላይ ምን ተጽዕኖ አለው?

3. የጤና አገልግሎትን በሚመለከት የጤና ጣቢያዎች ከአጠቃላይ እና ከሴቶች-ተኮር የጤና አገልግሎቶች ወደ ኮቪድ-19 የጤና አገልግሎት መሸጋገራቸው ሴቶች ላይ ያለው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እርጉዝ ሴቶች የቅድመ ወሊድ እንክብካቤን የማግኘት ተግዳሮቶች እያጋጠሟቸው ነው? መልሱ አዎ ከሆነ እባክዎን ይግለጹ።

a.i. እነዚህን ተግዳሮቶች እያስከተለ ያለው ምንድንነው?

a.ii. ሴቶች እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት እየተቋቋሙ ነው?

a.iii. ሴቶችን ለመርዳት የሚጠቅሙ አገልግሎቶች ወይም ድጋፎች አሉ?

ለ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሴቶች ለመውለድ ወይም ፅንስ ለማስወረድ የህክምና እርዳታ ሲፈልጉ ምን ተግዳሮቶች ያጋጥሟቸዋል?

a.i. እነዚህን ተግዳሮቶች እያስከሰተ ያለው ምንድን ነው?

a.ii. ሴቶች እነዚህን ተግዳሮቶች እንዴት እየተቋቋሙ ነው?

a.iii. ሴቶችን ለመርዳት የሚጠቅሙ አገልግሎቶች ወይም ድጋፎች አሉ?

ሐ. ሴቶች ከኮቪድ-19 ራሳቸውን የሚጠብቁበት ግብዓቶች አሏቸው?

መ. በወረርሽኙ ምክንያት በዕርስዎ አካባቢ ያሉ ሴቶች የእጅ መታጠቢያ ውሃ ለማግኘት የበለጠ እየተቸገሩ ነው?

a.i. መልሱ አዎ ከሆነ ተጽዕኖቹ ምንድን ናቸው?

ሠ. ሴቶች ራሳቸውን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች እንደ ጭንብል፣ ፊት መከለከያ እና የእጅ ማጽጃዎች በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ?

a.i. መልሱ አይችሉም ከሆነ መከላከያዎቹን ለማግኘት መሰናከል የሚሆኑባቸው ምንድን ናቸው?

ረ. ሌሎች ለሴቶች የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች በአሉታዊ መልኩ ተጽዕኖ ተደርጎባቸዋል? መልሱ አዎ ከሆነ ያስረዱ።

4. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በዝቷል?

ሀ. መልሱ አዎ ከሆነ የተወሰኑት ለጥቃቶቹ መንስኤ ናቸው የሚባሉት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ለ. በወረርሽኙ ወቅት ጾታን መሰረት ያደርጉ ጥቃቶች በሚደርሱባቸው ወቅት ሴቶች ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እያደረጉ ነው?

ሐ. ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለመመልከት የህግ አስከባሪ አካላት ዝግጁ ሆነው ይገኛሉ?

a.i. እነዚህን ሪፖርቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ እየፈቱ ነው?

a.ii. ሴቶች ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለህግ አስከባሪ አካላት ሪፖርት ለማድረግ ደህንነት ይሰማቸዋል?

a.ii. 1. መልሱ አይ ከሆነ ለምን?

a.iii. እንደ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች ጾታን መሰረት ያደረጉ ጾታዊ ጥቃቶች ረፖርቶች ጨምረዋል?

a.iv. ጾታን መሰረት ካደረጉ ጥቃቶች የተረፉ ተጠቂዎች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ ያገኛሉ?

a.v. በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት የደረሰባቸው ተጠቂዎች ምን ዓይነት አገልግሎቶች እና የድጋፎችን ማግኘት ይችላሉ?

5. በኮቪድ-19 ወቅት ሴቶች ላይ ያለው የቤት የስራ ጫና ጨምሯል?

ሀ. ይህ የሴቶችን ስነልቦናዊ፣ አእምሮአዊ እና አካላዊ ሁኔታ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምን ይመስላል?

ለ. የቤት ስራ ጫና መጨመሩ በሴቶችና ቤተሰቦቻቸው ላይ የሚያስከትለው ተጨማሪ ውጤት ምንድን ነው?

ሐ. ባሎች፣ ልጆች እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና ከዚያም ባሻገር በሴቶች ላይ ያሉ የስራ ጫናን ለመቀነስ ምን ማድረግ ይችላሉ?

6. ሴቶች ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በሚመለከት፣ ከበሽታው ራሳቸውን እንዴት እንደሚከላከሉና ወደ ሌላው እንዳያሰራጩት ምን ማድረግ እንዳለባቸው በቂ መረጃ አላቸው?

ሀ. መልሱ አይ ከሆነ መረጃው እንዳይኖራቸው ያደረገው ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው?

ለ. የኮቪድ-19 መረጃ፣ ስለ ኮቪድ-19 ክትባት ጨምሮ መረጃው ለሴቶች በተሳካ ሁኔታ ተደርሽ እንዲሆን ምን መደረግ ይገባል?

ሐ. ሴቶች አሁን ስለ ኮቪድ-19 ክትባት በቂ እውቀት አላቸው?

7. በኮቪድ-19 ወቅት የትምህርት ቤቶች መዘጋት ሴቶችና ልጃገረዶችን በምን መልኩ ተጽዕኖ አድርጎባቸዋል?

ሀ. ከታዳጊ ወንዶች ይልቅ ልጃገረዶች ትምህርታቸውን ለመከታተል ከብዷቸው ነበር?

ለ. የትምህርት ቤት መዘጋት በወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶች ውጤቶች እና በሌሎች የትምህርት ሂደታቸው ላይ ምን ተጽዕኖ አሳድሯል?

ሐ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ልጃገረዶች ከትምህርታቸው ያስተጓጎሉ ሌሎች መንሰኤዎች ምን ነበሩ?

8. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሴቶችን እና ልጃገረዶችን በስነልቦናዊ፣ አእምሮአዊ እና አካላዊ ጤንነት ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ምን ይመስላል?

ሀ. ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ ከጀመሩ በኋላ ሁኔታዎች ለሴቶች እና ልጃገረዶች እየተሻሻሉ ነው?

ለ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና ከዚያም ባሻገር ሴቶችን ለመደገፍ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ማድረግ ይችላሉ?

 

ወጣቶችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

 

1. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወጣቶችን ከትምህርታቸው እና ከስራው አንፃር በምን መልኩ እየጎዳው ነው?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ወጣቶች በትምህርታቸው ምን አይነት ተግዳሮቶች እያጋጠሟቸው ይገኛሉ?

a.i. ትምህርታቸው ተቋርጦ ከነበረ ወጣቶች ዳግም ትምህርታቸውን መከታተል ችለዋል? መልሱ አይ ከሆነ እባክዎን ሁኔታውን ያስረዱ።

ለ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ወጣቶች አሁን ምን አይነት ማህበራዊ ተግዳሮቶች እያጋጠሟቸው ነው? ለምሳሌ፣ ወጣቶች ራሳቸውን ከማህበረሰቡ ከማግለል ጋር በተገኛኘ ወይም እንደ ድብርት ያሉ ስነ ልቦናዊ ጉዳዮች፣ ወይንስ ማህበራዊ ክህሎታቸው ገና ያልዳበረ በመሆኑ ተግዳሮቶችን እያስተንገዱ ነው?

a.i. እነዚህ ማህበራዊ ተጽዕኖዎች በወጣቶች ላይ የሚያስከትሉት ጫናዎች ምንድን ናቸው?

ሐ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ወጣቶችን ለመደገፍ ምን ዓይነት ስርዓቶች አሉ?

a.i. የምክር አገልግሎቶች ለወጣቶች ተደራሽ ናቸው?

a.i.1. መልሱ አይ ከሆነ የሚያስከትለው ውጤት ምንድን ነው?

a.ii. ወረርሽኙ ያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም እየጣሩ ያሉ ወጣቶችን ከመደገፍ አንጻር የቤተሰብ አባላት ማህበረሰቡ ያለው አስተዋዕጾ ምን ያህል ነው? እባክዎ በዝርዝር ያስረዱ።

መ. በወረርሽኙ ሳቢያ እንደ መገለል እና የስራ እድል እጦት ያሉ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ወጣቶች እንዴት እየተቋቋሙ ነው?

2. የጤና አገልግሎትተቋማት ከአጠቃላይ አገልግሎቶች ወደ ኮቪድ-19 ጤና አገልግሎቶች በመሸጋገራቸው ወጣቶች ላይ ያመጣው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

ሀ. የወሲብ እና የስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል?

a.i. መልሱ አዎ ከሆነ ወጣቶች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

3. ወጣቶች ስለ ወረርሽኙ እና እራሳቸውን ከበሽታው እንዴት እንደሚከላከሉ እንዲሁም ኮቪድ-19ን ከማሰራጨት እንዴት መጠንቀቅ እንደሚችሉ በቂ መረጃ አላቸው?

ሀ. መልሱ አይ ከሆነ በወጣቶች ዘንድ መረጃው እንዳይኖር ዋነኛ ምክንያት ነው የሚባለው ምንድን ነው?

ለ. የኮቪድ-19 ክትባቶችን ጨምሮ ስለ ኮቪድ-19 መከላከል መረጃ ወጣቶች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ምን ማድረግ ይቻላል?

4. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የወጣቶች ስነልቦናዊ፣ አእምሮአዊ እና አካላዊ ጤንነት ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራል?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እንዲሁም ከዚያም ባሻገር ወጣቶችን ለመደገፍ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

 

አረጋዊያንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

 

1. ኮቪድ 19 በአረጋውያን የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ምን ተጽዕኖ እያሳደረ ነው?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአረጋውያን ምን ምን ተግባራት ተዘግተዋል?

a.i. አረጋውያን እንደ ምግብ፣ ውሃ እና መድኃኒት ያሉ የዕለት ተዕለት አስፈላጊ ነገሮችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ?

a.i.1. ካልሆነ ተጽዕኖው ምንድን ነው?

2. ኮቪድ-19 ለአረጋውያን የበለጠ አደገኛ ነው?

ሀ. አረጋውያን ከሌሎች ሰዎች በበለጠ ፍጥነት በኮቪድ-19 ይታመማሉ?

ለ. በኮቪድ-19 ምክንያት የአረጋዊያን ሆስፒታል ተኝቶ ታካሚና ሞት ቁጥር ጨምሯል?

a.i. መልሱ አዎ ከሆነ ለምን? አረጋዊያን ከሌላው ይልቅ ለኮቪድ ተጋላጭ የሚያረጋቸው ምንድን ነው?

3. አረጋውያን በኮቪድ-19 መከላከል እና መስፋፋት ላይ ጠቃሚ መረጃ ማግኘት ይችላሉ?

ሀ. በየነ መረብ እና የዲጂታል ሚዲያዎችን ተጠቅሞ መረጃ የማግኘት አጠቃቀም ችሎታ ማጠር ምክንያት አረጋዊያን የኮቪድ-19 መረጃ ከማግኘት ያግዳቸዋል? መልሱ አዎ ከሆነ መረጃዎችን ለማግኘት አረጋዊያን ምን አማራጭ መጠቀም ይችላሉ?

ለ. የኮቪድ-19 ክትባቶችን ጨምሮ ኮቪድ-19ን ስለመከላከል ያሉ መረጃዎችን ለአረጋውያን ተደራሽ ለማድረግ ምን ማድረግ ይቻላል?

ሐ. አረጋውያን በአሁኑ ጊዜ ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች በቂ እውቀት አሏቸው?

4. የጤና አገልግሎትተቋማት ከአጠቃላይ አገልግሎቶች ወደ ኮቪድ-19 ጤና አገልግሎቶች በመሸጋገራቸው ወጣቶች ላይ ያመጣው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

5. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአረጋውያን ማህበራዊ ሕይወት ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

ሀ. አረጋውያን በማህበራዊ ሕይወታቸው ውስጥ አካላዊ መራራቅ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ እንዴት እየተቋቋሙ ነው?

ለ. የማህበራዊ መገለል መጨመር አረጋዊያን ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

6. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአረጋዊያን ስነልቦናዊ፣ አእምሮአዊ እና አካላዊ ጤንነት ላይ እንዴት ተጽዕኖ ያሳድራል?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እንዲሁም ከዚያም ባሻገር አረጋዊያንን ለመደገፍ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

 

በሽታን የመከላከል አቅማቸው የሰዳከመ ሰዎችን የሚመለከት ጥያቄ

 

1. የአንድ ሰው በሽታን የመከላከል አቅሙየተዳከመ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?

ሀ. የሰውን በሽታ የመከላከል አቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ በሽታዎች ወይም ሁኔታዎች ምንድናቸው?

2. ኮቪድ-19 በሽታ የመከላከል አቅማቸው ለተዳከመ ሰዎች የበለጠ አደገኛ ነው?

ሀ. የተዳከመ የበሽታን የመቋቋም አቅም ያለባቸው ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በበለጠ ፍጥነት በኮቪድ-19 ይታመማሉ?

ለ. በሽታ የመከላከል አቅማቸው ለተደከመ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል የመተኛት እና የሞት ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው?

a.i. ከሆነ ለምን? የተዳከመ የበሽታ መቋቋም አቅም ያላቸው ሰዎችን ለኮቪድ-19 የበለጠ ተጋላጭ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?

3. ኤችአይቪ በደማቸው ያለባቸውን ሰዎች ጨምሮ የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች የጤና አገልግሎት ተቋማት ከአጠቃላይ የህክምና አገልግሎቶች ወደ ኮቪድ-19 ጋር በተያያዙ አገልግሎቶች መዘዋወራቸው ያሳደረባቸው ጫና ምንድነው?

ሀ. አስፈላጊ ቀዶ ጥገናዎች ወይም ህክምናዎች ተሰርዘዋል ወይም ዘግይተዋል?

ለ. የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን መድሃኒት ማግኘት ይችላሉ?

ሐ. እነዚህ በጤና አጠባበቅ ሥርዓት ላይ የሚደረጉ ለውጦች በሽታን የመከላከል አቅማቸው በተዳከመ ሰዎች ጤና ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?

መ. የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች የማጠናከሪያ ክትባቶችን ጨምሮ የኮቪድ ክትባቶችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ?

4. የተዳከመ የበሽታ መቋቋም ስርዓት ያላቸው ሰዎች ከኮቪድ-19 ራሳቸውን ለመጠበቅ ምን ልዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው?

5. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሽታ የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች ላይ ስነልቦናዊ፣ አእምሯዊ እና አካላዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ያለው እንዴት ነው?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና ከዚያም ባሻገር የበሽታ መከላከያ አቅማቸው የተጎዱ ሰዎችን ለመደገፍ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

 

ስደተኞች እና በአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

 

1. ተፈናቃዮችና ስደተኞች በኮቪድ-19 የመታመም እድላቸው የሰፋ ነው?

ሀ. መልሱ አዎ ከሆነ ለምን እና እንዴት?

a.i. ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ከኮቪድ-19 ራሳቸውን መጠበቅ ይችላሉ? ካልሆነ፣ እባክዎ ጭንብል፣ የእጅ ማጽጃን እና ክትባቶችን ከማግኘት ረገድ የሚያጋጥሟቸውን ማንኛቸውንም ችግሮች ይግለጹ።

2. ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ስለ ወረርሽኙ እና እራሳቸውን እንዴት ከበሽታው መጠበቅ እንደሚችሉ እንዲሁም እንዳያሰራጩት ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ በበቂ ሁኔታ ያውቃሉ?

ሀ. መልሱ አይ ከሆነ ይህ መረጃ እንዳይኖራቸው ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው?

ለ. የኮቪድ-19 ክትባቶችን ጨምሮ ስለ ኮቪድ-19 መከላከያ እርምጃውች መረጃዎች በበቂ ሁኒታ ለስደተኞች እና ተፈናቃዮች ለማድረስ ምን ማድረግ ይቻላል?

ሐ. ስደተኞች እና ተፈናቃዮች አሁን ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች በቂ እውቀት አሏቸው?

3. ከገንዘብ አንጻር ወረርሽኑ ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን እንዴት ተጽዕኖ እያደረገ ነው?

ሀ. በወረርሽኙ ጊዜም ስደተኞች አነስተኛ ንግዳቸውን መቀጠል ችለዋል?

a.i. መልሱ አይ ከሆነ የለተለት ኑሮዋቸውን በምን መልኩ ተጽዕኖ አሳደረ?

a.ii. ስደተኞች እነዚህን ተጽዕኖዎች እንዴት እየተቋቋሙ ነው?

4. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለስደተኞች እና ተፈናቃዮች የምግብ ዋስትና እጦት ተባብሷል?

ሀ. መልሱ አዎ ከሆነ ለስደተኞች እና ተፈናቃዮች የምግብ ዋስትናን ለመደገፍ የሚረዱ አገልግሎቶች አሉ? እንዴት?

ለ. ስደተኞች እና ተፈናቃዮች የምግብ ዋስትና እጦትን እንዴት ይቋቋማሉ?

5. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በስደተኞች እና ተፈናቃዮች ላይ በስነልቦናዊ፣ አእምሯዊ እና አካላዊ ጉዳት እንዴት ያደርሳል?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና ከዚያም ባሻገር ስደተኞችን እና ተፈናቃዮችን ለመደገፍ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ማድረግ ይችላሉ?

 

ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ ጥያቄዎች

 

1. አንድ ሰው ልዩ ድጋፍ ያስፈልገዋል ወይም አካል ጉዳተኛ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?

2. ኮቪድ-19 ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወይም የአካል ጉዳተኞችን የዕለት ተዕለት ኑሮ እንዴት እየነካ ነው?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች ከየትኞቹ እንቅስቃሴዎች ታግደዋል ወይም ተከልክለዋል?

a.i. ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች እንደ ምግብ፣ ውሃ እና መድሃኒት ያሉ የዕለት ተዕለት አስፈላጊ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ?

a.i.1. መልሱ አይ ከሆነ የዚህ ውጤቶች ምን ነበሩ?

3. ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች ስለ ወረርሽኙ እና እራሳቸውን ከበሽታ እና ከኮቪድ-19 እንዴት መከላከል እንደሚችሉ በበቂ ሁኔታ መረጃው አላቸው?

ሀ. መልሱ አይ ከሆነ ይህ መረጃ እንዳይኖራቸው ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው?

ለ. የኮቪድ-19 ክትባቶችን ጨምሮ ስለ ኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች መረጃ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወይም ለአካል ጉዳተኞች የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማድረስ ምን ማድረግ ይቻላል?

ሐ. አሁን ላይ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት በቂ እውቀት አሏቸው?

4. ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ ምን ልዩ እርምጃዎችን ወስደዋል?

5. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች አገልግሎቶችን የሚያቋርጠው እንዴት ነው?

ሀ. ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች የሚፈልጉትን ድጋፍ እና እንክብካቤ ማግኘት ይችላሉ?

a.i. መልሱ አይ ከሆነ የአገልግሎቶቹ መቋረጥ ያስከተለው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

6. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ እንዴት ተጽዕኖ እያሳደረ ነው?

ሀ. ልዩ ድጋፍ የሚሹ ወይም አካል ጉዳተኞች በማህበራዊ ህይወታቸው አካላዊ ርቀትን ከመተግበር አንጻር ያለውን ተጽዕኖ እንዴት እየተቋቋሙት ነው?

ለ. ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወይም አካል ጉዳተኞች ማህበራዊ መገለል በሚያስፈልግበት ወቅት ያለባቸው ተጽዕኖ ምንድን ነው?

7. ኮቪድ-19 ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እና ለአካል ጉዳተኞች የበለጠ አደገኛ ነው? ለምን ሆነ ወይም ለምን አልሆንም?

8. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው፣ አካል ጉዳተኛ እና የአዕምሮ ህመም ያለባቸውን በአእምሯዊ፣ ስነልቦናዊ እና አካላዊ ጤናቸው ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን ይመስላል?

ሀ. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና ከዚያም ባሻገር ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ወይም አካል ጉዳተኞችን ለመርዳት በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጅ፦ ኒዮ ብራውን፣ የፍሪላንስ ጸሐፊ እና የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ይህ ግብአት በካናዳ የአለም ጉዳዮች ካናዳ መንግስት በኩል በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ የህይወት አድን፣ የህዝብ ጤና እና የክትባት ኮምዩኒኬሽን ከሳህራ በታች ባሉ አፍሪካ (ወይም ቫክስ) ፕሮጀክት አካል ነው።