የዶሮዎች ውጫዊ ጥገኛ ተዋሲያን፤ ተፅዕኖ እና ቁጥጥር/አስተዳደር

Notes to broadcasters

Save and edit this resource as a Word document

ማስታወሻ ለአቅራቢ

በማሊገጠራማውአካባቢዎችየሚኖረውአብዛኛውሰውዝናብላይጥገኛበሆነግብርናእናከብትናዶሮእርባታላይየተሰማራነው፡፡ባህላዊዘዴዎችንበመጠቀምዶሮዎችንያረባሉ፣ይኼብዙቤተሰቦችንለመርዳትአስችሏል፡፡በአሁኑጊዜየዶሮበሽታዎችንእናጥገኛተዋሲያንንበተከታታይነትተቆጣጥረውባገኙትከፍተኛልምድአንዳንድየመንደሩአርሶአደሮችለሌሎችአርሶአደሮችዶሮዎቻቸውንየሚንከባከቡባቸውመንገዶችላይምክርይለግሳሉ፡፡

የዶሮ አርቢ አርሶ አደሮችን ከሚያጋጥሙ ዋና ዋና ተግዳሮቶች ውስጥ ውጫዊ ጥገኛ ተዋሲያን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ እነዚህ ውጫዊ ጥገኛ ተዋሲያን ያደጉ ዶሮዎችን እና የተወሰኑ ቀናት ዕድሜ ያላቸውን ጫጩቶች ያጠቃሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ በቀላሉ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ አርሶ አደሮች አነዚህን ጥገኛ ተዋሲያንን ለማከም የሚጠቀሙባቸው ምርቶች በስፋት ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በባለሙያዎች የሚመሩ አይደሉም፡፡

በዚህፅሁፍውስጥበመጀመሪያውየማሊክልልባላንዶጉኬዬስበሚባልመንደርውስጥበዶሮእርባታላይከተሰማሩአርሶአደርአዳማሳኮጋርእንገኛለን፡፡አቶሳኮየዶሮውጫዊጥገኛተዋሲያንንየፀረ-ወባምርቶች፣ናፍጣእናነጭጋዝ/ ኬሮሲንንበመጠቀምነውየሚቆጣጠሩአቸው፡፡ነገርግንበእንስሳትህክምናትምህርትቤትባለሙያከሆኑትወ/ሮኩሊባሊእንደምንሰማውእንደዚህአይነትምርቶችጥቅምላይእንዲውሉባለሙያዎችአይመክሩም፡፡

ወ/ሮኩሊባሊውጤታማየሆኑብዙምርቶችጥገኛተዋሲያንንለማከምእንደሚያገለግሉየመፍትሄሀሳብታቀርባለች፡፡በተጨማሪምአርሶአደሮችከንፅህናጋርየተያያዙአርምጃዎችንእንዲተገብሩትመክራለች: – ለምሳሌየዶሮቤቶችንበመደበኛነትማፅዳትንእናየፀረ-ተባይመድሃኒቶችንበመጠቀም፡፡

ተናጋሪዎቹንየሚወክሉየድምፅተዋንያንንበመጠቀምይኼንንፅሁፍእንደመደበኛየአርሶአደርፕሮግራምማቅረብትችላለህ፡፡ይኼየሚሆንከሆነበፕሮግራሙመነሻላይድምïቹቃለመጠይቆቹውስጥየተካተቱትየዋናዎቹ/የትክክለኞቹሰዎችሳይሆኑእነሱንየሚወክሉየድምፅተዋንያንእንደሆኑለአድማጮችመንገርህንእርግጠኛሁን፡፡

በተጨማሪምይኼንንፅሁፍእንደጥናታዊፅሁፍ/ማጣቀሻወይምበሀገርህውስጥሊኖርስለሚገባውየጥገኛተዋሲያንአያያዝ/ቁጥጥርየራስህንፅሁፍለማዘጋጀትእንደመነሻነትመጠቀምትችላለህ፡፡

የዶሮ አርቢ አርሶ አደሮችን እና ባለሙያዎች እና ዶሮዎችን በተመለከተ እውቀት ያላቸውን ሰዎች አነጋግር፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልትጠይቃቸው ትችላለህ፡፡

  • በአካባቢዎየዶሮእርባታጠቀሜታምንድንነው?
  • የትኞቹ ውጫዊ ጥገኛ ተዋሲያን በአካባቢዎ ይገኛሉ; የተለመዱ ናቸው; ከፍተኛ ችግሮችን ያስከትላሉ?
  • ለእነዚህ ጥገኛ ተዋሲያን አርሶ አደሮች እና ባለሙያዎች ምን አይነት መፍትሔዎች አገኙ?

የመግቢያ እና የመውጫ ሙዚቃዎችን (intro and outro) ጨምሮ ይኼ ፅሁፍ ይፈጃል ተብሎ የተገመተው ጊዜ 20 ደቂቃ ነው፡፡

Script

አቅራቢ ፡ የተወደዳችሁአድማጮችእንደምንአደራቹ; በዚህማለዳእንዴትየዶሮውጫዊጥገኛተዋሲያንንመቆጣጠርእንደምንችልእንማራለን፡፡ጥገኛተዋሲያንእንደቁንጫ፣ቅማልእናመዥገርያሉፍጡራንናቸው፡፡

ባላንዶጉውስጥበሰብልእርሻእናዶሮእርባታላይከተሰማሩትአቶአዳማሳኮጋርእናወጋለን፡፡ባላንዶጉበማሊየመጀመሪያክልልበኦሶቢዲያኛክፍለሀገርውስጥየምትገኝትንሽገጠራማመንደርነች፡፡

የማሳላይድምïች ፡ ዶሮዎች፣እንሰሳት/ከብቶች

አቅራቢ ፡ በማሽላማሳዎችበተከበበችአነስተኛመንደርውስጥእንገኛለን፡፡በርቀትጥቂትየጭቃቤቶችንንማየትእንችላለን፡፡በዙሪያውባሉትማሳዎችአርሶአደሮችከማሽላገለባጋርየተገኛኙስራዎችንእየሰሩነው፡፡ሌላኛውየመንደሩጎንፀጥያለነው፡፡ልጆችመንገድላይእየተጫወቱነው፡፡እዚህያለነውስለውጫዊጥገኛተዋሲያንየዶሮእርባታላይየተሰማራአርሶአደርንአግኝተንጥያቄዎችለመጠየቅነው፡፡

እንደምንአደሩአቶሳኮ?

አዳማሳኮ ፡ እንደምንአደርክ?

አቅራቢ ፡ ለአድማጮቻችንራስዎንማስተዋወቅይችላሉ; ምንእንደሚሰሩይንግሩአቸዋል፡፡

አዳማሳኮ ፡ እንደምንአደራቹ? ስሜአዳማሳኮነው፡፡ባላንዶጉመንደርውስጥነውየምኖረው፡፡የሰብልአርሶአደርነኝ፡፡ከግብርናባሻገርሌላስራላይምተሰማርቻለሁ፡፡በዚህሀገርበአንድሥራብቻኑሮንመምራትከባድነው፡፡ለዛነውሁልጊዜበተለያዩየስራመስኮችላይመሰማራትየሚመከረው፡፡

አቅራቢ ፡ ሌላውሥራዎምንድነው?

አዳማሳኮ ፡ እዚህእንዳሉሌሎችአርሶአደሮችሁሉዶሮእናጅግራአረባለሁ፡፡ከምዕራባዊያንአገራትከሚመጡትዝርያዎችበስተቀርሁሉንምአይነትየዶሮዝርያዎችንአረባለሁ፡፡ከምዕራባዊያንአገራትየሚመጡትንብዙምአልወዳቸውም፡፡

አቅራቢ ፡ ዛሬዶሮዎችንሊያስቸግሩስለሚችሉትጥቃቅንፍጡራን፣ስለውጫዊጥገኛተዋሲያንእናወጋለን፡፡እንደደርሶአደርስለነዚህጥገኛተዋሲያንሊነግሩኝይችላሉ?

አዳማሳኮ ፡ ዶሮዎችንየሚያጠቁአንዳንድጥገኛተዋሲያንንአውቃለሁ፤በተለይቁንጫወይምበባምባራቋንቋንዴሌስለሚባሉትቀይጥገኛተዋሲያን፡፡ቁንጫዎችዶሮዎችማታማታበሚያርፉበትየዛፍቅርንጫፎችላይነውየሚኖሩት፡፡ሙሉስብስቡንማጥፋትየሚችሉበጣምአደገኛጥገናተዋሲያንናቸው፡፡

አቅራቢ ፡ ዶሮዎችዎማታማታየዛፍቅርንጫፎችላይነውየሚያሳልፉት?

አዳማሳኮ ፡ አዎአንዳንዶቹግንሁልጊዜአይደለም፡፡እነዚህጥገኛተዋሲያንዶሮዎችየሚተኙበትንቦታይወዳሉ፣ለምሳሌየዶሮቤቶችንወይምዛፎችን፡፡የዶሮዎችንደምሙሉበሙሉሊመጡይችላሉ፡፡ግድግዳዎችላይ፣በጡብመካከልባሉአርማታዎችውስጥእናበዛፍቅርፊትውስጥይኖራሉ፡፡ማታዶሮዎችበሚተኙበትሰዓትይወጣሉ፡፡የዶሮዎችእግርናታፋላይጥቃትያደርሳሉ፡፡የዶሮቤትአቅራቢያያለንዛፍቀረብብለህካስተዋልክእነዚህንተዋሲያንታያለህ፡፡እነሱንለመግደልመደረግየሚገባውነገርምሽትላይቢሆንየተሻለነው፡፡

አቅራቢ ፡ ለምንድነውይኼእርምጃምሽትላይመወሰድያለበት?

አዳማሳኮ ፡ በዛንወቅትነውመኖሪያቸውንትተውዶሮዎችንየሚያጠቁት፡፡ወደዶሮቤትበቀንቢሄዱምንምነገርአያዩም፡፡

የዶሮቅማልየሚባልሌላትንሽነጭጥገኛህዋስአለ፡፡በባምባራቋንቋቼግኒሚይባላል፡፡ይኼጥገኛህዋስበርግጥትንሽነው፡፡አዲስበሚጣሉእንቁላሎችላይበመቆየትወደእናትዶሮዎችላባዎችውስጥይገባል፡፡ይኼሲከሰትዶሮዎችንወዲያውኑማከምአለባቹ፡፡ካልሆነዶሮዎችንበማስቸገርእንቁላሎቻቸውንትተውእንዲሄዱያደርጋቸዋል፡፡በጣምትንሽከመሆኑየተነሳየዶሮቅማልንበአይንለማየትይከብዳል፡፡የተወሰኑቀናትዕድሜያላቸውንጫጩቶችብቻነውመግደልየሚችለው፡፡ያደጉትንአይገድልም፡፡

መዥገርወይምበባምባራቋንቋትሬፊንየሚባልሌላጥገኛህዋስአለ፡፡ጥቁርእናእንደቅማልትንሽነው፡፡በዶሮክንፎችእናታፋዎችሥርእናበሁሉምበተደበቁየዶሮክንፎችውስጥቀስቀስያድጋል፡፡ጥገኛተዋሲያንበሬዎችእናላሞችንበሚያጠቁትመልኩዶሮዎችንምያጠቃሉ፡፡ይኼማለትዶሮዎችንካልገደሉበቋሚነትበላባቸውስርይቆያሉ፡፡መዥገርዶሮዎንበፍፁምትቶትአይሄድም፡፡የዶሮዎችንደምበመምጠጥበፍጥነትስለሚገድላቸውበጣምአደገኛጥገኛህዋስነው፡፡

አቅራቢ፡እነዚህጥገኛተዋሲያንእርሶበከፍተኛደረጃበሚተማመኑበትየዶሮእርባታ/ግብርናላይከፍተኛጉዳትእንደሚያደርሱእገነዘባለሁ፡፡ነገርግንእነዚህጎጂፍጡራንከዬትእንደሚመጡሊነግሩኝይችላሉ?

አዳማሳኮ ፡ ስለዚህጉዳይእራሴንብዙጥያቄዎችእጠይቃለሁ፡፡አንዳንድጊዜከኩስይሆንየሚመጡትብዬራሴንእጠይቃለሁ፡፡ለዶሮዎችዎአዲስቤትየሚገነቡከሆነመጀመሪያአካባቢምንምአይነትጥገኛተዋሲያንንአያዩም፡፡ነገርግንየዶሮቤቱእያረጀሲሄድተዋሲያንንበየቦታውያያሉ፡፡

አቅራቢ ፡ የዛፍላይጥገኛተዋሲያንስ? ከዬትይመጣሉብለውያስባሉ?

አዳማሳኮ ፡ ዛፍላይየሚኖሩዶሮዎችኩሳቸውንበቅርንጫፎችወይምበዛፎችስርይጥላሉ፡፡ጠዋትላይቦታውንየማይጠርጉትከሆነወደዛለመሄድይቸገራሉ፡፡እነዚህኩሶችዝናብአጥቦእስኪወስዳቸውድረስዛፎችላይተጣብቀውይቆያሉ፡፡የኩስብዛትየነዚህጥገኛተዋሲያንምንጭሊሆንይችላ

ብዬአስባለሁ፡፡

አቅራቢ ፡ የዶሮአርቢለሆነየእንስሳትህክምናቴክኒሻንቃለመጠይቅአድርጌነበር፡፡ሁልጊዜጠዋትጠዋትየዶሮቤትንበመጥረግመሳሪያውንበፀረ-ተባይመድሃኒትማፅዳትአለብንይላል፡፡ስለዛምንያስባሉ?

አዳማሳኮ ፡ አዎእሱልክነው፤ግንእኛአርሶአደሮችባለሙያዎችችላየሚሏቸውንነገሮችእናውቃለን፡፡የእነርሱሕግጋትሁልጊዜአይሰሩም፡፡ለምሳሌስለመሳሪያነገሮሀል፤ነገርግንእኛምንምአይነትመሳሪያየለንም፤ዶሮዎቻችንንየምናረባውውጪላይነው፡፡የነሱጥናትያንንከግምትአያስገባም፡፡

አቅራቢ ፡ ዛፎችእናእንቁላሎችላይያሉትንእናበዶሮቤቶችውስጥየሚገኙትንጥገኛተዋሲያንእንዴትነውየሚቆጣጠሩት?

አዳማሳኮ ፡ በግሌየዲዝልዘይትን/ናፍጣንነውየምጠቀመው፡፡በፊትየዶሮቅማልንቲሞርራምቦበሚልምርትነበርየምቆጣጠረው፡፡ግንምርቱሁሉንምዶሮዎቼንእያወደመብኝእንደሆነተረዳው፤እናምእሱንአቁሜናፍጣንመጠቀምቀጠልኩ፡፡

አቅራቢ ፡ ዶሮጥገኛህዋስእንዳለውእንዴትነውየምናውቀው? ዶሮዎችካልታከሙበተዋሲያኑአማካይነትምንአይነትጉዳትሊከሰትይችላል?

አዳማሳኮ ፡ እነዚህተዋሲያንበዶሮዎችላይበግልፅማየትየምትችላቸውየተለዩምልክቶችንያሳያሉ፡፡ቅማሎችበዶሮላይበሚታዩበትወቅትዶሮዋቀስበቀስክብደቷንእያጣችትሄዳለች፤ይሄጥንካሬእስከማጣትድረስያደርሳታል፡፡በ30 ቀናትውስጥካልታከመችይሄጥገኛህዋስይገድላታል፡፡

የዶሮቁንጫንበተመለከተዶሮዋእንቁላልስትጥልበምታሳየውባህሪይየቁንጫውተጠቂመሆኗንመናገርትችላለህ፡፡እንቁላሎችዋላይበተቀመጠችበትጥቂትደቂቃዎችውስጥበመነሳትመንቁሯንተጠቅማቁንጫውንከሰውነቷለማስወገድወዲያወዲህትሮጣለች፡፡አንድቦታመቆየትአትችልም፤ከሞላጎደልየእብደትባህሪይታሳያለች፡፡ይሄጥገኛህዋስዶሮዋንአይገድላትም፤ግንበጣምእረፍትይነሳታል፡፡ጥገኛህዋሱከተወሰነጊዜበኋላይጠፋል፤ያለምንምህክምና፡፡

መዥገርእጅግበጣምአደገኛውጥገኛህዋስነው፡፡ዶሮዋንበማየትውዲያውኑሊለዩትይችላሉ፡፡ክብደቷንታጣለች፤ብዙእንቅስቃሴአታደርግምወይምምግብአትመገብም፡፡መዥገሮችበጣምአደገኛናቸው፡፡ስለዚህዶሮዋበተወሰኑሳምንታትውስጥካልታከመችትሞታለች፡፡

አቅራቢ ፡ በዚህመንደርባለሙያዎችንወይምየዶሮህክምናመድሀኒቶችንየምታገኙባቸውቦታዎችአሉ?

አዳማሳኮ ፡ እንደዚህዓይነትባለሙያዎችየሉንም፤ግንመድሀኒቶቹንየሚሸጡየመንገድላይቸርቻሪዎችአሉ፤ከጊዜብዛትየእንስሳትሀኪሞችብለንነውየምንጠራቸው፡፡ታናሽወንድሜለሳምንትገበያወደአቅራቢያው/ጎረቤትመንደርበሚጓዝበትወቅትለምፈልጋቸውመድሀኒቶችመግዣገንዘብእሰጠዋለሁ፡፡

አቅራቢ ፡ ራሳቸውንወደእንስሳትህክምናየቀየሩትቸርቻሪዎችንታምናላችሁ?

አዳማሳኮ ፡ እኔየማምነውአንዱንየመንገድላይቸርቻሪብቻነው፡፡ጉድለቶችእንዳሉበትአውቃለሁ፤ነገርግንበጣምነውየሚረዳኝ፡፡ልታናግረውከፈለክወደቤቱልወስድህእችላለሁ፡፡

አቅራቢ ፡ ደስይለኛል፤ግንለአሁኑውይይታችንንእንቀጥል፡፡ጥገኛተዋሲያንበዶሮእርባታስራዎላይምንዓይነትተፅእኖዎችያሳድራሉ?

አዳማሳኮ ፡ ተዋሲያኑጎጂከመሆናቸውየተነሳስራውላይውድመትሊያደርሱይችላሉ፡፡ጉዳትካደረሱበኋላሳይሆንአስቀድመህህክምናመስጠትአለብህ፡፡አስቀድመህሕክምናየማታደር

ከሆነየሚደርሰውንጉዳትቁጭብለህማየትብቻነውየሚሆነውስራህ፤ዶሮዎችህንማዳንአትችልም፡፡

የዶሮእርባታከምታስበውበላይበጣምጠቃሚነው፡፡ለምሳሌበመንደሬውስጥኦሙፉህየሚባልሰውአለ፡፡በሺየሚቆጠሩጅግራዎችአሉት፡፡ከጅግራዎቹሽያጭለሚገኘውገቢምስጋናይግባውናወደመካመሄድእንደቻለነግሮኛል፤በተጨማሪምእናቱንእናወንድሙንወደዛመላክችሏል፡፡ኦሙሁለትየእንቁላ

ማስፈልፈያዎችንጨምሮሌሎችመሳሪያዎችእንዳሉትምበተጨማሪልነግርህይገባል፡፡

አቅራቢ ፡ ደንበኞችበጥገኛተህዋሲያንየተጠቁዶሮዎችንወይምአውራዶሮዎችንይጠላሉ?

አዳማሳኮ ፡ ስለዶሮገበያበቂእውቀትየሌላቸውደንበኞችእነዚህንዝርዝርጉዳዮችአያስተውሉም፡፡በጥገኛተዋሲያኑየተጠቁዶሮዎችወይምአውራዶሮዎችያንያህልክብደትየላቸውም፡፡በተጨማሪምስጋቸውአነስተኛስብነውያለው፡፡ነገርግንበቂእውቀትያላቸውደንበኞችያንያውቃሉ፡፡እንደዚህዓይነትዶሮዎችንለምግብነትከተጠቀምክጥሩጣዕምአይኖራቸውም፡፡

አቅራቢ ፡ ላበረከቱትአስተዋፅዎበጣምአመሰግናለሁ፤አሁንወደመድሀኒትቸርቻሪውሊወስዱኝይችላሉ?

አዳማሳኮ ፡ አዎእንሂድ፡፡

SFX :በደረቅሳርላይየኮቴድምጽ

አዳማሳኮ ፡ ይሄውእዚህነውየሚኖረው፡፡ቤቱንእናመድሀኒቱንየሚሸጥበትትልቅጠረጼዛይታይሀል?

SFX፡ በር ተከፍቶ ሻጩ ወደ ውጭ ይመጣል፡፡ ወደ አዳማ እና አቅራቢው የሚመጣ ሰው የኮቴ ድምፅ፡፡

አቅራቢው፣አዳማሳኮእናመድሀኒትቸርቻሪውሰላምታይለዋወጣሉ፡፡

ካንቴ፡እባካችሁተቀመጡ፡፡

አቅራቢ ፡ በዶሮየውጫዊጥገኛተዋሲያንላይየሬድዮፕሮግራምእያዘጋጀንነው፤እናምዛሬእዚህየተገኘነውምንእንደሚሰሩለመመልከትነው፡፡ነገርግንወደዝርዝርጉዳዮችከመግባታችንበፊትእባኮዎንራስዎንለአድማጮቻችንያስተዋውቁ፡፡

ካንቴ፡ሙሳካንቴእባላለሁ፡፡እዚህባላንዶጉውስጥየዶሮእርባታስራነውየምሰራው፤በተጨማሪምየዶሮእርባታላይየተሰማሩየመንደርሰዎችየእንስሳትህክምናአገልግሎትተወካይነኝ፡፡የመንደሩየእንስሳትግብርናክትትልናቁጥጥርሀላፊነኝ፡፡እናምእዚህላሉትየእንስሳትግብርናአርሶአደሮችሁሉአማካሪነኝ፡፡

ጠረጼዛላይእየተደረደሩያሉየመድሀኒትጠርሙሶችድምፅ፡፡

አቅራቢ ፡ ለዚህ ስራ የወከልዎ መንደሩ ነው ወይስ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት? ለዚህ ስልጠና አግኝተዋል?

ካንቴ፡አንዳንድነገሮችበራሳቸውጊዜይከሰታሉ፡፡እኔንበተመለከተየተከሰተውይሄውነው፡፡በጣምየምወደውስራነው፡፡እናምጥቅሙንባወኩጊዜነውውጤታማየዶሮእርባታአርሶአደርመሆንየቻልኩት፡፡በአንድወቅትከ300 በላይዶሮዎችነበሩኝ፡፡እነዚህንሁሉዶሮዎችይዞበሽታዎችንማስወገድየሚቻልነገርአልነበረም፡፡በመንደሩውስጥየእንሰሳትህክምናባለሙያዎችስላልነበሩከሳምንታዊገበያእገዛቸውበነበሩምርቶች/መድሃኒቶችአማካይነትቀስበቀስእንዴትበሽታዎቹንማከምእንደሚቻልተማርኩኝ፡፡

መጀመሪያላይትክክለኛውንመጠንመድሃኒትበቅጡስላላወኩመድሃኒቶቹበሥራዬላይየተወሰኑችግሮችፈጥረውነበር፡፡ነገርግንምስጋናከተማውስጥላገኘኋቸውየእንሰሳትሀኪሞችይሁንናቀስበቀስእያንዳንዱንነገርእንዴትመቆጣጠርእንደሚቻልተማርኩኝ፡፡

አንድቀንአስታውሳለሁ፡፡አሥርዶሮዎችንኦክሲቴትራሳይክሊን10% በሚባልመድሃኒትአከምኳቸው፡፡ከሁለትሰዓትበኋላሁሉምሞቱ፡፡ለምንእንደሆነታውቃለህ; በርግጥለአደጉዶሮዎችኦክሲቴትራሳይክሊን5% በቀንሁለቴለጫጩቶችደግሞአንድጊዜመጠቀምነበረብኝ፡፡

አሁንግንየተወሰኑስልጠናዎችንአግኝቻለሁ፡፡እናምከዚህበኋላተመሳሳይአይነትስህተትአልሰራም፡፡ዛሬከሞላጎደልየዚህመንደርአርሶአደሮችለዶሮዎቻቸውሕክምናበሚፈልጉበትወቅትየሚጠሩት/የሚተማመኑበትየእንሰሳትሀኪምሆኛለሁ፡፡ይኼኑሮነው፡፡ነገሮችንከራስህልምዶችነውየምትማረው፡፡

SFX፡ ካንቴ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይስቃል፡፡ እጁ የመድሃኒት ሳጥኖችን ሲፈልግ የሚያወጣው ድምፅ፡፡

አቅራቢ ፡ ዶሮዎችንየሚያጠቁውጫዊጥገኛተዋሲያንንለመዋጋትየትኞቹንመድሃኒቶችነውየምትጠቀመው?

ካንቴ ፡ እዚህከሞላጎደልለሁሉምየዶሮእናእንስሳትበሽታዎችየምንጠቀመውአንድመድሃኒትብቻነው፡፡ነገርግንእንደበሽታዎቹእናየእንስሳትአይነትመጠንይለያያል፡፡ይኼመድሃኒትአልበን300 ሚ.

ይባላል፡፡ይኼመድሀኒትበሁሉምገበያእናእንደኛያሉየመንገድላይቸርቻሪዎችጋርይገኛል፡፡

ነገርግንከውጫዊጥገኛተዋሲያንጋርበተያያዘከገበያልትገዛቸውየምትችለውየተለያዩውጤታማዱቄቶችአሉ፡፡ግንአሁንአርሶአደሮችለጥገኛተዋሲያንመፍትሔአግኝተናልብለውያስባሉ፡፡አብዛኞቻችንእንደራምቦእናሌሎችምርቶችያሉየፀረ-ወባምርቶችንነውየምንጠቀመው፡፡ሌሎችአርሶአደሮችናፍጣወይምነጭጋዝንይጠቀማሉ፡፡እኔየፀረ-ወባምርቶችንወይምናፍጣእናነጭጋዝሞክሬአላውቅም፤ምንምእንኳንሰዎችእነዚህምርቶችበጣምውጤታማፀረ-ጥገኛተዋሲያንናቸውቢሉም፡፡ባለሙያዎችእነዚህምርቶችችግርሊፈጥሩይችላሉብለውእስካሁንአልነገሩንም፤ግንከዚህየበለጠትኩረትመስጠትአለብን፡፡

አቅራቢ ፡ አቶካንቴበጣምአመስግናለሁ! የተወደዳቹአድማጮቻችንከሞላጎደልወደፕሮግራማችንፍፃሜላይደርሰናል፤ግንከዛበፊትየባለሙያንአስተያየትእንሰማለን፡፡ወ/ሮኩሊባሊበሰማናቸውነገሮችላይዝርዝርጉዳዮችንትነግረናለች፡፡

አቅራቢ ፡ እንዴትአደርሽእመቤት?

/ሮ ኩሊባሊ ፡ እንዴት አደርክ?

አቅራቢ ፡ ራስሽንለአድማጮቻችንማስተዋወቅትችያለሽ?

/ሮ ኩሊባሊ ፡ ወ/ሮ ኩሊባሊ አሳናቱ ቡአሬ እባላለሁ፡፡ የዶሮ እርባታ ስራ ቴክኒሻን ነኝ፡፡ በተጨማሪም መምህርት ነኝ፡፡ ካቲቦጉ ውስጥ በሚገኝ Institute Polytechnique Rural de Formation et de Recherché Appliqué ውስጥ ነው የተማርኩት፡፡ ካዬስ ኦሱቢዲያኛ ውስጥ ነው የምኖረው፡፡

አቅራቢ ፡ እባክሽንዶሮዎችንስለሚያጠቁትውጫዊጥገኛተዋሲያንንገሪን፡፡

/ሮኩሊባሊ ፡ እነዚህተዋሲያንኤክቶፓራሳይትተብለውምይጠራሉ፡፡በዶሮዎችቆዳላይነውየሚኖሩት፡፡በዶሮቤትውስጥያሉዶሮዎችንእናሌሎችእንስሳትንበመንከስደማቸውንይመጣሉ፡፡እነዚህተዋሲያንዶሮዎችምግባቸውንበልተውካብላሉበኋላየምግቦቹንሁሉንምንጥረነገሮችከዶሮዎቹውስጥበመምጠጥይወስዳሉ፡፡ለዚህነውዶሮዎቹክብደታቸውንየሚያጡት፡፡የቆዳእናሌሎችየሰውነትህዋሳትምእንዲቆጡያደርጋሉ፡፡

ጥገኛተዋሲያኑመርዛማማናቸው፡፡መርዛማነገርወደዶሮዎቹደምበማስገባትእንዲታመሙያደርጓቸዋል፡፡በተጨማሪምእነዚህተዋሲያንየዶሮአካላትመጉረብረብእናጉዳትን/ቁስለትንያስከትላሉ፡፡

በአጠቃላይውጫዊጥገኛተዋሲያንከዶሮዎችኩስወይምሌላመንጋ/ስብስብውስጥባሉዶሮዎችአማካይነትነውየሚከሰቱት፡፡በተጨማሪምየዶሮቤትንፅህናጉድለትእናየግድግዳዎችቀዳዳ/ክፍተትየጥገኛተዋሲያንእንቁላልመጣያናመራቢያስለሚሆንምቹሁኔታንይፈጥርላቸዋል፡፡

አቅራቢ ፡ ለነዚህለተለያዩጥገኛተዋሲያንየትኞቹህክምናዎችናቸውጥቅምላይየሚውሉት?

/ሮ ኩሊበሊ ፡ እነዚህን ተዋሲያን ለመቆጣጠር ብዙ አይነት ምርቶች/መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ ምስጦችን የሚገድሉትን አካራሲድ እና ፀረ-ተባይ መድሃኒቶችን ጨምሮ፡፡ በምትኖርበት ሀገር ላይ በመመስረት እነዚህ ምርቶች የተለያዩ አይነት ስያሜዎች ሊኖራቸው ይችላል፡፡ እዚህ አካባቢ ያሉት አንዳንድ መጠሪያዎች ሴፑ፣ ከርባላብ፣ሄክሲፕራሜትሪን እና ሳይፐርሜትሪን ናቸው፡፡ አርሶ አደሮች እነዚህን መድሃኒቶች ከውሀ ጋር በመቀላቀል ዶሮዎች ላይ ይረጫሉ ወይም ዶሮዎቹን ውህዱ ውስጥ ይነክራሉ፡፡ በተጨማሪም የዶሮ ቤት ውስጥ መርጨት ያለባቸው መድሃኒቶችም አሉ፡፡

አቅራቢ ፡ ጥገኛተዋሲያንንናፍጣወይምፀረ-ወባመድሃኒቶችንተጠቅሞመቆጣጠርንበተመለከተምንታስቢያለሽ?

/ሮኩሊባሊ ፡ እነዚህንምርቶችተጠቅሞጥገኛተዋሲያንንመቆጣጠርአይመከርም፡፡እነዚህምርቶችአርሶአደሮችምክንያቱንሳያውቁዶሮዎችንሊገድሉይችላሉ፡፡

አቅራቢ ፡ ለዶሮእርባታአርሶአደሮችሌላምክርአለሽ?

/ሮኩሊባሊ ፡ ለዶሮእርባታአርሶአደሮችሁልጊዜምቢሆንአንድአይነትምክርነውየምንሰጠው፡፡የዶሮቤትማፅዳትንያሉየንፅህናእርምጃዎችን፣የጠቀስኳቸውንመድሃኒቶችመጠቀምን፣የዶሮቤትወለልንማፅዳትእናበየወሩየዶሮቤትውስጥእናውጪውንፀረ-ተባይመድሃኒትመርጨትንመተግበርአለባቸው፡፡ሁሉምዘመናዊእናባህላዊየዶሮእርባታአርሶአደሮችንሁልጊዜየንፅህናእርምጃዎችንመውሰድእንዳለባቸውእመክራለሁ፡፡ምክንያቱምየማንኛውምየግብርናሥራስኬትየንፅህናአጠባበቅሁኔታዎችላይየተመሰረተነው፡፡

አቅራቢ ፡ ወ/ሮኩሊባሊበጣምአመሰግናለሁ፡፡

/ሮ ኩሊባሊ ፡ እኔም አመሰግናለሁ፡፡

አቅራቢ ፡ውድአድማጮችበሳሄልክልልለዶሮዎችተደጋጋሚሞትስለሆኑትውጫዊጥገኛተዋሲያንበተለያዩእንግዶቻችንአማካይነትብዙቁምነገሮችንቀስመናል፡፡

በኦሶቢዲያኛየሚገኙበዶሮእርባታላይየተሰማሩአባዛኛዎቹአርሶአደሮችእነዚህንጥገኛተዋሲያንየሚዋጉትየመንደራቸውንቴክኒሻኖች፣የሕክምናእናንፅህናአጠባበቅምክሮችንበመከተልነው፡፡ነገርግንጥቅምላይመዋልየማይገባቸውን፣የማሳውድመትንእናየዶሮዎችንሞትሊያስከትሉየሚችሉትንናፍጣንእናፀረ-ወባምርቶችንምይጠቀማሉ፡፡

በጣምከፍተኛጉዳትከሚያደርሱትሶስቱየጥገኛተዋሲያንአይነቶች(ቅማል፣ቁንጫእናመዥገር) እናምንአይነትጉዳቶችንሊያደርሱእንደሚችሉተምረናል፡፡በተጨማሪምአርሶአደሮችዶሮዎቻቸውበጥገኛተዋሲያንመያዝአለመያዛቸውንእንዴትመለየትእንደሚችሉእናእነዚህተዋሲያንእንዴትእንደሚዛመቱምተምረናል፡፡

በመጨረሻምበምንአይነትመድሃኒቶችእናየንፅህናአጠባበቅእርምጃዎችጥገኛተዋሲያኑንመከላከልእንደምንችልተምረናል፡፡ግንከሁሉምበላይየተማርነውነገርገጠርበሚኖረውሕዝብእናዶሮአርቢዎችላይሊያደርሱየሚችሉትንከፍተኛተፅዕኖነው፡፡

ፕሮግራሙንስላዳመጣቹእናመሰግናለን፡፡በሚቀጥለውፕሮግራማችንሌላግብርና-ነክርዕሰጉዳይይዘንእንቀርባለን፡፡እናምተከታተሉን፡፡ትኩረትሰጥታችሁስላዳመጣቹንበድጋሜእናመሰግናለን! በቅርቡእንገናኛለን፡፡

Acknowledgements

ምስጋና

አዘጋጅ: – ቡባከር ጋኩ፣ የፊልም ባለሙያ፣ ባማኮ-ማሊ

አርታኢ: – ሙሳኮኔየLivestock Industry Unit, Local Service of Animal Products (SLPLA)

ሀላፊ፣ቦጎኒ- ማሊ

የመረጃምንጮች

ቃለ መጠይቆች: – አዳማ ሳኮ ፣ ሙሳ ካንቴ እና አሳናቱ ቡአሬ፣ ግንቦት 26፣2016 እ.ኤ.አ

gac-logoአፌርስካናዳበኩልበካናዳመንግስትየገንዘብድጋፍየሚተገበርፕሮጀክት