የተጠቆሙ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች፦ በኮቪድ-19 ክትባት ዙሪያ መረጃዎች እና የመከላከያ መንገዶች

ጤና

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ለስርጭት ባለሙያዎች ማስታወሻ

እነዚህ ጥያቄዎች የተነደፉት የስርጭት ባለሙያዎች እንደ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ የማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካዮች ካሉ የኮቪድ-19 ባለሙያዎች ጋር ቃለ መጠይቅ እንዲያደርጉ ይረዷውኣል። ጥያቄዎችቹ የተነደፉት የስርጭት ባለሙያዎ ች የኮቪድ-19 ክትባቶችን አሰራር፣ ውቴታማነታቸውን፣ ሊያስከትሉት ስለሚችሉት የጎንዮሽ ህመም፣ እንዲሁም ከተከተቡ በኋላ በሽታውን ለመከላከል ሊወሰዱ ስለሚገቡ እርምጃዎች በሚመለከት መረጃዎችን የስርጭት ባለሙያች በፕሮግራማቸው አማካኝነት አየር ላይ እንዲያውሉ እንዲረዳቸ ውበማሰብ ነው።

ቃለ መጠይቁን ሲያቅዱ፣ ከተጠያቂ(ዎች) ጋር ለመወያየት እንዲረዳ ከሦስት እስከ አምስት ጭብጥ ሃሳቦችን መርጦ ማዘጋጀቱ ጥሩ ነው። ጭብጡን በጥልቀት ለመመርመር እና ለአድማጮችዎ የሚፈልጉትን መረጃ ለመስጠት ሲባል የተወሰኑ ወይም ሁሉንም ከጭብት ሃሳቦቹ ጋር ተዛማች የሆኑ ጥያቄዎችን ይጠይቁ። የቃለ መጠይቁን ወሰን መገደቡ አድማጮችዎም ሆኑ ተጋባዥ እንግዶችዎ መረጃ ከመጠን በላይ እንዳያጨናንቃቸው እና ትኩረት መስጠታቸውን እንዳያቆሙ ያደርጋል።

ስለዚህ ርዕስ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመሸፈን ከፈለጉ ከአንድ ተጋባዥ እንግዳ ጋር ወይም በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን በጥልቀት ማጋራት ከሚችሉ ሰዎች ጋር ተከታታይ ቃለመጠይቆችን ያዘጋጁ። ጥሩ ቃለመጠይቆች በንቃት ማዳመጥን እንዲሁም ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ያስታውሱ። እነዚህን ጥያቄዎች ለውይይትዎ እንደ መመሪያ ይጠቀሙ ነገር ግን ውይይቱን የሚመራበትን ቦታ የሚያመራበትን ለመከተል እንዲረዳ በነዚህ ብቻ አይወሰኑ።

በእነዚህ ውይይቶች ወቅት ዋና ዋና ልማዳዊ አባባሎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊነሱ ይችላሉ። እነዚህን ከተጋባዥ እንግዳዎ ጋር እና በማህበረሰብዎ ውስጥ ታዋቂ የሆኑ ሌሎች ልማዳዊ አባባሎች ላይ ማወያየት እና አስተሳሰቦቹ መሻራቸውን ያረጋግጡ።

በመጨረሻም፣ ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች በውይይትዎ ወቅት የሚወጣው መረጃ ቴክኒካል እና ሳይንሳዊ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም አድማጭ ሊረዳው በሚችለው ግልጽ እና ቀላል ቃላት ቴክኒካል ፅንሰ-ሀሳቦችን እንዲያብራሩ ተጋባዥ እንግዳዎን ሁል ጊዜ ይጠይቁ። እንግዳዎ የተወሳሰበ ወይም ቴክኒካል ቃላትን ከተጠቀሙ እንዲያብራሩት ይጠይቋቸው – ሃሳቡ ለእርስዎ ግልጽ ቢሆንም አድማጮችዎ ላይረዱት ይችላሉ።

Script

1. ኮቪድ-19ን ለመዋጋት በአፍ ከሚወሰዱ የተለመዱት መድሃኒቶች ይልቅ ለምን ክትባትን ማዘጋጀት ተፈለገ?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ክትባትን ማዳበሩ መድሃኒትን ለማዘጋጀት ከሚወስደው ጊዜ እና ክብደት አንጻር የተሻለ አማራጭ ነው?

a.i.1. የኮቪድ-19 ክትባቱን ለማዳበር ምን ያህል ጊዜ ፈጀ?

ሀ. የኮቪድ-19 ክትባቱ እንዴት በፍጥነት ሊዳብር ቻለ?

a.ii. በአሁኑ ወቅት ኮቪድ-19ን ለማከም የሚረዱ ወይም በሽታውን የሚከላክሉ መድሃኒቶች አሉ?

a.ii.1. መልሱ አሉ ከሆነ በዚህ አካባቢ ይገኛሉ?
a.ii.2. መልሱ የሉም ከሆነ እነዚህ መድሃኒቶች በቅርቡ አቅርቦት ላይ ይገኛሉ ብለው ያምናሉ?

2. የኮቪድ-19 ክትባትን መከተቡ ምን ምን ጥቅሞችን ያስገኛል?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. በኮቪድ-19 በሽታ መያዙ ነው ወይስ የኮቪድ-19 ክትባቱን መውሰዱ ነው የበለጠ አደጋው የሚያመዝነው?

3. የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰዱ ሰዎችን እንዴት ነው ከበሽታው የሚታደጋቸው?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ክትባቱ ሆስፒታል መተኛትን፣ ከባድ ሕመምን ወይም በኮቪድ-19 ምክንያት ሞትን ከመከላከል አንጻር ምን ያህል ውጤታማ ነው?

a.ii. ሰዎች በኮቪድ-19 ከመያዝ ከመከላከሉ አንጻር ክትባቱ ምን ያህል ውጤታማ ነው?

a.iii. የኮቪድ-19 ክትባት ከበሽታው ለመከላከል ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል?

a.iv. አንዳንድ ሰዎች ክትባት ከተከተቡ በኋላም በኮቪድ-19 በሽታ እንደሚያዙ ሰምቻለሁ። ይህ ለምን ሆነ?

a.v. የኮቪድ-19 ክትባቱ በሁሉም የኮቪድ-19 ዝርያዎች ላይ ውጤታማ ነው? ለምሳሌ በዴልታ እና ኦሚክሮን?

a.vi. አሁን ኮቪድ-19 ኖሮብኝ የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ እችላለሁ?

a.vi.1. ከዚህ ቀደም ኮቪድ-19 ይዞኝ ያገገምኩ ከሆነ የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ እችላለሁ?

a.vi.2. አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 መያዛቸው ወደፊት በበሽታው እንዳይያዙ ያደርጋቸዋል ብለው ያስባሉ። ይህ አስተሳሰብ ትክከል ነው?

ሀ. ከዚህ በፊት ኮቪድ-19 ይዞት የሚያቅ ሰው ክትባቱን ሊወስድ ይገባል?

a.vii. አንድ ዙር የኮቪድ-19 ክትባት በቂ ነው ወይስ ከአንድ በላይ ያስፈልገኛል?

a.vii.1. ከአንድ በላይ ዙር የሚያስፈልገኝ ከሆነ፣ ከመጀመሪያው ዙር በኋላ ምን ያህል ጊዜ ቆይቼ ሁለተኛውን ዙር መከተብ አለብኝ?

a.vii.2. የማጠናከሪያ ክትባቶች ምንድን ናቸው?

ሀ. ማጠናከሪያ ክትባቶችን እነ ማን ሊከተቡ ይገባል?

ለ. የማጠናከሪያ ክትባትን መቼ ልወስድ ይገባል?

ሐ. የማጠናከሪያ ክትባቶች በዚህ አካባቢ ይገኛሉ?

4. የተለያዩ የኮቪድ-19 ክትባቶች አሉ እያንዳንዳቸው በተለየ ኩባንያ የተዘጋጁ ናቸው። አንድ ሰው የትኛውን የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ እንዳለበት እንዴት መምረጥ ይገባዋል?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ክፍያ አለው?

a.ii. አድማጮች በአካባቢያቸው የክትባት ማዕከል የት ማግኘት ይችላሉ?

5. አንድ ሰው የኮቪድ-19 ክትባት እንዳይወስድ ሊያደርጉት የሚችሉ የህመም ወይም የጤና ሁኔታዎች አሉ?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ለነፍሰ ጡር ሴቶች የኮቪድ-19 ክትባቱን መውሰድ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

a.ii. ጡት ለሚያጠቡ እናቶች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

a.iii. የኮቪድ-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላ ምን የጎንዮሽ ህመሞች ሊኖሩ ይችላሉ?

a.iii.1. እነዚህ የጎንዮሽ ህመሞች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ናቸው?

a.iii.2. የጎንዮሽ ህመሞች ካልተከሰቱብኝ ክትባቱ አልሰራም ማለት ነው?

a.iii.3. እንደየክትባቶቹ አይነት የጎንዮሽ ህመሞቹም ይለያያሉ?

a.iv. ስለ ኮቪድ-19 ክትባት በማህበረሰቡ ውስጥ እየተሰራጩ ያሉ የተሳሳቱ ልማዳዊ አባባሎች አሉ። ምን ዓይነት የተሳሳቱ አባባሎችን ሰምተዋል እንዴትስ እነዚህን አሳሳች አባባሎች ማስወገድ ይችላሉ?

a.iv.1. አንዳንድ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶች መካንነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ ብለው ይጨነቃሉ። እነዚህ ስጋቶች እውነትነት አላቸው?

6. የኮቪድ-19 ክትባት በኮቪድ-19 እንድያዝ ያደርገኛል?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. የኮቪድ-19 ክትባት ከተከተቡ በኋላ የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ሪፖርቶች አሉ። ስለዚህ ጉዳይ ምን አስተያየት አለዎት?

a.ii. የኮቪድ-19 ክትባት ከ65 አመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ክልሎች ለሚገኙ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

a.iii. ህጻናትና ታዳጊዎች የኮቪድ – 19 ክትባትን መከተባቸው ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

a.iv. ሌላ ህክምና ላይ ያለ ወይም ሌላ መድሃኒት እየወሰደ ያለ ሰው የኮቪድ-19 ክትባት ሊወሰድ ይችላል?

7. አንዳንድ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቶች ደኅንነታቸው ያጠራጥራቸዋል። ይህ ጥርጣሬያቸው ክትባቱ የዳበረበት ፍጥነትን እና በሚዲያ ላይ ያሉ ውጤታማነታቸው ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዘገባዎችን በሰሙ ቁጥር የበለጠ ይባባሳል። የኮቪድ-19 ክትባቶች ደህንነታቸው ያማያጠራጥር እንደሆነ በምን መልኩ ሊያረጋግጡዋቸው ይችላሉ?

8. ኮቪድ-19 እና የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት ወደፊት ምን ይጠበቃል?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ወደፊትም የኮቪድ-19 ክትባቶችን ማስፈለጋቸውን ይቀጥላሉ?

a.ii. ሰዎች መከተብ ያለባቸው የተወሰኑ ወራት ወይም ወቅቶች አሉ? ለምሳሌ ጉንፋን የሚበዛባቸው ቀዝቃዛ ወራት?

9. ከክትባት በተጨማሪ ግለሰቦች እና ማህበረሰቡ በኮቪድ-19 እንዳይጠቁ ምን አይነት ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ሰዎችን ከኮቪድ-19 ለመከላከል እና በሽታው ወደ ሌሎች እንዳይሰራጭ ምን አይነት የፊት መሸፈኛዎችን መጠቀሙ ውጤታማ ያደርገዋል?

a.ii. አንዴ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የሚጣል ጭንብልን ከተጠቀምኩ በኋላ ነገ ወይም ለተወሰኑ ቀናት ደግሜ ለጠቀመው እችላለሁ?

a.iii. የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እንደ ክፍል እና ውህዶች ባሉ በዝግ ስፍራዎች ውስጥ ባሉ ሰዎች በመካከላቸው ምን ያህል አካላዊ ርቀት መጠበቅ አለበት?

a.iv. ኮቪድ-19ን ለመከላከል ሰዎች እጃቸውን ምን ያህል ጊዜ መታጠብ ይኖርባቸዋል?

a.v. ከተከተብኩ በኋላም እነዚህን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰዱን መቀጠል አለብኝ? አዎ ከሆነ ለምን?

a.v.1. ጭንብል መጠቀም፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና ሌሎች ጥንቃቄዎችን እስከ መቼ ነው ነው መፈጸሙን የምንቀጥለው?

a.vi. ጤናማ አመጋገብና አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረግ ከኮቪድ-19 ሊጠብቀን ይችላል?

10. ሰዎች ለኮቪድ-19 የመጋለጥ እድላቸውን ከፍ የሚያደርጉ ህመሞች ወይም የጤና ሁኔታዎች አሉ?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. አዎ ከሆነ እነዚህ የጤና ሁኔታዎች ምንድናቸው?

a.ii. ሰዉን የበለጠ ተጋላጭ ለምን ያደርጉታል?

a.iii. እነዚህ በሽታዎች ወይም የጤና ሁኔታዎች ያሉባቸው ሰዎች ከኮቪድ-19 ራሳቸውን ለመከላከል ሊወስዷቸው የሚገቡ ልዩ እርምጃዎች አሉ?

a.iv. ከእነዚህ የጤና ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ያለው ሰው በኮቪድ-19 ሲታመም፣ ሥር የሰደደ ሕመም ከሌለው ሰው ጋር ሲወዳደር በተለየ ሁኔታ ያለው ተጽንዖ ምን ይመስላል?

a.v. በተለይ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሆኑት ሰዎችን ከበሽታው እንዴት መጠበቅ እንችላለን?

a.vi. እነዚህ የጤና ሁኔታዎች ወይም ሕመም ያለባቸውን ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባቱን መስጠቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው?

11. በተቻለ መጠን በርካታ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባትን መከተባቸ አስፈላጊ ሆኖ የተገኘው ለምንድነው?

ሀ. ተያያዥ ጥያቄዎች፦

a.i. ስለ ኮቪድ-19 ክትባቱ ጥርጣሬ ላላቸው አድማጮች ለመናገር የሚፈልጉት ነገር አለ?

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጅ፦ ጄምስ ካሩጋ፣ ጋዜጠኛ፣ ኬኒያ

ይህ ግብአት በካናዳ የአለም ጉዳዮች ካናዳ መንግስት በኩል በተደረገው የገንዘብ ድጋፍ የህይወት አድን፣ የህዝብ ጤና እና የክትባት ግንኙነት ከሳህራ በታች ባሉ አፍሪካ (ወይም ቫክስ) ፕሮጀክት አካል ነው።