English, Français

Script 105.13

Script

ውጤታማ የአርሶ አደር ፕሮግራም አቅራቢ ማለት ምን ማለት ነው?

ውጤታማ አቅራቢዎች የአርሶአደሩን አሰራር ለማሻሻል በሚያስችል ዘዴ ስብእናቸውን እና የስርጭት ሙያቸውን አቀናጅተው ይጠቀማሉ፤አየር ላይ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማቅረብም የአርሶአደሮችን እና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት እንዲሻሻል ያደርጋሉ፡፡ አቀራቢው ፕሮግራሙን ማራኪ እና በአድማጮች ዘንድ የማይረሳ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

በነገራችን ላይ፤ የአርሶአደር ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆኑ(ወይም አዘጋጅ እና አቅራቢ ከሆኑ) መመሪያዎችንን እዚህ ይመልከቱ /here “ውጤታማ የፋርም ሬድዮ ፕሮግራም ኣዘጋጅ የመሆን ዘዴ”/

ጥቆማ ለጣቢያ አመራሮች፡- በአንዳንድ ጣቢያዎች አመራሮች የተለያዩ አዘጋጆችን በአቅራቢነት የቀያይራሉ፡፡ ይህም ከአመራር አኳያ አዘጋጆች የተለያዩ ልምዶችን እንዲያገኙ ስለሚያስችል ሊያስኬድ ይችል ይሆናል፡፡ ከአድማጮች አኳያ ግን ብዙም የሚያስኬድ አይሆንም፡፡ አንድ አድማጭ ከአንድ የሬድዮ ፕሮግራም ጋር የሚኖረው ቁርኝት በቀዳሚነት ከአቅራቢው ጋር የተያያዘ ነው፡፡. አቅራቢው ውጤታማ ከሆነ አድማጩ ከአቅራቢው እና ከፕሮግራሙ ጋር ጠንካራ እና አዎንታዊ የሆነ የስሜት ትስስር ይገነባል፡፡ በአንፃሩ አቅራቢው ሁሌም የሚቀያየር ከሆነ አድማጩ ከፕሮግራሙ ጋር ያለው ግንኙነትም ይዳከማል፤ ጣቢያውም ሆነ ፕሮግራሙ ችግር ላይ ይወድቃል፡፡

አድማጮቼን በተሻለ መልኩ ለማገልገል ውጤታማ አቀራረብ እንዴት ሊረዳኝ ይችላል?

 • አርሶአደሮች ስለስራቸው ጠንቃቃ እና አዎንታዊ ሰሜት እንዲኖራቸው ለማገዝ እችላለሁ፡፡
 • አርሶአደሮች ድምፆቻቸውን እንዲያሰሙ እና እንዲያዳምጡ ማገዝ እችላለሁ፡፡
 • አርሶአደሮች ከንግግር ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ ማገዝ እችላለሁ፡፡

ውጤታማ አቅራቢ መሆን በምን መልኩ የተሻሉ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጀት ያስችለኛል?

 • ማዳመጥን እና መናገርን ያስተምረኛል፡፡
 • በግልፅ የመግባባትን አስፈላጊነት ትኩረት እንድሰጥበት ያደርገኛል፡፡
 • ቃለመጠይቆቼን እና ውይይቶቼን ማቀድ እንዳለብኝ ያረጋግጥልኛል፡፡
 • ማራኪ እና የማይረሱ የሬድዮ ፕሮግራሞች እንዳዘጋጅ ይረዳኛል፡፡

አስራሁለት ቁልፍ የአቀራረብ ስራዎች

 1. የጣቢያህ ፖሊሲዎችን አክብር፡፡
 2. አርሶአደር አድማጮችህን ተረዳ እንዲሁም አክብር፡፡
 3. የአድማጮችህን አመኔታ አግኝ፡፡
 4. በግልፅ ተግባባ፡፡
 5. የአድማጮችህ መመሪያ ሁን፡፡
 6. እውነታ ላይ የተመሰረተ ቅንነት አራምድ፡፡
 7. አርሶአደሮች ድምፃቸውን እንዲያሰሙ አግዛቸው፡፡
 8. ቃለመጠይቆችህን እና ውይይቶችህን አቅድ፡፡
 9. ጥሩ አድማጭ ሁን፡፡
 10. ከንግግር ወደ ተግባር መሸጋገርን አራምድ፡፡
 11. ፕሮግራምህን ሳቢ እና የማይረሳ መሆኑን እርግጠኛ ሁን፡፡
 12. ግብረመልስህን እየተጠቀምክ አሻሽል፡፡

ዝርዝር
የጣቢያህ ፖሊሲዎችን አክብር፡፡

ጣቢያዎች አዘጋጆች አድማጮቻቸውን በጥራት ለማገልገል በሚያስችል መንገድ የሚመሩበት ፖሊሲ ሊኖረቸው ይችላል፡፡ ስራዎችህ በሙሉ የጣቢያህን ፖሊሲዎች የጠበቁ መሆን አለባቸው ስለሆነም ከስራዎችህ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ፖሊሲዎችን በትክክል መገንዘብ ይኖርብሃል፡፡(ለምሳሌ ያህል ለገጠር ፋርም ሬድዮ ጣቢያዎች የሚውል በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የተዘጋጀ ፖሊሲ ቀጥሎ ይመልከቱ፡፡ (እነዚህ ቮይስ እና ፌይር የተሰኙት የፕሮግራም ደረጃዎች እና የፕሮግራም ዓላማ መግለጫን ያካትታሉ፡፡)

አንድ ፖሊሲ ለአርሶአደር አድማጮችህ ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትIአጋዥ መስሎ ከታየህ ከአመራርህ ጋር ተወያይበት ፡፡ ምናልባት መብራሪያ መስጠት ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡ አልያም ጣቢያህ ፖሊሲውን መልሶ ለማየት ሊስማማ ይችላል፡፡

አርሶአደር አድማጮችህን ተረዳ እንዲሁም አክብር፡፡

አነስተኛ ደረጃ አርሶአደሮች ለበርካታ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በበርካታ አካባቢዎች የአፈር ይዘት የተሟጠጠ መሆን ፤ በየገዜው የኣየር ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መዛባት እና አባዛኞቹ የተሰበሰቡ የሰብል ምርቶች ገበያ ከመድረሳቸው በፊት መባከናቸው ተጠቃሽ ናቸው፡፡ መማር ከቻልክ እና የአርሶአደር አድማጮችህ ችግሮቻቸውን መገንዘብ ከቻልክ ይበልጥ ውጤታማ አርሶ አደሮች እንዲሆኑ ለማድረግ ግማሽ መንገድ ላይ ደርሰሃል ማለት ነው፡፡

ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ የአርሶ አደሮችን ማሳዎች እና የአትክልት ቦታዎቻቸውን ለመጎብኘት ሞክር፡፡ ወንድ እና ሴት አርሶ አደሮችን የመጠየቅ ልምድ ይኑርህ፡፡ ለምሳሌ:

 • ከባለፈው ጋር ሲነፃፀር ቤተሰበችህን/ሽን ምን ያህል በደምብ ትመግባለህ/ትመግቢያለሽ?
 • ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የሰብል ማሳዎች ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?
 • የማሳ ምርታማነትን ለማሻሻል ምን ታደርጋለህ/ታደርጊያለሽ?
 • ገበያላይ የምታገኚያቸው የምርት ግብአቶች ዋጋ ምን ያህል ፍትሃዊ ናቸው?
 • በእርሻ ስራ የሚያጋጥሙህ/ሽ ትልልቅ ፈተናዎች ምን ምን ናቸው?

አየር ላይም አርሶ አደሮችን አክብር፡፡ ለምሳሌ ምርት ከተሰበሰበ በኋላ በሚያጋጥም ብክነት ዙሪያ የሚደረግን ውይይት ለማስተዋወቅ የሚከተለውን እንደ አንድ ኣራጭ መጠቀም ይቻላል፡፡

“ዛሬ በአቡጃ ዩኒቨርሲቲ የሰብል ሳይንስ ሀላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ጆን ዙማ ከእኛ ጋር ናቸው፡፡.የበቆሎ (አያያዝን) አቀማመጥን አስመልክቶ ከሶስት የአካባቢያችን አርሶ አደሮች ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ይሰጡናል”

ሌላ ዘዴም ቀጥለን እንይ

“ዛሬ ሁሉም ምርታችሁ ለገበያ እንዲበቃ በበቆሎ ምርት ኣያያዝ ላይ ያለውን ችግር እንታገለዋለን፡፡ ሱዛን ቻኮ ዞንጋ መንደር አጠገብ ሁለት ሄክታር ቦቆሎ ዘርታለች፡፡ ባለፈው ዓመት ጠቅላላ የቦቆሎ ምርቷ ጤናማ ሆኖ ለመሸጥ በቅቷል፡፡ ፕሮፌሰር ጆን ዙማ በአቡጃ ዩኒቨርሲቲ የሰብል ሳይንስ ሀላፊ ናቸው፡፡ ዊልያም ቡላዎ አንድ ሄክታር ቦቆሎ ይዘራል ሆኖም ግን ባለፉት ሁለት የምርት ወቅቶች ምርቱ በተባይ ሳቢያ ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ እናም ሜሪ ጌቾ ክዋማሉ ውስጥ ለበቆሎ ምርቷ አዲስ የጎተራ ዲዛይን ስታፈላልግ ቆይታለች፡፡”

ልዩነቱ በሁለተኛው ምሳሌ አርሶ አደሮቹ የዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ለውይይቱ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው መተዋወቃቸው ላይ ነው ፡፡ ይህም ትልቅ አክብሮትን ይገልፃል፡፡

በመጨረሻም ስሞችን እና ቦታዎችን በትክክል እወቅ፡፡ የአካባቢ መንደሮችን ወይም የሰዎችን ስም በተደጋጋሚ አሳስቶ የመጥራትን ያህል ክብርን የሚያጓድል ነገር የለም፡፡ ማስተካከያ ሲሰጥም ይቅርታ በመጠየቅ ጭምር አስተካክል፡፡

1) የአድማጮችህን አመኔታ አግኝ፡፡

አድማጮች ከሬድዮ አቅራቢዎች ጋር ግንኙነት እስኪገነቡ ድረስ ያድማጮችን አመኔታ ማግኘት ያስፈልገል፡፡አመኔታ ቀስ በቀስ የሚገነባ እና በርካታ ሃሳቦች እና ተግባራትን የሚጠይቅ ሂደት ነው፡፡

ለምሳሌ ከባለስልጣን ወይም ከባለሙያ ጋር ቃለመጠይቅ ስታካሂድ እየሰሩ ባሉበት መልካም ስራ ላይ እንዲያተኩሩ አታድርግ፡፡ ይልቁንም አርሶ አደሮች ሊመለሱላቸው የሚፈልጉዋቸው ጥያቄዎችን ጠይቅ፡፡ (Click here to see our guide: “How to hold officials to account.”) በዚህ ሁኔታ አድማጮችህ ድምፃቸውን እንደምታሰማላቸው ያረጋግጣሉ፡፡

አመኔታን ማግኘት የአንተን ታማኝነት ይጠይቃል፡፡ በየሳምንቱ ከአድማጮችህ ጋር ነህ? የአየር ሁኔታ እና የገበያ ሁኔታ ዘገባ በመደበኛነት ታቀርባለህ? ታሪኮችን ለማቅረብ በቃልህ መሰረት ትገኛለህ? በቀጣይ ሳምንት አንድን መንደር እንደምትጎበኝ ቃል ከገባህ እንደምታደርገው እርግጠኛ ሁን፡፡

የሰራኸውን ስህተት በግልፅ ማሳወቅም ተገቢ ይሆናል፡፡ በእርግጥ ሁሌም እርግጠኛ እና እውነተኛ ለመሆን ትሞክራለህ ሆኖም ግን አየር ላይ ስህተት ይፈጠራል፡፡ በሚቀጥለው ክፍል ”ባለፈው ፕሮግራም በዶላ እና በታንገር መካከል የመንገድ ማሻሻያ ስራው አልተጀመረም ብዬ ነበር ሆኖም ግን የጥገና ስራዎች ሰኔ 15 መጀመራቸውን እና መስከረም ላይ ይጠናቀቃሉ ተብሎ አንደሚጠበቅ ተረጋግጧል” በማለት ስህተትህን ማረም ታማኝነትህን ከፍ ያደርገዋል፡፡.

በግልፅ ተግባባ፡፡

አድማጮችህ አልተረዱህም ማለት ከአድማጮችህ ጋር በትክክል አልተግባባህም ማለት ነው ፡፡ይህ በተለየ በአርሶ አደሮች ፕሮግራም የሚያጋጥም ፈተና ነው ምክንያቱም በአርሶ አደር ፕሮግራሞች ውስብስብ የሆኑ ሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊ ስያሜዎችን መጠቀም ግድ ስለሚሆን ነው፡፡ አንድ ቃለመጠይቅ ሰጪ ስለ አፍላቶክሲን ማውራት ቢጀምር “ይህ ለእኔ አዲስ ቃል ነው አፍላቶክሲን ምን ማለት እንደሆነ ታብራራልኝ?” በማለት ጠይቅ ፡፡ እንደዚሁም ውይይትህ ቴክኒካዊ በሆኑ አባባሎች ከታጨቀ ዋና ዋና ነጥቦችን ለይተህ ግልፅ ማብራሪያ ስጥ፡፡

አየር ላይ ለማነጋገር ከምትፈልጋቸው አርሶአደሮች መካከል የተወሰኑት ከአነጋገር ዘዴያቸው ወይም ዓይነ አፋር ከመሆናቸው የተነሳ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን አርሶ አደሮች ነጥቦቻቸውን በግልፅ እንዲተላለፉ ለማድረግ ክብራቸውን ሙሉ በሙሉ በመጠበቅ እገዛ አድርግላቸው፡፡ ለምሳሌ እንዲህ በማለት እንዲያራሩልህ አድርግ፡- “አቶ ዙምባ ሙሉ መልዕክቶን አልሰማሁትም እባክዎትን ቢደግሙልኝ ?” ወይም “አቶ ዙምባ ስለ ማጠራቀሚያ ዕቃ አንስተዋል ሆኖም ግን የተሻለው ከጭቃ ወይስ ከብረት የተሰራው ነው”

የፓነል ውይይት ከተወሳሰበ በቃለ አጋኖ ድምፀት እንደሚከተለው መልሰው፡ “አንዴ ቆዩ!እኔ ምናልባትም የተወሰኑ አድማጮችም አልያዝናችሁም ይህ ሁሉ ባሞኖ መንደር ውስጥ ቦቆሎ ለሚያመርት አንድ አምራች የለው ትርጉም ምንድነው ?”

የተወሳሰቡ ቁጥሮች ሬድዮ ላይ በግልፅ ለመግባባት አስቸጋሪ መሆኑንም አስታውስ፡፡ ቁጥሮች አርሶ አደር ሊያስታውሰው በሚችል በስዕላዊ መልኩ አይቀየሩም ፡፡ ለምሳሌ፡- ቀጣዩን ይዘት በአድማጮች ዘንድ ለማስታወስ አስቸጋሪ ነው “ገመዶችህን በአንድ ነጥብ አምስት ሜትር አራርቃችሁ አስቀምጡ፡፡ ቀጥሎ በየሰላሳ ሴንቲሜትሩ ጉድጓዶች በመቆፈር ሁለት ሁለት ዘሮችን ጨምሩባቸው” ቁጥሮችን የግድ መንገር ካለብህ በተቻለ መጠን ግልፅ ለማድረግ ሞክር፡፡ ታሪኩን በምታቀርብበት ጊዜ ቁጥሮችን ቢያንስ ሁለት ጊዜ አስተዋውቅ፤ በፕሮግራሙ በስተመጨረሻም ደግመህ አስታውስ፡፡

የአድማጮችህ መመሪያ ሁን፡፡

ፕሮግራም በምታቀርብበት ጊዜ ዋናው አቅራቢ ብቻ አይደለህም በንግግርህ አድማጮችህን ትጋብዛለህ፤ ታሳያለህ ፤ ታወራቸዋለህ፤ ትመግባቸዋለህ፤ እንዲሁም በራሳቸው መንገድ ታስተላልፍላቸዋለህ፡፡

ይህ በሚከተለው መንገድ ይተገበራል:-

 • መጀመሪያ ላይ ሰላምታ በማቅረብ
 • የፕሮግራሞችህን ይዘት በማስተዋወቅ
 • ከፕሮግራሙ ጋር የት እንደሆኑ በመጠቆም እና ቀጥሎ ም ላይ እንደሚያተኩሩ በማሳወቅ
 • የተወሳሰቡ ነጥቦችን በማብራራት
 • ለማዳመጣቸው በማመስገን እና
 • ቀጣዩን ፕሮግራም በማስተዋወቅ

(Click here for our guide “ጀሮን የሚይዙ የፕሮግራም ማስታወቂዎች፣ መግቢያ እና መውጫዎችን አዘገጃጀት”)

አብዛኛዎቹ አድማጮችህ እቤታቸው ውስጥ ብቻቸውን ወይም ከአንድ ወይም ከሁለት ሰዎች ጋር ሊሆኑ ይችላሉ፡፡አድማጮችህ ጋር ስትደርስ በአእምሮህ ውስጥ አንድ የሚያደምጥህን ሰው አስቀምጥ እናም በቀጥታ ከእርሱ ጋር እንደምታወራ ሁን፡፡ ለምሳሌ፡-በል “መች እንዝራ በሚል ሀሳብ ላይ እንደሆናችሁ አውቃለሁ ስለዚህም የኤክስቴንሽን ሰራተኛችንን ለዛሬ አምጥቼላችኋለሁ፡፡ አስፈላጊ መረጃዎችን ይነግራችኋል፡፡ ” አትበል: “ይህ አርሶ አደሮች ዘር መዝራት ስለሚጀምሩበት ጊዜ የሚያስቡበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም የኤክስቴንሽን ወኪላችን ለአርሶ አደሮች ጥሩ ሀሳቦች አሉት”

እውነታ ላይ የተመሰረተ ቅንነት አራምድ፡፡

ከፍ ሲል እንደተገለፀው የአነስተኛ መጠን አርሶ አደሮች ስራ ፈተናዎች የበዙበት እና ሁኔታዎች ተስፋ አስቆራጭ የሚመስሉበት ወቅቶችም ያሉበት ነው፡፡በአንፃሩ የአርሶ አደር ፕሮግራምህ አርሶ አደሮች በግልም ሆነ በቡድን አዎንታዊ ለውጦችን ለመፍጠር ፤ የቤተሰቦቻቸውን እና የማህበረሰቦቻቸውን ህይወት ለማሻሻል የሚያስችላቸው ስሜት መፍጠር አለበት፡፡

የአርሶአደር አደር ፕሮግራሞች ገለልተኛ አይደሉም ፡፡ ለአነስተኛ አርሶ አደሮች የሚወግኑ ናቸው፡፡ ይህ ማለት የማያሳስቡ ናቸው ማለት አይደለም፡፡ በአርግጥ የአየር ሁኔታ ለውጥ፤ ዝቅተኛ የአፈር ይዘት፤ እና የብድር እጥረት የመሳሰሉ የአርሶ አደሮች ዋና ዋና ችግሮችን አንስቶ ማወያየቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ችግሮች የሚነሱበት አግባብ አርሶ አደሮች እርሻቸውን እና ህይወታቸውን ለማሻሻል ከሚችሉበት አጠቃላይ አቅጣጫ ጋር በማስተሳሰር ሊሆን ይገባል፡፡

ነገሮች ከባድ በሚሆኑበት ጊዜም ትክክለኛ የመፍትሔ መንገዶች አሉ፡፡ ለምሳሌ እንበል ወደ ገበያዋ ከተማ የሚወስደው መንገድ በከባድ ዝናብ ሳቢያ ጎድጓዳ ሆኗል፤ መንግስት እንዲሰራው ቃል የገባ ቢሆንም፡፡ አርሶ አደሮቹ ቦቆሎአቸውን ወደ ገበያ ለማቅረብ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ቅሬታ አየር ላይ ማቅረብ ትፈልጋለህ፡፡ ሆኖም ግን ቦቆሎ ወደ ገበያ እስኪጓጓዝ እንዴት መያዝ እንዳለበት የሚያስተምሩ ታሪኮችንም ማቅረብ ትችላለህ፡፡ በተጨማሪም የመንገዱ ጥገና መቼ እንደሚጀመር ለአርሶ አደሮቹ እስኪገለፅ ድረስ በየሳምንቱ ወደሚመለከታቸው የመንግስት አካላት መደወል ይቻላል፡፡

ይህ አጠቃላይ የአዎንታዊ ስሜት በቅድሚያ የሚቀርበው በአንተ በፕሮግራሙ አቅራቢ ነው፡፡ ከፕሮግራሙ መግቢያ በቃለመጠይቆች እስከ መጨረሻዋ ቃል ድረስ የአርሶ አደሩ ፕሮግራሙን የምትቃኘው አንተው ትሆናለህ፡፡

አርሶአደሮች ድምፃቸውን እንዲያሰሙ አግዛቸው፡፡
ጥሩ የግብርናፕ ሮግራም ሁለት ዓላማዎች አሉት፡፡ ለአርሶ አደሮች ሁለት ጥቅሞችን ይሰጣል:

 • የሚፈልጉትን መረጃ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ እና
 • ለእነርገሱ ስላለው አስፈላጊነት የመናገር ዕድልን

ሁለተኛው ዓላማውም የመጀመሪው ያህል አስፈላጊ ነው፡፡

ከፍ ሲል እንደተገለፀው , አርሶ አደሮች እንደ አስተማሪዎች ፣ ጠበቆች ወይም እንደ ጋዜጠኞች ህዝብ ፊት ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲናገሩ ጊዜኣቸውን የሚያጠፉ አይደሉም፡፡ አርሶ አደሮች ረጅም ሰዓታትን የሚያሳልፉት በማሳዎች እና አትክልት ቦታዎቻቸው ከእንስሳዎች እና ከእፅዋት ጋር ነው ፡፡ የአንተ ስራ በሬድዮ በኩል ውጤታማ ተግባቢ እንዲሆኑ ማገዝ ነው፡፡

ቢቻል አርሶ አደሮች ቃለመጠይቅህን በሚመቻቸው ቦታ ፤ በቤታቸው ፤በመንደራቸው ፤ በማሳቸው ወይም በገበያ ቦታቸው አድርግላቸው፡፡ በህይወታቸው አዎንታዊ ጎን ላይ አስተያየትህን በመስጠት ጀምር፡፡ (ለምሳሌ: “ያቺ ልጅህ ማሳዎችህ ላይ ትልቅ አጋዥህ እንደሆነች እወራረዳለሁ” ወይም “ስለጠፋው የኤክስቴንሽን ወኪል ባለፈው ሳምንት የሰጠኸው አስተያየት ብዙ ድጋፍ አግኝቷል፡፡ ”) ምቾት እና ተጋዥነት የሚሰማቸው ሰዎች ቀጣይ ጥያቄዎችን በአዎንታ ለመቀበል ዝግጁነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡

ሴት አርሶ አደሮች ከወንዶች ይልቅ እንዲናገሩ በተለያየ መልኩ ማበረታትን ይፈልጋሉ፡፡ አንድን መንደር ስትጎበኝ ከሴቶች ጋር ለብቻ ስብሰባ ይኑርህ፡፡ (በተሰባጠረ ቡድን ሁሉንም የመናገር ድርሻ ለባሎቻቸው ሊሰጡ ይችላሉ፡፡) የስልክ መስመሮች ካሉህ አንዱን መስመር ለሴት ደዋዮች ብቻ እንዲሆን አድርግ፡፡ በዚህ መንገድ ቢያንስ አየር ላይ የሚወጡት ግማሾቹ ሴቶች እንደሚሆኑ ለማረጋገጥ ትሞክራለህ፡፡ ሴቶች ሌሎች ሴቶች አየር ላይ መሆናቸውን ባወቁ ቁጥር በራሳቸው ጊዜ አየር ላይ የመናገር ተነሳሽነታቸው ይጨምራል፡፡

(Click here for our guide: “ሴት አርሶ አደሮችን በተሻለ ሁኔታ የማገልገል ዘዴ)

በመጨረሻም አርሶ አደሮች በአንድ ችግር ላይ በመወያየትና እርምጃ በመውሰድ አዎንታዊ ለውጥ ሲያስመዘግቡ ከእነሱ ጋር በዝግጅግት መልኩ አክብር፡፡ ምስጋናን ሁላችንም እንወዳለን በርካታ አርሶ አደሮችንም በቀጣይ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ያነሳሳቸዋል፤ እንዲሁም አዲስ ነገርን(የተሸሻለ የእርሻ ግብኣትን) ለመተግበር የሚያስችል በራስ የመተማመን ስሜትን ይፈጥርላቸዋል፡፡

ቃለ መጠይቅህን እና ፓነልህን አቅድ

እንደ አቅራቢ አብዛኛው ስራህ ወንድ እና ሴት አርሶ አደሮች ፤ ሽማግሌዎች ፤ ባለሙያዎች ፤ሃላፊዎች እና ፖለቲከኞች መጠየቅን ያካትታል፡፡ ምናልባትም ጋዜጠኛ ለመሆን ምክንያቶች አንዱ ከሰዎች ጋር መወያየት ስለሚያስደስትህ ሊሆን ይችላል፡፡ መልካም! ሆኖም ግን በመልካም ውይይት መደሰት ጎበዝ ጠያቂ ከመሆን ጋር የተለያየ ነው፡፡ውይይት እንደ ተወያዮቹ ፍላጎት ከርዕስ ወደ ርዕስ እየተቀያየረ የሚከናወን ወሬ (ጨዋታ) ነው፡፡ ሆኖም የአርሶ አደር ፕሮግራም ቃለመጠይቅ ዓላማ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለአድማጮች አስፈላጊ በሆነ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ አስፈላጊ መረጃ፣እውነታዎችን እና አስተያየቶችን ከኢንተርቪው ሰጪዎች ማግኘት ነው፡፡ ቃለመጠይቅ አድራጊ አንተው ቃለ መጠይቁን መቆጣጠርና ለአድማጮችህ ጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብሀል፡፡ ይህ ማለት ቃለ መጠይቅህን አስቀድመህ ማቀድ እና ቃለ መጠይቁ ከሚሰጡህ ሰዎች የተሸለ መረጃ ለማግኘት የሚረዱህን ጥያቄዎችህን እና ማስታወሻዎችህን መፃፍ ይኖርብሀል ማለት ነው፡፡ ልምድ ያለው ቃለ መጠይቅ ሰጪ በሚገጥመን ሁኔታ ቃለ መጠይቁን ራሱ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንዳይወስደው ለማድረግ ተጨማሪ የመከታተያ ጥያቄዎችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ (Click here for our guide “ውጤታማ የቃለመጠይቅ ዘዴ” and read the section of that guide entitled “Learn about the three main kinds of interview you will do.” And click here for our guide “How to conduct an effective panel discussion.”)

2) ጥሩ አድማጭ ሁን

ቃለ መጠይቅን ማቀድ እና አቅጣጫውን መቆጣጠር አስፈላጊ ቢሆንም ቃለ መጠይቅ ሰጪው የሚናገረውን ነገር በጥንቃቄ መከታተልም ግድ ይላል፡፡ ጥያቄዎችህን በሙሉ ላታነባቸው ትችላለህ፤ ተናጋሪው ጥቄዎችህን በሙሉ እንደመለሰልህ ተስፋ ልታደርግ ትችላለህ፡፡

አንድ የፃፈችውን ጥያቄ በዝርዝር ስትከታተል የነበረች ነገር ግን መልሶችን ለማዳመጥ ስላልቻለች አቅራቢ በምሳሌነት እንመልከት፡፡

“ሚስዝ ስሚዝ የቦቆሎ ምርትሽ በዚህ ዓመት እጥፍ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ እውነት ነው ?”
“አዎ …ግን ከዛ በኋላ ባለቤቴ ሞተ እና በቤተሰቦቹ መሬቱን እንድለቅ ተገድጃለሁ፡፡ ”
“እንኳን ደስ ያለሽ ! ለምርቱ መሻሻል ምክንያቱ ምን ነበር ትያለሽ ?”

ቃለ መጠይቅ ስታደርግ ወይም ፓነል ውይይት ስትመራ ብቻ ሳይሆን ምን ጊዜም ጥሩ አድማጭ ሁን፡፡ ማሳ ላይ ከአርሶ አደሮች ጋር ስትነጋገር አዳምጥ፡፡ ከአርሶ አደሮች ጋር ስትነጋገር አድምጥ፡፡ ያላሰብካቸው ነገሮችን ትማራለህ፡፡

ከንግግር ወደ ተግባር መሸጋገርን አራምድ፡፡

ጥሩ መረጃ እና ጥሩ ውይይት ለአርሶ አደር ፕሮገራም ቁልፍ ጉዳዮች ቢሆኑም ወደ ተሻለ እርሻ ለመሸጋገር ግን ሁሌም በቂ አይሆኑም፡፡ ሆኖም የተሻሻሉ የግብርና ተመኩሮዎች ለአነስተኛ ግብርና አርሶ አደሮች መቋቋምና ማደግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ምክንያቱም አንተ በርካታ ቃለ መጠይቆችን እና ፓነል ውይይቶችን ስለምትመራ ነገሮችን ከንግግር ወደ ተግባር ማንቀሳቀስ ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ፡- ከምርት ስብሰባ በኋላ የቦቆሎ አቀማመጥ ላይ በሚያተኩር ፓነል ውይይት መጨረሻ ላይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማቅረብ ትችላለህ፡፡:

“ቦቆሎን በመስመር መዝራት የተሸለ ምርት እንደሚያስገኝ ሁሉም የተስማማ ይመስለኛል፡፡
ሱዛን ቦቆሎ ትዘሪያለሽ፡፡ በዚህ ዓመት ምን የተለየ ነገር ለመስራት አስበሻል?
“አርሶ አደሮች በዚህ ዓመት ትክክለኛ የማከማቻ ቋት እንዲኖራቸው አምራቾች ማህበር ምን ማድረግ አለባቸው? በየትኛው ቀን ማህበሩ የህንን ይተገብራል ?
“የመንገዱ ጥገና ለዚህ መንግስት ቅድሚ ትኩረት ስለማይመስል ቅድሚያ ለማሰጠት ምን መደረግ አለበት? ይህንን ኃላፊነት ማን ይወስዳል ?”

ፕሮግራምህን ሳቢ እና የማይረሳ መሆኑን እርግጠኛ ሁን፡፡

ማራኪ ሆኖ ካላገኘኸው ማንም ቢሆን በሬድዮ ፕሮግራም ተጠምዶ አይቀርም፡፡ አስፈላጊ መረጃ ልትሰጥ ትችላለህ ፤አርሶ አደሮች አስተያየቶቻቸውን እንዲያሰሙ ዕድል ልትሰጥ ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ፕሮግራሙ ስሜትን የማይገዛ ከሆነ አርሶ አደሮች ኣያዳምጡትም፡፡ ወደ አየር ሁኔታ እና ገበያ ዘገባ ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ወደ ሌላ ሳቢ የሬድዮ ጣቢያ ሊቀይሩ ይችላሉ፡፡ ይህ በተለይ አርሶ አደሮች ማዳመጥ የሚችሉት ብዙ አማራጭ ጣቢያ እንዳላቸው ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

ፕሮግራምን ሳቢ እና የማይረሱ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፡፡ የተወሰኑትን እነሆ:

 • ለአድማጮችህ የሚመች ሙዚቃ ጋብዝ፡፡
 • አድማጮችህ ስሜት በሚሰጥ ምክንያት እንዲያደምጡህ የሚያስችል የይዘት መግቢያ አዘጋጅ፡፡ለምሳሌ እንዲህ አትበል፡- “ዛሬ ሱዛን አላሮ ስለ መርዝ ልታነጋግረን አብራን ስለሆነች ደስ ብሎናል፡፡” በምትኩ እንዲህ በል: “ባለፈው ሳምንት በቡላዋኖ መጠጥን ከመርዝ ጋር ቀላቅለው በመጠጣታቸው ሁለት ልጆች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ ልጆቻችሁ ደህንነታቸው ምን ያህል የተጠበቀ ነው? ዛሬ ሱዛን አላሮ ልጆቻችሁ እና ቤታችሁ ከመርዞች የተጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ትረዳችሁአለች፡፡ ”
 • ውድድሮችን በመጠቀም አርሶ አደሮች ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያስታውሱ እርዳቸው፡፡ (ለምሳሌ “በመስመር ለመዝራት የሚያስፈልጉንን ሁሉንም መለኪያዎችን እና ቅደም ተከተሎችን የያዘ ዝርዝር ላኩ፡፡ አሸናፊው ‘ቅድሚያ ለአርሶአደሮች ’ የሚል ቲ-ሸርታችንን ያገኛል፡፡) ወይም ልጆች የሚወዱት የምርጥ ምግብ አሰራር ውድድር ላይ ይሳተፋል፡፡
 • በመደበኛነት የግብርናን አዝናኝ ጎን የሚያሳይ ቀለል ያለ ይዘት ይኑርህ፡፡ (ከጎተራዋ ቦቆሎ ከሚሰርቀው እንስሳ ጋር የገጠመችውን ሴት በቀጣይም ምን እንደምታደርግ ቃለ መጠይቅ አድርግላት)
 • በራስህ ካጋጠሙህ እና ከሰራሃቸው ስህተቶች የሚያዝናናውን ለአድማጮችህ አቅርብ፡፡ ለምሳሌ ጥሩ አትክልተኛ ባትሆን እና አትክልቶችን እንከባከበለሁ ብለህ ለመድረቅ የዳረግክበትን ስህተት ቢኖር በሚያዝናና መልኩ ታቀርበዋለህ፡፡ አድማጮችህ በስሜት ከአንተ ጋር ሆነው በታሪኮችህ ይዝናናሉ፡፡
 • የፕሮግራምህን የአቀራረብ ቅደም ተከተል እንዲለያይ አድርግ፡፡ ለምሳሌ ቀለል ያለውን ፕሮግራም ከበድ ከሚለው ቀጥሎ እንዲቀርብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
 • አድማጮች ይዘቱን ባይወዱትም እንኳን አንድ የሚፈልጉት ነገር እንዳለ አውቀው ፕሮግራሙን በጉጉት እንዲጠብቁት የሚያስችል ምልክት አሰማቸው ፡፡ በአውቶብስ ስትጓዝ የመንገድ ዳር ምልክቶች የት እየሄድክ እንደሆነ ይነግሩሃል፡፡ በሬድዮ ፕሮግራምም ምልክቶች ተመሳሳይ ድርሻ አላቸው፡፡ ለምሳሌ፡-በፕሮግራምህ አጋማሽ እንዲህ ማለት ትችላለህ፡ “ስለ አዳዲስ የንብ ቀፎዎቿ ስትነግረን የቆየችው ንብ ጠባቂዋ ሱዛን ኩቾ ነበረች፡፡ ቀጥሎ: ነቀዞችን ከሰብሎቻችን እነዴት ማሰወገድ እንችላለን፡፡” እነዚህ ምልክቶች ለአድማጮች ምቾትን ይሰጣሉ፡፡ በተለይም ዘግይተው ሬድዮአቸውን ለሚከፍቱ፡፡

ከምንም በላይ ፕሮግራምህን በሚያጓጓ፣ በጋራ የመከባበር ስሜት ፣ እና በሚያነቃቃ መንፈስ ስታቀርብ ሳቢ የመሆን ዕድል ይኖረዋል፡፡

ውስብስብ ርዕሰ ጉዳዮች አሰልቺ መሆን የለባቸውም፡፡ ውስብስብ በመሆኑ ብቻ አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ከመጋፈጥ ወደኋላ እንዳትል፡፡ የአድማጮችህን ጀሮ ለማግኘት እና ውስብስብ ጉዳይ ወደአካተተው ይዘት እንዲዘልቁ ለማስቻል ፕሮግራምህን ሳቢነት ባለው ታሪክ ጀምር፡፡ (Click here for our guide on “Storytelling.”)

ግብረመልስህን እየተጠቀምክ አሻሽል፡፡

የሬድዮ ፕሮግራም አቅራቢዎች በማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ታዋቂነት አላቸው፡፡ ስለምትሰራው ጥሩ ስራ የሚነግሩህ አድናቂዎች ይኖሩሃል፡፡ የእነዚህ ዓይነት አስተያየቶችን ማግኘት አስደሳች ቢሆንም ከዚያም በላይ ይጠበቅብሃል፡፡ የአቀራረብ ስልትህን በትኩረት ከሚከታተሉ አድማጮች መስማት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ፡ አስፈላጊ ቁምነገሮችን በሚገባ እንደሸፈንክ አታስብ፡፡

አጋዥ የሆኑ ግብረመልሶችን የማግኘት ዘዴዎች:

 • ጣቢያህ የተመረጡ ቡድኖች ከአድማጮች ጋር ውይይት እንዲያዘጋጅ አበረታታ ዊልያም ባቶ በ ‘ቅድሚያ ለ አርሶ አደሮች ’አቀራረብ ምን ይመችሃል ? “ እንዴት ሊያሻሽል ይችላል? ‘ቅድሚያ ለ አርሶ አደሮች ’ ላንተ ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን ይዳስሳል የመሳሰሉ ጥያቄዎች ማካተትህን አትዘንጋ፡፡
 • ራስን የመገምገም ዲሲፕሊን አዳብር፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን በመጠቀም ስራዎችህን እንዴት እያከናወንክ እንደሆነ እና እንዴት ማሻሻል እንደምትችል በመደበኛነት ራስህን ጠይቅ፡፡
 • በጣቢያህ ለሚገኙ ሌሎች አቅራቢዎች ከፕሮግራሞቹ አንዱን ክፍል እንዲያዳምጡልህ ጠይቅ፤ የዝግጅት ስራ ዝርዝሮችህንም ስጣቸው፡፡ የታዘቡትን እና የማሻሻያ መመሪያዎችን እንዲያካፍሉህ የሚያስችልህ ስብሰባ አዘጋጅ፡፡ (ለራሳቸውም ተመሳሳይ ዕድል ስጣቸው)
 • ከአለቃህ ጋር በዓመታዊ ግምገማ በመሳተፍ ፕሮግራሞችህ ከላይ በተዘረዘሩት የአቀራረብ ዘዴዎች መሰረት ፕሮግራሙ እንዴት ግቡን እንዲመታ እንደደረግክ አስረዳ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ማሻሻል የምትችልባቸው መስኮችን ለይ ፤ ማሻሻያዎቹን ለማሳካት የሚያስፈልጉህ ድጋፎችንም ለይ፡፡ (ለምሳሌ፡ ስልጠናና አመራርነት)

ከላይ እንደተገለፀው ውጤታማ የፕሮግራም አዘጋጅነት በርካታ ሙያዎችን የሚጠይቅ ትልቅ ሀላፊነት ነው፡፡ሆኖም ግን ከላይ የተጠቀሱት እያንዳንዱ ዋና ዋና ስራዎችን በመተግበር ማሻሻሉን ከቀጠልክበት ልታሳካው ትችላለህ፡፡ አንተ ባሻሻልክ ቁጥርም የአርሶ አደር አድማጮችህ የግብርና ተመኩሮዎቻቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት እንዲያሻሽሉ ትረዳቸዋለህ፡፡

መልካም ዕድል ለዚሁ አስፈላጊ እና ፈታኝ ስራ

Acknowledgements

ምስጋና
በ ዶግ ዋርድ፣ ቼር፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል እና በ ሸላግ ሮጀርስ ሆስት ፣ ቀጣዩ ምዕራፍ ሲ ቢ ሲ ሬድዮ

Information Sources

የመረጃ ምንጭ
1) V.O.I.C.E program standards የቮይስ ፕሮግራም ደረጃዎች
2) F.A.I.R. journalism standards for farmer radio programs ፌይር የጋዜጠኝነት ደረጃዎች ለ አርሶ አደር ሬድዮ ፕሮግራሞች
) የፕሮግራም ዓላማ መግለጫ The program purpose statement:
አንድ የፕሮግራም ዓላማ መግለጫ ሶስት ይዘቶች አሉት፡፡
• የፕሮግራሙን ዓላማ ይሰይማል
• የሚጠበቁት ተደራሲያንን ይሰይማል እንዲሁም
• ግቡን ለመምታት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የሰይማል፡፡

አንድ የፕሮግራም ዓላማ መግለጫ በፕሮግራሙ ስራ ላይ የተሰማሩ ሁሉ እንዲጠብቁት እና እንዲያስታውሱት በተቻለ መጠን አጭር ነው፡፡
ቀጥሎ በ ቮይስ ደረጃ መሰረት ለአርሶ አደር ፕሮግራም የተዘጋጀ የፕሮግራም ዓላማ መግለጫ ነው፡፡
“ንቁ አርሶ አደሮች!” የኔሩዳ ክልል ወንድ እና ሴት አርሶ አደሮችን ስኬታማ እንዲሆኑ ይረዳሉ፡፡
– አርሶ አደሮች የሚፈልጉትን መረጃ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ይስጣል፤,
– አርሶ አደሮች በአስፈላጊ የግብርና ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ ዕድል ይሰጣል፡፡ እንዲሁም፤
– supports ግብርናቸውን ለማሻሻል አዳዲስ ዘዴዎች የተገበሩ አርሶ አደሮችን ይደግፋል፡፡

gac-logoፕሮጀክቱ ካናዳ መንግስት የፋይናንስ ተቋም በካናዳ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት በኩል በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የሚሳለጥ ነው፡፡
ይህ ሰነድ ወደ አማርኛ የተተረጎመው በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለስቴፕልስ ፕሮጀክት በሰጠው ድጋፍ ነው፡፡