ስለ... የሬዲዮ ስክሪፕቶችን እያነበብክ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ለመለማመድ የሚያስፈልጉ የአርሶ አደር ስትራቴጂዎች

ጥቅምት 2, 2020

አቅራቢ 1: እንደምን አደራችሁ አድማጮቻችን አቅራቢ 2: አዎ ሁላችሁም እንደምን አደራችሁ፡፤ ስለአየር ንብረት ለውጥ መችም ሳትሰሙ አትቀሩም፡፡ አቅራቢ 1: (ይስቃል) እንዴት አይሰሙም፡፡ ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥ እለታዊ ሃቅ ነው፡፡ ያለተጠበቁ ዝናባማና ደረቅ ወቅቶች እንዲሁም ጎርፍ እና ድርቅ ደጋግመው ያጋጥሟቸዋል፡፡ አቅራቢ 2: አዎ ትክክል ነው፡፡ ያንን ታሳቢ አድርገን የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን ከተለዋዋጭ የአየር ሁኔታ…