ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ቁልፍ ቃላት ትርጉም

Script

Save and edit this resource as a Word document

ከ2020 መጀመርያ አካባቢ ጀምሮ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮችን ጨምሮ በአለም ዙርያ ተሰራጨቷል፡፡ እንደማንኛውም የጤና ችግሮች ስለኮቪድ-19 ሲወራ አንዳንድ የሚጠቀሱ ስሞች አሉ፡፡ እነዚህ ስሞች የራሳቸው ትርጉሞች አሏቸው፡፡ የገጠር የራዲዮ ጋዜጠኞች እና አድማጮቻቸው የቫይረሱን ባህሪ እና እራሳቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ስለነዚህ ቃላት የጋራ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ቁልፍ ስሞች በሁሉም ተቀባይነት ያለው ትርጓሜ ከሌላቸው በስተቀር ማደናገር እና የተሳሳተ መረጃ ማስተላለፍ ሊፈጠር ይችላል፡፡

ከዚህ በታች ጤና ባለሙያዎች እና ሌሎችም ስለኮቪድ-19 ሲያወሩ የሚጠቀሙባቸው 41 በጣም የሚደጋገሙ እና አስፈላጊ የሆኑ ቃላት ተዘርዝረዋል፡፡

1. አንቲባዮቲክ / Antibiotic ጀርሞችን የሚገድል መድሃኒት

2. አሲምፕቶማቲክ/Asymptomatic የበሽታ ምልክት የማያሳይ

3. የተመጣጠነ ምግብ / Balanced diet ሰውነትን ለመጠበቅ እና የተስተካከለ ተግባር እንዲኖረው የሚያስፈልጉ ሁሉም ይዘቶች ያሉት የበለጸገ እና የተለያየ ምግብ\

4. መከላከያ እርምጃዎች/Preventive measures በበሽታው ላለመያዝ የሚረዱ እርምጃዎች

5. ለስላሳ/Benign ገር፣ ጉዳት የሌለው፣ ከባድ ያልሆነ

6. የሕክምና ፍተሻ / Clinical testing በአዲስ መድሃኒት ላይ የሚደረግ ምርምር

7. የተረጋገጠ ኬዝ / Confirmed case ተመረምሮ በሽታው የተገኘበት ሰው

8. ንክኪ የነበራቸው ሰዎች / Contact persons ቫይረሱ ከነበረበት ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች

9. ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ፍለጋ / Contact tracking ቫይረሱ የተገኘበት ሰው ከመታመሙ በፊት በቅርብ ንክኪ የነበራውቸን ሰዎች መለየት

10. ወረርሽኝኝ መገደብ/Containing an epidemic ወረርሽኝን ማቆም፣ ማገድ፣ ወይም መቆጣጠር

11. ኮቪድ-19 / COVID-19 የአሁኑ የኮሮናቫይረስ በሽታ ስም

12. የተነጠለ የበሽታ ምልክት / Discrete symptom በርግጠኝነት መለየት የማይቻል፣ እራሱን በግልጽ የማያሳይ ምልክት

13. ከጀርም ማጽዳት / Disinfect ጤነኛ ማድረግ፡፡ በሽታ የሚሸከሙ ጀርሞችን ማጽዳት፣ ማስወገድ

14. የመረጃ ማደናገር / Disinformation ውሸት የሆነ መረጃን፣ ታስቦበት ወይም ታቅዶበት ያልተረጋገጠ መረጃን ማሰራጨት

15. ዲስፕኒያ / Dyspnea የመተንፈስ ችግር፣ ትንፋሽ ማጠር

16. የድንገተኛ ጊዜ እቅድ / Emergency plan በአሁኑ ሰኣት አገራችን እያለፈችበት እንዳለው የኮቪድ-19 ሁኔታ አይነት ጊዜ ላልተጠበቁ ሁኔታዎች የሚወጣ እቅድ፡፡ የድንገተኛ እቅድ የወረርሽኙን ተጽእኖ ለመቀነስ እና ሁኔታውን ወደነበረበት መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስፈልጉ እርምጃዎችን ይዘረዝራል፡፡

17. ወረርሽኝ / Epidemic ብዙ ሰዎችን ባንድ ጊዜ እና ባንድ ቦታ ላይ የሚያጠቃ በሽታ

18. ጤናማ አመጋገብ / Healthy eating የሰውነትን ትክክለኛ አሰራር የማይጎዳ ወይም የማይረብሽ ምግብ

19. የውሃ እና አልኮሆል ውህድ / Hydro-alcoholic solution ውሃ እና አልኮሆል የተቀላቀለበት ፈሳሽ

20. የግል ንጽህኛ ልማዶች / Hygienic practices ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ድርጊቶች

21. በሽታ የመከላከል ስርኣት / Immune system ሰውነት እራሱን ከውጫዊ በሽታ አምጪ ህዋሳት ለመከላል የሚጠቀምበት ስርአት

22. ከበሽታ የመከላከል ችሎታ / Immunity የሰውነት እራሱን ከበሽታ የመከላከል ችሎታ

23. የመባዣ ጊዜ / Incubation period ቫይረሱ ከያዘበት በሽታ እስከሚጀምርበት ድረስ ያለው ጊዜ

24. መበከል / Infect በበሽታ መበከል ወይም ማስያዝ

25. ወደ ውስጥ መተንፈስ / Inhale በትንፋሽ ጋዝን ወደ ሳምባ ማስገባት

26. ከቤት አለመውጣት / Lockdown በኮቪድ-19 የበሽታውን ስርጭት ለመገደብ ሲባል ቤት ውስጥ መቆየት እና ከቤት አለመውጣት ማለት ነው፡፡ በመንግስት ባለስልጣናት የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡

27. የማኔጅመንት መመርያ / Management guidelines የጤና ሚንስቴር የበሽተኞች ሕክምና መመርያ

28. የአፍንጫ መደፈን / Nasal congestion አፍንጫ በተጠራቀመ ፈሳሽ ሲደፈን፡፡ የአፍንጫ መደፈን ስሜት

29. የወረሽኝ ክስተት / Outbreak of disease ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በድንገት መጨመር

30. አለም አቀፍ ወረርሽኝ / Pandemic በሰፊ የዐለም ክፍል ወይም በብዙ ክፍለ አለማት አብዛኛውን ሕዝብ የሚያጠቃ ወረርሽኝ

31. በሽታ አምጪ ተህዋስ / Pathogen በሽታ የሚያመጣ ተህዋስ

32. ስርጭት / Propagation መስፋፋት፣ መበተን፣ መጨመር

33. ቀሳ / Quarantine ለተወሰነ ጊዜ ከሰው ተለይቶ መቀመጥ

34. ራስን ከሰለው መለየት / Self-confinement ግለሰቡ ሌሎችን ለጉዳት ወይም ለበሽታ ላለማጋለጥ በራሱ ውሳኔ ቤት ውስጥ ሲቆይ

35. ማህበራዊ እርቀት / Social distancing አንድ ሰው ከሌሎች ሰዎች እራሱን የሚያርቅበት እርቀት

36. ማሰራጨት / Spreading ማሰራጨት፣ መበተን፣ ማስፋፋት

37. አድልኦ እና መገለል / Stigmatize መውቀስ፣ ጥፋተኛ ማድረግ፣ መተቸት፣ መክሰስ

38. በሽታው እንዳለበት የሚጠረጠር /Suspected case የበሽታው ምልክት ታይቶበት መመርመር ያለበት ሰው

39. የበሽታ ምልክት / Symptom የአንድ በሽታ መገለጫ የሆነ ምልክት

40. ሲንድሮም / Syndrome የአንድ በሽታ መገለጫ የሆኑ ምልክቶች ስብስብ

41. ምርመራ / Test ለበሽታው ምርመራ ለማድረግ ከአንድ ሰው ናሙና መውሰድ

Acknowledgements

ምስጋና

የጽሑፉ አዘጋጅ፡- አዳማ ዞንጎ፣ አማካሪ፣ የራዲዮ አሰልጣኝ፣ የቲያትር ደራሲ እና አዘጋጅ

የጽሑፉ ገምጋሚ፡- የሊዮ ጤና ዲስትሪክት (ሲሲሊ ፕሮቪንስ) ቺፍ ሜዲካል ኦፊሰር እና ዶ/ር ሌአንድሬ ኮሚ የባሰኩይ/ዋጋዱጉ ጤና ዲስትሪክት ቺፍ ሜዲካል ዶክተር፣ ቡርኪና ፋሶ

ይህ ጽሑፍ በግሎባላ አፌይርስ ካናዳ በኩል ከካናዳ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጀ፡፡