Notes to broadcasters
Save and edit this resource as a Word document
ለስርጭት ባለሙያዎች ማስታወሻ
እነዚህ ጥያቄዎች የተነደፉት የስርጭት ባለሙያዎች እንደ ሃሰተኛ ዜና፣ የተሳሳተ መረጃ እና የሀሰት መረጃ እንዲሁም እንደ እውነት መፈተሽ ባሉ ጉዳዮች ላይ በቂ መረጃ መስጠት ከሚችሉ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ እንዲያደርጉ ነው። እነዚህን ባለሙያዎች በሀገር ውስጥ የሚዲያ ድርጅት ወይም ማህበረሰብን መሰረት ባደረገ በመገናኛ ብዙሃን ማንበብና መጻፍ፣ ሂሳዊ አስተሳሰብ፣ እውነታን ማረጋገጥ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና የሚሰጥ ቡድን ውስጥ ሊያገኙ ይችላሉ። ጥያቄዎቹ የተነደፉት ሀሰተኛ ዜናዎችን፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን እና ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዴት ለይተው ማወቅ እንደሚችሉ ላይ መረጃ ሰጭ ውይይቶችን እንዲፈጥሩ ለመርዳት ነው።
ጥያቄዎቹ የተነደፉት ሀሰተኛ ዜናዎችን፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን እና ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዴት ለይተው ማወቅ እንደሚቻል መረጃ ሰጭ ውይይቶችን እንዲያዘጋጁ ለመርዳት ነው።
የሃሰት ዜና፣ የተሳሳተ መረጃ እና ሃሰተኛ መረጃ አዲስ ክስተቶች እንዳልሆኑ ልብ ማለት ያስፈልጋል። ከበፊትም ጀምሮ የነበሩ ናቸው። ነገር ግን፣ ዛሬ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሚዲያ እና በይነመረብ፣ በበለጠ በቀላሉ ሊሰራጩ ይችላል – እና በዚህም የበለጠ ጉዳት ያደርሳሉ። ቃለ መጠይቁን ሲያቅዱ፣ ከተጠያቂዎች ጋር ለመወያየት እንዲረዳዎ ከሦስት እስከ አምስት ጭብጦች መካከል እያሰባጠሩ መጠቀሙ ይመረጣል። ቃለ-መጠይቁን በነዚህ ጭብጦች መገደቡ ቃለ መጠይቁ ትኩረት ሳቢ እንዲሆን ይረዳል፣ ይህም ለተመልካቾችዎ የበለጠ ጠቃሚ እና በመረጃ ከማጨናነቅ ይቆጠባል። ጭብጡን በጥልቀት ለመመርመር እና ለአድማጮችዎ የሚፈልጉትን መረጃ ለመስጠት የተወሰኑትን ወይም ሁሉንም ተያያዥ ጥያቄዎች ይጠይቁ።
ስለዚህ ርዕስ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመሸፈን ከፈለጉ ከተመሳሳይ እንግዳ ጋር ወይም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ እውቀት ካላቸው ሌሎች እንግዶች ጋር ተከታታይ ቃለ ምልልሶችን ያዘጋጁ። ጥሩ ቃለመጠይቆች የሚባሉት ተናጋሪውን በንቃት በማዳመጥ እና ጥሩ ተያያዥ ጥያቄዎች በማንሳት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ያስታውሱ። እነዚህን ጥያቄዎች ለውይይትዎ እንደ መመሪያ ይጠቀሙ ነገር ግን በማንኛውም ቃለ መጠይቅ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ተያያዥ ጥያቄዎችን ለመጨመር ወይም ለማስወገድ ይዘጋጁ።
በእነዚህ ውይይቶች ወቅት ተደጋጋሚ አባባሎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊነሱ ይችላሉ። ከእንግዳዎ
Script
1. እባክዎ የተሳሳተ መረጃ ምን እንደሆነ ያስረዱ።
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. የተሳሳተ መረጃ የት ሊገኝ ይችላል? ለምሳሌ በበየነ መረብ፣ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ወይም በዋትሳፕ ላይ ሊገኝ ይችላል? ከነዚህ ውጭስ የት ሊታይ ወይም ሊሰማ ይችላል?
a.ii. የተሳሳተ መረጃ ምን ይመስላል? ለምሳሌ በምስሎች፣ በቪዲዮዎች፣ በጽሁፍ መጣጥፎች፣ በድምጽ ቅጂዎች፣ ወዘተ… በኩል ሊሰራጭ ይችላሉ?
a.ii.1. እባክዎ አድማጮቻችን ሊለይዋቸው የሚችሉትን ምሳሌዎች ያጋሩን።
2. የተዛባ መረጃ ምንድን ነው?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. በተሳሳተ መረጃ እና በተዛባ መረጃ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
a.ii. በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ አደገኛ የሚባሉ የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎች የትኞቹ ናቸው?
a.iii. What are the most dangerous types of misinformation and disinformation in our community?
3. ሃሰተኛ ዜና ምንድን ነው? ከተሳሳተ መረጃ እና ከተዛባ መረጃ ይለያል? የሚለይ ከሆነ በምን መልኩ ነው የሚለየው?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. የሃሰት ዜና የት ሊገኝ ይችላል?ለምሳሌ ለምሳሌ በበየነ መረብ፣ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ወይም በዋትሳፕ ላይ ሊገኝ ይችላል? ከነዚህ ውጭስ የት ሊታይ ወም ሊሰማ ይችላል? ከነዚህ ውጭስ የት ሊታይ ወይም ሊሰማ ይችላል?
a.ii. እንደ ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ እና ጋዜጣ ባሉ ባህላዊ የመገናኛ ብዙሃን ሃሰተኛ ዜናዎች ሊሰራጩ ይችላሉ ወይስ በበየነ መረብ ብቻ ነው እነዚህ ሃሰተኛ ዜናዎች የሚሰራጩት?
a.iii. ሃሰተኛ ዜና ምን ይመስላል? ለምሳሌ በምስሎች፣ በቪዲዮዎች፣ በጽሁፍ መጣጥፎች፣ በድምጽ ቅጂዎች፣ ወዘተ… በኩል ሊሰራጭ ይችላል?
a.iv. ሃሰተኛ ዜናን በቀላሉ መለየት ይቻላል? በቀላሉ መለየት የሚቻል ከሆነ እንዴት ሊለይ ይችላል?
a.v. እባክዎ የሃሰተኛ ዜና ምሳሌዎችን ያጋሩ።
a.vi. በሃሰተኛ ዜና እና ስህተት ያለበት ዜና ዘገባ መካከል ልዩነት አለ? መልሱ አለ ከሆነ ልዩነቱ ምንድን ነው?
a.vii. እባክዎ አድማጮቻችን ሊያስታውሱት የሚችሉትን ማንኛውንም ታዋቂ ወይም የቅርብ ጊዜ ሃሰተኛ ዜና ምሳሌዎችን ያጋሩን።
a.vii.1. ይህ ሃሰተኛ ዜና የፈጠረው ጫና ምን ነበር?
4. አንዳንድ የተለመዱ የተሳሳቱ መረጃዎች፣ የተዛቡ መረጃዎች እና ሃሰተኛ ዜና ምንጮች ምንድናቸው?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. ሐሰተኛ ዜና በብዛት የሚስፋፋባቸው መድረኮች የትኞቹ ናቸው?
a.ii. ሃሰተኛ ዜናን በማን በኩል ሊሰራጭ ይችላል?
5. የተሳሳተ መረጃ፣ የተዛባ መረጃ እና ሃሰተኛ ዜና ያላቸው አደጋዎች ምንድናቸው?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. እባክዎ የተሳሳቱ መረጃዎች፣ የተዛቡ መረጃዎች እና ሃሰተኛ ዜናዎች በማህበረሰባችን ወይም በአገራችን እንዴት ጉዳት እንዳደረሱ አንዳንድ ምሳሌዎችን ያጋሩ።
a.ii. ለተሳሳተ መረጃ፣ የተዛባ መረጃ እና ሃሰተኛ ዜና የበለጠ ተጋላጭ የሆነው ማነው?
a.iii. የተሳሳቱ መረጃዎች ሊበለጽጉ እና ሊጨምሩ የሚችሉባቸው የተለዩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
6. በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት እና የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት በርካታ የተሳሳቱ መረጃዎች፣ የተዛቡ መረጃዎች እና ሃሰተኛ ዜናዎች ነበሩ?
ሀ. መልሱ አዎ ነበሩ ከሆነ ለምን?
ለ. በርካታ ሃሰተኛ ዜናዎችን እና የተዛቡ መረጃዎችን የሚያመነጩ የሚመስሉ ጉዳዮች አሉ? ለምን?
ሐ. የተዛቡ መረጃዎች እና ሃሰተኛ ዜናዎች ለምን ይፈጠራሉ?
a.i. ሰዎች ሃሰተኛ መረጃዎችን ከመፍጠር እና ከማሰራጨት ምን ያገኛሉ?
7. በርካታ ሃሰተኛ ዜናዎች የተነደፉት “አስደንጋጭ እይታ” (“Shock Value”) ለመፍጠር ነው። “አስደንጋጭ እይታ” ምንድን ነው? ከተሳሳተ መረጃ፣ የተዛባ መረጃ እንዲሁም ሃሰተኛ ዜና ጋር ያለው ተዛምዶ ምንድን ነው?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. እባክዎ አድማጮቻችን የሚያውቁትን ከ“አስደንጋጭ እይታ” (“shock value”) ኖሯቸው ከተሰራጩ መረጃዎች መሃል አንዳንድ ምሳሌዎችን ይስጡ።
a.ii. ሃሰተኛ ዜናዎች ሲፈጠሩ በዜናው ተከታታይ ዘንድ የተለየ ስሜታዊነትን ለመቀስቀስ ታስቦ ነው? ለምን?
8. በመገናኛ ብዙኃን አውድ ውስጥ “ሂሳዊ አስተሳሰብ” ማለት ምን ማለት ነው? የተሳሳቱ መረጃዎችን፣ የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም ሃሰተኛ ዜናዎችን ለመለየት እንዴት ጥቅም ላይ ሂሳዊ አስተሳሰብን እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል ይችላል?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. ሰዎች በበየነ መረብ ላይ፣ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያ፣ በጋዜጣ፣ በቴሌቪዥን ስለሚያዩት ወይም በሬዲዮ ስለሚሰሙት ነገር በጥሞና ማሰብ እና ማመዛዘን የሚችሉት እንዴት ነው?
a.ii. ሰዎች በመገናኛ ብዙኃን ስለሚያዩዋቸው ነገሮች በጥሞና እና በማመዛዘን ለማሰብ ኣንዲረዷቸው የሚጠቅሙ ምክሮች እና ዘዴዎች አሉ?
9. አንድ ሰው የተሳሳተ መረጃ፣ የተዛባ መረጃን ወይም ሃሰተኛ ዜናን እንዴት ሊለይ ይችላል?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. ሰዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን ወይም ሃሰተኛ ዜናዎችን ለመለየት በበየነ መረብ ጨምሮ ሊያገኟቸው መተግበሪያዎች አሉ?
a.ii. “ምንጭን ማረጋገጥ” ሲባል ምን ለማለት ነው?
a.iii. ሰው የተሳሳተ መረጃን፣ የተዛባ መረጃን እንዲሁም ሃሰተኛ ዜናን መለየት መቻሉ ለምን አስፈላጊ ሆነ?
a.iv. እውነታን መፈተሽ ማለት ምን ማለት ነው?
a.iv.1. ሰዎች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የሚያዩትን፣ በሬዲዮ የሚሰሙትን ወይም በጋዜጣ ላይ የሚያነቡትን መረጃ ለመፈተሽ ምን አይነት ዘይቤዎችን መጠቀም አለባቸው?
a.iv.2. አንድ ሰው የተሳሳተ መረጃ፣ የተዛባ መረጃ እና ሃሰተኛ ዜናን ከለየ በኋላ ምን ማድረግ አለበት?
10. የውሸት ዜና አጋሩ እንበል፣ አሁን ምን ማድረግ አለብዎት?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. የተሳሳተ መረጃን፣ የተዛባ መረጃን እንዲሁም ሃሰተኛ ዜናን ማጋራት ወይም መፍጠር በህግ ያስቀጣል?
a.ii. አንድ ሰው ለምሳሌ በዋትስአፕ ቡድን ውስጥ ምስልን፣ ሚም ወይም ስዕላዊ መግለጫን አይቶ ከእውነት የራቀ ነው ብሎ ካሰበ ምን ማድረግ አለበት?
11. አድማጮች የተሳሳቱ መረጃዎችን፣ የተዛቡ መረጃዎችን እንዲሁም ሃሰተኛ ዜናዎችን ከመዋጋት አንጻር ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?
ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦
a.i. የተሳሳቱ መረጃዎችን፣ የተዛቡ መረጃዎችን እና ሃሰተኛ ዜናዎችን ለመዋጋት በማህበረሰብ ሀብት እና አጋርነት ረገድ የትኞቹን መጠቀም እንችላለን?
Acknowledgements
ምስጋና፦
አዘጋጅ፦ ቴድ ፊዶ፣ ፍሪላንስ ጸሃፊ፣ ሌጎስ፣ ናይጄሪያ