ኮቪድ-19 በፍሬሽ አትክልት አቅርቦት ላይ ያሳደረው ተጽእኖ እና አርሶ አደሮች እና ሌሎችም ከችግሩ አንጻር እየወሰዷቸው ያሉ እርምጃዎች

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ማስታወሻ ለአሰራጮች

ኮቪድ-19 ከ1918ቱ ስፓኒሽ ፍሉ ጋር የሚነጻጸር የክፍለ ዘመናችን እጅግ አስፈሪ መቅሰፍት ነው፡፡ለበሽታው ገና መድሃኒት ስላልተገኘ በአለም ዙርያ ያሉ መንግስታት የወረርሽኙን ስርጭት ለመቆጣጠር ሰዎች በቤታቸው ውስጥ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ይሄ እንቅስቃሴን ማገድ ይባላል፡፡ ይህ እርምጃ የቫይረሱን መራባት እና ስርጭት ይገታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን በምስራቅ ዛምቢያ እንዳሉት የግብርና ማሕበረሰቦች የእንቅስቃሴ እግዱ ምርታቸውን በሚገዟቸው የከተማ ነዋሪዎች ላይ ጥገኛ የሆኑት አርሶአደሮች ላይ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡ ፍሬሽ አትክልቱን ከከተማ ውጭ ከሚመጡ አርሶ አደሮች የሚገዙት የከተማ ነዋሪዎች ላይም ተጽእኖ አሳድሯል፡፡

ይህ ጽሑፍ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች ችግሩን ለማሸነፍ ምን እያደረጉ እንደሆነ ይመረምራል፡፡ የተለመደው ምንጭም የደረቀባቸው የከተማ ነዋሪዎች ፍሬሽ አትክልት ለማግኘት ምን እያደረጉ እንደሆነ ይመረምራል፡፡

ተናጋሪዎቹን የሚወክሉ የድምጽ ተዋንያንን በመጠቀም ይህንን ጽሁፍ በመደበኛ የግብርና ፕሮግራማችሁ ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ ይህን የምታደርጉ ከሆነ አድማጮቻችሁን የሚናገሩት ሰዎች ተዋንያን እንጂ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው እውነተኛዎቹ ሰዎች  አለመሆናቸውን ንገሯቸው፡፡

በተጨማሪም በራሳችሁ አገር ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች እና ሌሎች ባድርሻ አካላት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ምን እያደረጉ እንደሆነ ፕሮግራም ለመሥራት ይህንን ጽሁፍ እንደ ምሳሌ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ፡፡ አነስተኛ አርሶ አደሮችን፣ የስነ ምግብ ባለሙያዎችን፣ የግብርና ኢኮኖሚስቶችን፣ የተለያዩ የግብርና ገበያ ተሳታፊዎችን እና የጤና መስርያ ቤት እና የባህል ህክምና ተወካዮችን በማነጋገር ታሪካችሁን ልታቀርቡ ትችላላችሁ፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልትጠይቋቸው ትችላላችሁ፡-

  • በሃገራችሁ ያለው የበሽታው መያዝ መጠን እና የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና እንዳይሰራጭ ለማድረግ እየወሰዱት ያለው እርምጃ
  • በእነዚህ የቁጥጥር እርምጃዎች ስር አነስተኛ አርሶ አደሮች ችግሮችን እንዴት እየተቋቋሙ እንደሆነ
  • ማህበረሰቦች እነዚህን እርምጃዎች ለመታዘዝ እያደረጓቸው ያሉ ሥራዎች (ለመፍትሄ እርምጃዎች ለመታዘዝ የታመኑ የማህበረሰብ ጤና ሠራተኞች ያላቸውን አስፈላጊነት አካትቱ)

* ይህ ጽሁፍ ሚያዚያ እና ግንቦት 2020 እኤአ በምስራቃዊ ዛምቢያ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ሲሆን ከዚያ

Script

የድምጽ ኢፌክት:
ስልክ ይደውላል

ካምቦሊ:
ሃሎ፣ ካምቦሊ ካንያንታ ነኝ ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት፡፡ ማን ልበል?

ፊሊዩስ:
ፊሊዩስ ቻሎ ጄሬ እባላለሁ፡፡ ብሪዝ ኤፍኤም ላይ ግብርና የንግድ ሥራ ነው የሚለው ፕሮግራም አዘጋጅ ነኝ፡፡ በስልክ ቃለመጠይቅ ላደርግሎት እችላለሁ?

ካምቦሊ:
ስለምን ጉዳይ?

ፊሊዩስ:
የግብርናው ማሕበረሰብ እና የገበያ አጋሮቻቸው ላይ ኮቪድ-19 ያመጣው ተጽእኖን በተመለከተ፡፡

ካምቦሊ:
ኮቪድ-19 ተብሎ ስለሚጠራው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማለትህ ነው?

ፊሊዩስ:
አወ፡፡ በቅርብ የሰዎች እንቅስቃሴ ላይ እግድ ከተጣለ ወዲህ አትክልቶቻቸውን ለመሸጥ ወደ ገበያ የሚመጡ አርሶ አደሮቹ ቁጥር መቀነሱን እያየን ነው፡፡ የአትክልት ገበያ አከፋፋዮችም እግዱ ወደ አርሶ አደሮች ሄደው አትክልት እንዳይገዙ እያደረጋቸው ነው፡፡ እስኪ የአትክልት ገበያውን የአቅርቦት ሰንሰለት ከአርሶአደሮች ጀምሮ፣ በነጋዴዎች አድርጎ ሸማቹ ጋር እስከሚደርስ ምን እንደሚመስል አጭር ማብራርያ ስጡኝ፡፡

ካምቦሊ:
የቺፓታ ኢኮኖሚ በግብርና ላይ የተመሰረተ ሲሆን ወረዳው ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው ማለት በሚቻል ደረጃ የእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ሚና አላቸው፡፡ እዚህ ሰንሰለት የትኛውም ቦታ ላይ የሚፈጠር መሰናክል ሰንሰለቱን በሙሉ ይጎዳል፡፡

ፊሊዩስ:
እስኪ ይህ እንዴት እንደሚሆን ያብራሩ፡፡

ካምቦሊ:
ቀላል ነው፡፡ መንደር ውስጥ ያሉት አርሶ አደሮች አትክልት ያበቅላሉ፣ ነገር ግን እንደ ጨው፣ ስኳር እና ሳሙና የመሳሰሉ መሰረታዊ ሸቀጦች የሏቸውም፡፡ የከተማ ነዋሪዎች ደግሞ እነዚህነ ሸቀጦች በቀላሉ ያገኛሉ ከእርሻ የሚመረቱ ምርቶች ግን የሏቸውም፡፡ አርሶ አደሮች ደግሞ ማንኛውንም ምግብ ለማምረት እንደ ዘር፣ ማዳበርያ እና የግብርና ኬሚካሎችን የመሳሰሉ ግብኣቶችን ከከተማ ማግኘት አለባቸው፡፡

መጨረሻ ላይ አርሶአደሩ ከተማ ሄዶ ምርቱን መሸጥ አለበት፡፡ በዚህ መልክ አርሶ አደሩ ገንዘብ ስለሚያገኝ ቤት የሚፈልጋቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ተጨማሪ አትክልት ለማምረት የሚፈልጋቸውን ግብኣቶች ጨምሮ መግዛት ይችላል፡፡ ኮሮናቫይረስ አስከሚመጣ ድረስ ይህ የእሴት ሰንሰለት ለሁሉም ሰው በደንምብ ይሠራ ነበር፡፡

ፊሊዩስ:
ወረርሽኙ የእሴት ሰንሰለቱን እንዴት ጎዳው? ሰዎች እየታመሙ በመሞታቸው ነው?

ካምቦሊ:
እንደሱ አይደለም፡፡ ችግሩ እግዱ በድንገት በሃገሪቱ ዙርያ መታወጁ ነበር፡፡

ፊሊዩስ:
እስኪ የእግዱን ትርጉም በቀላል ቋንቋ ግለጹት፡፡

ካምቦሊ:
አሁን ካለው ሁኔታ አንጻር እግድ ማለት መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ባለበት ለማቆም ያወጀው እንቅስቃሴን የመወሰን እርምጃ ነው፡፡ ፖሊስ እና ሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊ ሰዎች ብቻ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ ለማረጋገጥ ከተማውን እያሰሱ ነው፡፡

ፊሊዩስ:
አስፈላጊ ሰዎች የሚባሉት እነማን ናቸው? ሁሉም ሰው አስፈላጊ ይመስለኝ ነበር፡፡

ካምቦሊ:
አዎ ሁሉም ሰው አስፈላጊ ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ሁሉም ሰው እንዲወጣ እና እንዲቀላቀል ቢፈቀድ ቫይረሱ ከሰው ሰው እየዘለለ ብዙ ሰዎች ታመው ይሞቱ ነበር፡፡ ስለዚህ መንግስት ሁሉም ሰው ወጥቶ እንዲዞር አይፈቅድም – ሆስፒታል የሚሠሩ የሕክምና ባለሙያዎች እና ሙያቸው በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ጥቂት ሰዎች ብቻ ይፈቀድላቸዋል፡፡ እነዚህም ፖሊሶች እና ሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት ናቸው፡፡ ቀሪው ሰው እገዳው እስከሚነሳ ድረስ ቤቱ እንዲቆይ ይጠበቃል፡፡

ፊሊዩስ:
አርሶ አደሮች አስፈላጊ አይደሉም? እነሱ ከሚያመርቱት ምግብ ውጭ መመገብ አንችልም እኮ፡፡

ካምቦሊ:
በርግጥ አርሶአደሮች ወሳኝ ናቸው፡፡ ነገር ግን እንደ አሁን የሞት እና የሕይዎት ጉዳይ በሆነ ሁኔታ እነሱም መገደብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ አለበለዚያ ይህ ነገር በአለም ዙርያ 50 ሚሊዮን ሕዝብ እንደገደለው እንደ 1918ቱ የስፓኒሽ ኢንፈሉዌንዛ ሊሆን ይችላል፡፡

ፊሊዩስ:
አርሶ አደሮች ምርታቸውን ለመሸጥ ወደከተማ መምጣት ካልቻሉ ለጊዜውም ቢሆን ምርታቸውን የሚሸጡበት ስለሌላቸው ይበላሻል ማለት ነው፣ ገቢም አይኖራቸውም፡፡

ካምቦሊ:
በትክክል! አርሶ አደሮች ገቢ አይኖራቸውም፣ እዚህ ከተማ ያለን እኔና አንተም ፍሬሽ አትክልት አይኖረንም፡፡ በርግጥ ከውጭ የመጡ አትክልቶች ሱፐርማርኬት ውስጥ ይገኛሉ፣ ነገር ግን ዋጋቸው ውድ ሲሆን ፍሬሽም አይደሉም፤ በተጨማሪም ብዙ ሰዎች ልውጠ ህያዋን ናቸው ብለው ስለሚቆጥሯቸው ለጤናቸው ተስማሚ አይደሉም ብለው ያስባሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ፍሬሽ አትክልቶችን ከአርሶ አደሮች ማግኘት ይመርጣሉ፡፡ አሁን ሱፐር ማርኬቶች በከፊል ተከፍተዋል፤ ቁጥራቸው አነስ ያለ ገብያተኛም እየጎበኛቸው ነው፡፡

ፊሊዩስ:
በዚህ የእግድ ወቅት አርሶ አደሮች እና የከተማ ደንበኞቻቸው ችግሩን እንዴት እየተቋቋሙት እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ማነጋገር የምችላቸውን
አንዳንድ
ሰዎች ቢጠቁሙኝ፡፡

ካምቦሊ:
እሺ፡፡ በእርሻው ጥሩ ሥራ እየሠራ ያለው አቶ ግሬቫዚዮ ባንዳ አለ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ብዙ አትክልት፣ ቲማቲም እና ሌሎች ሰብሎችን እያበቀለ ለዋናው ገበያ ያቀርባል፡፡ አሁን ምርቶቹን ለመሸጥ ወደ ከተማ ሲመጣ ስለማላየው በዚህ ሁኔታ እንዴት እየባጀ እንደሆነ አላውቅም፡፡

ፊሊዩስ:
እግዱ የገሬቫዚዮ የግብርና ንግድ ሥራ ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንዳሳደረበት ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ከተማ ውስጥ ያሉ አንድ ሁለት የአትክልት ሸማቾችስ? ላነጋግረው የምችል ሰው ይኖራል?

ካምቦሊ:
(እየሳቀ) አዎ፣ ከራስህ ጋር ላገናኝህ እችላለሁ፡፡ አንተም ፍሬሽ አትክልት ለማግኘት አርሶአደሮችን የምትጠብቅ የከተማ ነዋሪ ነህ፡፡ እራስህን ማነጋገር ትችላለህ፡፡

ፊሊዩስ:
(እሱም እየሳቀ) ልክ ሊሆኑ ትችላለህ፡፡ ቢሆንም እርሶም ከአርሶአደሮች ፍሬሽ አትክልት የሚገዙ የከተማ ነዋሪ ነዎት፡፡ ስለዚህ በኔ ፋንታ እርሶን ቃለ መጠይቅ አደርግሎታለሁ፡፡

ካምቦሊ:
እኔ ሙያዬ የግብርና ኢኮኖሚስት ስለሆነ ለቃለመጠይቁ አልመጥንም፡፡ ግን ደሞ ለሰዎች ለኣመታት ስንመክር የነበረውን የጓሮ አትክልትን ጠቀሜታ ለማሳየት ዕድል ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች የውሃ ሒሳባችን ይጨምራ ብለው ምክራችንን ቸል ብለዋል፡፡ ይሄ ደካማ ምክንያት ነው፡፡

ፊሊዩስ:
እንዴት ማለት?

ካምቦሊ:
የጓሮ እርሻዎች ትልቅ ስላልሆኑ ውሃ አያባክኑም፡፡ ለምሳሌ እኔ አንድ መደብ ቲማቲም፣ አንድ መደብ ሽንኩርት እና ሁለት መደብ አትክልት አለብ፡፡ እነሱን ለማጠጣት ቆሻሻ ውሃ እጠቀማለሁ፡፡ ሳሙናና ዘይት ዝስከሌለበት ድረስ ቆሻሻ ውሃ ችግር የለውም፡፡ ሪሳይክል ማድረግ ማለት ነው፤ ይህም የሚመከር ነው፡፡ሁሉም ሰው ሊደርገው ይገባል!

ፊሊዩስ:
ግን ያደርጉታል?

ካምቦሊ:
በቃ አማራጭ ስለሌለ አሁን ማድረግ አለባቸው፡፡ ካሁኑ አንዳንድ ሰዎች የአትክልት መደብ እና ቀልዝ አዘገጃጀት ለመማር እኔ ጋ መጥተዋል፡፡ ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሰዎችንም በረንዳዎቻቸው ላይ አትክልት በባልዲ እንዴት ማብቀል እንደሚችሉ አስተምራለሁ፡፡

ፊሊዩስ:
ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ አሁን እባኮት አንዳንድ ስ

ክ ቁጥሮችን ይስጡኝ፡፡ አትክልተኛውን አቶ ግሬቫዚዮ ባንዳን እና ምናልባት የፍሬሽ አትክልት የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ አንድ ሁለት ተጨማሪ ሰዎችንም ማነጋገር አለብኝ፡፡

ካምቦሊ:
እሺ የግሬቫዚዮ ስልክ ቁጥር ____________.

ፊሊዩስ:
ይዣለሁ፡፡ አመሰግናለሁ ጓደኛዬ፡፡ ይህንን ፕሮግራም ለማዘጋጀት ስላስቻሉኝ ፕሮግራሜ ላይ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

የድምጽ ኢፌክት: የሙዚቃ መሸጋገርያ እየጠፋ ስልክ ሲደውል ይሰማል

ግሬቫዚዮ:
ሃሎ ማን ልበል?

ፊሊዩስ: ፊሊዩስ ቻሎ ጄሬ እባላለሁ ከብሪዝ ኤፍኤም፡፡ አሁን በኮቪድ-19 ወቅት የግብርና ስራዎትን እንዴት እያካሄዱ እንደሆነ ሊያናግሩኝ ጊዜ ይኖረወታል?

ግሬቫዚዮ:
አዎ ማውራት እንችላለን፡፡ ፕሮግራምዎትን አዳምጣለሁ፡፡ ግብርና የንግድ ሥራ ነው እኛ አርሶ አደሮች እራሳችንን ለመግለጽ እና ለመደመጥ የምንችልበት ስፍራ እንደሆነ ሁል ጊዜ ይናገራሉ፡፡ አሁን በእግዱ የተነሳ የግብርና የንግድ ስራ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ መንግስት እንዴት ሆነን እንድንኖር ነው የሚጠብቀው?

ፊሊዩስ:
ወደዚ ከመግባታችን በፊት ከእግዱ በፊት እንዴት እንደነበር ይንገሩኝ እስኪ፡፡

ግሬቫዚዮ:
በጣም ጥሩ ነበር፡፡ የኔ እርሻ በማይደርቀው የሉቴምብዌ ወንዝ አጠገብ ነው ያለው፡፡ በእግር የሚረገጥ የውሃ መሳብያ አለኝ፡፡ በመሆኑም አመቱን ሙሉ ብዙ ውሃ አለኝ፤ አንዳንድ ጓደኞቼ የውሃ ምንጮቻቸው አመቱ ሲገፋ ይደርቁባቸዋል፡፡ ትልቅ የእርሻ ቦታና ብዙ አትክልት አለኝ፡፡

ፊሊዩስ:
ሌላ ጊዜ እንዴት ነው አትክልት የሚሸጡት?

ግሬቫዚዮ:
አብዛኛውን ጊዜ ከተማ ወዳለዉ አትክልት ገበያ ወስጄ አከፋፋዮች በብዛት ይገዙኛል፡፡ ይሄ ግን ለኔ ብዙም አይመቸኝም፣ ነጋዴዎቹ በነጻ የመውሰድ ያህል ዋጋ እስኪቀንስ ድረስ አርሶአደሩን ይከራከሩታል፡፡ ስለዚህ አንዳንዴ ከሆስፒታ

እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተሻለ ኮንትራት ለማግኘት ደጅ እጠናለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሳይክሌ እየዞርኩኝ በቀጥታ ለተጠቃሚዎች እሸጣለሁ፡፡

ፊሊዩስ:
የእንቅስቃሴ እግድ ከተጣለ ወዲህ ምን ችግሮች ያጋጥሙሃል?

ግሬቫዚዮ:
መጀመርያ እግዱ በድንገት ነው የመጣብን፤ ለመሰብሰብ የደረሰ ብዙ አትክልት ነበረን፡፡ ምርቱን እንዴት እንደማስወግደው ሁሉ ግራ ገብቶኝ ነበር፡፡ ለጨውና ለሳሙና ገንዘብ ስለሚያስፈልገን፣ አትክልቱም ካልተሰበሰበ ስለሚበላሽ ወደ ከተማ ተደብቄ ለመግባት ደጋግሜ ሞክሬ ነበር፡፡

ፊሊዩስ:
ወደከተማ መሄድ ግን ድፍረት አልነበረም?

ግሬቫዚዮ:
በርግጥ ድፍረት ነበር፡፡ መንገድ ላይ የሚታዩ ሰዎች በሙሉ አስፈላጊ ሠራተኞች መሆናቸውን እና ማስክ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ፖሊስ በየቦታው ነበር፡፡ በተጨማሪም ከሌላው ሰው ቢያንስ በአንድ ሜትር መራቅ አለብህ፤ አትክልት ስትሸጥ ይሄ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ደሞ ሳሙና ወይም ስኳር እና ሌሎች አስፈላጊ ሸቀጦችን ለመግዛት ወደ ማንኛውም ሱቅ ከመግባትህ በፊት እጅህን በሳኒታይዘር ኬሚካል ማጽዳት አለብህ፡፡

ፊሊዩስ:
በጣም ተቸግረው ነበር ማለት ነው፡፡

ግሬቫዚዮ:
አዎ፣ በጣም፡፡ በቫረሱ ብለከፍ ይዜው ወደ መንደሬ ስለምሄድ እና በኔ ተነሳ ብዜ ሰዎች ሊሞቱ ስለሚችሉ እያደረግሁት የነበረው ነገርም አደገኛ እንደነበር ተረዳሁ፡፡

ፊሊዩስ:
በርግጥ በጣም አሳዛኝ ይሆን ነበር፡፡ ግን ደግሞ የአትክልት ምርተዎት ሊበላሽ ነው፡፡ ምንድን ነው የሚያደርጉት?

ግሬቫዚዮ:
ሆስፒታሉን አነጋግሬ በራሳቸው ትራንስፖርት መጥተው አትክልቶቹን እንደሚወስዱ ነግረውኛል፡፡ የሆስፒታሉ ሠራተኞች አስፈላጊ ሠራተኞች ስለሆኑ በነጻነት መንቀሳቀስ ይችላሉ፡፡ ከነሱ ጋር መሥራት ችግሩ ሒሳብ ወዲያው አይከፍሉም፣ እኛ ደግሞ ገንዘብ በጣም እንፈልጋለን፡፡

ፊሊዩስ:
እና ምን ሊያደርጉ ነው?

ግሬቫዚዮ:
ባካባቢው ካሉ መንደሮች እየመጡ አትክልቶቼን የሚገዙ ሰዎች ስላሉ እኔ እድለኛ ነኝ፡፡

ፊሊዩስ:
እግዱ መንደሮች ላይ ምንም ተጽእኖ የለውም ማለት ነው?

ግሬቫዚዮ:
እንደሱ አይደለም፡፡ ግን እዚህ ያን ያህል ቁጥጥር የለም፡፡ የፊት ማስክ ካደረግን እና ከሃምሳ ሰው በላይ ካልተሰበሰብን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንችላለን፡፡

ፊሊዩስ:
ግን ብዙ አትክልት አለኝ ብለው ነበር፡፡ ለሆስፒታሉ አንዴ የሚሸጡት እና መንደርተኛው እየተንጠባጠበ የሚገዛው ብክነት ለመቀነስ በቂ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ስብለዎትን ላለማጣት ምን እያቀዱ ነው?

ግሬቫዚዮ:
ባለቤቴ በጣም ፈጣሪ ናት፡፡ አትክልቶቹን ትሰበስብና በስሱ አብስላ መደርደርያ ላይ አድርጋ ጥላ ሥር ታደርቀዋለች፡፡ ሙፉትሳ ብለን እንጠራዋን፡፡ እግዱ እንዳበቃ ሙፉትሳውን ለከተማ ሰዎች መሸጥ ታስባለች፡፡ ደረቅ አትክልት ከተማ ውስጥ በከፍተኛ ዋጋ ይሸጣል፣ እንደ ፍሬሽ አትክልትም ቶሎ አይበላሽም፡፡ እንዲያውም እየቆየ ሲሄድ የበለጠ ይጣፍጣል፡፡

ፊሊዩስ:
ውነትም ባለቤተዎት በጣም ፈጣሪ ናቸው፡፡

ግሬቫዚዮ:
ብዙ ቲማቲም ስላለን ባለቤቴ የቲማቲም ድልህ መሥራት ታስባለች፡፡ ቢሆንም ዋናው ግባት ስኳር ስለሆነ እግዱ እስከሚነሳ ለማግኘት እንቸገራለን፡፡ ከእግዱ ያገኘነው መልካም ነገር ቢኖር ምርታችን ላይ እሴት መጨመር ማሰብ መጀመራችን ነው፡፡

ፊሊዩስ:
ስላነጋገሩኝ አመሰግናለሁ፣ አቶ ባንዳ፡፡ መጀመርያ ላይ አትክልቶችን በመኖርያ መንደር ለሚኖሩ ሰዎች ቀጥታ እሸጣለሁ ብለውኝ ነበር፡፡ ደውዬ የማነጋግራቸው የአንድ ሁለት ደምበኞችን ስልክ ቁጥር ሊሰጡኝ ይችላሉ?

ግሬቫዚዮ:
ምናልባት ወይዘሮ ሚሪያም ምዋሌን ማነጋገር ትችላለህ፡፡ ቋሚ ደምበኛዬ ነበሩ፡፡ አሁን ፍሬሽ አትክልት ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡ የስልክ ቁጥራቸው _____________፡፡

ፊሊዩስ:
ስለትብብረዎት አመሰግናለሁ፡፡ ከእግዱ በኋላ ቋሚ ደምበኛዎት እንደምሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡

የድምጽ ኢፌክት:
ሙዚቃዊ መሸጋገርያ እየጠፋ ሲሄድ ስልክ ይደውላል

ሚሪያም:
ሃሎ ማን ልበል?

ፊሊዩስ:
ፊሊዩስ ቻሎ ጄሬ እባላለሁ፡፡ እኔ …

ሚሪያም:
(ያቋርጡታል) ብሪዝ ኤፍኤም የሚሠሩት የአርሶአደሩ ጓደኛ፡፡ እንኳንም ደወሉ! ግን … እኔ አርሶ አደር አይደለሁም፡፡ ከአርሶአደሮች እና ከግብርና ጋር ያለኝ ግንኙነት አትክልታቸውን መግዛቴ ነው፡፡ ስለዚህ በግብርና የንግድ ሥራ ነው ፕሮግም ላይ ለመቅረብ ጥሩ ተወዳዳሪ የሆንኩ አይመስኝም፣ ተሳስቻሁ?

ፊሊዩስ:
ኧረ ጥሩ ተወዳዳሪ ነዎት፡፡ ከአርሶ አደሮች አትክልት እንደሚገዛ ሰው ላነጋግረዎት እፈልጋሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ በዚህ እግድ ጊዜ ችግሮች ያጋጠመዎት ይመስለኛል፡፡

ሚሪያም:
በጣም እንጂ፡፡ እገዳው ኮቪድ-19ን ለመከላከል ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ገበያ ወይም ሱቅ መሄድ ስለማንችል እስር ቤት ሆኖብናል፡፡ ቤተክርስትያን እንኳን መሄድ አንችልም፤ ትምህርት ቤቶችም ተዘግተዋል፡፡ ስለዚህ ጎረኖ ውስጥ እንደተቀመጡ ፍየሎች ሰው ሁሉ ቤቱ ቁጭ ብሏል፡፡

ፊሊዩስ:
ሰው ሁሉ ቤት በመሰብሰቡ ደስ ሳይለዎት አይቀርም፡፡

ሚሪያም:
እንደ ቤተሰብ ተቀራርበን በመገኘታችን እና እርስ በራሳችንም የተሻለ ለመተዋወቅ መቻላችን ጥሩ ነው፡፡ ባለቤቴም አሁን ቢራ ሊጠጣ ስለማይወጣ እየለፈለፈና እንደ እርጥብ ቆሻሻ እየሸተተ አይመጣም፡፡

ልጆቹም አሁን ብዙ እያነበቡ፣ እየጻፉ እና ቴሌቪዥን እያዩ እና እየተጫወቱ ነው፡፡ ሲሰለቻቸው ግን ድብድብ ስለሚጀምሩ የተከታታይ ድብድቦች ዳኛ እሆናለሁ!

ፊሊዩስ:
(በስሱ እየሳቀ) ይገርማል ምንም ጥሩ ነገር ቢኖር ሁል ጊዜ አብሮት የማይመች ነገር ይኖራል፡፡

ሚሪያም:
አዎ፣ ያሳዝናል፡፡ ግን ገና ምኑን ሰማህና፡፡ በእግዱ ምክንያት ምግብ እንደልባችን እያገኘን አይደለም፡፡ ቤት ውስጥ የሚበላው ምግብ መጠን ግን ጨምሯል፡፡ አትክልት ገበያ መሄድ ሳልችል አርሶ አደሮችም አትክልታቸውን ወደከተማ ይዘው መምጣት ሳይችሉ ይህን ሁሉ የተራበ አፍ እንዴት ላስተናግደው? እውነት እልሃለሁ እግዱ በተነሳ ጊዜ ብዙ ሰዎች አጥንታቸው ቀርቶ ነው የሚገኙት!

ፊሊዩስ:
እና እንዴት ነው የቤተሰብዎትን እለታዊ ፍላጎት የሚያሟሉት?

ሚሪያም:
ከባድ ነገር ነው፡፡ ደግነቱ ዱቄት ስላለኝ እሱን ከተለያዩ ነገሮች ጋር ጠብሼ ለቁርስ አቀርባለሁ፡፡ እግድ ከመጣሉ በፊትም የገዛኋቸው የደረቁ አደንጓሬዎች እና ሙፉትሳ አለኝ፡፡

ፊሊዩስ:
ስለሙፉትሳ ሲያነሱ፣ ግሬቫዚዮ ባንዳ ከሚባሉ አርሶ አደር ጋር እያወራሁ ነበር፡፡ ባለቤታቸው አትክልቶቻቸውን ለሽያጭ ወደ ሙፉትሳ በመቀየር ሥራ እንደተጠመዱ ነግረውኝ ነበር፡፡ ሙፉትሳ ከተራው ፍሬሽ አትክልት የተለየ ጥቅም አለው?

ሚሪያም:
በግሌ ሙፉትሳ ብዙ ጥቅም አለው እላለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ምርት በሚያንስበት ጊዜ አትክልቶችን ሳይበላሹ ማቆያ ዘዴ ነው፡፡ ጥላ ውስጥ ስለሚደርቅ በጣም ጥሩ ጣዕም አለው፡፡

በመሆኑም በፍሬሽ አትክልት ውስጥ ያለው አብዛኛው ምግብ ለረጅም ጊዜ ተጠብቆ ስለሚቆይ ውሃው የወጣለት የተጠራቀመ ምግብ ነው፡፡ ፍሬሽ አትክልት ሲበስል መጠኑ ይቀንሳል፤ ሙፉትሳ ደግሞ የደረቁት ቅጠሎች ውሃ ሲስቡ መጠኑ ይጨምራል፡፡

ፊሊዩስ:
ሙፉትሳ ፍሬሽ አትክልትን መተካት ይችላል እያሉኝ ነው?

ሚሪያም:
መተካት እንኳን አይችልም፡፡ አሁንም ፍሬሽ አትክልት ያስፈልገናል፡፡ አለበለዚያ እንደ ዱሮ ምስኪን መርከበኞች በስከርቪ ነው የምናልቀው፡፡

ፊሊዩስ:
አርሶ አደሮች በወረርሽኙ ምክንያት ምርታቸውን ወደ ገበያ ስለማያመጡ እንዴት ነው ፍሬሽ አትክልት እያገኛችሁ ያላችሁት?

ሚሪያም:
የግብርናው ባለስልጣን አቶ ካምቦሊ በጓሯችን አትክልት ማብቀል እንድንጀምር ስላበረታቱን አትክልት ለማግኘት ችለናል፡፡

ፊሊዩስ:
በቅርብ አነጋግሪያቸው ነበር፤ በፕሮግራሜ ላይ ስለጓሮ አትክልት ለመነጋገር ፈቃደኝነታውን ገልጸውልኛል፡፡

ሚሪያም:
በጣም ጥሩ ነው፡፡ የጓሮ እርሻ መጀመር ውሃ ብቻ የሚያባክን ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ግን የሚደፋ ውሃን አትክልቶችን በማጠጣት ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚረዳ ተገንዝቢያለሁ፡፡

ፊሊዩስ:
እና?

ሚሪያም:
ፕሮግራምህ ላይ ምን እንደሚሉ ለመስማት እጠብቃለሁ፡፡ ከሰማኋቸው በኋላ የራሴ ጓሮ እጀምራለሁ፡፡ ኮቪድ-19 እና እገዳው እንዴት ችግር መቋቋም እንዳለብን ጠቃሚ ትምህርት አስተምረውናል፡፡

ፊሊዩስ:
ትክክል ነው ወይዘሮ ምዋሌ፡፡ ከዚህ ሁኔታ እኔም ብዙ ተምሬያለሁ፡፡ ለምሳሌ የግብርና ሥራ ማለት አርሶአደሮችን ብቻ ሳይሆን ከገበሬዎች የሚገዙትን ነጋዴዎች እና ከእነሱ የሚገዙትን እንደርሰዎ ያሉትን ሸማቾች እንደሚጨምር ስለተረዳሁ ፕሮግራሜን ማስፋት አለብኝ፡፡

እንደርሰዎ ያሉ ሰዎች በትንሹ የጓሮ አትክልት እንዲያመርቱ ማበረታታትንም ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ወይዘሮ ምዋሌ የሚቀጥለውን የግብርና የንግድ ሥራ ነው ፕሮግራም በብሪዝ ኤፍኤም ይጠብቁ፣ ምክንያቱም በቅርቡ እርሶ ከኔ ኮከቦች አንዷ ይሆናሉ!

የድምጽ ኢፌክት:
ሙዚቃዊ መሸጋገርያ

ፊሊዩስ:
አድማጮች ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙ ችግር እንዳመጣ እሙን ነው፤ ይህንን ፕሮግራም በምንቋጭበት ሰኣት ለችግሩ በቅርብ የሚታይ መፍትሄ የለም፡፡ በርግጥ አርሶአደሮች፣ የግብርና ምርት አከፋፋዮች እና ሸማቾች ችግሩን እንዴት እየተቋቋሙት እንደሆነ አንዳንድ ሃሳቦችን አይተናል፡፡ ቢሆንም ጭንቁ ይበዛል፡፡

በዚህ ፕሮግራም የተነሱ አንዳንድ ችግሮችን ለመፍታት ምናልባት አርሶ አደሮች እና የከተማ ነዋሪዎች በጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ቁጥጥር በሚደረግበት ከጀርም በጸዳ አካባቢ ሊገናኙ ይችላሉ፡፡ የጤና ባለስልጣናት ለምርመራ እና የቅርብ ንክኪን ፈልጎ ለማግኘት የሙቀት መለኪያዎች ይኖሯቸዋል፡፡

ሌላው አሳሳቢው ጉዳይ ውሃ ነው፡፡ በገጠር የሚኖሩ ብዙ አርሶ አደሮች በቫይረሱ እንዳይያዙ እጃቸውን የሚታጠቡበት ውሃ በቀላሉ አያገኙም፡፡ እንድያውም እጃቸውን ቶሎ ቶሎ የመታጠብ እና የማህበራዊ መራራቅን አስፈላጊነትንም አያውቁትም፡፡

ያም ሆኖ አርሶ አደሮች በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ድህነትን እና ረሃብን ለማጥፋት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተባበሩት መንግስታትን የዘላቂ ልማት ግቦች ለማረጋገጥ ቁልፍ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ስነምግብን ለማሻሻል እና ግብርናን ይበልጥ ዘላቂ ለማድረግ የአርሶ አደሮችን አስተዋጽኦ መደገፍ አለብን፡፡

ኮቪድ-19 እውነተኛ ችግር እንደሆነ አስታውሱ፡፡ ስለዚህ ደህንነትዎን ለመጠበቅ የመቆጣጠርያ እርምጃዎችን ሁሉ ጠብቁ፡፡ በተጨማሪም ችግሩን ለመቋቋም የተቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ እንደጠቀስኩት አርሶአደሮች ድህነትን እና ረሃብን ለማጥፋት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ሊኖራቸው ይችላል፡፡

Acknowledgements

ምስጋና:

የጽሑፉ አዘጋጅ፡- ፊሊዩስ ቻሎ ጄሬ፣ ግብርና የንግድ ሥራ ነው አዘጋጅ፤ ብሪዝ ኤፍኤም፣ ቺፓታ፣ ዛምቢያ
የጽሑፉ ከላሽ፡- ኤሊዛቤት ዊልሰን፣ ጋዜጠኛ እና የተግባቦት ባለሙያ

Information sources

የመረጃ ምንጮች

ቃለ መጠይቆች:

ካምቦሊ ካንያንታ፣ የግብርና ኢኮኖሚስት፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ ቺፓታ፣ ዛምቢያ፣ ሚያዚያ 2020
ግሬቫዚዮ ባንዳ፣ የአትክልት አርሶ አደር፣ ካዉዙ ሰፈራ አካባቢ፣ ቺፓታ፣ ዛምቢያ፣ ሚያዚያ 2020

ወይዘሮ ሚሪያም ምዋሌ፣ የቤት እመቤት፣ CS 19, ኦልድ ጂም የመኖርያ ሰፈር፣ ቺፓታ፣ ዛምቢያ፣ ግንቦት 2020
ይህ ጽሑፍ በግሎባ አፌይርስ ካናዳ በኩል ከካናዳ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡